Gamo nation

Gamo nation Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gamo nation, Digital creator, Arba Mintch.

ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠ የሐዘን መግለጫዶ/ር ስምዖን ሽብሩ ከአባታቸው አቶ ሽብሩ ጨጨ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አምኔ ጎሌ በቀደሞው ጋሞ አውራጃ በኦቾሎ ቀበሌ ግንቦት 29/1960 ዓ/ም...
05/09/2025

ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠ የሐዘን መግለጫ

ዶ/ር ስምዖን ሽብሩ ከአባታቸው አቶ ሽብሩ ጨጨ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አምኔ ጎሌ በቀደሞው ጋሞ አውራጃ በኦቾሎ ቀበሌ ግንቦት 29/1960 ዓ/ም ተወለዱ፡፡ ዶ/ር ስምዖን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በላንቴ 1ኛ ደረጃና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡ ዶ/ር ስምዖን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በባዮሎጂ የትምህርት መስክ ሐምሌ 3/1984 ዓ/ም፣ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ የትምህርት መስክ ሐምሌ 2/1991 ዓ/ም እንዲሁም የ3ኛ ዲግሪያቸውን ቤልጂየም ሀገር ከሚገኘው አንተወርፕ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 17/2008 ዓ/ም በ ‹‹Terrestrial Ecology›› የትምህርት ዘርፍ አግኝተዋል፡፡

ከ1985-1991 ዓ/ም ድረስ በተለያዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና በአርባ ምንጭ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም በመምህርነት፣ ከ1992-1996 በጂቲዜድ ፕሮጀክት ባለሙያ በመሆን የሰሩት ዶ/ር ስምዖን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ነሐሴ 24/1996 ዓ/ም ተቀላቅለዋል፡፡ ከመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራቸው ባሻገር በተለያዩ የኃላፊነት መስኮች ዩኒቨርሲቲውን ያገለገሉት ዶ/ር ስምዖን ከሐምሌ 1/1997-መጋቢት 1/1999 ዓ/ም የተከታታይ ትምህርት ማስተባበሪያ ኃላፊ፣ ከግንቦት 19/2000 ዓ/ም-ሐምሌ 19/2001 ዓ/ም የጥናት፣ ምርምርና ሕትመት ማስተባበሪያ ኃላፊ፣ ከሐምሌ 20/2001 ዓ/ም- ጥር 8/2004 ዓ/ም የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት፣ ከግንቦት 23/2008 ዓ/ም- ሕዳር 9/2010 ዓ/ም የምርምር ዳይሬክተር፣ ከሕዳር 10/2010- ጥር 30/2013 ዓ/ም ድረስ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት በመሆን ዩኒቨርሲቲውን አገልግለዋል፡፡

ከነሐሴ 25/2012 ዓ/ም ጀምሮ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት አካዳሚክ ማዕረግ ያገኙት ዶ/ር ስምዖን ከግንቦት 20/2017 ዓ/ም ጀምሮ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን በመሆን ሕይታቸው እስካለፈበት ዕለት ድረስ አገልግለዋል፡፡

ዶ/ር ስምዖን ባለትዳርና የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ 57 ዓመታቸው ነሐሴ 30/2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በዶ/ር ስምዖን ሽብሩ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ የሥራ ባልደረቦች፣ ጓደኞችና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ነገ ቅዳሜ ጳጉሜ 1/2017 ዓ/ም በ8 ሰዓት በአርባ ምንጭ መድኃኔዓለም ካቴድራል የሚፈጸም ይሆናል፡፡

05/09/2025
💁ይሄው ጋሞ❤❤❤ጋሞ ማለት በአጭሩ በዚህ ፎቶ እልፍ ማብራሪያ ይሰጠዋል ። በአጭሩ የሌላዉን ደስታ እንደ ራሱ ቁጥሮ የሚፈነጭና ደስታን ከልቡ የሚጋራ በሌላው ሀዘን ታሳ ታሳ እያለ ደረቱን እየ...
05/09/2025

💁ይሄው ጋሞ❤❤❤

ጋሞ ማለት በአጭሩ በዚህ ፎቶ እልፍ ማብራሪያ ይሰጠዋል ። በአጭሩ የሌላዉን ደስታ እንደ ራሱ ቁጥሮ የሚፈነጭና ደስታን ከልቡ የሚጋራ በሌላው ሀዘን ታሳ ታሳ እያለ ደረቱን እየደቃ ከሀዘንተኛ ጋር አብሮ የሚያነባ።

የአርባምንጭ ከነማ እግር ኳስ ቤተሰቦች እስከ ወላይታ ሶዶ ድረስ በመጓዝ የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ደስታ ተጋርተዋል ።

👉ጋሞ ደሬ ሆላ ነስ❤❤🙏

ለአቶ ማሞ ምህረቱ ሽኝት ተደርገላቸው   በተገኙበት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው ለብሔራዊ ባንክ ገዥ ለነበሩት አቶ ማሞ ምህረቱ የሰንብት ሥነ ሥርዓት  አካሂዷል፡፡በዚህ ልዩ ፕሮግራም አቶ ማሞ በ...
04/09/2025

ለአቶ ማሞ ምህረቱ ሽኝት ተደርገላቸው

በተገኙበት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው ለብሔራዊ ባንክ ገዥ ለነበሩት አቶ ማሞ ምህረቱ የሰንብት ሥነ ሥርዓት አካሂዷል፡፡

በዚህ ልዩ ፕሮግራም አቶ ማሞ በተለይም መንግስት በቅርብ ግዚያት የወሰዳቸውን ታሪካዊና ውጤታማ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ በብሔራዊ ባንክ ገዥነትና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባልነት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ለሚጠብቃቸው የስራ ኃላፊነት በብቃት እንደሚወጡ በመተማመን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

04/09/2025
ከታች በምስሉ የምናየው የአእዋፋት ዝርያ ስም እርኩም ይባላል፦በጣም ዝምተኛና እህል የማያበላሽ ሰውን የማይተናኮል የወፍ ዝርያ ነው፦እባብና ሌሎች በመርዝ የሚገድሉ ነፍሳት መርዛቸው አይጎዳውም...
01/09/2025

ከታች በምስሉ የምናየው የአእዋፋት ዝርያ ስም እርኩም ይባላል

፦በጣም ዝምተኛና እህል የማያበላሽ ሰውን የማይተናኮል የወፍ ዝርያ ነው
፦እባብና ሌሎች በመርዝ የሚገድሉ ነፍሳት መርዛቸው አይጎዳውም
፦የሚበላውን ለማግኘት ካልሆነ በስተቀር ዝም ብሎ እንደሌሎች አእዋፋት ብዙ ቦታ ላይ አይታይም
፦ሲራመድ አንገቱን ደፍቶ መሬት መሬት እያየ ነው ይህም የትህትና ምሳሌ ነው ይባላል
፦ማነኛውንም ግዳይ ሲጥል ከመጉረሱ በፊት ወደ ሰማይ ቀና ይላል (አመስግኖ እየበላ ነው ይባላል

፦ሲራመዱ ሴትና ወንዱ ሁለት ሁለት ሆነው በፍጹም አይነጣጠሉም ብቻውን ከታየ ጓደኛዋ ሞቷል ትዳሯ ወይንም ትዳሩ ፈርሷል ማለት ነው ከዚያም በኋላ በፍጹም ከሌላ እርኩም ጋር ግንኙነት አይኖረውም እንቁላል ጥለው ለመቀፍቀፍ(ለመፈልፈል)አርባ ቀን ይወስድባቸዋል ጫጩት ለማሳደግ 3 ዓመት ሙሉ በአንድ ላይ ይደክማሉ ይህም የጥሩ ባለትዳር ምሳሌ ነው ይባላል

፦አንድ እርኩም እርኩም ከ50 እስከ ሰባ ሰማንያ ዓመት በሕይወት እንደሚኖር ሳይንስ ያረጋገጠ ሲሆን በአፈ ታሪክ ግን በመቶዎች የሚቆጠር ዘመንን ይኖራል ይባላል
በሁለት እርኩሞች መሃል ማለፍ እድሜን ያስረዝማል ይባላል ሥጋቸው ከማይበላ አእዋፋት መካከል ቢሆንም የእርኩም ሥጋ የበላ ሰው ቶሎ አያረጅምም ስለሚባል እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች በሽምግልና ዘመናቸው እንደ ወጣት ሲሆኑ እገሌማ የእርኩም ሥጋ በልቷል ይባላል

፦እርኩም እንዲህ መልኩ ጥቁር ሆኖ እንኳን ሲታይ ግርማ ሞገስና ደስ የሚል ነገር አለው

እናልህ ወዳጄ አንተም እንደ እርኩም ከመብላትህ በፊት አመስግን በሕይወትህ ስክነት የሚባል ነገር ይኑርህ ለጓደኝነት ቦታ ይኑርህ ለትዳርህ ከእርኩም በላይ ታማኝ ሁን
ማንንም የማትተናኮል የዋህና ቸር ሁን ከራስህ ሕይወት ውጪ ማንንም መጥቀም ባትችል እንኳን ማንንም አትጉዳ
ማን ያውቃል ከእርኩሙ በላይ እድሜህን ያረዝምልሃል የማንም መርዛማ ነገር እንዳይጎዳህ ያደርግሃል ግርማ ሞገስና ክብርን ያለብስሃል
እንደ እርኩም ትሁት ሰብእናንና ሰቢረ ክሳድን ገንዘብ አድርግ
ከእርኩሙ ባንበልጥ እንኳን እንደ እርኩሙ መኖር እንዴት ያቅተናል?

  ✋በአሁን ጊዜ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሁሉም ክልል ዉስጥ ከሚገኙ ከተማ መስተዳድሮች መካከል በንፅፅር ብንመለከት አርባ ምንጭ ከተማ በሁሉም መመዘኛዎች የተሻለ የሚባል ከንቲባ አላት ። ዶክተር መ...
01/09/2025



በአሁን ጊዜ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሁሉም ክልል ዉስጥ ከሚገኙ ከተማ መስተዳድሮች መካከል በንፅፅር ብንመለከት አርባ ምንጭ ከተማ በሁሉም መመዘኛዎች የተሻለ የሚባል ከንቲባ አላት ። ዶክተር መስፍን መንዛ በእውቀት በትጋትና በቅንጅት 7/24 የምሰራና ለከተማዋ አሻጋሪ የተሻሉ ዘመናዊ አዳድስ ሀሳቦችን በፈጠራ እያከለ እየሰራ ይገኛል ።

ዶክተር መስፍን መንዛ ከንቲባ ሆኖ ከተሾሙበት እለት ጀምሮ በከተማዋ ቆሞ የቆዩ ፕሮጀክቶችን ወደስራ በማስገባትና አዳድስ ፕሮጀክቶችን አስጀምሮ ከዚህ ቀደም በከተማዋ ባልተለመደ መንገድ በአጭር የወራት እድሜ ዉስጥ እንድጠናቁ በልዩ ዉሳኔና ቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ። የአርባምንጭ ከተማ የበጀት ብክነትን ለማስቀረት ልዩ ልዩ አማራጮች እየተጠቀመ ይገኛል ።

ዶክተር መስፍን መንዛ ከምንም በላይ ሌብነትን እጅግ የሚፀየፍ መሆኑ ለአርባምንጭ ከተማ አንድ መልካም እድል ነዉ። ይሄም ከግብር ከፋዩና ለልማት ከህዝብ የምሰበሰብ ገንዘብ በተገቢው መንገድ ለታለመለት አላማ እንድዉል ያስችላል ።

በዚህ አያያዝ ሌሎች አመራሮች ፣ በየሴክተሩ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ፣ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ፣ ባለሀብቶች ፣ ወጣቶችና ተቋማት አስፈላጊዉን ድጋፍ ማድረግ ከቻሉና በትጋት መስራት ከቻሉ በዶክተር መስፍን መንዛ የመሪነት (የከንቲባነት) ዘመን አርባምንጭ ከተማ በአጭር አመታት ዉስጥ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚገኙ ለኑሮ ለቱሪዝም ለኢንቨስትመንትና ለኮንፈረንስ ግንባር ቀደም ተመራጭ 3 (ሶስት) ምርጥ ከተሞች መካከል አንዷ እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለም።

❤❤❤

ጠንካራ መሪ ላይ ለምን??በኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ውስጥ የሰላም፣ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት ክልል ለመፍጠር ራዕይ ሰንቆ እና ራዕዩን አጋርቶ በሁሉም መስክ እመርታ እንዲመዘገብ ክቡር ...
01/09/2025

ጠንካራ መሪ ላይ ለምን??
በኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ውስጥ የሰላም፣ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት ክልል ለመፍጠር ራዕይ ሰንቆ እና ራዕዩን አጋርቶ በሁሉም መስክ እመርታ እንዲመዘገብ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ጠንካራ አመራር እየሰጠ ስለመገኘቱ ሁሉም ሰው ህያው ምስክር ነው። ታዲያ ይህ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ውዥንብር በእርሳቸው እና ጥቂት የፊት አመራሩ ላይ ለምን ይነዛል? ለሚለው ጥያቄ እንደውስጥ አዋቂ ጥቂት ሀቀኛ መረጃ ለማጋራት:-

1ኛ. በፖለቲካ ሜዳው የተሸነፉ እና በአጥፊ የአመራር ተግባራቸው እንዲያርፉ የተደረጉት ሀሳባቸው እና ዕቅዳቸው በመክሸፉ
2ኛ. ክልሉን በእጅአዙር የመዘወር፣ የመቦጥቦጥ እና የፊት አመሪሩን የራሱ ተልዕኮ አስፈፃሚ ለማድረግ ያቀዱት በአመራሩ ወጥ አቋም መና በመቅረቱ

3ኛ. አንዳንንድ የሀሰተኛ ሚዲያ ስፖንሰሮች በወንጀል ተጠርጥረው በመታሰራቸው ያለመክሰም የህልውና ትግል ውስጥ በመግባታቸው

4ኛ. የፊት መሪዎች ከህዝቡ ጋር ከዚህ በፊት በበነበሩ ዘመናት ባልታየ ሁኔታ ተቀራርቦ፣ ተናቦ እና ተማምኖ መሄድ በመጀመሩ ፀጉራቸውን ከመንጨት አልፈው ከእውነት የራቁ ማደናገሪያ ውሸቶችን በመደጋገም የቁራ ጩሄት ተያይዘውታል። ይህ ደግሞ በድህረእውነት ዘመን ማህበራዊ ሚዲያን ለእኩይ ተለዕኮ የሚጠቀሙ በበረከቱበት ጊዜ የሚጠበቅ ነው። ዋናው ጉዳይ እውነትን ማወቅ፣ መረዳት እና አለመወዛገብ መቻል ነው።

እያንዳንዱ በጊዜ ሂደት እየተጋለጠና እየተነቀለ መቀጠሉ ስለማይቀር ሁሉም ሰው ሀገራዊ ራዕያችን እና ክልላዊ ዕቅዶቻችን ስኬት ላይ ትኩረቱን ማድረግ ያስፈልጋል። ''ውሸት ስለተደጋገመ እውነት አይሆንም!''
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንልን!!
Brish Zewdie 🙏👌

  በማህበራዊ ሚድያዎች በጥላቻ፣ በሀሰተኛ መረጃና በፌክ አካውንት WT Media እና ሌሎችም ማንነታቸውን ደብቀው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ር/መስተዳድር በአቶ ጥላሁን ከበደና በክልሉ ከፍተኛ ...
30/08/2025



በማህበራዊ ሚድያዎች በጥላቻ፣ በሀሰተኛ መረጃና በፌክ አካውንት WT Media እና ሌሎችም ማንነታቸውን ደብቀው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ር/መስተዳድር በአቶ ጥላሁን ከበደና በክልሉ ከፍተኛ የህዝብና የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ላይ የጥላቻ ዘመቻ የሚያካህዱትን ህዝብን የማይወክሉትን አጥብቄ እቃወማለሁ!

ኃላፊ

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመጠቀም ህዝብን ከህዝብ ጋር፣ ህዝብን ከመንግስት ጋር ለማጋጨት እና ከሌሎች የአገ...
29/08/2025

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመጠቀም ህዝብን ከህዝብ ጋር፣ ህዝብን ከመንግስት ጋር ለማጋጨት እና ከሌሎች የአገራችንና የክልላችን ሰላም ለማናጋት በውስጥና በውጭ ከምንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በትስስር በመሥራት የተጠረጠሩ 9 ግለሰቦችን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት ጀምሯል፡፡

እነዚህ ተጠርጣሪዎች ማንነታችን አይታወቅም በሚል የክልሉን ህዝብ ስላምና ለዘመናት የቆየ አብሮነት እንዲሸረሸርና ጥርጣሬ እንዲፈጠር ምንም መሠረት የሌላቸውን ሀሰተኛ መረጃዎች በማሰራጨት ለዚሁ ተግባራቸው ከጀርባቸው ሆነው ጥቅም የሚሰጧቸውን ጥቂት ግለሰቦች ፍላጎት ለማሳካት ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ ናቸው፡፡

ተጠርጣሪዎች የጥላቻ ንግግርን፣ ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት እና ስም የማጥፋት እኩይ ሥራ እንደ አንድ የገቢ ማግኛ ምንጭ አድርገው እየተጠቀሙ ቆይተዋል፡፡

የክልሉ ፖሊስ ህግ በማስከበር የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በማንኛውም በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን በህግ ቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ የማጣራት ሥራውን አጠናክሮ የሚቀጥል ስለሆነ ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ፈጻሚዎችን በሀሳብና በገንዘብ በመደገፍ የራሳቸውን ድብቅ ዓላማ ለማሳካት ከጀርባ ሆነው የሚሠሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የእነዚህን ግለሰቦች መሠረተ-ቢስ መረጃ በመቃወምና የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ የክልሉ ፖሊስ በሚያደርገው እንቅስቃሴ መረጃ በመስጠት ከፍተኛ ትብብር የሚያደርጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን እያመሰገነ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ፖሊስ እየወሰደ ያለውን ሕጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያሳውቃል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን
ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ/ም
ወላይታ ሶዶ

Address

Arba Mintch

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo nation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share