15/10/2025
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ለወጣቶች ስብዕና ልማት (Mindset) የተዘጋጀ ስልጠና መድረክ ተካሂዷል።
ይህ ስልጠና የወጣቱን የዕውቀት ደረጃቸውን ከፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡና በፈጠራ ስራ ራሳቸውን እንዲያዳብሩ የሚረዳ ነው።
ዋና አላማውም
👉 የግለሰብ ፣የተቋማትና የሀገር ሠላም ፣ ለዉጥ ፣ልህቀትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ወጣቶች ሚናቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ፣
👉 በስብዕና የተካነ፣ በአፈፃፀም ብቁ ፣በአተገባበር የላቀ ፣ሠላምና ዕድገት ተኮር (Mindset) ያለው ወጣት ለመፍጠር፣
👉 የግለሰቦችና የማህበረሰብ አዕምሮ ዉቅር(Mindset) መቀየር፣
👉 የህዝብ የሥራ ትጋትና የሰላም ባህል ግንባታ እንዲጨምር ማስቻል፣
👉 የህዝብ በጎ ፈቃድና ማህበራዊ ኃላፊነት ስብዕና እንዲዳብር ማስቻል እና ከተግዳሮት (challenge) መማር የቻለ ወጣት መፍጠር ዋና ዋና አለን ያነገበ መድረክ ነው።
ባደጉ ሀገራት ሆነ ባላደጉ ሀገራት ይህንን ኃይል በአግባቡ መጠቀም፣ ስብዕና ግንባታ ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ መስራት ሀገር ለምታስበው እድገትና ስኬት ቁልፍ ድርሻ ያለው በመሆኑ እንደሀገር ለወጣቱ ትውልድ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል።
የስብዕና ልማት ስራ አዲስ ባህል ሳይሆን በውስጣችን ያለውን እምቅ ኃይል፣ እውቀትና አቅም በመጠቀም ለሀገር ብልጽግና አሻራችንን የምናሳርፍበት ትልቅ መድረክ ነው ።
ይህ የስብእና ልማት (Mindset) ስልጠና በነገው እለትም በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ እና ከዘፈኔ ከተማ ለተወጣጡ ወጣቶች የሚሰጥ ሲሆን በቀጣይም በዞኑ በሌሎች መዋቅሮችም የሚቀጥል ይሆናል።