Areka News Network-Ann

Areka News Network-Ann News

07/06/2025
19/04/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላምና ጤና አደረሳችሁ/አደረሰን !

የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት፣ በትንሳኤው ደግሞ ሠላምን ያበሰረበት ታላቅ በዓል ነው።

ህዝበ ክርስቲያኑ ላለፉት ሁለት ወራት በፆም፣ በስግደት፣ በይቅርታና ንሰሃ በመግባት ኢየሱስ ክርስቶስ ያለፈባቸውን የመከራ ቀናትና ትንሳኤ በማሰብ ለዛሬዉ የዋዜማ ቀን ደርሷል።

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰዉ ልጆች የከፈለውን የፍቅር ዋጋ የምናስብበት በመሆኑ እኛም በወንድማማችነት፣ በይቅርታ፣ በአንድነት፣ በመደጋገፍና ከቂምና ጥላቻ በመራቅ መንገዱን የምንከተልበት ሊሆን ይገባል።

ክልላችን ብዝሃ ባህል፣ ቋንቋ፣ እምቅ የመልማት ፀጋ፣ ያልተነኩ የገፀ ምድርና ከርሰ-ምድር ሀብቶች፣ ለኢንቨስትመንት ምቹና ሳቢ ከባቢ እንዲሁም በጋራ ለመልማትና ለመበልፀግ የቆረጡ ታታሪ ሕዝቦች የሚገኙበት ክልል ነዉ።

ፓርቲያችን የክልሉን ሕዝቦች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ብልጽግና ለማረጋገጥ በከተማና በገጠር ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

በክልላችን በሁሉም ዘርፎች የጀመርናቸው የልማት ዉጥኖች፣ መንግስታዊ ኢንሼቲቮች፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎችና ተስፋ ሰጪ ዉጤቶች እያመጡ ነገን ይበልጥ እንድንናፍቅና እንድንተጋ አድርገዉናል።

ከተባበርንና ከተጋገዝን የክልላችን ብሎም የሀገራችን ብልጽግና ካቀድነዉ ባጠረ ጊዜ እንደሚሳካ አመላካች ዉጤቶች እየታዩ ሲሆን ክልላዊ አንድነታችንን በማጠናከር ለጋራ ራዕያችን ስኬት መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን የመጠየቅ፣ የመደጋገፍና የመረዳዳት ኢትዮጵያዊ ባህላችንን በመጠበቅ እንዲሆን በዚህ አጋጣሚ አደራ ለማለት እወዳለሁ።

በድጋሜ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ ።

አቶ ገ/መስቀል ጫላ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

19/04/2025

የአረካ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አስራት ብርሃኑ ለ2017 ዓ.ም የስቅለትና ትንሳኤ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

በዓሉ የሠላም ፣የፍቅር ፣የደስታ ፣የመተሳሰብና የብልፅግና እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ

ኢየሱስ ክርስቶስ መከራና ሞት፣ ግፍና ስቃይን፣ ሲዖልና መቃብርን አሸንፎ የተነሣበት የስቅለትና ትንሣኤ በዓል በየዓመቱ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በልዩ ሁኔታ ይከበራል።

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍፁም ፍቅር ለማሳየት አንድያ ልጁን ልኮ በማስተማር፣ በመፈወስ እና በመስቀል በመዋል በሶስተኛም ቀን ሞትን ድል በመንሳት በትንሳኤው የሰው ልጅ ሀጥያት ለማስተሰረይ የከፈለውን ዋጋ እያሰብን በዓሉን በፍቅር ሊናከብረው ይገባል።

ለሰው ልጆች መዳንና ለፍቅር የተከፈለውን ዋጋ ትምህርት አድርገን በመውሰድ እርስ በርሳችን በመተሳሰብ፣ በመቻቻል፣ በመከባበርና ሠላምን በመዝራት የበዓሉን አስተምሮ በተግባር ማሳየት አለብን።

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሰው ልጆች ደህንነት ሲል ያጋጠመውን መከራ ፣ ስቃይና ግርፋት በፅናት ተቋቁሞና ሞትን አሸንፎ የዲያብሎስን ቀንበር ሰብሮ የሰውን ልጅ ወደ ብርሃን ያሻገረበት የፅናት ፣ የአሸናፊነትና የነፃነት በዓል ተምሳሌት በመሆኑ አርአያነቱ የጎላ ነው።

ይቅር ባይነት፣ መቻቻልና መተሳሰብ አሻጋሪ ዕሴቶች በመሆናቸው በየአቢይ ፆም ወቅት የእምነቱ ተከታዮች ያሳየነውን የይቅር ባይነትና የመተሳሰብ ዕሴቶቻችንን የሁልጊዜ ማድረግ ይጠበቅብናል።

እጅግ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የከተማችን ነዋሪዎች በመሉ ከተማችንን አንድ ደረጃ ከፍ ማድረግ የምንችለው በትብብር ስንሰራ ብቻ ነው። ስለዚህ በዕድገት ጎዳና ላይ የምትገኘውን ከተማችንን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ከመንግሥት ጎን በመሆን የትብብር እጃችሁን እንደምታጠናክሩ እምነቴ የፀና ነው።

በያዝነው ዓመት የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት ለመፈጸም ሁሉን አቀፍ ጥረት ሊደረግ ይገባል።

እንደ ከተማ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክረን ለማስቀጠልና ያሉንን እምቅ ፀጋዎችን ወደ ተጨባጭ ሀብት በመቀየር እምርታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ በርትተን መስራት ይጠበቅብናል።

በዓሉን ስናከብር ካለን በማካፈል ፥አቅመ ደካሞችን በመርዳት በፍጹም በፍቅርና ደስታ መሆን ያስፈልጋል።

አቶ አስራት ብርሃኑ
የአረካ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
መልካም በዓል

ይህ ባህርዳር ወይም አዋሳ እንዳይመስላችሁ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ እየተሠራ የሚገኝ ኮሪደር ልማት ነው!
08/04/2025

ይህ ባህርዳር ወይም አዋሳ እንዳይመስላችሁ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ እየተሠራ የሚገኝ ኮሪደር ልማት ነው!

 ! የባለራዕይ አመራር ስለ ዘላቂ ለውጥ የሚያመለከት ነው። ይህ ተወዳጁ የህዝብ መሪ በዞናችን በሁሉም ዘርፎች የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን እና ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጡ ተጨባጭ ስራዎች...
12/03/2025

!

የባለራዕይ አመራር ስለ ዘላቂ ለውጥ የሚያመለከት ነው። ይህ ተወዳጁ የህዝብ መሪ በዞናችን በሁሉም ዘርፎች የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን እና ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጡ ተጨባጭ ስራዎችን በጥቂት ወራት ውስጥ መሰራት የቻለና እየሰራ የሚገኝ ተወዳጅ መሪ ነው። በዚህ መሠረት፣ ባለራዕይ አመራር ማህበረሰቡን ወደ ማሻሻያ እና ወደ ልማት የሚያመራ ዋና መሪ ናቸው።

ከቃል በላይ ተግባር የሚመሰክረው ቆራጥና ጀግና መሪ፣ እጅግ ከፍተኛ ብስለት የሞላበትን አመራር ጥበብ በመጠቀም ውጤት እያሰመዘገቡ ያሉ ጀግና መሪያችን ናቸው የተከበሩ አቶ ጴጥሮስ።

ደግሞም እውነተኛ ባለራዕይ መሪ ለዘላቂ ለውጥ የሚሠሩ ሲሆን፣ ተፅዕኖአቸው እጅግ በጣም የጎላ ይሆናል። ትውልዶችን ለልዩ ለውጥ ይሰራሉ። ስለዚህ፣ ባለራዕይነት መሪ የህዝብ ዕድገት ለማስቻል አስፈላጊ እንደሆነ ይታየኛል ለዚህ ደግሞ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪያችን የተከበሩ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም ማሳያ ናቸው።



ፈጣሪ_ሀይልና_ጉልበት፣ጤናና_እድሜ፣ይስጥልን_ጀግና_መሪያችን!!

የወላይታ ህዝብ እድገትና ልማት ጠላት የሆኑ የሰይጣን ቃል አቃባዮችን አሽቀንጥረን ለማጣል የሚንገደድበት ጊዜ ላይ መሆናችን ስንቶቻችን እናውቃለን?ግለሰቦቹ ለራሳቸው ምቹ አካባቢና ቦታ እየኖሩ...
12/03/2025

የወላይታ ህዝብ እድገትና ልማት ጠላት የሆኑ የሰይጣን ቃል አቃባዮችን አሽቀንጥረን ለማጣል የሚንገደድበት ጊዜ ላይ መሆናችን ስንቶቻችን እናውቃለን?

ግለሰቦቹ ለራሳቸው ምቹ አካባቢና ቦታ እየኖሩ በብዙ ሥራ አጥ ወጣቶች ተከባ የተለያዩ ልማቶች ናፋቂ ሆኖ የሚገኘውን ወላይታ ለልማት የሚመጡ ባለሀብቶችና የተለያዩ ድርጅቶች በአካባቢው እንዳያለሙ ለማሸበር ለት ቀን እየሰሩ የሚገኙ የዲያስፖራ ክንፍ ነውጠኞች ናቸው። እነሱም አቶ አንዱዓለም ታደሰ፣ Isaak Ferenj ፣ስደተኛ Natinael Gecho Betalo ፣ስደተኛ Tajura Lambebo Gota እና ተከታዮቹ ናቸው።

እግለሰቦቹ ለወላይታ ህዝብ ምንም አይነት ልማት እንድሰራ የማይፈልጉ ፣ ጥላቻን ያረገዙ ፣ ከፋፋይ አጀንዳ ተሸክመው የሚጓዙ፣ በአካባቢው ሰላም እንዳይኖርና ልማት እንዳይሰራ እንቅፋት እየሆኑ ይገኛሉ።

እነዛ የሰይጣን ተላላኪዎች በዚህን ጊዜ ወላይታን እየመሩ የሚገኙ መሪዎች የአካባቢውን ሥራአጥነት ቁጥር ታሳቢ በማድረግ ከዚህ በፊት እየተሰሩ የቆሙ ልማቶችም ብሆነ አድስ የልማት ሥራዎችን ከፈደራል እና ክልል ከሚገኙ አካላት ጋር በመተባበር አግባብ በሆነ ሁኔታ እየሰሩና እያሰሩ የሚገኙ ድንቅ መሪዎች ስም የማጥፋት ዘመቻ የከፈቱ ፀረ ወላይታ ናቸው።

ከላይ በስም የተጠቀሱ ግለሰቦችና የነሱ አጀንዳ አራጋቢ ተከታዮቻቸው የወላይታን ህዝብ የልማት ፍላጎት ባላገናዘበ ሁኔታ በአካባቢው ምንም አይነት ልማት እንዳይሰራ አካባቢው የሁኬት ቀጠና እንድሆን በየቀኑ አጀንዳ ይዘው ህዝብን እያሸበሩ ይገኛሉ።

የሌላ አካባቢ ዲያስፖራዎች ለአካባቢው ህብረተሰብ በስሙ የተሻለ ልማት ይሰራሉ፤ የኛዎቹ ደግሞ ለግል ፍላጎታቸው የሚጥሩ ናቸዉ።

ማንም እንደሚያውቀው ወላይታ ሰላማዊ አካባቢ በመሆኗ ከየትም አካባቢ የሚመጡ አልሚ ባለሀብቶች በአካባቢው ደስተኛ ሆነው ልማት እየሰሩ ይገኛሉ።

እነዚያ አውሬዎች ከዚህ በፊትም ብሆን የወላይታን ወጣት እያሳሳቱ ለተለያዩ የጥፋት ድርጊት እያጋለጡ አካባቢው ላይ ሰላም እንደሌለ በማስመሰል የጥላቻ ዘር ፍሬ እየበተኑ የቆዩ እንደሆኑ የወላይታ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል።

ባለፉት ሁለት አመታት የወላይታ መንግስት ሠራተኛ ደመወዝ አጥተው ስሰቃይ ምንም ያልመሰላቸው ፣ የተለያዩ መሰረተ ልማት ሥራዎች በግለሰቦች ተተንኮል ሴራ ተኮላሽቶ ስቆም ዝምታውን የመረጡ እና ወዘተ ዛሬ ይህ ሁሉ በተሻሉ አመራሮች ጥሬት መስመር ስይዝ ለሥራአጥ ወጣቶች ሥራ እድልን ለመፍጠር በታሰበ መንድ አንዳንድ ሜጋ ፕሮጄክቶች ወደ ሥራ ስገቡ እነዚያ አዋቂ ነኝ ባይ አሸባሪዎች እያደናቀፉ እንደሆነ መላው የወላይታ ህዝብ ልያውቅ ይገባል።

እነዚያ ግን ዲያስፖራ ነን ባዮች እና ጥቅት ስደተኞች ለወላይታ አሻራቸውን ለማሳረፍ ከመፈለጋቸው ይልቅ ሌሎች መጥተው እንደዳይሰሩ አካባቢው የሁኬት ቀጠና እንድሆን ታትረው እየሰሩ ይገኛሉ።

ከዚህ በኋላ የወላይታ ህዝብ የራሱን የውስጥ አንድነትን በማጠናከር ከሚሰሩ አመራሮች ጋር በመተባበር ለወላይታ የተሻለ ልማት ለመስራት የውስጥ አንድነትን ያጠናከረ መሆኑን እነዚያ አደናቃፊ ኃይሎችና አጀንዳ ቀያሪዎች ልያውቁት ይገባል።

አንድ የተማረ ዲያስፖራ ዶ/ር ታምራት እራሾ ለተወለደው አካባቢና ላሳደገው ማህበረሰብ በራሱ ወጪ በዳሞት ወይዴ ወረዳ ግራራ አካባቢ 12 ኪ/ሜ ጠጠር ፕስታ መንገድ ስያሰራ ያያችሁ ይመስለኛል እነዚያ ከላይ በስም የተጠቀሱ ግለሰቦች ግን በሌሎች ባለሀብቶችና መንግስት የሚሠሩ ልማቶችን በመቃወም በህዝብ ዘንድ ፀብ እየዘሩ ይገኛሉ። ስለዚህ መላው የወላይታ ህዝብ እነዛ አውሬዎችን አደባባይ ወጥተው ማዉገዝ አለበት!!

ለወላይታ ህዝብ ዘላቂ ዕድገትና ልማት ለማምጣት እየተጋ የሚገኝ ማርሽ ቀያርና ጀግና መሪየሀገር ለውጥ እድገትና ከፍታ የሚፋጠነው በመሪዎች የአመራር ብቃት፤ ሰርቶ የማሰራት ጥበብና ብልሃታቸው ...
10/03/2025

ለወላይታ ህዝብ ዘላቂ ዕድገትና ልማት ለማምጣት እየተጋ የሚገኝ ማርሽ ቀያርና ጀግና መሪ

የሀገር ለውጥ እድገትና ከፍታ የሚፋጠነው በመሪዎች የአመራር ብቃት፤ ሰርቶ የማሰራት ጥበብና ብልሃታቸው ከፍ ሲል ነው።

መሪ የሀገር ለውጥ ምሳሌ ሊሆን የሚችለው በሱ የመሪነት ጊዜ የታዩ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ እድገት ከፍታዎች የተገኙ ሲሆን ብቻ ነው።ይህንን በጥቂት ወራት ውስጥ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን ማየት ችለናል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም የመሪነት ብቃትም ከዚሁ አንፃር የሚለካ ነው። በወላይታ ዞን ባለፉት ጥቂት ወራት አመልካች ውጤቶች በተጨባጭ የተጀማመሩ ትላልቅ ፕሮጀክት ልማቶች እየተከናወኑ የቻሉት በዚህ መሪና ከእሱ ጋር ያሉ አመራሮች ጥረት ነው።

መሪዎች ሀሳባቸው ዕቅዳቸው በጥበብ የተሞላ፤ ህዝባዊ ፍቅር ያላቸው፥ ሀገርና ሰው ወዳድ ሲሆኑ፤ ሰርተው በማሰራት አርአያ ሲሆኑ የዚያን ጊዜ ለውጥ ትፈጥናለች ፍትህ ትነግሳለች ትውልድ ይነቃቃል።ለዚህም የተጀማመሩ ስራዎች ህያው ምስክር ናቸው።

ይህንን የተጀማመሩ የልማት ስራዎችን ለማደናቀፍ በዋና አስተዳዳሪው ላይ ስብዕና የሚነኩና ሀሰተኛ መረጃዎች ጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ሆነው በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ጀምረዋል።

እንዲሁም በወላይታ እና አከባቢውን የስጋትና የሁከት ቀጠና ለማድረግ አቅዶ እየሰሩ ይገኛሉ። ይህ ሰላም ወዳዱ በመላው ወላይታ ህዝብ ትብብር እየከሸፈ ይገኛል።

ይህ ዘመቻ ደግሞ ለእሱ ጀግንነትንና ጥንካሬን የሚገለጽ እንጅ ክብር የሚቀነስ አይደለም ምክንያቱም በዚህች ሀገር መልካም፤ ደግ እና ጀግና ሰዎችን ሌቦች፣ ሥነምግባር የሌላቸውና ፀረ-ሰላም ሀይሎች አይወዱትም፡፡

የዞናች ዋና አስተዳዳሪውና ሌሎች የፊት አመራሮችም የዕድል ጉዳይ ሆኖ በጥበብ የተካኑ ናቸው። ወላይታ ተለውጣ አምራ ደምቃና ለምታ ለሀገር ተምሳሌት እስክትሆን አያርፉም ሁሌም በስራ ላይ ናቸው ፥እንቅልፍ የላቸውም አይደክሙም ለነሱ የህዝብ ለውጥ ከሁሉም ነገር በፊት ተቀዳሚ ተግባራቸው ነው።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪን የወላይታ የበኩር ልጃችን አድርገን እንወስዳዋለን ምክንያቱም ወላይታ በእሱና በሌሎች የአመራርነት ብቃት ፈክታ ስለታየች፣ የተወዘፉ ጥያቄዎች እየተመለሱ፣ ልማቶች ስለተንሰራፉባት፤ ለውጥ ስለገነነባት...!

በወላይታና አከባቢው ሁከትና ውዥንብር ለመፍጠር በውጭ ሀገር ሆነው ከግብረአበሮቹ ጋር በመሆን እየሰሩ ያሉ አሸባሪዎች፤የወላይታ ህዝብ ሠላምና ልማት እንቅልፍ የነሳቸው እነዚህ አካላት በወላይታ...
09/03/2025

በወላይታና አከባቢው ሁከትና ውዥንብር ለመፍጠር በውጭ ሀገር ሆነው ከግብረአበሮቹ ጋር በመሆን እየሰሩ ያሉ አሸባሪዎች፤

የወላይታ ህዝብ ሠላምና ልማት እንቅልፍ የነሳቸው እነዚህ አካላት በወላይታ ውስጥ የሚኖሩ ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን በፈረንሳይ እና ኬንያ ሀገር ቁጭ ብለው ሀሰተኛ እና የተቀነባበሩ መረጃዎች በየደረጃው የሚገኙ የህዝብ መሪዎች ሰብዕና የሚነኩ ሀሰተኛና የተቀነባበሩ መረጃዎች እያሰራጩ ይገኛሉ።

እነዚህ አካላት የወላይታን ህዝብ ሠላምንና መረጋጋትን የማይፈልጉ እና የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት በቡድን ተደራጅተው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ዘመቻ ከፍተዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያምን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ላይ የህዝቡን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የጀመራቸውን ስራዎችን እንዳይሰሩ ለማድረግ እና ለማደናቀፍ በተለያዬ ጊዜ ስብዕና የሚነኩ መረጃዎችን እያሰራጩ ይገኛሉ።

1ኛ. የወላይታ ታይምስ ፔጅ ባለቤት ናትናኤል ገቾ ይባላል። አሁን በኬንያ ነው የሚኖረው። ግለሰቡ ሴሰኛ፣ ለገንዘብ ብሎ የገዛ ቤተሰቹን እና ወዳጆቹን የካደ፣ የሰውን ምስት አስረግዞ ከሀገር ኮብልሏል። ይህ ግለሰብ ሀይማኖት የሌለውና 24:00 ሠዓት በሚባል መልኩ በጫትና በመጣጥ ቤቶችን ጊዜውን የሚያሳልፉ ነው።

2ኛ.ታጁሬ ላምቤቦ ይባላል፣ ይህ ግለሰብ ከዱባይ ሀገር የመጣችውን አገባሻለሁ ብሎ አብሮ ጥቂት ቀናት ከኖረ በኃላ ከአምስት ዓመት በላይ በሰው ቤት ህይወቷን ለመቀየር ለፍታ ሰርታ ያመጣችውን ገንዝብ ሠርቆ በስደት ወደ ኬንያ ገብቷል። ይህች ምስክን ሴት አሁን እርጉዝ ናት። የሚትበላውንና የምትጠጣውን በማጣት በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንድትወድቅ አድርጓታል።

3ኛ.ሌላውና አሸባሪው እና የNuso አካውንት ባለቤት ሚኖታ ማቴዎስ ይባላል። አሁን የሚኖረው በፈረንሳይ ነው። ግለሰቡ የወላይታ ህዝብን ለማዳከም ገንዘብ ተከፍሎለት ዓላማ አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

እነኚህ አካላት ለወላይታ ህዝብ ዕድገትና ልማት የሚመኙ ሳይሆኑ ወላይታን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ከአሸባሪዎች ጋር አቅዶ እየሰሩ ናቸው። ሰለዚህ ህዝቡ የእነዚህ እኩይ ዓላማን "ሆ ብሎ ተነስቶ" ማክሸፍና መታገል ያስፈልጋል።

በሀሰተኛና የተቀነባበረ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ያደገ፣ የበለጸገ፣ የለማ ህዝብና ሀገር የለም። ሁሌም ከመተቸት ህዝቡን የሚጠቀሙ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እናድርግ።

እኔ የህግ አወቂ ነኝ በማለት ከሙያ ስነምግባር ባፈነገጠ መንገድ ታላቁን የወላይታ ህዝብ ለማወክ የሚፈልግ አካል ማንም ቢሆን መውደቂያው እጅግ የተፋጠነ ይሆናል።ለተማሪነው ሙያ ፣ከህዝብ ያገኘ...
08/03/2025

እኔ የህግ አወቂ ነኝ በማለት ከሙያ ስነምግባር ባፈነገጠ መንገድ ታላቁን የወላይታ ህዝብ ለማወክ የሚፈልግ አካል ማንም ቢሆን መውደቂያው እጅግ የተፋጠነ ይሆናል።

ለተማሪነው ሙያ ፣ከህዝብ ያገኘነው ውክልና በአግባቡ ሲንጠቀም ነው መጨረሻው ሊያምር የሚችለው። በእድልም ሆነ በእውቀት አንድ ነገር ሲናገኝ ቆም ብሎ ማሳብ ከምንም በላይ ቀዳሚ ሊሆን የሚገባ ጉዳይ ነው።

ወደ ዛሬው መልዕክት ጋር ሲመጣ አቶ አሰፋ አየለ የተባለው ጠበቃ ነኝ ባዩ እኔ የህግ አወቂ ነኝ በማለት በየጊዜው ህዝብን በማወክ የግል ዓላማውን ለማሳካት በየጥሻ ቤቱ እንዲሁም በየማህበራዊ ድረ ገፅች በግልና በተለያዩ ሀሰተኛ አካውንቶች መልዕክቶችን እያሰራጨ መሆኑን በግልጽ የተረጋገጠ ጉዳይ ሆኗል።

አቶ አሰፋ አየለ የሙያ ስነምግባሩን ወደ ጎን በመተው በተለያዩ ጊዜ ህዝብን ከሚጠቅሙ ይልቅ የሚጎዱ ሀሳቦችን ሲያንጸባርቅ ቆይቷል። መንግሰትና ህዝብ አብሮ እንዳይኖር ፣ ብሔር ከብሄር ጋር ፣አንድ አካባቢ ከሌላው አከባቢ ጋር እንዲጋጭ መርዝ እየረጨ የቆየ ግለሰብ ነው።

ከወትሮው በተለየ መንገድ ሰሞኑ ወላይታ ሶዶን ማዕክል በማድረግ በአራቱ አቅጣጫ ጀግናውን የወላይታ ህዝብ በሰፈር ጭምር ለማከፋፈል እየሠራ መቆየቱን በተደረገው ጥብቅ ክትትል ያገኘነው የቪዲዮ እና ኦዲዮ መረጃ ያመላክታል።

በጣም አሳዛኙ ነገር በወላይታ በርካታ የተማሩና በህግ ዕውቀት ከፍ ያሉ ጠበቃዎች ባሉበት ራሱን ጣሪያ ላይ በመስቀል ከእኔ በላይ የለም ይላል። እኔ የህዝብ ተወካይ ነኝ ይላል ። ማነው ቆይ ውክልና የሰጠው?

የተማረ የህግ አወቂ ሰው በቅድሚያ የግል ስነምግባሩን ያስተካክላል ፥ራሱን ደግሞ ለስራው ያዘጋጃል እንጂ ሁልጊዜ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ በመውጣት ማንም ባልሰጠው ውክልና እኔ የህዝብ ነኝ በማለት ተራ የሆነ የሰፈር ወሬ እየፈቨረክ አይውልም።

በመግቢያው እንደ ጠቀስኩት አቶ አስፋ አየለ ከሚሆነው ድርጊት ሲንመለከት የህግ አወቂ ነኝ የሚለውን ከግል ጥረት ይልቅ በዕድል ያገኘ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል።

አሁንም ቢሆን ከዛ ድርጊት የማይወጣ ከሆነ እመኑኝ ህዝብ ይተፈዋል። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከህዝብ አይን የሚያመልጥ አንዳች ነገር አይኖርም!!

የመጨረሻ ምክር ሊሰጥህ አቶ አስፋ መጀመሪያ ለሙያው ክቡር ይኑርህ ! በተጨማሪ ከሰፈርተኝነት ውጣ!!

#ሰናይ ምሽት!

በአቶ ባዳሞ የሚመራው   ተብለው የሚጠራው ፔጅ ሰሞኖ ቆይ ምን አስቦ ነው የሚንቦጫረቀው ? እኔን ግን በጣም የሚያሳዝነኝ ፈረንሳይ እና ጣሊያን ሀገር ቁጭ ብሎ የዛ መርዛማ ሰውየው የፖለተካ ...
07/03/2025

በአቶ ባዳሞ የሚመራው ተብለው የሚጠራው ፔጅ ሰሞኖ ቆይ ምን አስቦ ነው የሚንቦጫረቀው ? እኔን ግን በጣም የሚያሳዝነኝ ፈረንሳይ እና ጣሊያን ሀገር ቁጭ ብሎ የዛ መርዛማ ሰውየው የፖለተካ መጠቀሚያ መሆናቸው ነው ።

ወላይታ ለራሱ የሚሆነውን ጠንቅቆ ያውቃል። ዛሬ ላይ ወላይታ በጠንካራ አመራሮች በልማት ጎዳና ላይ ትገኛለች ከሌቦች ቀንበር ተላቃለች ይህ የማይካድ ሀቅ ነው።

ተብሎ የሚጠራው ፔጅ ሰሞኑ ከዛ መርዛማው ጋር ያልተፈለገ ጋብቻ በመፍጠር ወላይታን ከሌቦች ፣ከሰራቅዎች እና ከተደራጁ ዘራፊዎች ያዳኑ ጀግና የወላይታ አመራሮች ስም የማጥፋት ዘመቻ መክፈቱን በግልጽ አይችላሁ። ይህ ደግሞ ከበስተጀርባው ምን እንዳለውም መገመት ቀላል ነው።

በግልጽ አማርኛ ወላይታ ከተደራጁ ዘራፊዎች ቀንበር ወጥታ ዛሬ ላይ በልማት ጎዳና ላይ ትገኛለች።

Address

Areka
79

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Areka News Network-Ann posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share