Areka News Portal - ANP

Areka News Portal - ANP Real and timely Information all over wolaita

04/06/2025

. ........ ፖራ ወላይቶ
😭😭😭😭😭😭😭😭😭
🙄🙄🙄🙄😭😭😭😭😭
የወላይታ ዞን አንዳንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች በ12 ሚሊዮን ብር የታክስ ስወራ ቅሌት ከሀብታሞች ጋር በመመሳጠር ተከሰሱ።

በወላይታ ዞን በርካታ የአካባቢ የመንግስት ባለስልጣናት ከሀብታሞች ጋር በመመሳጠር ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ከቀረጥ ለማምለጥ መሞከራቸው ከታወቀ በኋላ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ቅሌት እየተፈጠረ መሆኑን ገቢዎች የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ አመልክቷል።

ለምርመራው ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳረጋገጡት የወላይታ አንዳንድ አመራር አካላት ተደማጭነት ካላቸው የንግድ ባለቤቶች ጋር በመቀናጀት የፋይናንሺያል መረጃዎችን በማጭበርበር፣ የንግድ ገቢን ለመደበቅ እና መደበኛ የታክስ ኦዲት እንዳይደረግ ለማድረግ ጥረት አድርገዋል።

“የታክስ ግዴታዎች ሆን ተብሎ በተጭበረበሩ ሰነዶች እና በህገወጥ ስምምነቶች የተዘገበ ስለመሆኑ አስተማማኝ ማስረጃ አግኝተናል” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የገቢ ከፍተኛ ባለሙያ ተናግረዋል። "ይህ የገንዘብ ህግ መጣስ ብቻ ሳይሆን የህዝብ አመኔታ ክህደት ነው።" ብለዋል።

የተጠረጠረው እቅድ የግንባታ ተቋራጮች፣ የሆቴል ባለቤቶች እና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አስመጪና ላኪ ድርጅቶችን ያካተተ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች አመራር አካላት ግምገማዎችን ለመቀየር እና የማስፈጸሚያ እርምጃዎችን ለማዘግየት ጉቦ እንደሚቀበሉ ተነግሯል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው አመራሮች ማንነት በይፋ ባይገለጽም፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና ተቃዋሚዎች ግልጽነትና ፈጣን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ መጠየቅ ጀምረዋል።

ሰሙ እንዳይጠቀስ የሚፈልግ መረጃ ሰጪ "ይህ የሚያሳየው በሕዝብ ተቋሞቻችን ላይ ሙስና ምን ያህል ሥር የሰደደ መሆኑን ነው" ብለዋል። "ለሆስፒታል፣ ለትምህርት ቤት እና ለመንገድ መሄድ የነበረባቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር በግል ኪስ ውስጥ ገብቷል።"

የህግ ባለሙያዎች ቅሌቱ ሙስና፣ ማጭበርበር፣ የታክስ ህግን ማደናቀፍ እና የመንግስት መስሪያ ቤቶችን አላግባብ መጠቀምን ጨምሮ ክስ ሊመሰርት እንደሚችልና ይህም በኢትዮጵያ በተሻሻለው የፀረ-ሙስና ህግ መሰረት ከባድ እስራት እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ጉዳዩ በቀጣዮቹ ቀናት ለፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለተጨማሪ ምርመራ እና ክስ ሊቀርብ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

10/05/2025

ዘሩን እንብላ ወይስ እንዝራው ⁉

የጃ - WAR ማንነት ሲገለጥ! ጃል ጃዋር መሃመድቀደም ብሎ ብዙ ተከታይ እና ምዕመን የነበረዉ ጀዋር መሃመድ ከበቡሽ ከጊዜው ጋር መዘመን ባልቻለዉ ፖለቲካዊ እይታዉና አስተሳሰቡ እንዲሁም የለ...
16/11/2024

የጃ - WAR ማንነት ሲገለጥ! ጃል ጃዋር መሃመድ
ቀደም ብሎ ብዙ ተከታይ እና ምዕመን የነበረዉ ጀዋር መሃመድ ከበቡሽ ከጊዜው ጋር መዘመን ባልቻለዉ ፖለቲካዊ እይታዉና አስተሳሰቡ እንዲሁም የለቀዉ ያለዉ የአመፅ ፖለቲካ አዉራነቱ በብዙዎች ዘንድ ያለዉን ተቀባይነት እየሸረሸረ እያጠፋ የት ይኑር የት ማንም ግድ እስከማይሰጠዉ ድረስ ደርሷለ፡፡ ይህ አልዋጥለት ያለዉ ጀዌ ይሄን ሰሞን የሸኔ ቃል አቀባይ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡ የኦሮሚያ ህዝብ በሰላም ግቡ እያለ በአደባባይ የሚለምናቸዉን ፣ መንግስት የሰላም በሩን ወለል አድርጎ ከፍቶላቸዉ እየተቀበላቸዉ ያሉትን የሸኔ ታጣቂዎችን ከኔ በላይ ለእናነት ብሎ የባጥ የቆጡን እየቀባጠረ ይገኛል፡፡ ይህ ሰዉ በዚህ ልክ ሲዘቅጥ መመልከት ግን አሳፋሪ ነገር ነዉ ፡፡ ታረክ ይመዘግበዋል በትዝብት ይይዘዋል ፡፡

በጌታሁን ጋረደው (Getahun Garedew) እና በ ናትናኤል ጌቾ (Natnael Gecho) የሚመራው Wolaita Times የተባለ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ የደቡቧ ፈርጥ በሆነችው አርባ ምንጭ...
23/10/2024

በጌታሁን ጋረደው (Getahun Garedew) እና በ ናትናኤል ጌቾ (Natnael Gecho) የሚመራው Wolaita Times የተባለ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ የደቡቧ ፈርጥ በሆነችው አርባ ምንጭ ከተማ በማንኛውም መንገድ የልማት እንቅስቃሴዎችን ሲያዩ አይናችው ይቀላል፣ “አርባምንጭ ስታዲየም ሊገነባ ነው” ሲባል ያዙኝ ልቀቁኝ ? የወንድም ህዝብ ልማት በክፉ ለምን?

የአርባምንጭ ስታዲየም “የአንድ ሺህ ብር ፕሮጀክት” በመባል ይታወቃል። ጋሞ የሃሳብ ምንጭ፣ የገንዘብ ምንጭ እና ሰላም ምንጭ የጋሞ አመራሮች አስተባባሪነት የጋሞ ህዝብና የጋሞ ወዳጆች የገንዘብ ምንጭነት አርባምንጭ ስታዲየም እውን ይሆናል።

በወላይታ ህዝብ ስም የተከፈተ ሚዲያ ይሁን እንጅ ከታላቁ የወላይታ ህዝብ ለይተን ነው የምናየው። በእነዚህ ከፋፋይ፣ ፀረ ልማትና ፀረ ብልፅግና በሆኑ ግለሰቦች የሚሰራጩ ማንኛውም መረጃ የፅንፈኞች እንጅ የወላይታን ህዝብን እንደማይወክል እተማመናለሁ ነገር ግን የወላይታ ምሁራንና አባቶች ፅንፈኞች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማረምና በማስተማር ሞራላዊ ግዴታቸውን በመወጣት ለህዝቦች ዘላቂ ልማትና ሰላም በጋራ እንዲሰሩ በታላቅ አክብሮት እጠቁማለሁ።

እኛ ስራ ላይ ነን!

ኢትዮጵያ በትምህርቱ ዘርፍ ከተማሪ ምገባ ጀምሮ እያስመዘገበችው ያለው ውጤት ለሌሎች ሃገራት ተነሳሽነትን እንደሚፈጥር አለም ባንክ ዘግቦታል
13/09/2024

ኢትዮጵያ በትምህርቱ ዘርፍ ከተማሪ ምገባ ጀምሮ እያስመዘገበችው ያለው ውጤት
ለሌሎች ሃገራት ተነሳሽነትን እንደሚፈጥር አለም ባንክ ዘግቦታል

ወትሮም ስማችን ይለያል፤አቅማችን ተወዳዳሪ የለዉም‼የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች💪
13/09/2024

ወትሮም ስማችን ይለያል፤አቅማችን ተወዳዳሪ የለዉም‼የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች💪

በወላይታ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈአረካ፣ ሐምሌ 29/ 2016 (Areka News Portal) በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 5 ሠዓት ገደማ በወላይታ ዞን ካዎ...
05/08/2024

በወላይታ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አረካ፣ ሐምሌ 29/ 2016 (Areka News Portal)
በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 5 ሠዓት ገደማ በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

እስከ አሁን የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ መረጋገጡን እና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል መገለጹን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከክረምቱ ማየል ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደራሽ ውኃ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የሚያስከትሉት አደጋ በመሆኑ ሕብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡
Areka News Portal - ANP

⚠️⚠️⚠️
05/08/2024

⚠️⚠️⚠️

በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ አደጋ ለሞቱት ወጎኖች መጽናናትን እመኛለሁ።ወንድም ህዝብ በሆነው በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ዛሬ ...
22/07/2024

በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ አደጋ ለሞቱት ወጎኖች መጽናናትን እመኛለሁ።

ወንድም ህዝብ በሆነው በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ለሞቱት ወጎኖች የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልፃለሁ።

በሰው፣ በንብረትና በአከባቢወ ላይ ያደረሰው አደጋ እጅግ የሚያሳዝንና ልብ የሚሰብር በመሆኑ ጥልቅ ሀዘን ተስምቶናል።

ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች እና ወዳጆች ከልቤ መጽናናትን፥ ለነፍሳቸው ዘላለማዊ እረፍትን እንድያገኙ እመኛለሁ።

ዜናውን በሰማው ጊዜ በተለይም የሟቾች ቁጥር ከ55 በላይ በመደረሱ እጅግ የሚያስደነግጥና የሚያሳዝን በመሆኑ ያጋጠመውን የተፈጥሮ አደጋ በጋራ በመሆን ወንድም የሆኑ በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ነዋሪዎች ከጎናችሁ ነን።

ለሞቱት ወገኖቻችን፣ መላው ቤተሰቦችና ባልደረቦቻቸው እና በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች እንዲሁም ለመላው ዞን ህዝቦች በራሴና በ Areka News Portal ስም መፅናናትን እመኛለሁ።

Address

Areka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Areka News Portal - ANP posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share