Benishangul Gumuz Media

Benishangul Gumuz Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Benishangul Gumuz Media, Media/News Company, assosa, Asosa.

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ የክልሉን ህዝብና መንግስት የመረጃ ፍላጎት በጋዜጠኝነት መርህ ላይ የተመሰረቱ አስተማሪ፣አዝናኝ፣ አሳዋቂ ዜናዎች፣ ፕሮግራሞች እንዲሁም ዶክመንተሪዎች ሰርቶ በማቅረብ በኤሌክትሮኒከስ ሚዲያ እና በማህበራዊ ሚዲያ የአየር ሰዓት ሽፋን ለማዋል የተቋቋመ ድርጅት ነዉ።

Almáktabá áddahilú mbá Ikqilíím Benishangúl Gumúz daaó ajjáiza maabí mbágú shákqáló ashúkqúlá pqiishíéqí tha almeezaníá ...
05/08/2025

Almáktabá áddahilú mbá Ikqilíím Benishangúl Gumúz daaó ajjáiza maabí mbágú shákqáló ashúkqúlá pqiishíéqí tha almeezaníá mbá 2017rú HI.

Hamlé;29/11/2017HI (BGM) Asósa: Shá álé ákkada annatííjá almáktabá áddahilió mbá Ikqilíím Benishangúl Gumúz muusqó albarnámij hu áné dáá ajjáiza u alwárgá áshukurú maabí mbágú shákqáló ashúkqúlá pqiishíéqí tha almeezaníá mbá 2017rú HI.

Abbá Tafarí Abábe mbá ma agúr tha almáktabá áddahilúyú mbá Ikqilíím Benishangúl Gumúz mín aañá zííné, shá máré ádqañthiña addáhílí álmaktabaló ashán maré shákqálá ashúkqúlá sqárí ñinéñ bikqó maré shá máré muusqa albarnámíjá ájjaizó hu u mbá áshukurú ñinéñ roothóne.

Almáktabáló thá sqiríñá kqithané shá áné buura algíbir alú 4.6maliyú gádáráné áné buura alú 110 min míá u tha almaazaníá mbá 2018HI 8 maliún shá máré adá buura alú kqithaga máré sqiríñ ñinéñ pqúlíñónáneqi.

Tha almáktabá áttálmíá álbilaanúyú mbá álmudunú maabá ma agúr u mbá maaó wakkalá mín tha almáktabá ágúrá álqikqiliimú na abbá Mahámmad Almáhi, alqikqilíímá Benishangúl Gumúz shá áné gádaraqi faadá áhuhiné álúéqí ma booló kqedqe u shá áné móótha dqokqothá áshaqabú roothá pqiishí ñinéñ maané ñinéñ kqalóóne.

Ádam Hisén ñinéñ muusqóne hu.

የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን በማጠናከር ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን መደገፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ‎‎የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ከክልሉ ፋይና...
05/08/2025

የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን በማጠናከር ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን መደገፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑ ተገለጸ፡፡

‎የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ከክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ጋር በመሆን በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ቶንጎ ከተማ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የቤት ግንባታ እና ጥገና ሥራን አስጀምረዋል፡፡

‎የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ሥራ አስኪያጅ አቶ አጄሊ ሙሳ መርሀ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት ሚዲያው ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የቤት እድሳት እና አዲስ ግንባታ እንደሚያከናውን ጠቁመዋል።

‎በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተጀመሩ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ያሉት ስራ አስኪያጁ በጎነትን ያለማንም ቀስቃሽነት መተግበር እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል።

‎የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዚያድ አብዱላሂ በበኩላቸው እንደ ክልል የአቅመ ደካማ ቤቶችን መጠገንና መገንባት፣ ደጋፊ ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎችን ለማከናወን እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ዓቅመ ደካሞችን ለመደገፍ በሚደረገው ጥረትም በተቋማት ከሚደረጉ ድጋፎች ባሻገር የወረዳው አመራሮች፣ የከተማው በጎ አድራጊ ወጣቶች እንዲሁም የማህበረሰቡ ተሳትፎ ቀጣይነት እንዲኖረውም ጠይቀዋል፡፡

‎የማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከማል እንድሪስ እንዳሉት ደግሞ አቅመ ደካሞችን ለመደገፍ እንደ ክልል ትኩረት ተሰጥቶት ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰው ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን አመስግነዋል፡፡

‎በልዩ ወረዳው በበጎ አድራጎት ስራ የተሰማሩ ወጣቶችም በክረምቱ መርሀ ግብር የችግኝ ተከላ፣ የእርሻ ስራ እንዲሁም የቤት እድሳት ስራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የቤት ዕድሳትና ጥገና የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በበኩላቸው መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የመልሶ ግንባታና ጥገና ስላደረገላቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

‎ከበጎ ፍቃድ ስራዎች ጎን ለጎን በግብርናው ዘርፍ የተሰሩ የልማት ስራዎች የተጎበኙ ሲሆን የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡

በሞላሽ አሸንፍ

ግብር  ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ብሎም ለህዝቦች የልማት ተጠቃሚነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ ።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ያስመ...
05/08/2025

ግብር ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ብሎም ለህዝቦች የልማት ተጠቃሚነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ያስመዘገበውን ከፍተኛ አፈጻጸም በማስመልከት ለመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የምስጋናና የእውቅና ፕሮግራም አካሂዷል ።

በእውቅና ፕሮግራሙ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ አበበ የህብረተሰቡን እና የክልሉን የመልማት አቅም በሚፈለገው ልክ ማሳደግ የሚቻለው ግብርን በአግባቡ መሰብሰብ ሲቻል ነው ብለዋል።

እንደ ክልል ባለፈው የ 2017 የግብር ዘመን የተለያዩ የገቢ አማራጮችን በመጠቀም 4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የእቅዱን 110 በመቶ በመሰብሰብ ከዕቅድ በላይ መፈጸሙን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል ።

ባለፈው የግብር ዘመን እንደ ክልል ለተመዘገበው ከፍተኛ አፈጻጸም በየደረጃው የሚገኙ የተቋሙ ሰራተኞች ሚና ከፍተኛ ነበር ያሉት አቶ ተፈሪ በ2018 የግብር ዘመንም የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ከማዘመን ባለፈ ክልሉ ያለውን የገቢ አቅም ለይቶ በመስራት 8 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዙን ጠቁመዋል ።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ እና የከተማ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ መሀመድ አልማሂ በበኩላቸው ክልሉ ወጭውን በራሱ አቅም ለመሸፈን በተለይም የክልሉን ህብረተሰብ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ከወትሮው በበለጠ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

የተሰጣቸው እውቅና ለተግባርና ሀላፊነታቸው የበለጠ እንዲተጉ ተነሳሽነት የሚፈጥር ነው ያሉት ዕውቅና የተሰጣቸው የተቋሙ ሰራተኞች ከግብር የሚገኝ ገቢ ለሀገር ብሎም ለህዝብ የልማት ስራዎች የሚውል መሆኑን በመረዳት ግብር ከፋዩ የህብረተሰብ ክፍል በአግባቡ እንዲከፍል ለማስቻል የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል ።

ዘገባው የሪፖርተራችን ሀና መንገሻ ነው ።

የፋይናንስ ተቋማት ተደራሽነትን በማስፋት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ ላይ ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ የክልሉ ፋይናንስ አካታችነት ግብረ ኃይል ከተለያዩ ተቋማት ለተወጣጡ ባለድርሻ...
05/08/2025

የፋይናንስ ተቋማት ተደራሽነትን በማስፋት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ ላይ ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ የክልሉ ፋይናንስ አካታችነት ግብረ ኃይል ከተለያዩ ተቋማት ለተወጣጡ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳዳር የፋይናንስ ዘርፍ አማካሪ ከፍተኛ ባለሙያ እና የክልሉ የፋይናንስ አካታችነት ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ደሬሳ እጀታ ስልጠናው የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፋይናንስ ተቋማት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ አለመሆን የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማሳደግ ተግዳሮት መሆኑንም አቶ ደሬሳ የተናገሩት።

በመሆኑም ሴቶችን በተለያዩ የልማት ዘርፎች ተሳታፊና በኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ የፋይናንስ ተቋማት ተደራሽነትን ማስፋት ወሳኝ በመሆኑ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተደራሽ የሴቶችን የኢኮኖሚያዊ አቅም ማጎልበት ይገባል ብለዋል።

በቀጣይም ከስልጠና መድረኩ ያገኙትን ዕውቀት በመጠቀምና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።

በስልጠናው ከግልና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተወጣጡ የግብረ-ኃይሉ አባላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል፡፡

በሃይማኖት አዳሜ

በየዓመቱ የሚተከሉ ችግኞች የአካባቢን ስነ-ምህዳር ከመለወጥ ባለፈ ፍሬ አፍርተው ህብረተሰቡን መጥቀም እስኪጀምሩ ድረስ በቂ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው የክትትልና ቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ የክል...
05/08/2025

በየዓመቱ የሚተከሉ ችግኞች የአካባቢን ስነ-ምህዳር ከመለወጥ ባለፈ ፍሬ አፍርተው ህብረተሰቡን መጥቀም እስኪጀምሩ ድረስ በቂ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው የክትትልና ቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ የክልሉ ግብርና ቢሮ ብልጽግና ፓርቲ ህብረት አስታወቀ፡፡ የፓርቲው አባላት "በኡራ ወረዳ ሩብዮ ቀበሌ" የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ኡስማን መሀመድ እንዳሉት በየዓመቱ የክረምት ወራትን ተከትሎ የሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በህብረተሰቡ ዘንድ እየተለመደና ባህል እየሆነ መጥቷል ብለዋል፡፡

እንደ ሀገር የሚተከሉ ችግኞች ላይ ሁሉም ዜጋ በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል ያሉት አቶ ኡስማን በዋናነትም የፓርቲው አባላት የግንባር ቀደምነት ሚናቸውን እንዲወጡ እየተሰራበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ብርሀኑ ኢትቻ እንዳሉት የችግኝ ተከላ በየዓመቱ ቁጥሩ እያደገ መምጣቱን አውስተው በክልሉ በአንድ ጀምብር ከዕቅድ በላይ የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርም ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ በያዝነው የክረምት ወራት ከ75 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል ታቅዶ በስፋት እየተሰራበት መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ብርሀኑ እስካሁንም ከ45 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን አስረድተዋል፡፡

የሚተከሉ ችግኞች ያሉበትን ቦታ መለየት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ሁሉም ዜጋ በሀላፊነት ችግኞች እንዲቀጸድቁ ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያደርግም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በክልሉ ግብርና ቢሮ የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ታደሰ ቢራቱ እንዳሉት ደግሞ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙ የተራቆተ መሬቶች መልሰው እንዲያገግሙ ግብ ጥሎ እየሰራ መቆየቱን አስታውሰው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር መተግበር ከጀመረ ወዲህ ተጨማሪ አቅም እንደፈጠረለት ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ምርት መስጠት ያቆሙ መሬቶች አገግመው ምርት መስጠት መጀመራቸው የዘላቂ መሬት አያያዝና የአረንጓዴ አሻራ ውጤት መሆኑንም ነው አቶ ታደሰ የገለጹት፡፡

ችግኝ ሲተክሉ ያገኘናቸው የክልሉ ግብርና ቢሮ ብልጽግና ፓርቲ ህብረት አባላት በበኩላቸው ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ማሳደጉ ላይ በንቃት እንደሚሳተፉ ተናግረዋል፡፡

በስንታየሁ አድማስ

በ2018 ግብር ዘመን 1 ቢሊየን 2 መቶ 80 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን የአሶሳ ከተማ ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ። መምሪያው የ2017 ግብር ዘመን  አፈፃፀም ግምገማ  እና በ2018 ግብር...
05/08/2025

በ2018 ግብር ዘመን 1 ቢሊየን 2 መቶ 80 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን የአሶሳ ከተማ ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው የ2017 ግብር ዘመን አፈፃፀም ግምገማ እና በ2018 ግብር ዘመን እቅድ ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

የአሶሳ ከተማ ገቢዎች መምሪያ ሃላፊ አቶ አብዱላሂ መሀመድ በ2017 ግብር ዘመን በተሰራው የገቢ ግብር አሰባሰብ ሂደት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልፀው በ 2018 የግብር ዘመንም 1 ቢሊየን 2 መቶ 80 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል።

በ2018 ግብር ዘመንም ከተማው የደረሰበትን እድገት ያማከለ ገቢ ለመሰብሰብ በጋራ ቁርጠኝነት ለመስራት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

መምሪያው ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጅን ተግባራዊ ማድረጉ የተሻለ ገቢ እንዲሰብብ ማስቻሉንም አቶ አብዱላሂ አስታውቀዋል።

በቀጣይ ከተማዋ ያላትን የገቢ አቅም በመጠቀም እና ፍትሀዊ የሆነ የገቢ አሰባሰብን በመዘርጋት የከተማዋን እድገት ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱልከሪም አብዱራሂም በበኩላቸው በ2017 ግብር ዘመን የገቢዎች መምሪያ ያሳየው የተሻለ የገቢ ግብር አሰባሰብ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህም የከተማዋን እድገት ማፋጠን ያስቻለ ትልቅ ተግባር ነው ብለዋል።

ከንቲባው አክለውም ግብር የአንድ ከተማ መሰረት በመሆኑ መምሪያው ለሚያደርገው ጥረት ከተማ አስተዳድሩ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል።

ግብር ከፋዩ ማህበረሰብም ግብርን በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ከንቲባው አሳስበዋል።

አስተያየታቸውን ያነሱ የመምሪያው ባለሙያዎችም መምሪያው ፍትሀዊ የሆነ ግብር ለመሰብሰብ በጥናት የተረጋገጠ የግብር አጣጣል ተመን መከተል እንደሚገባ እና የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በአግባቡ መመለስ የሚያስችል አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል።

የግብር አሰባሰቡ ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣቱንም ገልፀዉ ለስራው ስኬታማነት የቁሳቁስና የሰዉ ሀይል እጥረት መኖሩንም ጠቁመዋል።

በሙያዉ የሰለጠነ እና የበቃ ባለሙያ መመደብ ከዘርፉ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑንም አመላክተዋል።

በግብር አሰባዘቡ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ቀርፎ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ እንዲያስችል የፍትህ እና ሌሎች የሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ከመምሪያዉ ጎን አንዲሆኑም ጠይቀዋል።

በግብር ከፋዮች በኩል የሚስተዋለዉን የደረሰኝ አቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ መምሪያው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት እንዳለበት የተናገሩት ደግሞ የመድረኩ ታዳሚ ግብር ከፋዮች ናቸው።

መምሪያዉ ለሚያደርገዉ የገቢ ግብር አሰባሰብ ስኬታማነትም ግብር ከፋዮች የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

በመጨረሻም መምሪያው ላስመዘገበዉ የተሻለ ገቢ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው አካላት እና ግብር ከፋዮች እውቅና አበርክቶላቸዋል።

ሪፖርተራችን ዘመናይ የሽዓለም እንደዘገበው።

05/08/2025

Arabic News 29 11 2017

05/08/2025

Komo News 29 11 2017

05/08/2025

Gumuz News 29 11 2017

"ጓንዷ"ን በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ገለጸ(አሶሳ፣ ሐምሌ 28/2017 ዓ/ም) የጉሙዝ ብሔረሰብ የዘመን መለዋጫ የሆነውን የጓንዷ በዓል ...
04/08/2025

"ጓንዷ"ን በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ገለጸ

(አሶሳ፣ ሐምሌ 28/2017 ዓ/ም) የጉሙዝ ብሔረሰብ የዘመን መለዋጫ የሆነውን የጓንዷ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ገለጸ።

አስተባባሪ ኮሚቴው ከጳጎሜ 1-5/2017 ዓ/ም ለሚከበረው የጉሙዝ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ "ጓንዷ" በዓል ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ እና የበዓሉ አከባበር አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መለሰ ኪዊ፣ የጉሙዝ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ጓንዷን ባህሉን እና እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

"ጓንዷ ለሠላም፣ ለልማትና ለህዳሴያችን" በሚል መሪ ቃል የሚከበርው በዓሉ፣ ሲምፖዚየምን ጨምሮ የብሔረሰቡን ታሪክ፣ ወግ፣ ባህል እና እሴቱን በሚገልጹ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል ብለዋል መረጃው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በደረሰው የጀልባ መስጠም በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለጸ አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2017(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴ...
04/08/2025

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በደረሰው የጀልባ መስጠም በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2017(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በደረሰው የጀልባ መስጠም በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ የደረሰውን አደጋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እያጣራ መሆኑን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን እንደሚመኝ ባወጣው የሀዘን መግለጫ አስታውቋል።

መንግሥት ዜጎች በተለያዩ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዲችሉ ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶችን በማከናወን በርካታ ዜጎችን የዕድሉ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑንም አመልክቷል።

ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ብቻ የውጭ ሀገራት የሥራ ሥምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና ከሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል መረጃው ኢዜአ ነው።

Address

Assosa
Asosa
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Benishangul Gumuz Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Benishangul Gumuz Media:

Share