
19/07/2025
የጋዛ ተፈናቃዮችን በኢትዮጵያ ለማስፈር የቀረበውን እቅድ አሜሪካዊው ሴናተር ‹‹አሳፋሪና አሳዛኝ ነው›› አሉት፡፡ የአሜሪካው ሴናተር ክሪስ ዛን ሆለን ዛሬ በኤክስ ገፃቸው ላይ በፃፉት አስተያየት ፍሊስጤማዊያንን ከጋዛ አስወጥቶ በሌሎች አገራት ውስጥ ለማስፈር እቅድ መውጣቱን ማንበባቸውን ጠቅሰዋል፡፡
እስራኤል ባወጣችው በዚህ እቅድ መሰረት የጋዛ ተፈናቃዮችን ኢትዮጵያን ጨምሮ በተወሰኑ አገራት ለማስፈር የአሜሪካን እገዛ መጠየቋን አውስተዋል፡፡ ሴናተሩ ጨምረውም ‹‹ይህ እቅድ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው›› በማለት ተቃውሟቸውን ገልፀዋል፡፡
ሲቀጥሉም ‹‹ፍሊስጤማዊያንን ከጋዛ ለማንሳት በሚደረገው በዚህ ጥረት ላይ አሜሪካ ከማንም ወገን መቆም የለባትም፡፡ ለዚህ ድርጊትም አንተባበርም›› ብለዋል፡፡ የዲሞክራት ፓርቲ አባል የሆኑት እኚህ ሴናተር ለፍሊስጤማዊያን ድምፅ በመሆን ከዚህ ቀደም አስተያየት በመስጠት የሚታወቁ ናቸው፡፡
ዘ-ሐበሻ ዜና