13/12/2025
የምስራቅ መስቃን ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በቀጣይ ቀናት በሚሰጠው የጠቅላላ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና እና የሚደረጉ የሕዝብ መድረኮችን አስመልክቶ ለአጠቃላይ ለወረዳው አመራሮች ኦረንቴሽን ሰጠ።
ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም
"በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እመርታ!" በሚል መሪ ርዕስ ላይ በቅርቡ ጠቅላላ አመራሩ ሰፊ ስልጠና መውሰዱ ይታወቃል።
ይህንኑ ስልጠና ለአጠቃላይ ለወረዳው ውስጥ ያሉ ጠቅላላ የፓርቲው አባላትን ለማሰልጠን ያለመ የቅድመ_ዝግጅት ለአጠቃላይ አመራሩ ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።
እንደሚታወቀው የብልጽግና ፓርቲ በተከታታይነት የአመራሩና የአጠቃላይ አባላት የፓለቲካ አቅም የሚገነቡ ወቅታዊና ዕውቀትን የሚያስጨብጡ የተለያዩ ስልጠናዎችን በተከታታይ እያወረደና እያሰለጠነ ይገኛል።
በዚህም መሰረት በፓርቲው የሚወርዱ ወቅታዊ ሀገራዊ ፣ አከባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በመተንተንና በማካተት የወረዳው የፓርቲ አባላት አቅም ለመገንባትና ለማብቃት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን እና ይህም በቀጣይ የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተነስቷል።
መድረኩን የመሩት የወረዳው ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድኑር ስርሞሎ እንደ ወረዳ የፓርቲ አባላት አቅም የሚገነቡ ስልጠናዎች ከአመራሩ በተጨማሪ ጠቅላላ አባላት ላይም በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለበት አብራርተው ሁሉም የወረዳው አመራር በቁርጠኝነት ተግባራቶቹን ማሳካት እንደሚጠበቅ ለአመራሩ አሳስበዋል።
በመድረኩ ላይ የተሳተፉት ጠቅላላ የወረዳው አመራሮች ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ከስልጠናው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ጀምሮ ስልጠናው በስኬት ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የወረዳው ረዳት የመንግስት ተጠሪና የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ብራቱ በመድረኩ ተገኝተው ፣ ስልጠው ልዩ ፖለቲካዊ ትርጉም ተሰጥቶት መመራት ያለበት መሆኑን አንስተዋል ፣ መድረኮቹ የተሳኩ እንዲሆኑ በሁሉም ማህበራዊ መሰረቶች ተደራጅተው የሚገኙ የፓርቲ አባላት ስልጠናው አንድም አባል ሳይንጠባጠብ በተገቢው በሁሉም መድረኮች በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲሰጥ አቅጣጫ አስቀምጠው የተለያዩ ስልጠናውን የሚመሩና አሰልጣኞች እና #የተለያዩ ንዑሳን #ኮሚቴዎችን አሳውቀው ኦረንቴሽኑ ተጠናቁዋል።
ወቅታዊና ፈጣን መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከታች ባለው ሊንክ በመግባት like shere follow ያድርጉ 👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=10006508462855