Amsalu A Sabero

Amsalu A Sabero Innovative work

06/11/2024

Donald Trump declares victory in US presidential election, telling supporters "we made history" - follow live: https://bbc.in/3CfYSEk

  newsፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ። ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ...
17/09/2024

news
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ። ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ። ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ እመኛለሁ።

Professor Beyene Petros embodied the spirit of peaceful political struggle, playing a pivotal role in fostering a culture of non-violence and constructive political dialogue in Ethiopia. I am deeply saddened to hear of his passing after a prolonged period of medical care. May his legacy endure, and may he rest in eternal peace.

05/06/2024

በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤ በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ- ኢሳ 45:2-3

02/06/2024

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:13
ይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።

Arsenal 4 Manchester united 0
12/05/2024

Arsenal 4 Manchester united 0

12/05/2024

"የብርሃን ጊዜ መቷል"~በኢሳይያስ 60
---------------------------

በዚህ ክፍል ኢሳያስ ስለ ማንነታችን እና እግዚአብሔር ያደረገልንን እየነገረን ነው። በኢሳይያስ 59 ላይ ጌታ ስለ ሙሉ ኃጢአታችን እና እግዚአብሔር በራሱ ክንዱ የሚሰጠውን ቤዛ አስታውሶናል። ቤዛው ወደ ጽዮን ይመጣል (59፡20)፣ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገብቶ ኃጢአታቸውን ይቅር ይላል። በኢሳይያስ 59፡21 ጽዮን የተዋጁ የቃል ኪዳኑ ሕዝብ ምሳሌ እንደሆነች እንማራለን። እነዚህ ከኃጢአታቸው ነጻ መውጣት የሚሹ ናቸው። ኢሳይያስ 60 እኛ ማን እንደሆንን የሚገልጸው እግዚአብሔር ባደረገልን ነገር ነው። ይህን ምእራፍ ስናነብ አሁን ስለተቤዠን ማን መሆን እንዳለብን በማየት ማንበብ አለብን።

እኛ የክርስቶስ የብርሃኑ ኃይል ነፃብራቅ ብርሃን ነን። ፀሀይ የብርሃን ምንጭ እንደሆነች ጨረቃም ከፀሀይ ወደ ምድር እንደምታንጸባርቅ ሁሉ ኢየሱስም የብርሃን ምንጫችን ነው እና እኛም ያንን ብርሃን ለሌሎች ማንጸባረቅ አለብን። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡9 ላይ “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤” ይላል። ኤፌሶን 5፡8-9 ደግሞ "ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ" ብሎ ያስቀምጣል።

ኢየሱስ እንድንከተለው የነገረን ለዚህ ነው፣ እና ለምን ቅዱሳን እንድንሆን የተነገረን፣ እና ለምን ፈቃዱን እንድናደርግ እና ትእዛዙን እንድንታዘዝ የተነገረን እኛ ኢየሱስ በእኛ ዉስጥ የሚያዩት ሰዎች ነን። ስለ ኢየሱስ ያላቸውን አስተሳሰብ የሚመሠረተው ራሳችንን በምንኖርበት መንገድ ወይም በምን ዓይነት ብርሃን እንደምናንጸባርቅ ነው። የምንወደውን የኢየሱስን ክብር እና ብርሃን ማንጸባረቅ አለብን። ወዳጆች ሆይ ከብርሃናችን ምንጭ ከሆነዉ ኢየሱስ በራቅን ቁጥር ነጸብራቅያችን እየደበዘዘ ይሄዳል። ብርሃን እንደሆንን መረዳታችን ወደ ኢየሱስ ለመቅረብ በትጋት መሥራት ያለብን ለምን እንደሆነ እንድንገነዘብ ይረዳናል።

ዛሬ በጨለማ ሕይት ውስጥ እየተጓዝክ ነዉ ወይንስ ወደ ጌታ ብርሃን መጥተሃል? ዛሬ ወደ ኢየሱስ ቀርበሃል ወይንስ የክርስቶስ ነፀብራቅህ ደብዝዞ እስኪያልቅ ድረስ ጠፍቷል። በቁጥር 3 ላይ ኢሳይያስ እስራኤላውያን በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች ላይ የሚኖራቸውን ኃይለኛ ተጽዕኖ እየተናገረ ነው። አንተም ተነሥተህ ታበራ ዘንድ አበረታታሃለሁ፥ ወደ ክርስቶስ በመምጣት ከተስፋ መቁረጥ ጨለማ በክብር ወደ ብርሃኑ ሙላት መጠጋትና ለሌሎች ማንፀባረቅ ያስፈልጋል!

ላመነዉ ሰዉ እንዲህ ይሆንለታል፡-
👉ታላቅ ብርሃን ወደ ቤቱ ወደ ሕይወቱ ስለመጣ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወቶለታልና ተነስቶ ማብራት ይሆንለታል፥
👉ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን በሚሸፍንበት ጊዜ በአንተ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል ክብሩም በአንተ ላይ ይታያል፤
👉አሕዛብም ወደ ብርሃንህ ነገሥታትም ወደ መውጫህ ጸዳል ይመጣሉ።
👉ዓይኖችህን አንሥተህ በዙሪያህ ስትመለከት፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችህ ከሩቅ ይመጣሉ፥ ሴቶች ልጆችህም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል።
👉በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንተ ስለሚመለስ፥ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንተ ስለሚመጣ፥ አይተህ ደስ ይልሃል፥ ልብህም ይደነቃል ይሰፋማል።
👉የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ።
👉የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።
👉እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለእግዚአብሔር ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመጡ ዘንድ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።
👉በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ፥ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል።
👉በሮችሽም ሁልጊዜ ይከፈታሉ፤ ሰዎች የአሕዛብን ብልጥግና የተማረኩትንም ነገሥታቶቻቸውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊትና ቀን አይዘጉም።
👉ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።
👉የመቅደሴንም ስፍራ ያስጌጡ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው ባርሰነቱም፥ ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ።
👉የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።
👉ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።
👉 የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የያዕቆብ ኃይል፥ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
👉በናስ ፋንታ ወርቅን፥ በብረትም ፋንታ ብርን፥ በእንጨትም ፋንታ ናስን፥ በድንጋይም ፋንታ ብረትን አመጣለሁ። አለቆችሽንም ሰላም፥ የበላይ ገዢዎችሽንም ጽድቅ አደርጋለሁ፤
👉 ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ።
👉 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፥ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አያበራልሽም።
👉እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም ጨረቃሽም አይቋረጥም።
👉ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እከብር ዘንድ የአታክልቴን ቡቃያ፥ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ።
👉ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሹ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር በዘመኑ ይህን አፋጥነዋለሁ።

----------------------------
ድንቁ ኢየሱስ ድንቅ ያደርጋል!

18/09/2023

ይባረክ
#ይህ ትንቢታዊ የቃሉ አዋጅ አሜን ላለው ሰው ሁሉ በጌታ ስም ዓመቱን ሙሉ አገኘው መዝሙር 91
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
² እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።


⁴ በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።
⁵ ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥
⁶ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።
⁷ በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።
⁸ በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።
⁹ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
¹⁰ ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
¹¹ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
¹² እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።
¹³ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
¹⁴ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።
¹⁵ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
¹⁶ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።

Address

Awassa
BILTSGINA

Telephone

+251924742603

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amsalu A Sabero posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amsalu A Sabero:

Share

Category