Ethio Press

Ethio Press Trusted News where you can find

በዓለማችን የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ጣራ በነካበት በዚህ ወቅት " ሼል " የተሰኘው ግዙፉ የኢነርጂ ኩባንያ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ ማስመዝገቡ ተሰምቷል።ሼል በዓመቱ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት 9....
10/05/2022

በዓለማችን የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ጣራ በነካበት በዚህ ወቅት " ሼል " የተሰኘው ግዙፉ የኢነርጂ ኩባንያ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ ማስመዝገቡ ተሰምቷል።

ሼል በዓመቱ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት 9.13 ቢሊዮን ዶላር ያገኘ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ካገኘው 3.2 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ በሦስት እጥፍ ገደማ ያደገ ነው።

ነገር ግን ድርጅቱ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከሩሲያ የነዳጅ እና ጋዝ ገበያ መውጣቱ 3.9 ቢሊዮን ዶላር እንዲያጣ እንዳደረገው አሳውቋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ተዳክሞ የነበረው የዓለም ኢኮኖሚ ማንሰራራት ሲጀምር የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ እየጨመረ ቢመጣም የቅርቡ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ ጣራ እንዲነካ አድርጎታል።

የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ መጨመር ለኢነርጂ ኩባንያዎች ከፍተኛ ትርፍ እንዲያገኙ እያደረጋቸው ይገኛል።

ምዕራባውያን ለሩሲያ ስጋት ሆነው ቀጥለዋል " - ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲንእኤአ ሜይ 9 ሩሲያውያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ሶቪዬት ሕብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችውን ድ...
09/05/2022

ምዕራባውያን ለሩሲያ ስጋት ሆነው ቀጥለዋል " - ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን

እኤአ ሜይ 9 ሩሲያውያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ሶቪዬት ሕብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችውን ድል አስበው ይውላሉ።

ይህ የድል በዓል ቭላድሚር ፑቲን ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ትልቅ ትርጉም ተሰጥቶት ነው የሚከበረው።

በዕለቱ ሩሲያ ያላትን ዘመን አፈራሽ ጦር መሳሪያ ለዓለም የምታሳይበት ቀን አድርገውታል።

ከዩክሬን ጋር ጦርነት ላይ ያሉት የሩስያው መሪ የዛሬውን የድል ቀን ምክንያት በማድረግ ከዩክሬን ጋር እየተደረገ ያለውን ጦርነቱ የተመለከተ አዲስ ውሳኔ ያስተላልፋሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ፑቲን በዛሬው በዓል ላይ ጦርነቱ ማብቃቱን አልያም በዩክሬን ላይ አዲስ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ ይወሰዳል ብለው ይናገራሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር።

ነገር ግን " ምዕራባውያን ለሩሲያ ስጋት ሆነው ቀጥለዋል " ከማለት ውጪ ፑቲን ያሉት ነገር የለም።

ፑቲን በዩክሬን እየተፋለሙ ላሉት ወታደሮቻቸው "እየተዋጋችሁ ያላችሁት ለሩስያ ደኅንነት ነው” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት ዓመታዊ የፖለቲካ ምክክር አካሄዱኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት ዓመታዊ የፖለቲካ ውይይታቸውን ዛሬ  በአዲስ አበባ አካሄደዋል።ውይይቱ የተካሄደው በአውሮፓ ኅብረ...
06/05/2022

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት ዓመታዊ የፖለቲካ ምክክር አካሄዱ

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት ዓመታዊ የፖለቲካ ውይይታቸውን ዛሬ በአዲስ አበባ አካሄደዋል።

ውይይቱ የተካሄደው በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያን እና በፓሲፊክ ሀገራት መካከል በተደረሰው የኮቶኑ አጋርነት ስምምነት አንቀጽ 8 መሠረት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያን የልዑካን ቡድን በመወከል እንዲሁም በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረትን በመወከል አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ የምክክር መድረኩን መርተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት እና የአውሮፓ ኅብረት እና የኢትዮጵያ ግንኙነትን በሚመለከት የተወሰዱ የሰብአዊ እና የተጠያቂነት እርምጃዎችን ጨምሮ የተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጋራ ተጠቃሚነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

አቶ ደመቀ በመክፈቻ ንግግራቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜን ያለውን ግጭት ለማስቆም እና የሀገሪቱን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እያከናወናቸው ያሉ የተለያዩ እርምጃዎችን ዳሰሳ አቅርበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነትን ማስፋት፣ በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ስር የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ በመሆን የሰላም ተነሳሽነትን መደገፉን እና ሁሉንም ያሳተፈ ሀገራዊ ውይይትን ጠቅሰዋል።

የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በሰሜኑ ግጭት ወቅት በሁሉም አካላት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ጨምሮ መንግሥት የወሰደውን የተጠያቂነት እርምጃ በተመለከተ አብራርተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ግብረ-ኃይል በማዋቀር የጥሰት ተግባራትን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጋራ ምርመራ እና ምክረ-ሐሳቦቹን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት እንዲሁም ወንጀለኞችን ወደ ሕግ እንዲቀርቡ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ፣ ለትግራይ ክልል ያልተቋረጠ ሰብአዊ ድጋፍን ለማረጋገጥ እስካሁን የተወሰዱ እርምጃዎችን በቪዛ አሰጣጥ፣ ዕርዳታ ሰጭዎች ወደ ትግራይ ይዘውት የሚገቡት መጠን፣ ኬላዎችን በመቀነስ እና ሰብአዊነት ድጋፎች መጨመርን በመጥቀስ አብራርተዋል።

አቶ ምትኩ በኢትዮጵያ በድርቅ እና በግጭት ለተጎዱ ወገኖች ለሚደረገው ድጋፍ የሰብአዊ አጋሮች ምስጋናቸውን አቅርበው፣ የአማራ እና አፋርን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የድጋፍ መሠረቱን ማስፋት እና ለዘላቂ ልማት እና መልሶ ማቋቋም ሥራዎች ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል። .

በምክክር መድረኩ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ለሁለቱም ወገኖች አሁን ካጋጠሟቸው ፈታኝ ሁኔታዎች አንፃር ወቅታዊ መሆኑን ገልጸው በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት እና ድርቅ እንዲሁም በአውሮፓ የሩስያ እና የዩክሬን ግጭት አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የሩሲያ እና ዩክሬንን ግጭት በተመለከተ ሁለቱ ሀገራት ችግራቸውን በሰላማዊ መንገድ፣ በድርድር እንዲፈቱ የያዘችውን አቋም በምክክር መድረኩ ላይ በድጋሚ አሳውቃለች።

ውይይቱ ከሰብአዊ መብት ጥሰት እና ከተጠያቂነት እርምጃዎች በተጨማሪ በኢትዮጵያ ስላለው የንግድ ሁኔታ ከአውሮፓ ባለሃብቶች አንፃር የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት እና የዳበረ ኢኮኖሚ ለመገንባት ስለሚያስችለው ጉዳይ ተወያይተዋል።

የአውሮፓ ኅብረ

ሁሌም ግጭቱ እንዲቆም ፣ ሰብአዊ እርዳታ በሁሉም ቦታ እንዲዳረስ እንዲሁም ሰላምን የሚያመጣ ውጤታማ ድርድር እንዲደረግ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ " - አንቶኒዮ ጉተሬዝየተባበሩተ መንግስታት ድር...
06/05/2022

ሁሌም ግጭቱ እንዲቆም ፣ ሰብአዊ እርዳታ በሁሉም ቦታ እንዲዳረስ እንዲሁም ሰላምን የሚያመጣ ውጤታማ ድርድር እንዲደረግ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ " - አንቶኒዮ ጉተሬዝ

የተባበሩተ መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲያበቃ ከሁለቱም ወገኖች ጋር በርካታ ግንኙነቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ይህን የተናገሩት በዚህ ሳምንት የምዕራብ አፍሪካ አገራት በሆኑት በሴኔጋል፣ በኒጀር እና በናይጄሪያ ጉብኝት ባደረጉበት ጊዜ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ነው።

ዋና ፀሀፊው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ከህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር ግንኙነቶችን በመፍጠር ጦርነቱ መቋጫ እንዲያገኝ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠርና በመጨረሻም በውይይት ሰላም እንዲወርድ አዘውትረው ሲጥሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ጉተሬዝ ፥ " ሁሌም ግጭቱ እንዲቆም፣ ሰብአዊ እርዳታ በሁሉም ቦታ እንዲዳረስ እንዲሁም ሰላምን የሚያመጣ ውጤታማ ድርድር እንዲደረግ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ " ሲሉ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሰላም እንዲመጣ ቁርጠኛ መሆኗን ገለፀች!!የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በቢሯቸው በኩል በኢትዮጵያ ግጭቶችን ለማስቆም እየተካሄዱ የሚገኙ ተግባ...
30/04/2022

አሜሪካ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሰላም እንዲመጣ ቁርጠኛ መሆኗን ገለፀች!!

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በቢሯቸው በኩል በኢትዮጵያ ግጭቶችን ለማስቆም እየተካሄዱ የሚገኙ ተግባራዊ ሥራዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

አሸባሪው ሕወሓት በፈጠረው ጦርነትና በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች እንዲሁም በተለያዩ ግጭቶች የተነሳ ብዙኃን ለችግር መጋለጣቸውን ያስታወሰው መግለጫው ይህንን ችግር ለመቅረፍ በፌዴራል መንግሥትና በክልሎች የተወሰደውን እርምጃ አድንቋል።

በተለይም በትግራይና አፋር ክልሎች በችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፎች እንዲደርሳቸው ለማስቻል የተከናወኑ ተግበራትን ያደነቁት ብሊንከን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም ያልተቋረጠ አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ በግጭት ለተጎዱ ወገኖች እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ተናግረዋል። አሜሪካም በዚህ ሂደት ውስጥ ድጋፉን ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን መግለጻቸውን ከሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ቢሮ ያገኘውን መግለጫ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ሁሉን ዐቀፍ ሰላም እንዲመጣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተወሰዱ እርምጃዎችን ያደነቀው መግለጫው በትግራይ ክልል ነገሮችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ጥረቶች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል።

አንድነቷ፣ ሉዓላዊነቷና እድገቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ለሚከናወኑ ተግባራት አሜሪካ ድገፏን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗንም መግለጫው አመልክቷል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ በድጋሚ ጠየቁ!የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ በድጋሚ ጠየቁ፡፡ዜሌንስኪ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራ...
29/04/2022

የዩክሬን ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ በድጋሚ ጠየቁ!

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ በድጋሚ ጠየቁ፡፡ዜሌንስኪ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ዲሜትሮ ኩሌባ በኩል ነው ጥያቄውን በድጋሚ ያቀረቡት፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ከዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሜትሪ ኩሌባ ጋር በስልክ ማውራታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ለሙሳ ፋኪ የደወሉት ኩሌባ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ለአፍሪካ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ንግግር ለማድረግ ከአሁን ቀደም ያነሱትን ጥያቄ ደግመው አንስተዋል፡፡ከህብረቱ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመመስረት እንፈልጋለን ስለማለታቸውም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለገባችበት ጦርነት ሰላማዊ መፍትሔዎች ሊፈለጉለት እንደሚገባ አስረግጠው መናገራቸውን ገልጸዋል፡፡

ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን " - ቭላድሚር ፑቲንየሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ጦርነት እጁን የሚያስገባ ማንኛውም አገር ላይ መ...
28/04/2022

ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን " - ቭላድሚር ፑቲን

የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ጦርነት እጁን የሚያስገባ ማንኛውም አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጸምበት አስጠነቀቁ፡፡

ይህን ለማድረግ ደግሞ አገራቸው ሩሲያ አቅምም ብቃትም አላት ብለዋል፡፡

‹‹ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን›› ሲሉ ብዙዎችን ያሳሰበ ንግግር አድርገዋል፡፡

አንዳንድ ተንታኞች ፑቲን በዚህ ንግግራቸው ለመጠቆም የሞከሩት ባለስቲክ ሚሳኤልና የኑክሊየር መሣሪያን ነው በማለት ግምት ወስደዋል፡፡

ፑቲን ከዚህ በፊት በለጦር ሹማምንቶቻቸው የኑክሊየር መሣሪያ በተጠንቀቅ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡

የፑቲን መራር ንግግር የተሰማው ምዕራባዊያን ለዩክሬን እጅግ ውስብስብና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመስጠት በተጠመዱበት ወቅት ነው።

በተለይም ባለፉት ቀናት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስቲን በኪየቭ ጉብኝት አድርገው ነበር።

በዚህ ጉብኝታቸው ለዩክሬን ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ እርዳታን ይፋ አድርገዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ የምዕራብ አገራት በጀርመን ተሰብስበው ለዩክሬን የሚደረገውን የጦር መሣሪያ እርዳታ እንዴት ከዚህም በላቀ መልኩ ማሳደግ ይቻላል በሚል ተወያይተው ነበር፡፡

በጦርነት ጣልቃ ያለመግባት ጥብቅ ፖሊሲን ትከተል የነበረችው ጀርመን ሳይቀር ያልተጠበቀ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ለዩክሬን 50 የአየር መቃወሚያ ታንኮችን እሰጣለሁ ብላለች፡፡

መረጃው የቢቢሲ ነው።

 የአሜሪካ ኤምባሲ ፤ የ Diversity Visa (ዲቪ) ን ጨምሮ ሁሉንም የስደተኛ እና ስደተኛ ያልሆኑ የቪዛ ሂደቶች እያስቀጠለ መሆኑን ገልጿል።ኤምባሲው አገልግሎቱን እየተጠባበቁ ያሉ ሁሉ ...
26/04/2022



የአሜሪካ ኤምባሲ ፤ የ Diversity Visa (ዲቪ) ን ጨምሮ ሁሉንም የስደተኛ እና ስደተኛ ያልሆኑ የቪዛ ሂደቶች እያስቀጠለ መሆኑን ገልጿል።

ኤምባሲው አገልግሎቱን እየተጠባበቁ ያሉ ሁሉ ፤ በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 እና በኢትዮጵያ ታውጆ በነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደኃላ የቀሩ ስራዎችን ለመስራት በሚደረገው ሂደት በትዕግስት እንዲጠብቁ መልዕክቱ አስተላልፏል።

የቪዛ ቃለመጠይቆች ሂደት ሚከናወነው በስቴት ዲፓርትመንት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በመመስረት መሆኑን የገለፀው ኤምባሲው ፤ አሜሪካውያንና ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በሁሉም የቪዛ መደቦች ላይ በተቻለ መጠን ብዙ ቃለ መጠይቆችን ለማድረግ በማቀድ በትጋት ስራቸውን እያከናወኑ ነው ብሏል።

በዚህም ሂደት ላይ ፤ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ሁሉንም አስፈላጊ ሰነዶች ይዘው ለቃለ መጠይቅ ዝግጁ ሆኖ በመምጣት የሁሉንም ሰው የጥበቃ ጊዜ እንዲቀንስ ለማድረግ ማገዝ ይችላሉ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ባይደን ታሪክን በደንብ መማር አለበት፤ ይህ ሳያውቅ ቱርክን ለመከራከር መሞከሩን ይቅር አንለውም " - ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋንየአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በፈረንጆቹ በ1915 በአርመን የተ...
26/04/2022

ባይደን ታሪክን በደንብ መማር አለበት፤ ይህ ሳያውቅ ቱርክን ለመከራከር መሞከሩን ይቅር አንለውም " - ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በፈረንጆቹ በ1915 በአርመን የተካደውን ክስተት ለሁለተኛ ጊዜ " የዘር ማጥፋት " ድርጊት ነው ብለው ገልፀው ነበር።

ይህንን አገላለፅ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ኮንነውታል።

ፕሬዝደንት ኤርዶጋን በቱርክ በፕሬዝዳንት ቤተመንግስት የነበረውን ስብሰባ በመሩበት ወቅት ነው የባይደንን ንግግር የኮነኑት።

ኤርዶጋን ፤ በአርመኒያ ተደርጓል ስለተባለው ወንጀላ፤ በጥቂት ሀገራት እና ፓርላመንቶች የሚሰጠው አስተያያት በቱርክ መንግስት ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ፕሬዝደንት ባይደን ለ1915 የአርመን ክስተት በውሸት እና በሃሰተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ኤርዶጋን " ባይደን ታሪክን በደንብ መማር አለበት፤ ይህ ሳያውቅ ቱርክን ለመከራከር መሞከሩን ይቅር አንለውም " ሲሉ ተናግረዋል።

የአርመን ሰዎች በዚህ የአርመንን እና የቱርክ ህዝብን ለማጋጨት አላማው ባደረገው ግብዝ አመለካከት ሲጎዱ ነበር፤ ይጎዳሉም ብለዋል።

በቱርክ እና በአርመን መካከል ያለፈ ቁርሾ ከማጋነን ይልቅ ሰለማዊ ግንኙት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ኤርዶጋን የቱርክ ላሉት የአርመን ፓትሪያሪክ መልእክት መላካቸውን ተነግሯራ።

በቱርክ የሚገኙ አርመኖች በመጀመሪያው የአለም ጦርነት የደረሰባቸውን መጥፎ ሁኔታ በቱርክ ተሰባስበው አስበዋል፡፡

ምንጭ ፦ አል ዓይን ኒውስ

የመን ውስጥ በ " ሁቲ ኃይሎች " ታስረው የቆዩ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ጨምሮ 12 ሰዎች ከእስር መለቀቃቸውን ኦማን አስታውቃለች።ታሳሪዎቹ የተለቀቁት የብሪታንያ፣ ኢንዶዥያ፣ ህንድ እና ፊሊፒን...
26/04/2022

የመን ውስጥ በ " ሁቲ ኃይሎች " ታስረው የቆዩ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ጨምሮ 12 ሰዎች ከእስር መለቀቃቸውን ኦማን አስታውቃለች።

ታሳሪዎቹ የተለቀቁት የብሪታንያ፣ ኢንዶዥያ፣ ህንድ እና ፊሊፒንስ መንግስታት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የኦማን ባለሥልጣናት ባደረጉት ጥረት እንደሆነ ነው የተነገረው።

ኢናቾ መኮንን የተባሉ ኢትዮጵያዊን ጨምሮ በእስር ላይ የነበሩት የብሪታንያ ፣ ፍሊፒንስ ፣ ማይናማር ፣ ኢንዶኔዥያ እና የህንድ ዜጎች ከየመን ሰነዓ ወደ ሙስካት መዘዋወራቸውን የኦማን ውጭ ገዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከታሳሪዎቹ አንዱ የሆነው የብሪታንያ ዜጋ በሁቲዎች በሀገር ክህደት ተጠርጥሮ ለ5 ዓመታት በእስር የቆያ ሲሆን ፤ የታሳሪው ቤተሰቦች በምርመራ ወቅት እጁ መሰረበሩን፣ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጤናው እንዲቃወስ መሆኑን ገልፀዋል።

ሁቲዎች ኢትዮጵያዊውን ግለሰብ ለምን እና መቼ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት በፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ ላይ የተገለፀ ነገር የለም።

ምንጭ፦ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት

ለኢትዮጵያ ብላችሁ ህይወታችሁን በመስጠት በዱር በገደሉ ለምትዋደቁ ለመከላክያ ሰራዊት አባላትና ለፌደራል እንዲሁም ለክልል የጸጥታ አካላት አማራ ሚሊሻ ፋኖ አፋር የሚሊሻ በሙሉ እንኳን ለፋሲካ...
24/04/2022

ለኢትዮጵያ ብላችሁ ህይወታችሁን በመስጠት በዱር በገደሉ ለምትዋደቁ ለመከላክያ ሰራዊት አባላትና ለፌደራል እንዲሁም ለክልል የጸጥታ አካላት አማራ ሚሊሻ ፋኖ አፋር የሚሊሻ በሙሉ እንኳን ለፋሲካ (ትንሳኤ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። በዚህ ትግል ህይወታችሁን ላጣችሁ በሙሉ የከፈላችሁልን የህይወት የደም ዋጋ ቀላል አይደለምና ነፍሳችሁን ይማረው

ለጀግኖቹ ቤተሰቦችና አሁንም በስራ ላይ ላሉ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አባላት በሙሉ መልካም በዓል

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ጃዋር እና እስክንድር ተያይዘው ከኢትዮጵያ እየወጡ ነው!በቅርብ ጊዚያት ከእስር የተፈቱት ጃዋር መሃመድና እስክንድር ነጋ ተከታትለው ከኢትዮጵያ ሊወጡ መሆኑ ተሰማ።ጃዋር መሃመድ ዛሬ ምሽት ወደ...
22/04/2022

ጃዋር እና እስክንድር ተያይዘው ከኢትዮጵያ እየወጡ ነው!

በቅርብ ጊዚያት ከእስር የተፈቱት ጃዋር መሃመድና እስክንድር ነጋ ተከታትለው ከኢትዮጵያ ሊወጡ መሆኑ ተሰማ።

ጃዋር መሃመድ ዛሬ ምሽት ወደ ጂዳ፣ ሳውዲ አረቢያ በረራውን የሚያደርግ ሲሆን እስክንድር ነጋ ደግሞ በፋሲካ ዋዜማ አገር ለቅቆ ይወጣል።

ጃዋር ከእስር ከተፈታ ዝምታን የመረጠ ሲሆን ጉዞው ሳውዲ ይብቃ ወይንስ ወደ ምድረ አሜሪካ ሄዶ እንደ በፊቱ የአክቲቪዝም ስራውን ይቀጥላል ወይንስ በኦፌኮ አመራርነቱ ሰላማዊ ትግል ያደርጋል የሚለው አጠያያቂ ሆኗል።

እስክንድር ባልደራስን እየመራ ውስጥ ውስጡን የፋኖ እንቅስቃሴን ይደግፋል እየተባለ ሲሆን ወደ አሜሪካ ተጉዞም የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ይሰራል የሚል ግምት አለ።

ጃዋርና እስክንድር የሚያደርጉት ጉዞ በ24 ሰዓታት ልዩነት ሲሆን ተነጋግረውና ለተመሳሳይ አላማ ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር የለም። ከዲያስፖራው ገንዘብ ከመሰብሰብ ባሻገር ሁለቱም ተጓዦች ከህወሃት፣ከሸኔ እንዲሁም ሌሎች ፅንፈኛና አክራሪ ቡድኖች የዲያስፖራ ክንፍ ጋር የመገናኘትና የማሴር ስራ ይሰራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከውጭ ሃገራት ሃይሎች ግብፅን ጨምሮ ሊመክሩ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም።

ጃዋር መሃመድና እስክንድር ነጋ ሚስቶችና ልጆቻቸው አሜሪካ ነዋሪ ሲሆኑ አካሄዳቸው ለመመለስ ይሁን አይሁን የተባለ ነገር የለም።

Address

Piasa
Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share