03/08/2024
Film really affini made it.
ከሰሞኑ የአፊኒን ፊልም የተመለከቱ ፊልም አፍቃሪያን ምን አሉ?
ከግለሰቦቹና ተቋማቱ ከማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻቸው ተቀነጫጭቦ የተወሰደውን እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል::
"እስካሁን ግርምቴ አለቀቀኝም ::
ዛሬ በአለም ሲኒማ ከውድ ባለቤቴ ጋር ያየነው ፊልም የኢትዮጵያን የፊልም ኢንዱስትሪ ትንሳኤ ከሚያበስሩ ፊልሞች ግንባር ቀደሙ እንደሆነ ተሰማኝ::
ፊልሙ መሀል እስክንደርስ ድረስ አማኑኤል ሀብታሙ የተጫወተውን ገፀ ባህሪ እያየሁ እሡ መሆኑን በጭራሽ አልጠረጠርኩም:: በሁዋላ ግን ባለቤቴን ስጠይቃት እሱ መሆኑን አረጋገጥኩ:: ግሩም ኤርሚያስ አንጀቴን እንዴት እንዳራስከው ተናግሬ አይወጣልኝም:: የሲዳምኛ ቋንቋን የተናገራችሁበት መጠን ለሙያ መሰጠት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንደ አዲስ አስተማረኝ:: የኢትዮጵያን ውበት በአስደናቂ አቀራረፅ ስላሳያችሁን ከልብ እናመሰግናለን:: ኑሩልን እድሜ እና ጤና ይስጣችሁ:: ይህንን ፊልም በፋይናንስ ያገዙትንም ለሀገር ውለታ እንደዋሉ ይቁጠሩት:: ተመልካቹም ግጥም ብሎ ሳየው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሌም ጥሩ ስራ ካገኘ እንደማይምር በደንብ ገብቶኛል:: ጸሃፊና ዳይሬክተሮቹም ፕሮዲውሰሩም ክሩውም ሁላችሁም በህይወታችሁ ታሪክ የማይረሳው አንድ ድንቅ ስራ ተሳክቶላችሁዋል እና የሃገር ባለ ውለታ ናችሁ:: እማንረሳው እሁድ እንድናሳልፍ ስለረዳችሁን ተባረኩልኝ::”
ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ
"ትላንት እሁድ በአጋጣሚ በአለም ሲኒማ ነበርኩ የሰው ስሜት የሚገርም ነበር ፊልሙ ሲጠናቀቅ እንደ እግር ኳስ ድጋፍ ጭብጨባና ፉጨት አዳራሹን ደባለቀው። ጨርሰን ስንወጣ የ 12:00 ሰዓት ተመልካች በዶፍ ዝናብ ውጪ ረጅም ሰልፍ ተሰልፏል የምንወጣውና የሚገባው መተላለፊያ አጣን ውስጤን ነዘረኝ ከፊል የራቀውን ተመልካች ወደ ሲኒማ የመለሰ ትልቅ ታሪክን ባህልን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ድንቅ ፊልም ። በዚህ ስራ ላይ የተሳተፈ ሁሉም ባለሞያ ትለቅ ክብር ይገባዋል :: በተለይም የአካባቢው ባህል በዚህ መልኩ ለህዝብ እንዲደርስ ላደረገው Sidama Regional State Culture, Tourism & Sport Bureau ክብረት ይስጥልን እናመሰግናለን::"
መላኩ መሌ ይርጋለም
"አፊኒ ፊልም " የሲዳማ ህዝብ የበለፀገ ባህል በሚያምር ሁኔታ የሚያሳይ አጓጊ ፊልም በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ አለም ሲኒማ ለህዝብ እይታ ክፍት መሆኑን ሳሳውቃችሁ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል።
Biru W.Gujo
"የአፊኒ ፊልምን ትላንት በአለም ሲኒማ አየሁት!
ከመሀል ሀገር የከተሙት ግሩም ኤርሚያስና አማኑኤል ሀብታሙ ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር የሚገርም የትወና ጥበብን አሳይተውበታል። ፊልሙ በአጠቃላይ የማህበረሰብ ጥናት ላይ ተመሥርቶ የጥበብ ከፍታን በሚያሳይ መልኩ ከተለመደው አቀራረብ ወጣ ባለ መቼትና ሲኒማቶግራፊ የተሠራ መሆኑ አስደንቆኛል።"
Endush Girma Guraro
የኢትዮጵያን ፊልም ለሚያከብሩ ማመስገኛ፣የኢትዮጵያን ፊልም ለሚንቁ መመስከሪያ የሆነውን ታላቁን ፊልም አፊኒ በአለም ሲኒማ ተመልከቱና አረጋግጡ።
አፊኒ ( ሰምተሀል)
Fitsum Kassahun
"የአፊኒ ባህል እሴት ከሲዳማ ፣ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ የዲሞክራሲ ተምሳሌት ነው
የሲዳማ ብሔር ባህላዊ እሴቶች ውስጥ ባህላዊ ግጭት አፈታት ስነ ስርዓት አንዱ ነው።
የሀገር ሽማግሌዎች ባህላዊ ስፍራ ላይ ተሰብስቦ "አፊኒ"ባህሉን በመጠቀም ጉዳዩን በጥልቀት በመረመር ግጭቱን ይፈታሉ።!!"
!! .Loolashe Tube
,,የሲኒማችንን ዕድገት በተወሰነ መጠን ከፍ ማለቱን ከምናይባቸውና ከሰሞኑ ምርጥ ፊልሞች አንዱ ነው ብዬ የማወራለት አፊኒ ነው።ይህ ፊልም በመታየት ላይ ይገኛል እንድታዩት እጋብዛችኋለሁ። ,,
Buzayehu Eshetu
,,AFFINI "በቁጥር ብዛት በይዜትም ጥራት የኢትዮጵያን ባህሉን ለዘነጋዉ ማህበረሰብ በሚገባ ባህሉን ላስተዋወቀ እንዲሁም ዘመናዊነትን ፣ባህልን ፣ ቁም ነገርን፣ ቀልድን ፣ ትዝታን ፣ ሀዘንን ፣ ደስታን በተለያዩ ስሜቶች የተደረሱ የፊልም ዳይሬክቲንግ ፣ ካሜራ ማን ፣ ኤዲተር ፣ ፕሮዲዩሰር በመሆን በርካታ ጥራት ያላቸዉን ፊልሞች ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ ደረጃ የሚወዳደሩ የጥበብ ዉጤቶችን አበርክቷል::"
Asher Habesha Music
“Affini Film breaking the record”
Ethiopianism (ኢትዮጵያዊነት )
“በሲዳማ ባህል ውስጥ ለማንም ሳያዳላ እውነቱ ተመርምሮ ግጭት የሚፈታበት ሥርዓት ላይ የተሠራው አፊኒ የተሰኘ እነዚህን ድንቅ ተዋናዮች ያጣመረ አዲስ የአፊኒ ፊልም በሚገርም መልኩ ተሠርቶ ለዕይታ በቅቷል። “