Chuko town

Chuko town let change our town by cooperating

 !የቀድሞ አለታ ጩኮ ከተማ ከንቲባ እራሱን እንዳጠፋ ስሰማ በጣም አሳዝኖኛል።እያገለገለ ያለው ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆን እራሱን ለምን እንዳጠፋ ወይም  የሞቱ መንስኤ...
24/07/2025

!
የቀድሞ አለታ ጩኮ ከተማ ከንቲባ እራሱን እንዳጠፋ ስሰማ በጣም አሳዝኖኛል።
እያገለገለ ያለው ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆን እራሱን ለምን እንዳጠፋ ወይም የሞቱ መንስኤ የተጣራ ነገር የለም ።

መጽናናትን ለመላው ወዳጅ ቤተሰቡ፣ ለአለታ ጩኮ ከተማ ህዝብ እና ለሐዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እመኛለሁ።

መጋቢ ዘማሪ ዳዊት ዳንጊሶ ለምድራችን በረከታችን ነህ 🏟️🏟️🏟️🏟️በመዝሙርህ ተባርከንበታል። በአንተ ላይ ፀጋውን የገለጠው አምላክ ይክበር። አምላኬ አብዝቶ ይባርክህ
20/07/2025

መጋቢ ዘማሪ ዳዊት ዳንጊሶ ለምድራችን በረከታችን ነህ 🏟️🏟️🏟️🏟️
በመዝሙርህ ተባርከንበታል። በአንተ ላይ ፀጋውን የገለጠው አምላክ ይክበር። አምላኬ አብዝቶ ይባርክህ

የጭቆና ፅዋ ስያጠግቧት የከረመች Artist Ethiopia Bekelech ተፈታለች🥰በሲዳማ ክልል በበልሹ አሠራር ተሟጋች አርቲስት ኢትዮዽያ በቀለች ተፈታ ህዝቡን ተቀላቅላለች።እንኳን ለቤትሽ ...
24/06/2025

የጭቆና ፅዋ ስያጠግቧት የከረመች Artist Ethiopia Bekelech ተፈታለች🥰

በሲዳማ ክልል በበልሹ አሠራር ተሟጋች አርቲስት ኢትዮዽያ በቀለች ተፈታ ህዝቡን ተቀላቅላለች።

እንኳን ለቤትሽ አበቃሽ!

የቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ከእስራት ተፈቷል።ከዚህ በፊት በግፍ 13 አመት ተፈርዶበት በወህኒ ታስሮ  ቢሆንም በይግባኝ  የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በዛሬው ቀን በዋለ...
19/06/2025

የቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ከእስራት ተፈቷል።
ከዚህ በፊት በግፍ 13 አመት ተፈርዶበት በወህኒ ታስሮ ቢሆንም በይግባኝ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በዛሬው ቀን በዋለዉ ችሎት የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬን "ነፃ ነዉ" በማለት በነፃ እንዲሰናበቱ ዉሳኔ አሳልፈዋል።

ነፃ ወጥቻለሁ!

13 ዓመት ተፈርዶባቸዉ በማረሚያ ቤት የነበሩት የቀድሞው ከንቲባ አቶ ፀጋዬ ቱኬ በዛሬዉ ዕለት በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነበራቸው ችሎት የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰነባቸው የፍርድ ዉሳኔ በነፃ ተሰናብተው ከማረሚያ ቤት ወጥተዋል።

ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ስንብት መልስ ርቆ የቆየበት ወዳጅ ቤተሰቡ በደስታ ተቀብሎታል።

Tsegaye Tuke Kia- ፀጋዬ ቱኬ ክአ Hawalle minekki keeruy higootto።

 የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የአቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስን ያለመከሰስ መብት አነሳ።የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ባካሄደበት የክልሉ ሠ...
12/06/2025



የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የአቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስን ያለመከሰስ መብት አነሳ።

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ባካሄደበት የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን የአቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ደቦጭን ያለመከሰስ መብት ያነሳው ስልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም ከኮንትሮባንድ ንግድ ፣ ከህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር ፣ በሙስና ወንጀል እንዲሁም በሌሎች ወንጀሎች በመጠርጠራቸው ነው።

ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ 🏆🏆🏆🏆 አሸናፊ ሆነ።ሲዳማ ቡና በሚቀጥለው አመት ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር የሚሳተፉ ይሆናል።የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላ...
08/06/2025

ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ 🏆🏆🏆🏆 አሸናፊ ሆነ።

ሲዳማ ቡና በሚቀጥለው አመት ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር የሚሳተፉ ይሆናል።

የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ/አለን።

 ¿¿ፌዴሬሽኑ ለሰው ልጅ ክብር ልኖረው ይገባል። ይሄ ሁሉ ልፋት ደጋፍ ብዙ ቀናት ተዘጋጅቶ  ከደከመ በኃላ በዝግ ስታዲየም ማለት ምን ማለት ነው?ኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ የሚታስተናግድ አቅ...
08/06/2025

¿¿

ፌዴሬሽኑ ለሰው ልጅ ክብር ልኖረው ይገባል። ይሄ ሁሉ ልፋት ደጋፍ ብዙ ቀናት ተዘጋጅቶ ከደከመ በኃላ በዝግ ስታዲየም ማለት ምን ማለት ነው?
ኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋንጫ የሚታስተናግድ አቅም አላት ተብሎ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው ሀገራት አንዷ ናት። ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ከገጠማቸው ጨዋታውን ማራዘም ነው እንጂ በሠላም ሀገር በዝግ እስታዲየም የዋንጫ ጨዋታ ማካሄድ በሀገርቷ ላይ ሠላም ማስከበሩ ጉዳይ ስጋት እንዳለ ያመላክታል።

ደጋፊዉ ሜዳ የሚገባዉ ጨዋታ ለማየት እንጂ መፈንቀለ መንግስት ለማድረግ አይደለም።

እግዚአብሔር የፈቀደውን አድርጓል ዘማሪት የምስራች ከዚህ አለም በሞት ተለይታ ወደ ጌታ ሄዳለች።ወዳጅ፣ ቤተሰቦቿን እግዚአብሔር ያጽናና😭😭
02/06/2025

እግዚአብሔር የፈቀደውን አድርጓል
ዘማሪት የምስራች ከዚህ አለም በሞት ተለይታ ወደ ጌታ ሄዳለች።

ወዳጅ፣ ቤተሰቦቿን እግዚአብሔር ያጽናና😭😭

ህፃን ባምላክ ፍትህ አገኘች  ከ7ወር በፊት ያለ ፍርድ እስር ቤት ቁጭ ብለው የነበረው እናቷ እና የእንጀራ አባቷ ሁለቱም ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸዋል!ወላጅ እናት ወ/ሮ ሀና በየነ...
23/05/2025

ህፃን ባምላክ ፍትህ አገኘች

ከ7ወር በፊት ያለ ፍርድ እስር ቤት ቁጭ ብለው የነበረው እናቷ እና የእንጀራ አባቷ ሁለቱም ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸዋል!

ወላጅ እናት ወ/ሮ ሀና በየነ ትባላለች የድሬዳዋ ከተማ ገንደቆሬ ሰፈር ነዋሪ ስትሆን ከቀድሞ ባሏ ጋር የተፈታችው ይህቺ ሴት ከእሷ ጋር እየኖረ ባለው ሌላ ወንድ ከአብራኳ የወጣችውን የገዛ ሴት ልጅዋ ተገዳ መደፈሯን ስታውቅ እጮኛዋን በወንጀል እንዲቀጣ ማድረግ ሲገባት የ11 ዓመት ልጇ ላይ ፈርዳ መረጃ ለማድበስበስ በማሰብ ልጇን ላይ ጫና በመፍጠር በድብደባ አካላዊ ጉዳት ከማድረስ በተጨማሪ ከ5ተኛ ክፍል የትምህርት ገበታ እና ከጎረቤቶቿ በመነጠል ከማንም ሰው ጋር ምንም ግንኙነት እንዳታረግ በማድረግ ለብዙ ጊዜ ቤት ተዘግቶባት እና ስራ ቦታ ድረስ ከስሯ ሳትነጥላት ብትንቀሳቀስም መረጃ ለመደበቅ በቂ ሆኖ ስላላገኘችው በመጨረሻ በአብራኳ በወጣችው የገዛ ልጇ ላይ የሰራችው ተደጋጋሚ የአረመኔ ሥራ ሳያንሳት እጮኛዋን ከወንጀል ለማትረፍ መረጃ ለማጥፋት ህዳር 1 ቀን 2ዐ15 ከእጮኛዋ ጋር በመተባበር ቀጥቅጠው ህፃን በአምላክ ግርማን ገደሏት። በወላጅ እናቷ እና እንጄራ አባቷ ሕይወቷ ያለፈው ሕፃን በአምላክ ግርማ አበጋዝ ጉዳይ ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2017 የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት የቅጣት ውሣኔ ሰጥቷል። ሁለቱም ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸዋል!

በአሜሪካን ሀገር ኢትዮጵያን ከፍ ያደረገ ወጣት!! በሲዳማ ክልል አርበጎና ተወላጅ የሆነው ተማሪ በረከት  ባራሳ ዋሬ በአሜሪካን አይኦዋ ዩኒቨርስቲ እጅግ የተከበሩ ምሁራኖች ፣ ጥሪ የተደረገላ...
22/05/2025

በአሜሪካን ሀገር ኢትዮጵያን ከፍ ያደረገ ወጣት!!

በሲዳማ ክልል አርበጎና ተወላጅ የሆነው ተማሪ በረከት ባራሳ ዋሬ በአሜሪካን አይኦዋ ዩኒቨርስቲ እጅግ የተከበሩ ምሁራኖች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ከፍተኛ የዩኒቨርስቲው አመራሮች እና ተመራቂዎች እንዲሁም የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች በተገኙበት በተደረገው የምረቃ መርሃግብር ላይ በከፍተኛ ማዕረግ ከተመረቁ ጥቂት ተመራቂዎች ውስጥ ኢትዮጵያዊው ተመራቂ ተማሪ በረከት ባራሳ ዋሬ አንዱ ሲሆን ፤ ከፍተኛ ውጤት በማምጣቱም በዕለቱ ንግግር እንዲያደርግ የተጋበዘ ሲሆን ፤ '' ጥረት ፣ ትጋት ፣ የዓላማ ፅናት ያሰብንበት ቦታ እንደሚያደርሱ አምናለሁ።'' በማለት የህይወቱን ተሞክሮ በማንሳት በርካታ ወጣቶች ዘንድ መነቃቃትን ፈጥሯል።

በረከት ትውልዱ አርቤጎና፣ የልጅነት ዕድገቱ ሐዋሳ ሲሆን ለቤተሰቡ ሁለተኛ ልጅ ነው። ቤኪ ሐዋሳ በነበረው ቆይታ 2001/2008 በኦስስ አካዳሚ KG አጠናቋል። የዚያን ጊዜ ከKG ሲመረቅ በወላጆች በዓል ላይ ያቀረበው ግጥም ለምስክር ከሥር በቪዲዮ ቀርቧል። ኋላ ወላጆቹ እግዚአብሔር ረድቷቸው ወደ አሜሪካ ሀገር አቀኑ። በረከትም ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ እዛው በአሜሪካ ሀገር ተምሮአል። በረከት ባራሳ ከአይኦዋ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስ አናለትክስና ፋይናንስ (በሁለት ሜጀር) በመጀመሪያ ድግሪ በአመርቂ ውጤት ዘንድሮ ተመርቋል።

እኛም እንደ ኢትዮጵያዊ ኮርተናል እያለን ። እንደዚህ ያሉ ትንታግ የሆኑ ብርቱ ወጣቶች ማመስገን ፣ ማድነቅ መሰልጠን ነውና ንቡ ወጣት በረከት ባራሳ ዋሬ እንደ ሀገር ስላኮራኼን ትመሰገናለህ ፤ መልካም አዲስ ምዕራፍ ።

የጣሪያ መዝጋቱ ተመቸው ለመድፋየደርሶ መልስ ድልበደማቁ ብዕር ታርኩን ፅፏልArsenal 5 Madrid 1
16/04/2025

የጣሪያ መዝጋቱ
ተመቸው ለመድፋ
የደርሶ መልስ ድል
በደማቁ ብዕር ታርኩን ፅፏል
Arsenal 5 Madrid 1

16/04/2025

ዛሬም ታሪኩ ይደገማል

አርሰናል በታሪክ በማድሪድ ተሸንፎ አያዉቅም።
አይደለም መሸነፍ ጎል ተቆጥሮበት አያውቅም።

Address


Telephone

+251926864622

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Chuko town posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Chuko town:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share