14/08/2026
የክለቡ ቤት እንደገና በልጁ ተደምቋል
እንኳን ደህና መጣህ ይገዙ ቦጋለ
የጎል አምራቹ ይገዙ ቦጋለ ወደ እናት ክለቡ ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ተመልሷል!
በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከብ ጎል አስቆጣሪነት (የወርቅ ጫማ) የተሸለመው እና በአጥቂነት ብቃቱና በጎል አስቆጣሪነቱ የሚታወቀው ይገዙ ቦጋለ፣ ሲዳማ ቡናን ወደ ከፍተኛ አቋም ለመመለስ ባለው ቁርጠኝነት ወደ ክለቡ ተመልሷል።
ተጫዋቹ በዝውውሩ ወቅት ለክለቡ በነበረው ፍቅርና ለሲዳማ ቡና የማገዝ ቁርጠኝነትና ክለቡን ወደላቀ ደረጃ ለመመለስ ባለው ከፍተኛ ተነሳሽነት ከግል ጥቅሙ ይልቅ ክለቡን አስቀድሞ ለክለቡ የተሻለውን ለማበርከት በመወሰን ውሉን መፈረሙ ተረጋግጧል።
የይገዙ መመለስ የሲዳማ ቡናን የማጥቃት መስመር ከአምናው በእጅጉ ያጠናክረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ዘንድሮ ክለቡ በሊጉና በአፍርካ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ እንዲወጣ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
Samuel Nigatu Kirchoff Kidane Kifle