Abruzzi Media

Abruzzi Media Home Of News And Entertainment

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች  በሙሉየሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:-2014/15 የኢትዮ ዩኒቨርሲቲ መግቢያናየሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተ...
22/09/2022

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:-

2014/15 የኢትዮ ዩኒቨርሲቲ መግቢያና
የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ካምፖስ ጉዞ ሲያደርጉ #መያዝ #የተፈቀደላቸው፣ #መያዝ #የተከለከሉ እና #የጊዜ #ሠሌዳ እንደሚከተለው ያለው ሲሆን ተማሪዎች ከወዲሁ ራሣችሁን እንድታዘጋጁ ይሁን።

❶ #መያዝ #የተፈቀደላቸው
✡️አንሶላ፣
✡️ትራስ ጨርቅ፣
✡️የማታ ልብስ፣
✡️ደረቅ ምግብ፣
✡️ልብስ፣ቦርሳ፣
✡️የመፈተኛ ካርድ፣እርሳስ፣ላጲስ፣የማስታወሻ ደብተር፣ባዶ ወረቀት፤መጽሐፍ

❷፣ #መያዝ #የተከለከሉ
☸️ማንኛውም ድምፅ የሚቀዳ፤ቪዲዮ የሚቀዳ ወይም ፎቶግራፍ የሚያነሳ፤
☸️ካሜራ
☸️ማንኛውም ከቴሌ መስመርም ይሁን ከቴሌ ውጭ መልዕክት በድጂታል ቴክኖሎጂ መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ ውጤቶች(ታብሌት፣ኮሚፕዩተር፣ላብቶፕ፣ ስልክ፣አይፓድ፥ሃርድ ዲስክ፣ፍላሽ)

❸ #የጊዜ #ሠሌዳ
✡️ማህበራዊ ሳይንስ $social science dep't
➤26_28/1/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
➤29/01/2015 ኦሬንተሽን
➤30/01/2015_02/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።

✡️የተፈጥሮ ሳይንስ Natural Science dep't
➤05_06/2/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
➤07/02/2015 ኦሬንተሽን
➤08/02/2015_11/02/2015 ፈተናው
የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።

መልካም እድል!

ትምህርት ሚኒስቴር

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼እንኳን ለ 2015 ዓ.ም አዲስ ዓመት          በሰላም አደረሳችሁ🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼አዲሱ አመት የሰላም፤የጤና፤ የደስታ እና ስኬት እንዲሁም  የከፍታ ዘመን እንዲሆንልሆ እን...
11/09/2022

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እንኳን ለ 2015 ዓ.ም አዲስ ዓመት
በሰላም አደረሳችሁ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

አዲሱ አመት የሰላም፤የጤና፤ የደስታ እና ስኬት እንዲሁም የከፍታ ዘመን እንዲሆንልሆ እንመኛለን።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መልካም አዲስ አመት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
💚💛❤️

The 1st Ethiopian National Youth Olympic Games have started.The inauguration of ethiopian National Youth Olympic Games k...
02/06/2022

The 1st Ethiopian National Youth Olympic Games have started.

The inauguration of ethiopian National Youth Olympic Games kicked off today at the Hawassa University international Stadium.

Click the link to see more...

The 1st Ethiopian National Youth Olympic Games have started. The inauguration of ethiopian National Youth Olympic Games kicked off today at the Hawassa University international Stadium. More than 4,000 participants from all regions, Addis Ababa and Dire Dawa City Administration will participate in 1...

ከዚህ በፊት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስበስባ የተቀመጠው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ስብሰባ እንደሚቀመጥ ታውቋል።ምክ...
20/12/2021

ከዚህ በፊት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስበስባ የተቀመጠው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ስብሰባ እንደሚቀመጥ ታውቋል።

ምክር ቤቱ ዛሬ በ “any other business” ስር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ የሚወያይ ሲሆን ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት ፦
🇪🇪 ኢስቶኒያ
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇮🇪 አየርላንድ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇺🇸 አሜሪካ ናቸው።

የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ ጉዳይን በተመለከተ ለፀጥታው ም/ ቤት አባላት አጭር ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።

በትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጊዜ አንስቶ የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ ከአስር ጊዜ በላይ ስብሰባ የተቀመጠ ሲሆን የዛሬው ስብሰባ ባለፈው ሳምንት የተመድ የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ አካሂዶ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የተከሰቱ የመብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች አካል እንዲቋቋም በድምጽ ብልጫ ከወሰነ በኋላ ነው።

https://www.securitycouncilreport.org/whatsinblue/2021/12/ethiopia-meeting-under-any-other-business.php

የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ውስጣዊ የፖለቲካ ግጭቶች ለዘለቄታዊ ለመፍታት : አወዛጋቢ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን ጭምር ለብሄራዊ ውይይት እንደሚያቀርብ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደዔታ ሬድዋን ...
20/12/2021

የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ውስጣዊ የፖለቲካ ግጭቶች ለዘለቄታዊ ለመፍታት : አወዛጋቢ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን ጭምር ለብሄራዊ ውይይት እንደሚያቀርብ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደዔታ ሬድዋን ሁሴን ለቱርኩ ዜና ወኪል አናዶሉ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ብሄራዊ ውይይቱ ሕገ መንግሥቱን እስከማሻሻል እና ሕዝበ ውሳኔን እስከመፍቀድ ድረስ ሊዘልቅ እንደሚችል ሬድዋን አክለው ጠቁመዋል። የትግራዩ ሕወሃት በብሄራዊ ውይይቱ ይሳተፍ እንደሆነ ጥያቄ የቀረበላቸው ሬድዋን፣ ሕወሃት ብቸኛው የትግራይ ሕዝብ ወኪል አለመሆኑን በመጥቀስ ካሁኑ ቁርጥ ያለ መልስ መስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል። ሆኖም ቡድኑ ትጥቁን ከፈታ እና ተፈላጊ ወንጀለኞችን ለመንግሥት አሳልፎ ከሰጠ በብሄራዊ ውይይቱ የመሳተፍ ዕድሉ ላይዘጋ እንደሚችል ሚንስትር ደዔታው ጠቁመዋል።

[Wazema]

ከመላው ዓለም ወደ  #ኢትዮጵያ ለሚደረገው " ታላቅ ጉዞ ወደ ሐገር ቤት " የ30% ቅናሽ ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት አሳውቋል።አየር መንገዱ ፥ " ከአሁን ጀምሮ እስከ...
06/12/2021

ከመላው ዓለም ወደ #ኢትዮጵያ ለሚደረገው " ታላቅ ጉዞ ወደ ሐገር ቤት " የ30% ቅናሽ ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

አየር መንገዱ ፥ " ከአሁን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 11/ 2014 ዓ.ም ተመዝግበው ትኬትዎን ይግዙ ። ከታህሳስ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጥር 23 2014 ዓ.ም ይጓዙ " ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

Abruzzi media'ን በተለየያዩ አማራጮች ይከታተሉ

በ youtube

https://youtube.com/channel/UCSTMi4rzpPsP71kAw9cbEPg

በ Facebook

https://www.facebook.com/Abruzzi-Media-104580105333946/

በ Telegram

https://t.me/Abruzzimedia

የቢቢሲ (ወርልድ) የዓመቱ አሳፋሪ የሀሰት ዘገባየኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ለአንድ ሳምንት ማለትም ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ...
04/12/2021

የቢቢሲ (ወርልድ) የዓመቱ አሳፋሪ የሀሰት ዘገባ

የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ለአንድ ሳምንት ማለትም ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚዘጉ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

ት/ ቤት የሚዘጋው ያልተሰበሰብ ሰብል ለመሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት ዘመቻዎች በስፋት ለማካሄድ መሆኑ በግልፅ ተነግሯል።

ይህንን ዘገባ BBC World) /ቢቢሲ - ዋርልድ / 33.7 ሚሊዮን ተከታዮች ባሉት ይፋዊ የትዊተር ገፁ ላይ " ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነትን ለማጠናከር ትምህርት ቤቶችን ዘጋች "
በማለት የሀሰት ዜናን አሰራጭቷል።

ማስታወሻ፦ተማሪዎች ያልተሰበሰበ ሰብሎችን የመሰብሰብ ተግባር ቀድሞውንም የነበር ነው።

Abruzzi media'ን በተለየያዩ አማራጮች ይከታተሉ

በ youtube

https://youtube.com/channel/UCSTMi4rzpPsP71kAw9cbEPg

በ Facebook

https://www.facebook.com/Abruzzi-Media-104580105333946/

በ Telegram

https://t.me/Abruzzimedia

ሰበር የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት  ፣ የአፋር ልዩ ሃይል ፣ የአማራ ልዩ ሀይል እንዲሁም ሚሊሻዎች በቅንጅት  ከስትራቴጂካዊዋ ከተማ ጋሽና በተጨማሪ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊ...
01/12/2021

ሰበር

የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት ፣ የአፋር ልዩ ሃይል ፣ የአማራ ልዩ ሀይል እንዲሁም ሚሊሻዎች በቅንጅት ከስትራቴጂካዊዋ ከተማ ጋሽና በተጨማሪ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጥሯል።

ህብረተሰቡ የመለያ ቁጥሩ 003-100 የሆነውን የጄኖቪያን ፍራፍሬና ለውዝ እንዳይጠቀም ተከለከለ!ህብረተሰቡ የመለያ ቁጥሩ 003-100 የሆነውን የጄኖቪያን ፍራፍሬ እና ለውዝ የተባለ ስናክ ም...
19/11/2021

ህብረተሰቡ የመለያ ቁጥሩ 003-100 የሆነውን የጄኖቪያን ፍራፍሬና ለውዝ እንዳይጠቀም ተከለከለ!

ህብረተሰቡ የመለያ ቁጥሩ 003-100 የሆነውን የጄኖቪያን ፍራፍሬ እና ለውዝ የተባለ ስናክ ምግብ ምርት እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳሰበ፡፡የአለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ማስጠንቀቂያ ተቋም ፋብሪካውን ዋቢ አድረጎ ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በማለከው መረጃ መሠረት÷ የጄኖቪያን ፍራፍሬ እና ለውዝ የተባለ ስናክ ምግብ ምርት ሊስቴሪአ ሞኖሳይቶጅን በተባለ ጎጂና ገዳይ ተህዋስያን መበከሉ ተረጋግጧል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ የመለያ ቁጥሩ 003-100 የሆነውን እንዲሁም የተመረተበት ቀን ቤስት ቢፎር ጃኗሪ 12 2023 የሆነ የምግብ ምርት እንዳይጠቀም ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡ከባለስልጣኑ ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ ማንኛውም የህረተሰብ ክፍልና የሚመለከተው አካልም ከላይ የተገለፀውን ምርት ሲያገኝ በስልክ ቁጥር 8482 እና በአካባቢ ለሚገኝ ተቆጣጣሪ አካል በመጠቆም እንዲተባበር የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጥሪ አቅርቧል፡፡

Abruzzi media'ን በተለየያዩ አማራጮች ይከታተሉ

በ youtube

https://youtube.com/channel/UCSTMi4rzpPsP71kAw9cbEPg

በ Facebook

https://www.facebook.com/Abruzzi-Media-104580105333946/

በ Telegram

https://t.me/Abruzzimedia

ሲኤንኤን ፣ ቢቢሲ ፣ ሮይተርስ እና ኤፒ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለአራት የውጭ ሚዲያዎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፅፏል።እነዚህ ሚዲያዎች ሲኤንኤን (CNN)፣...
19/11/2021

ሲኤንኤን ፣ ቢቢሲ ፣ ሮይተርስ እና ኤፒ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለአራት የውጭ ሚዲያዎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፅፏል።

እነዚህ ሚዲያዎች ሲኤንኤን (CNN)፣ ቢቢሲ (BBC)፣ ሮይተርስ (Reuters) እና አሶሺየትድ ፕሬስ (AP) ናቸው።

በማስጠንቀቂያ ደብዳቤው ላይ ሚዲያዎቹ ፦

- TPLFን ዓላማ ለማገዝ በኢትዮጵያ ላይ የሀሰት ዜናዎች እና የዜና ትንታኔዎችን ማዘጋጀታቸው እና ማሰራጨታቸው ፥

- የህግ ማስከበር ዘመቻውን የዘር ማጥፋት (Genocide) ዘመቻ አድርገው ሪፖርት ማድረጋቸው ፥

- በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት መንግስት የሚያደርገውን ጥረት የሚያበላሽ ዘገባዎችን መስራታቸው፣

- በትግራይ ክልል መንግስት ረሃብንን እና አስገድዶ መድፈር እንደጦር መሳሪያ እንደተጠቀመበት ሪፖርት ማድረጋቸው ፤

- በሀገሪቱ መሪ ተቋማት ላይ የስም ማጥፋት ሪፖርቶችን ማዘጋጀታቸው፤

- የሀገሪቱን መሪ በዓለም አቀፍ መድረክ ለማጣጣል እና ሀገሪቱን ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና ውሥጥ የሚከቱ ዜናዎችን ማዘጋጀታቸው ተገልጿል።

ተቋማቱ የጋዜጠኝነት መርህን አክብረው እንዲሰሩ መደበኛ እና መደበኛ ባልሆነ መልኩ ተደጋጋሚ ምክርና ማሳሰቢያ ሲሰጥ መቆየቱን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፤ መገናኛ ብዙኃኑ ከድርጊታቸው ከመታቀብ ይልቅ አባብሰው መቀጠላቸውን አስታውቋል።

ለኢትዮጵያዊያን ደህንነት ሲባል የሚዲያ ተቋማቱ በቀጣይ ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት በመጠቀም የሰጣቸውን የሥራ ፈቃድ ለመሰረዝ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል።

በኢመብባ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ ኢድሪስ ተፈርሞ የወጣው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል ላይ በመሆናቸው ምክትላቸው ሥልጣን ተረክበዋል።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል እያደረጉ በመሆኑ ምክትላቸው የሆኑት ካማላ ሃሪስን ፕሬዝዳንት...
19/11/2021

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል ላይ በመሆናቸው ምክትላቸው ሥልጣን ተረክበዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል እያደረጉ በመሆኑ ምክትላቸው የሆኑት ካማላ ሃሪስን ፕሬዝዳንትነት ሥራውን መረከባቸውን ዛሬ የዋይትሐውስ ቃላቀባይ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ የጤና ምርመራቸውን ለማድረግ ወደ ሆስፒታል ያቀኑት ዛሬ ሲሆን ከማደንዘዣው እስኪነቁ ድረስ ነው ምክትላቸው የፕሬዝዳንቱን ሥራ እንዲሰሩ የወከሉት።

በአሜሪካ ታሪክ ካማላ ሀሪስ የፕሬዝዳንትነት ስልጣን የያዙ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል።

አሜሪካን እስካሁን ከመሯት ፕሬዝዳንቶች ጆ ባይደን በእድሜ የመሪውን ደረጃ ይይዛሉ ፤ በነገው ዕለት 79 ዓመታቸውን ይደፍናሉ።

NB : በአሜሪካ ፕሬዘዳንትነት ታሪክ እኤአ ከ2002 እስከ 2007 ዓመት ስልጣነ ላይ የነበሩት ፕሬዘዳንት ደብሊው ቡሽ ለህክምና ክትትል ሆስፒታል ሲገቡ ስልጣናቸውን ለምክትላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አሳልፈው ሰጥተው ነበር።

Abruzzi media'ን በተለየያዩ አማራጮች ይከታተሉ

በ youtube

https://youtube.com/channel/UCSTMi4rzpPsP71kAw9cbEPg

በ Facebook

https://www.facebook.com/Abruzzi-Media-104580105333946/

በ Telegram

https://t.me/Abruzzimedia

Address

Hawassa
Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abruzzi Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abruzzi Media:

Share