Mereja Plus

Mereja Plus News page

በመዲናዋ የተመረጡ የመንግሥት ተቋማት እስከ እሁድ ግማሽ ቀን ድረስ አገልግሎት ሊሰጡ ነው።_________በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የሥራ ቀናት መራ...
13/07/2025

በመዲናዋ የተመረጡ የመንግሥት ተቋማት እስከ እሁድ ግማሽ ቀን ድረስ አገልግሎት ሊሰጡ ነው።
_________

በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የሥራ ቀናት መራዘሙን የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው እንዳሳወቀው፥ አገልግሎት ፈላጊዎች በተመረጡ ተቋማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና እሁድ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የገለጸው።

አገልግሎቱም ከማዕከል መስሪያ ቤቶች ጀምሮ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን አስታውቋል።

Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
FB: https://www.facebook.com/MerejaPlus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus

ኢትዮጵያና ሩሲያ የብርና የሩብል የቀጥታ የምንዛሪ ልዉዉጥ ማድረግ ጀመሩየሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ከሩሲያ ሩብል ጋር በቀጥታ ከሚመነዘሩ ገንዘቦች ዝርዝር ውስጥ ማካተቱን አስታወ...
12/07/2025

ኢትዮጵያና ሩሲያ የብርና የሩብል የቀጥታ የምንዛሪ ልዉዉጥ ማድረግ ጀመሩ

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ከሩሲያ ሩብል ጋር በቀጥታ ከሚመነዘሩ ገንዘቦች ዝርዝር ውስጥ ማካተቱን አስታወቀ።ባንኩ እንዳስታወቀዉ ዉሳኔዉ ብርን ወደ ሩብል ሩብልን ደግሞ ወደ ብር መመንዘር የሚያስችል ነዉ።

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ጨምሮ የ12 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ሩብልስ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱን ከተወሰኑ ቀናት በፊት አስታውቆ ነበር።

ማዕከላዊ ባንኩ ዛሬ ሃምሌ 04 ቀን 2017 ዓ.ም. ማለዳውን ይፋ ባደረገው መረጃም ለ100 የኢትዮጵያ ብር 57.58 ሩብል ወይም ለ1 ብር 0.57 ሩብል የምንዛሬ ተመን አስቀምጧል።

ባንኩ ለኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ ተመን የኮድ ቁጥር 230 የሰጠ ሲሆን በየዕለቱም የምንዛሬ ተመኑን የሚያሳውቅ እንደሆነ ነው የገለጸው።

Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus

“ ቼልሲ ልክ እንደ እኛ ነው “ ኤንሪኬ___________የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የነገው የቼልሲ የፍፃሜ ጨዋታ ቀላል እንደማይሆን ተናግረዋል። ስለ ተጋጣሚያቸው ያነሱት ሉዊስ ...
12/07/2025

“ ቼልሲ ልክ እንደ እኛ ነው “ ኤንሪኬ
___________

የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የነገው የቼልሲ የፍፃሜ ጨዋታ ቀላል እንደማይሆን ተናግረዋል።

ስለ ተጋጣሚያቸው ያነሱት ሉዊስ ኤንሪኬ “ ቼልሲ ሲያጠቃ እና ሲከላከል ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ቡድን ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም “ በአካል ጠንካራ ከሆነ ቡድን ጋር የምናደርገው ከባድ ጨዋታ ይሆናል ቼልሲ የተሟላ ቡድን ነው ጨዋታው ቀላል አይሆንልንም።" ብለዋል።

" አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ እና የቡድኑን አጨዋወት አደንቃለሁ ፣ ትልቅ ቴክኒካል ብቃት እና ጥሩ ተጨዋቾች አሏቸው።" ኤንሪኬ

Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus

ከዩቲዩብ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው__________በኢትዮጵያ ለዘጠኝ ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረ...
11/07/2025

ከዩቲዩብ፣ ቲክቶክና ከሌሎች የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር ሊጣል ነው
__________

በኢትዮጵያ ለዘጠኝ ዓመታት ስራ ላይ የቆየውን የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ በሚገኝ ገቢ ላይ 15% ግብር ለመጣል የሚያስችል ንዑስ አንቀጽ መካተቱ ታውቋል።

በታቀደው የአዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ መሰረት፣ ከማህበራዊ ሚዲያ የሚገኝ ገቢ (ለምሳሌ ከዩቲዩብ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቲክቶክ እና ሌሎችም መድረኮች) ፣ በኢንተርኔት ከሚሰራጩ መረጃዎች እንደሚሁም ከሚፈፀሙ ግብይቶች፣ ከስፖንሰርሺፕ እና ከመሳሰሉት የዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ላይ ግብር እንደሚጣልባቸው በዝርዝር ያስቀምጣል።

በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዉይይት እየተደረገበት የሚገኘዉ ይህ ረቂቅ አዋጅ፤ እነዚህ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመደበኛነት የሚከናወኑ ከሆነ፣ የሚገኘው ገቢ በንግድ ስራ ገቢ ስር የሚመደብ ሲሆን፣ የንግድ ስራ ገቢ ግብርም የሚከፈልበት መሆኑን ይገልጻል።

ሆኖም፣ በአዋጁ የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ከሆነ፣ ገቢው “ሌሎች ገቢዎች” በሚለው ስር ተመድቦ ግብር እንዲከፈልበት ይደረጋል ይላል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ለዲጂታል ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች ለእያንዳንዱ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ የተከፈለውን ገንዘብ የሚያሳይ ሪፖርት ለታክስ ባለስልጣኑ የመላክ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ያስቀምጣል።

ይህን ተከትሎም የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት፣ ገቢያቸውን የማስታወቅ እና ሌሎች የታክስ ከፋይ ግዴታዎችን የመወጣት ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ያስገድዳል።

Source: capitalethiopia

Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus

በደቡብ ኢትዮጵያ ሦስት ሰዎች በአፈር ናዳ ሕይወታቸው አለፈ____________በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሣላማጎ ወረዳ ሦስት ሰዎች በአፈር ናዳ ተቀብረው ሕይወታቸው አለፈ፡፡ የአ...
10/07/2025

በደቡብ ኢትዮጵያ ሦስት ሰዎች በአፈር ናዳ ሕይወታቸው አለፈ
____________

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሣላማጎ ወረዳ ሦስት ሰዎች በአፈር ናዳ ተቀብረው ሕይወታቸው አለፈ፡፡ የአፈር ናዳው ዛሬ ጠዋት የደረሰው በወረዳው ዲሜ ገሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው ፡፡

የናዳ አደጋው የደረሰው ከፍተኛ የኤሌትሪክ ምሶሶ ተሸካሚ ለመትከል የጉድጓድ ቁፋሮ በማከናወን ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ መሆኑን የሣላማጎ ወረዳ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በናዳው የሦስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የጽህፈት ቤት ሃላፊው አቶ ግዳጁ ጨነቀ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የሟቾቹ አስክሬን በቁፋሮ የወጣ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ ተጎጂዎች ደግሞ በአቅራቢያ በሚገኝ የጤና ጣቢያ የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አቶ ግዳጁ ተናግዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ባለፈው ዓመት ክረምት ደረሶ በነበረው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከሦስት መቶ በላይ ሰዎችን ለሞት መዳረጋቸው አይዘነጋም።

Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus

አሜሪካ ለኢትዮጵያውን በምትሰጠው የመግቢያ ቪዛ ላይ ቁጥጥሯን አጠናከረች_____________በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ስደተኛ ላልሆኑ እና ወደ ዩናይትድ ስቴት መጓዝ ለሚፈልጉ ...
10/07/2025

አሜሪካ ለኢትዮጵያውን በምትሰጠው የመግቢያ ቪዛ ላይ ቁጥጥሯን አጠናከረች
_____________

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ስደተኛ ላልሆኑ እና ወደ ዩናይትድ ስቴት መጓዝ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ጊዜያዊ ቪዛ የሶስት ወራት ብቻ እንደሚሆን አስታወቀ። በዚህ የአጭር ጊዜ ቪዛ ኢትዮጵያውያን ወደ አሜሪካ መግባት የሚችሉት አንድ ጊዜ ብቻ እንደሚሆን ኤምባሲው ዛሬ ሐሙስ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

እርምጃው ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑን የገለጸው የአሜሪካ ኤምባሲ ውሳኔው ከዚያ በፊት የተሰጡ ቪዛዎች ላይ ተጽዕኖ እንደማያሳድር አረጋግጧል።

ስደተኛ ላልሆኑ ሰዎች የሚሰጥ ቪዛ የሌሎች ሀገራት ዜጎች ለቱሪዝም፣ ለንግድ፣ ለሕክምና እና የተወሰኑ ቋሚ ያልሆኑ ሥራዎች በጊዜያዊነት ወደ አሜሪካ እንዲገቡ የሚፈቅድ ነው።

እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያውያን የሚያገኙት ቪዛ ወደ አሜሪካ በተደጋጋሚ እንዲገቡ የሚፈቅድ (multiple-entry) እና እስከ አንድ አመት የሚቆይ ነበር። አዲሱ ገደብ በተለይ ተማሪዎች ፣ ነጋዴዎች፣ ባለሙያዎች እና ከቤተሰብ ጋር ለመገናኘት የሚጓዙ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።

በጎርጎሮሳዊው 2024 ብቻ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ 23,270 ቪዛ ስደተኛ ላልሆኑ ሰዎች እንደሰጠዩናይትድ ስቴትስውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መረጃ ያሳያል።

በዶናልድ ትራምፕ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያን ጨምሮ በ36 ሀገራት ላይ የጉዞ ዕቀባ የመጣል ዕቅድ እንዳለው ባለፈው ሰኔ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበው ነበር።

Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus

የ70 ዓመቱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ______የ70 ዓመት አዛውንቱ አቶ ዋሬ ጎበና፣ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እየወሰዱ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡በሱሮ በ...
10/07/2025

የ70 ዓመቱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ
______

የ70 ዓመት አዛውንቱ አቶ ዋሬ ጎበና፣ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እየወሰዱ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡

በሱሮ በርጉዳ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዋሬ፤ ሰባት ልጆቻቸውን ለማስተማር ሲሉ እሳቸው ከትምህርት ቤት መቅረታቸውን አስረድተዋል።

ትምህርት ዕድሜ አይገድበውም የሚሉት አቶ ዋሬ፤ በተለያየ ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ጥሩ ምሳሌ ናቸው።

Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus

ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ለሚገነባው የ3 ቢሊዮን ዶላር ማዳበሪያ ፋብሪካ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጠ___________የአፍሪካ ቀዳሚ ባለጸጋና የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑ...
10/07/2025

ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ለሚገነባው የ3 ቢሊዮን ዶላር ማዳበሪያ ፋብሪካ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጠ
___________

የአፍሪካ ቀዳሚ ባለጸጋና የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አሊኮ ዳንጎቴ፣ በኢትዮጵያ የ3 ቢሊዮን ዶላር ግምት ያለው ዘመናዊ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት በይፋ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

"ኢትዮጵያ የጋዝ ምርት በቅርቡ ለገበያ ማቅረብ ትጀምራለች። በዚህም ሰርቶ አዳሪ እንጂ አውርቶ አዳሪ አለመሆናችንንም በተከታታይ እያሳየን እንቀጥላለን። የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል፤ ከ40 ወራት በኋላም ተጠናቅቆ ስራ ይጀምራል። " ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የፋብሪካው ግንባታ በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ እንደሚከናወን የተገለጸ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በ40 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በማዳበሪያ አቅርቦት ላይ በተለይም ከሩሲያ እና ከሌሎች የውጭ ሀገራት የምታደርገውን ጥገኝነት በእጅጉ ይቀንሳል ተብሎለታል።

የማዳበሪያ ፋብሪካው ግንባታ ሲጠናቀቅ በአገር ውስጥ የዩሪያ እና ናይትሮጅን ማዳበሪያዎችን ያመርታል፤ ይህም ለኢትዮጵያ ገበሬዎች በቀጥታ ተደራሽ የሚሆን ከመሆኑም በላይ፣ በርካታ የስራ እድሎችን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለ 2017 የምርት ዘመን የሚያስፈልገውን 25 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት 1.3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት አፅድቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል።

Source: capitalethiopia

Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus

ፒኤስጂ ሪያል ማድሪድን 4 ለ 0 በማሸነፍ ለፍፃሜው አለፈ።__________በክለቦች ዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ፒኤስጂ ሪያል ማድሪድን 4 ለ 0 በማሸነፍ ለፍፃሜው አለፈ።በሚትላይፍ ስቴዲየም በ...
09/07/2025

ፒኤስጂ ሪያል ማድሪድን 4 ለ 0 በማሸነፍ ለፍፃሜው አለፈ።
__________

በክለቦች ዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ፒኤስጂ ሪያል ማድሪድን 4 ለ 0 በማሸነፍ ለፍፃሜው አለፈ።

በሚትላይፍ ስቴዲየም በተደረገው ጨዋታ ፋቢያን ሪዩዝ ለፒኤስጂ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኡስማን ዴምቤሌ እና ራሞስ አንድ፣ አንድ ግብ አስቆጥረዋል።

ፒኤስጂ የዘንድሮውን የክለቦች ዓለም ዋንጫ ለማንሣት ከቼልሲ ጋር ይፋለማል።

Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus

ተጠባቂ ጨዋታ ፔኤስጂ ከማድሪድ የፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ለፍጻሜ ለማለፍ ከስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ የሚገናኝበት ጨዋታ ትልቅ ግምት አግኝቷል፡፡ የ15 ጊዜ የ...
09/07/2025

ተጠባቂ ጨዋታ ፔኤስጂ ከማድሪድ

የፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ለፍጻሜ ለማለፍ ከስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ የሚገናኝበት ጨዋታ ትልቅ ግምት አግኝቷል፡፡

የ15 ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ማድሪድ ከወቅቱ የአውሮፓ ምርጡ ቡድን የሚደርገው ትንቅንቅ።

በግሉም በቡድንም ከፔኤስጂ ጋር የተሳካ አመት ያሳለፈው ሌላኛው ፈረንሳዊ አጥቂ ኡስማን ዴምቤሌ ለማድሪድ ተከላካዮች ትልቁ ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

በሌላ በኩል ኬይሊያን ምባፔ የቀድሞ ክለቡን ለመጀመርያ ጊዜ የሚገጥምበት ይሆናል፡፡

Telegram: https://t.me/Mereja_Plus
YouTube: https://www.youtube.com/
Tiktok: mereja.plus

(Mereja Plus) - አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ስልጣን እንደያዙ በርካታ ህጎች ላይ የፈረሙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንደኛው የአሜሪካን የውጭ እርዳታ የሚመለከት ነው፡፡በ2024 ብቻ አሜ...
23/01/2025

(Mereja Plus) - አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ስልጣን እንደያዙ በርካታ ህጎች ላይ የፈረሙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንደኛው የአሜሪካን የውጭ እርዳታ የሚመለከት ነው፡፡

በ2024 ብቻ አሜሪካ ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሀገራ 6.6 ቢሊዮን ዶላር የሰብአዊ እርዳታ ሰጥታለች ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአፍሪካ የሚደረግ ድጋፍ እንዲቋረጥ የፈረሙት የአስፈፃሚ ትዕዛዝ በአሜሪካ የሰብአዊ እርዳታ ላይ በእጅጉ በሚተማመኑ የአፍሪካ ሀገራት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተጽዕኖ ስጋትን ጭሯል፡፡

የትራምፕ ድጋፍን የማቋረጥ ውሳኔ አሁን ያሉ ግጭቶችን ሊያጠናክር ፣ ተጨማሪ ሰብአዊ ተግዳሮቶችን ሊፈጥር እና ችግር ባላባቸው አካባቢዎች አለመረጋጋትን ሊያባብስ እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡

ፕሬዝዳንቱ ሀገራት ከፖሊሲ ግቦቻቸው ጋር ያላቸውን ትስስር ለመገምገም ሁሉንም የአሜሪካ የውጭ እርዳታ ፕሮግራሞች ለ90 ቀናት እንዲታገዱ በስልጣናቸው የመጀመሪያ ቀን ወስነዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት በከፍተኛ ደረጃ እርዳታ ከሚያቀርብባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ ከግንባር ቀደሞቹ መሀል የምትጠቀስ መሆኑ ይታወቃል፡፡


https://m.youtube.com/

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ከ100 ሺዎች በላይ ሰዎች በከፍተኛ ምግብ እጥረት ችግር ላይ መሆናቸው ተነገረዋግ ኽምራ ዞን በተለያዩ አደጋዎች ምክንያት ከ2015 ጀምሮ እስከ አሁን ከ514 ሺ...
22/01/2025

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ከ100 ሺዎች በላይ ሰዎች በከፍተኛ ምግብ እጥረት ችግር ላይ መሆናቸው ተነገረ

ዋግ ኽምራ ዞን በተለያዩ አደጋዎች ምክንያት ከ2015 ጀምሮ እስከ አሁን ከ514 ሺሕ 319 ኩንታል በላይ የሚሆን የሰብል ምርት ላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አስታውቋል።

በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ሰብሉ ላይ አደጋ መድረሱን የገለጸው ጽ/ቤቱ፤ በተለይ በዝናብ እጥረት፣ በበረዶ፣አደጋዎች አስተናግዷል።

በተጨማሪ የኅብረተሰቡ ጤና በሽታዎች ስርጭት ችግር ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።



https://m.youtube.com/

Address

Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mereja Plus posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share