Biruh Tesfa

Biruh Tesfa Humanity First! Interested in ስነ-ፅሁፍ፣በጎ-አድራጎት፣ Football (የጣናው ሞገድ & Man.united)

19/02/2024

እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን!
*********//***********
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ግዜ በወሰዱት አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫና የሙያ ፈቃድ ፈተና 99% ተፈታኞች ፈተናውን አልፈው ለመመረቅ ብቁ ሆነዋል:: ደስ ብሎናል እንኳን ደስ አላችሁ!

Congratulatory News!

Nearly all graduating class students of the College of Medicine and Health Sciences, Hawassa University, who took the first university exit and licensure exam have successfully passed their test. Congratulations to you all!

Hawassa University
Ever to Excel!

Our Social Media Platforms:
***************
Website: https://www.hu.edu.et
You tube: www.youtube.com/
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Telegram: https://t.me/HUCommunicationsoffice
Email: [email protected]
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa

ትኩረት ለላሊበላ አብያተ-ክርስቲያናት !!ላሊበላ የአለም ቅርስ ነው ‼️
11/11/2023

ትኩረት ለላሊበላ አብያተ-ክርስቲያናት !!

ላሊበላ የአለም ቅርስ ነው ‼️

30/10/2023

♦"በግጭቱ ዐውድ የአየር/ድሮን 5 ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት የተነሳ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ሰዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል።..."
***
አማራ ክልል:- ለወራት የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ዐውድ እና አሉታዊ የሰብአዊ መብቶች እንድምታው - ኢሰመኮ..
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) በአማራ ክልል የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ላስከተለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዘላቂ እልባት ለመስጠት ሰላማዊ መፍትሔ ማፈላለግን ጨምሮ፣ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል የሚያግዙ አፋጣኝ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በተለያየ ጊዜ ባወጣቸው መግለጫዎች ማሳሰቡ ይታወሳል። ኮሚሽኑ ግጭቱ በሰብአዊ መብቶች እና በማኅበራዊ እንቅስቃሴ ላይ ያስከተለውን አሉታዊ ውጤት በቅርበት መከታተሉን ቀጥሏል፡፡ በዚህም መሠረት በተለይም የሚመለከታቸውን መንግሥታዊ ኃላፊዎችን፣ በግጭቱ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን፣ የዐይን ምስክሮችን፣ተጎጂዎችንና የተጎጂዎች ቤተሰቦችን በማነጋገር መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ሲያሰባስብ ቆይቷል።

ይህ መግለጫ ይፋ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ በክልሉ ብዙ ወረዳዎች ውስጥ የትጥቅ ግጭት የተከሰተ ሲሆን፣ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ የአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ የትጥቅ ግጭት ተካሂዶባቸዋል። በተጨማሪም እነዚህ አካባቢዎች ወይም ወረዳዎች በአንድ ወቅት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ በሌላ ወቅት በታጣቂው ቡድን (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚታወቀው) ቁጥጥር ሥር ውለዋል። የትጥቅ ግጭቱ በአንዳንድ አካባቢዎች በከባድ መሣሪያ እና አልፎ አልፎ በአየር/ድሮን ድብደባ ጭምር የታገዘ ነው።

በግጭቱ ዐውድ የአየር/ድሮን 5 ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት የተነሳ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ሰዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል። ለምሳሌ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በረኸት ወረዳ፣ መጥተህ ብላ ከተማ ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የአንድ ዓመት ከሰባት ወር ሕፃንን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች እንደተገደሉ እና የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው፤ በደብረ ማርቆስ ከተማ ጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ደግሞ ቢያንስ 8 ሲቪል ሰዎች እንደተገደሉ፣ እንዲሁም በደንበጫ ከተማ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በከባድ መሣሪያ ድብደባ ምክንያት ሲቪል ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችና የዐይን ምስክሮች አስረድተዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ጥቃትን አልያም ግጭትን በመሸሽ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ከቀያቸው ተፈናቅለው በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል። በምንጃር ወረዳ የአውራ ጎዳና ጎጥ ነዋሪዎች ከመስከረም 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከቀያቸው ተፈናቀለው ቢያንስ 3000 የሚሆኑት አሞራ ቤቴ ቀበሌ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤትና ክፍት ሜዳ ላይ (በዛፍ ሥር) ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ ሌሎች ቁጥራቸው ያልታወቀ መተሃራና አዋሽን ጨምሮ ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዋል። ለተፈናቃዮች የተወሰነ ድጋፍ በማኅበረሰቡና እና በአንድ ተራድዖ ድርጅት የተደረገ ቢሆንም፣ በቂ ባለመሆኑ በአሳሳቢ ሁኔታ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል። የነዋሪዎችን መፈናቀል ተከትሎ ሰብላቸው እንደወደመ፣ ንብረታቸው እንደተዘረፈ፣ የቤቶቻቸው ጣራያ እና በር እየተነቀለ እንደተወሰደ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ቤቶቻቸውን ከአጎራባች ክልል በመጡ ኃይሎች በኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ጭምር ማፍረስ እንደተጀመረ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግሥት ኃላፊዎች ያስረዳሉ።

በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚፈጸሙ ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች አሳሳቢነት ኮሚሽኑ በመስከረም 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ማሳወቁ የሚታወስ ነው። ሆኖም በተለይም በመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት የሚፈጸሙ ከሕግ ውጪ የሆኑ ግድያዎች አሁንም መቀጠላቸውን ኢሰመኮ ተዓማኒ መረጃዎችን እየተቀበለ ይገኛል። ግጭቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ሲቪል ሰዎች ውስጥ “ፋኖን ትደግፋላችሁ፣ ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ፣ መሣሪያ አምጡ፣ የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ” በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ተዓማኒ መረጃዎች ለኮሚሽኑ ደርሰውታል። እንደማሳያ በባሕር ዳር ከተማ፣ ሰባታሚት አካባቢ መስከረም 29 እና 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ሦስት ወንድማማቾችን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች፣ በሰሜን ጎጃም ዞን፣ አዴት ከተማ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ፍልሰታ ደብረ ማሪያም የሚኖሩ 12 የአብነት ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ሲቪል ሰዎች፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ አማኑኤል ከተማ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢያንስ 8 ሲቪል ሰዎች በቤት ለቤት ፍተሻ እንደተገደሉ ለመረዳት ተችሏል። እንዲሁም በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ፣ ግንደወይን ከተማ ሞጣ በር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም. አንድ በጥይት የቆሰለን ግለሰብ እናቱና እህቱ በባጃጅ አሳፍረው ወደ ሕክምና ተቋም በመውሰድ ላይ እያሉ፣ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ባጃጁን አስቁመው ሁሉንም ተሳፋሪዎች ካስወረዱ በኋላ “የቆሰለው እኛን ሲዋጋ ነው” በሚል ምክንያት የባጃጅ አሽከርካሪውን ጨምሮ አራቱን ሰዎች በጥይት እንደገደሏቸው ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አስረድተዋል።

በባሕር ዳር፣ በፍኖተሰላም፣ በጎንደር እና በወልድያ ከተሞች በትጥቅ ግጭቱ ቆስለው ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ የተወሰኑ ሲቪል ሰዎችና የታጣቂ ቡድኑ አባላት በመሆን በመንግሥት የጸጥታ አካላት የተጠረጠሩ ሰዎች ሕክምናቸው እዲቋረጥ ተደርጎ ወዳልታወቀ ስፍራ ከተወሰዱ በኋላ፣ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ወደ ሕክምና ተቋማቱ ሲመለሱ ቀሪዎቹ ያሉበት ሁኔታ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ማረጋገጥ አልተቻለም።

በሌላ በኩል በየደረጃው የሚገኙ ሲቪል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች፣ ግድያዎችና እገታዎች በታጠቁ ኃይሎች ተፈጽመዋል። ለምሳሌ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም. የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከባሕር ዳር ወደ ደብረ ታቦር ሲሄዱ አለምበር ከተማ አካባቢ በታጣቂዎች ተገድለዋል። በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች እንዲያመልጡ ተደርጓል።

ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል በተለይም ከመንግሥት ተቋማት ጭምር በሚደርሱት መረጃዎች መሠረት በግጭቱ ዐውድ የሚፈጸሙ የአስገድዶ መድፈር ድርጊቶች በጣም አሳሳቢ እና በአፋጣኝ ተገቢው ምርመራ ተደረጎ እርምጃ ሊወሰድበት የሚገባው ነው። የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት በተለያዩ የጤና ተቋማት መድረስ የቻሉትን ተጎጂዎች ቁጥር ብቻ መሠረት በማድረግ፣ ከሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ቢያንስ 200 የአስገድዶ መድፈር ተጎጂዎች በጤና ተቋማት ተመዝግበዋል፤ ከተጎጂዎች መካከልም የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሴቶች እና የጤና ባለሞያ ሴቶች ጭምር ይገኙበታል።

ከትጥቅ ግጭቱ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሲቪል ሰዎች እና የሲቪል የንግድ እና የመሠረተ ልማት ተቋማት ላይ ዝርፊያ፣ የማሳ ላይ ሰብል ውድመት ጨምሮ በሲቪል ሰዎች፣ በሕዝብ እና በመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል። ሕፃናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸው እና በአንዳንድ አካባቢዎች የትምህርት ተቋማት ለወታደራዊ አገልግሎት መዋላቸው አፋጣኝ ትኩረት የሚሻ ነው። የባለሞያዎች ማኅበራት እና የሕክምና ተቋማቱ በይፋ እንዳስታወቁት የማኅበራዊ አገልግሎትና የሕክምና ተቋማት አገልግሎት በማቋረጣቸው ምክንያት፣ ነዋሪዎችን፣ በአማራ ክልል የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን እና ስደተኞችን ለተባባሰ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሚያጋልጥ ነው። ለምሳሌ በደቡብ ጎንደር ወረታ እና እብናት የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለወታደራዊ አገልግሎት/ካምፕ ሲውሉ የነበሩ ሲሆን፣ በሸዋ ሮቢት ከተማ የደጃዝማች ተሰማ እርገጤ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በጀውሀ ከተማ የጀውሀ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በብቸና የበላይ ዘለቀ መሰናዶ ትምህርት ቤት ይህ መግለጫ ይፋ እስከተደረገበትም ወቅት ድረስ ለወታደራዊ አገልግሎት መዋላቸው ተገልጿል። የአዴት ሆስፒታል በደረሰበት ዘረፋና ጉዳት አገልግሎት መስጠት ያቆመ ሲሆን፣ የፍኖተሰላም ሆስፒታል በደረሰበት ጥቃት እንዲሁም በባሕር ዳር የሚገኘው ጥበበ ግዮን ሆስፒታል በሠራተኞች፣ ታካሚዎችና አስታማሚዎች ላይ በደረሰው ወከባ፣ ድብደባና እስራት ምክንያት አገልግሎት ተቋርጦ ከነበረባቸው የጤና ተቋማት መካከል ይገኙበታል።

በተለያየ ወቅት በአማራ ክልል አብዛኛው አካባቢዎች ተግባራዊ በተደረገው የእንቅስቃሴ ገደብ እና የሰዓት እላፊ እንዲሁም በጸጥታ መደፍረስ የተለያዩ ወረዳዎችን የሚያገናኙ የመንገድ መጓጓዣዎች በመቋረጣቸው አልያም ውስን በመሆናቸው ምክንያት፣ የንግድ እና የማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በፈጠረው ተጽዕኖ ነዋሪዎች ለአቅርቦት እጥረት እና ለዋጋ ንረት እንዲሁም ለተያያዥ ችግሮች ተዳርገዋል። የተለያዩ አምራች አካባቢዎች ምርት ያቋረጡ ሲሆን፣ በገንዘብ ዝውውር ላይ የተጣለው ገደብን ጨምሮ በአንዳንድ ተቋማት የደመወዝ ክፍያ መቋረጥም ነዋሪዎችን ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ዳርጓል። በተጨማሪም በተለይም በሰሜን ጎንደር እና በዋግኅምራ አካባቢዎች በተደራራቢ ምክንያቶች በርካታ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ የሚሹ መሆኑ ታውቋል። በክልሉ ውስጥ በተለየ ሁኔታ ከተፈቀደላቸው ተቋማት በስተቀር ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን፣ በተለይም በግጭት ላይ ባሉ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎትም ጨምሮ ተቋርጧል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ኮሚሽኑ በተደጋጋሚ ባቀረበው ጥሪ እንደገለጸው ግጭቱን በዘላቂነት ለመፍታት ለሁሉም ሰላማዊ አማራጮች አሁንም ቅድሚያ መስጠትን ጨምሮ፤ ተፋላሚ ወገኖች ሲቪል ሰዎችንና ንብረቶችን፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን እና መሠረተ ልማቶችን በማናቸውም ሁኔታ ዒላማ እንዳያደርጉ፣ በቁጥጥር ሥር የዋሉ የታጠቁ ኃይሎች አባላትና ሌሎች ተጠርጣሪዎችም ሁኔታ በሕጋዊ አግባብ ብቻ እንዲስተናገድ፤ በተለይም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እና ከሕግ ውጭ የተፈጸመ ግድያ በአስቸኳይ በማጣራት ተጠያቂነት እንዲረጋገጥና የማኅበራዊ አገልግሎቶች በተቻለ ፍጥነት እንዲቀጥሉ እንዲደረግ” አሳስበው፤ “ተፈናቃዮች አስፈላጊው የሰብአዊ ድጋፍ በአስቸኳይ እንዲደርሳቸው እንዲደረግ፤ ለመፈናቀል የዳረጋቸው ምክንያት እልባት አግኝቶ በዘላቂነት ወደ ቀያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ እንዲመቻች ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል፡፡

ፎቶግራፍ:- ከኢንተርኔት የተገኘ

30/10/2023

አርቲስት ጌትነት እንየው

አምነው የወደዱ፣
ወደው የተካዱ፣
ተክደው የራዱ፣
ፍርሃት አንሸራቶ ቁልቁል የጣላቸው፣
የብቸኛ ልቦች የትነው መውደቂያቸው?
የትነው መድረካቸው?
ማነው አጃቢያቸው?
እንዴት ነው ምታቸው?
የተካዱ ልቦች አጋር የራቃቸው፣
የሚያቀነቅኑት ምንድን ነው ዜማቸው?

የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው፣
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው፣
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው፣
ብቸኝነት ሰርጎ ብቻ ያስቀራቸው፣
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
ከየት ነው ጥሪያቸው?
በየት ነው ጉዟቸው?
የት ነው መድረሻቸው?
እንደ ሰብአሰገል ጠቅሶ የሚመራቸው፣
የቃተቱ ልቦች የታል ኮከባቸው?

መቼም ከአምላክ ትንፋሽ ከውሃ ከአፈሩ፣
ከእምንት እና እውነት ከፍቅር ሲሰሩ፣
ዝምተኛ ልቦች ጥንቱን ሲፈጥሩ፣
ተገፍትረው ወድቀው፣
ደቀው እንዳይቀሩ፣
በተስፋ ጸንተው ነው ዘላለም ሊኖሩ።

10/10/2023
11/09/2023

በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ እንኳን ለ2016 የዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን እያስተላለፍኩ መጪው አዲስ አመት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላቀ ከገባችበት እጅግ ውስብስብና ፈታኝ ችግር ውስጥ ወጥታ የምናይበት የሰላምና የእንድነት ብሩህ ዘመን ይሆን ዘንድ ልባዊ ምኞቴን ስገልፅ ይህ ሁሉ እንዲሆን የእግዚሐብሄር እረዳትነቱ እንዳይለየን እየለመንኩ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወሳኝ ጨዋታ  ዩናይትድን ከ አርሰናል ያገናኛል። እኛም የማሸነፍ ግምቱን ለቀያይ ሰይጣኖቹ ሰጠናል  Man United 2:1 Arsenal ድል ለዩናይትድ 💪🏾💪🏾💪🏾
03/09/2023

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወሳኝ ጨዋታ ዩናይትድን ከ አርሰናል ያገናኛል።
እኛም የማሸነፍ ግምቱን ለቀያይ ሰይጣኖቹ ሰጠናል Man United 2:1 Arsenal

ድል ለዩናይትድ 💪🏾💪🏾💪🏾

እንኳን ለሊቀ መላኩ ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !! 🙏
25/07/2023

እንኳን ለሊቀ መላኩ ለቅዱስ ገብርኤል
አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !! 🙏

17/07/2023

በአገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ዩኒቨርሲቲያችን በግምባር ቀደምትነት ተማሪዎችን በማሳለፉ እንኳን ደስ አለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ።
**************************************

በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተተገበረው እና በዩኒቨርሲቲያችን ባሉ 8 ኮሌጆች፣ 2 ኢንስቲትዩቶችና 1 ትምህርት ቤት ስር በሚገኙ 73 ትምህርት ክፍሎች ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።

በአጠቃላይ ካስፈተናቸው 3,089 ተማሪዎች ውስጥ 2,760(89.35%) ተፈታኞች በብቃት አልፈዋል። ፈተናውን ከወሰዱ 73 ትምህርት ክፍሎች መካከል 34 ትምህርት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ (100%) አሳልፈዋል።

ከአጠቃላይ ተፈታኞች መካከል በመደበኛ መርሐግብር ካስፈተናቸው 2,919 ተማሪዎች 2,703 (92.6%) ያለፉ ሲሆን ቀሪዎቹ 170 ተማሪዎች በተከታታይ መርሐግብር ተፈተነው 57(33.53%) ፈተናውን በብቃት አልፈዋል።

ይህም ውጤት በአገሪቱ ካሉ አቻ ተቋማት ቀዳሚ ያደርገዋል።

በዚህም መላው የዩኒቨርስቲያችን ማህበረሰብና አጋሮቻችን ከፍተኛ ኩራትና ደስታ ተሰምቷቸዋል። የተገኘው ስኬት አበረታችና ለቀጣይ ትልቅ ኃላፊነትን የሰጠን ነው።

ስለሆነም ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ የቴክኒክ ረዳቶች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ትምህርት ሚኒስቴርና ሌሎች አጋር አካላት እንዲሁም መላ የትምህርት ቤተሰቡ በትብብር ያስመዘገባችሁት ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን።
*******************************
ለልህቀት እንተጋለን!
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግኝኙነት ዳይሬክቶሬት
ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም

Congratulations on University of Gondar's University Exit Exam Achievements!!******************************
The Ethiopian University Exit Exam 2023 results have been announced.

Graduating students of the University of Gondar enrolled in 73 departments under 8 colleges, 2 institutes and 1 school, have been reported to have sat for the exam.

Of the total 3,089 prospective graduates who were registered, 2,760 (89.35%)have passed the exam. What is more, out of the 73 departments, 34 have got all of their examinees(100%) succeed in passing the exam.

Of the 2,919 examinees, registered under our regular programs, 2,703 (92.6%) have passed the exit exam. Besides, 57 (33.53%), out of the 170 graduating students under our continuing education programs, have passed the exam successfully.

These results put the University of Gondar on top of the list of similar higher education institutions in the country that have administered the exam.

Therefore, we would like to congratulate our students, teachers, parents, technical assistants, administrative staff, partners and the Ministry of on your collective achievement.

Our achievement is encouraging though, it leaves us with more responsibilities in the years to come.
******************
Devoted to Excellence!
Public and International Relations Directorate
July 09/2015

መልካም ዕለተ ሰንበት !
09/07/2023

መልካም ዕለተ ሰንበት !

Address

Hawassa
Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biruh Tesfa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share