
28/07/2025
ያልመከነ ተተኳሽ ፈንድቶ የሦሥት ህፃናት ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
ሦሥቱ ወንድሟሟች ናቸው ነው የተባለው።
ታዲያ አደጋው የተከሰተው ባለፈው ሀሞሌ 18ቀን 2017 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታሕታይ ቆራሮ ወረዳ ልዩ ስሙ ዓዲ መናብር መኾኑን የዘገበው ቲክቫህ ኢትዮጵ ነው።
ህፃናቱ ለጨዋታ በተንቀሳቀሱበት መንደራቸው አጠገብ የሚገኘው ጫካ ውስጥ የወደቀ ሹል ድምቡልቡል ብረት ያገኛሉ።
የልጅ ነገር ሆኖባቸው ብረቱ በደንጋይ እየቀጠቀጡ ሳጫወቱ ፈንድቶባቸው ወድያውኑ ህይወታቸው አልፈዋል።
በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው ያሉ ያልመከኑ ተተኳሾት በሰውና እንስሳት ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ቀጥሏል።
ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በትግራይ የተለያዪ ወረዳዎች የሚገኙ ያልመከኑ ተተኳሾች በማስወገድ ሰብአዊ ኃላፊነታቸው በመወጣት ላይ ቢገኙም ጦርነቱ ከተካሄደበት የቦታ የቆዳ ስፋት አንፃር በቂ እንዳልሆነ ይገለፃል።