22/07/2025
በከተሞች ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲመዘገብ የተጀመረዉ የክትትልና ድጋፍ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።
አቶ አሻግሬ ጀንበሬ ቢሮ ኃላፊ
የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት አመት በክልሉ በሚገኙ ከተሞች ሲያካሂድ በቆየዉ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት የነበሩ ጥናካሬዎች እና ጉድለቶች ላይ ያተኮረ ግምገማ አካሂዷል።
የግምገማ መድርኩን የመሩት የቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ የተካሄደዉ የክትትልና ድጋፍ ሥርዓታችን ከተለመደዉ አካሄድ ወጣ ባለ መንገድ ቴክኒካል ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ የቢሮ አመራሩ ተጠያቂነት ያለዉን አሰራር ዞኖችን ተከፋፍሎ በመመደብ የታችኛዉ መዋቅር ተቋም ግንባታ ላይ ያተኮረ የድጋፍ ስራ ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።
አመራሩ ባደረገዉ ክትትልና ድጋፍ ዉጤታማ የሆኑ ለዉጦች የታዩ መሆኑን ጠቅሰዉ በተፈጠረ የህዝብ ንቅናቄ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ በጉልበቱና በገንዘቡ የልማት ሥራዎቹን ከማገዝ ባለፈ እጅግ በሚያስደንቅ ተነሳሽነት የከተሞቹን ፕላን መሰረት በማድሩግ ያለምንም ካሳ ክፍያ ንብረቶቹን በማንሳት ጭምር አዳዲስ መንገዶች ከፈታ ስራን ሰርቷል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ እንደ ሀገር የተጀመረዉና በሐዋሳ ከተማ ተግባራዊ እየተደረገ ያለዉ የኮሪደር ልማት ሥራ ወደ ክልሉ ዋና ዋና ከተሞች በማስፋት እየተከናወነ ባለዉ ሥራ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዉ ይህንኑ ሥራ በሌሎች ከተሞችም ለማስቀጠል ያለዉ የተደራጀ የህዝብ ጥያቄ እየጨመረ በመምጣቱ በአግባቡ በመምራት ዉጤቴማ ማድረግን ይጠይቃል ብለዋል።
ከተሞች በሰበሰቡት ገቢ ከሚያሰሯቸዉ የልማት ስራዎች በተጨማሪ የክልሉ መንግስት ባስቀመጠዉ አቅጣጫ ቢሮዉ በጀት በመመደብ እተከናወነ ያለዉ ፍትሐዊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታና የአቅም ግንባታ ስራ ከትሞች ተወዳዳሪና ለነዋሪዎቻቸዉ ምቹ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ ለዘመናት የቆየዉን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እየተመለሰ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
የገጠር ማዕከላትን ፕላን በማስከበር ከተሞች የዘመናዊነት ገጽታን ይዘዉ እንዲያድጉ ይረዳቸዋል ያሉት የቢሮ ኃላፊ ከተሞች የከተሜነት መልክ ይዘዉ በሚፈለገዉ ስታንዳርድ መሠረት እንዲገነቡ እየተደረገ ያለዉ ድጋፍም የአመራሩን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።
በከተሞች ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን በማዘመን ቀልጣፋና እርካታን የሚያረጋግጥ ሥራ በመስራትና ዕድገታቸውን በዘላቂነት ለማስቀጠል እየተደረገ ያለዉን ጥረት ወደ ተጨባጭ ዉጤት ለመቀየር የቢሮዉ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በአዲሱ በጅ ት ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
በአጠቃላይ በዚህ ዓመት የተጀመረዉን የታችኛዉ መዋቅር ተቋም ግንባታ ስራ ላይ የታዩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠልና ክፍተቶቹን ደግሞ አርሞና የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ አካል አድርጎ ለመፈጸም ቀጣይነት ያለ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች የየከተሞቹን ሪፖርት በየከተሞቹ ካደረጉት የመስክ ምልከታ ጋር በማያያዝ ሰፊ ግምገማ አካሂደዋል።
በመድረኩ የቢሮዉ አመራሮች፣ የተለያየ ዘርፍ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በግምገማዉ በአንዳንድ ከተሞች የሚታየዉ የአመራር ብቃት ማነስ፣ የገቢ አማራጮችን በማስፋት ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ ለልማት ከማዋል ጋር የሚታዩ ጉድለቶች እና ሌሎች ችግሮች በቀጣይ በሚደረግ ድጋፍ በማረምና በማብቃት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።
በመጨረሻም ተሣታፊዎቹ ቢሮዉ ለሥራ ምቹ በማድረግ አዲስ እያስገነባና የግንባ