Bankers group

Bankers group Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bankers group, Digital creator, Awassa.

17/08/2022

#ኢትዮጵያ

06/08/2022

#ኢትዮጵያ

06/08/2022

ዳሸን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በአጋርነት ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ያለምንም መያዣ የሚሰጥ የቴሌብር የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀመረ፡፡ የሚሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

#ቴሌብር መላ (Micro Credit) ፡- ግለሰብ ደንበኞች፣ ነጋዴዎች እንዲሁም ወኪሎች በቴሌብር ሂሳባቸው
አማካኝነት አነስተኛ ብድር አገልግሎት የሚያገኙበት መንገድ ነው፡፡

#እንደ ኪሴ (Micro Overdraft) ፡-የቴሌብር ደንበኞች በአካውንታቸው ላይ ያላቸው ቀሪ የሂሳብ
መጠን በቂ ባልሆነበት ጊዜ የሚጠቀሙበት የብድር አገልግሎት ነው፡፡

#ሳንዱቅ (Micro Saving) ፡- ደንበኞች እንደየፍላጎታቸው ከወለድ ነፃ ወይም በየቀኑ የሚሰላ የወለድ መጠን የሚታሰብባቸው የቁጠባ አይነቶችን የሚጠቀሙበት የቴሌብር አገልግሎት ነው፡፡

06/08/2022
12/02/2022
16/01/2022

መንግስት ባንኮች ከሚሰበስቡት የውጪ ምንዛሬ ውስጥ 70% ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ አለባቸው ሲል ምን እያለ ነው? ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የለውም? (ተደጋጋሚ ሰሞነኛ ጥያቄ ነው!)።

ባንኮች የውጪ ምንዛሬ በመመንዘር (Foreign Exchange)፤ የውጪ ባለሀብቶች ከሚያመጡት (FDI)፤ ዜጎች ለቤተሰቦቻቸው ከሚልኩት (Remittances)፤ በውጪ ንግድ ከሚሳተፈው ማህበረሰብ፤ ወዘተ ያሰባስባሉ።

ባንኮች የሰበሰቡትን የውጪ ምንዛሬ በሙሉ የመጠቀም እድል የላቸውም! ምክንያቱም ማዕከላዊ ባንኩ የኢኮኖሚ ትኩረት ለሆኑ ሴክተሮች ቅድሚያ ለመስጠት የውጪ ገንዘቦችን ከባንኮች በመመሪያ ይወስዳል።

ለብዙ ጊዚያት ባንኮች ከሚያገኙት የውጪ ምንዛሬ 30% ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ሲያደርጉ ቆይተው ነበር፡ ላለፉት 6 ወራት ወደ 50% አደገ አሁን ላይ #በጊዚያዊነት 70% የውጪ ምንዛሬ ግኝታቸውን ወደ ማዕከላዊ ባንክ እንዲያስረክቡ ታዟል።

#ለምሳሌ፦ አንድ ባንክ በቅርቡ ከመጡ ዳያስፖራዎች አንድ ሚሊየን ዶላር መንዝሮ ቢሆን 700ሺ ዶላሩን ለብሄራዊ ባንክ በእለቱ የዶላር ምንዛሬ ያስረክባል ማለት ነው።

የመንግስት ውሳኔ የሚያመለክተው ከወቅታዊ ሁኔታዎች አንፃር በካዝናው የውጪ ምንዛሬ እጥረት እንደገጠመው ነው።

ይህ ገንዘብ በባንኮች እጅ ቢሆን እነሱ ያዋጣናል ለሚሉት እና በመንግስት ቅድሚያ እንዲሰጥ ለታዘዙት ሴክተሮች ሊያቀርቡት ይችላሉ! ነገር ግን መንግስት በዚህ ወቅት እንደ ሀገር አንገብጋቢ ለሚባሉ ሴክተሮች እና ጉዳዮች የውጪ ምንዛሬውን ለማዋል አልሟል ማለት ነው።

በዚህ ውሳኔ ባንኮች የውጪ ምንዛሬ በማቅረብ የሚያገኙት ትርፍ እንዲቀንስ ማድረጉ አይቀርም፤ የግል ሴክተሩ በግብዓት በውጪ ገበያ ጥገኛ በመሆኑ የምርት ሂደት ላይ መፈተኑ አይቀርም (ለጥቁር ገበያ አማራጭ ሊገፋቸውም ይችላል)፤ ማዕከላዊ ገበያው መሰረታዊ ሸቀጦችን ከውጪ እንደመሸመቱ ከዚህ ውሳኔ ማግስት የግል ሴክተሩ የውጪ ምንዛሬ ሲያንሰው ከውጪ ሸምቶ ለማቅረብ መቸገሩ አይቀርም (ዋጋ በጊዚያዊነትም ቢሆን እንዲያድግ ያደርጋል)፤ ወዘተ።

#ለምሳሌ፦ ከውሳኔው ድንገትነት የተነሳ ወደውጪ ምርት የሚልኩ አምራቾች ትዛዝ ቀድመው ተቀብለው ቢሆን ከዚህ ውሳኔ ማግስት የውጪ ምንዛሬ እጥረት ሲገጥማቸው ምርቱን አምርተው ለውጪዎቹ ካምፓኒዎች ለማቅረብ ሊቸገሩ ይችላሉ። ይህ አጋጣሚ ለኪሳራም ወደ ጥቁር ገበያም እንዳያመራቸው ስጋት መሆን ይችላል።

ለምን ውሳኔው ተወሰነ ማለት ከባድ ነው! ለረጅም ወራት ጦርነት፤ ድርቅ፤ የፀጥታ ችግር እና ውስን ማዕቀብ (እርዳታ እና ብድርን ጨምሮ)የያዘ ኢኮኖሚ ነው። "ከበጣም መጥፎ! መጥፎ!" እየወሰነ መሄዱ ተጠባቂ ነው።

ቢሆንም የግል ሴክተሩ የኢኮኖሚው ዋስትና መሆኑን በመረዳት ይህ ውሳኔ ይበልጥ ሊጎዳቸው የሚችላቸውን ሴክተሮች ልዩ ትኩረት በመስጠት በውሳኔው ማዕከላዊ ገበያው መሰረታዊ ችግር እንዳያስተናግድ ማድረግ ተገቢ ነው።

ውሳኔው በገበያው የሚቆይ ከሆነ ባንኮች በጥረት የሚሰበስቡት የውጪ ምንዛሬ ላይ መቀዛቀዝ ሊፈጥሩ እንዲሁም የውጪ ንግድ ሂደቱን ሊያዳክመው ስለሚችል ተለዋጭ ስትራቴጂ አስፈላጊ ነው።

👉Telegram:- https://t.me/wasealpha

24/07/2021
04/07/2021
14/04/2021

Find the best Ethiopian businesses and services near you. Best Ethiopian Hotels, Restaurants ,Nightlife, Travel and Tour, Food, Shopping, Entertainment ,car rental and Services.

Address

Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bankers group posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Bankers group:

Share