ሀማራ ሚዲያ - Hamara media

ሀማራ ሚዲያ - Hamara media Media/Production

በጣም የሚያሳዝን ዜና 💔የተወዳጁ ኮሜዲያን ወንደሠን አውራሪስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ የሰማነው እጅግ አሳዛኝ ዜና ነው።ለብዙ ዓመታት በሳቅ ሲያጥመቅ የኖረው ወንደሠን፣ እንደ ምንጮች ዘገባ...
30/11/2025

በጣም የሚያሳዝን ዜና 💔

የተወዳጁ ኮሜዲያን ወንደሠን አውራሪስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ የሰማነው እጅግ አሳዛኝ ዜና ነው።

ለብዙ ዓመታት በሳቅ ሲያጥመቅ የኖረው ወንደሠን፣ እንደ ምንጮች ዘገባ በድንገተኛ የልብ ህመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ስንሰማ ልባችን ተሰብሯል።

አስክሬኑም ለምርመራ በሚኒሊክ ሆስፒታል
እንደሚገኝ ተገልጿል።

አይ እቺ ዓለም...

* ነብስ ይማር ለኮሜዲያኑ!
* ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለአድናቂዎቹ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።

በስራዎቹ ሁሌም እናስታውስሃለን! ወንዴ 🙏🏽

💔💔💔

እጅግ ልብ የሚሰብር ዜና 😭የሁለት ወንድማማቾች ሕይወት በመኪና አደጋ አልፏል።ታላቅ ወንድም ሙዚቀኛ ይስሃቅ አብርሃም በዛሬው ዕለት ሕዳር 13/2018 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ አርባምንጭ ጉዞ...
23/11/2025

እጅግ ልብ የሚሰብር ዜና 😭
የሁለት ወንድማማቾች ሕይወት በመኪና አደጋ አልፏል።

ታላቅ ወንድም ሙዚቀኛ ይስሃቅ አብርሃም በዛሬው ዕለት ሕዳር 13/2018 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ አርባምንጭ ጉዞ ላይ እያለ በደረሰ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወቱ እንዳለፈ የመረጃ ምንጮቻችን ነግረውናል።

የወንድሙን መሞት የሰማው የወበዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪ አቤኔዘር አብርሃም በዛሬው ዕለት ህዳር 13/2018 ዓ.ም ከሚማርበት ዩኒቨርሲቲ የወንድሙን ቀብር ለመድረስ ከሆሳዕና ወደ ወላይታ ሶዶ እየተጓዘ ሳለ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን ዋዕዶሌ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በደረሰው የመኪና አደጋ ህይወቱ እንዳለፈ ዩኒቨርስቲው ገልጿል።

በዚህም ሁለቱ ወንድማማቾች በአንድ ቀን በመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

የወንድማማቾቹ ድንገተኛ ሕልፈት በአርባምንጭና አካባቢው ድንጋጤን ፈጥሯል።

በሁለቱ ወንድማማቾች ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ዱቡሻ ሚዲያ ኔትዎርክ እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው መፅናናትን ይመኛል።
ነፍሳችሁ በሰላም ትረፍ!

በምስራቅ አፍሪካ በሚካሄደው Iconic Award ላይ ኢትዮጵያን ወክላ በሁለት ዘርፎች እጩ ሆና በሁለት ዘርፍ በመወዳደር ላይ ያለችውን Yuti Nass ከዚህ በታች ባለው ሊንክ በመግባት Ic...
17/11/2025

በምስራቅ አፍሪካ በሚካሄደው Iconic Award ላይ ኢትዮጵያን ወክላ በሁለት ዘርፎች እጩ ሆና በሁለት ዘርፍ በመወዳደር ላይ ያለችውን Yuti Nass ከዚህ በታች ባለው ሊንክ በመግባት Iconic Content Creator of The Year እና Iconic Influencer ውስጥ በመግባት ይምረጧት።

https://vote.iconicawards.pro/categories

በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ በሚደረገው ደሞ በ24 ስዓት ልዩነተት ደጋግማቹ መምረጥ ትችላላቹ ።

በ Iconic Influencer በሰፊ ልዩነት እየመራች ሲሆን
በIconic Content Creator of The Year ደሞ በትንሽ ቁጥር እየተመራች ትገኛለች።

የአህዳውያኑ ቅዠት በሀዋሳ ዳግም ለምን ተቀሰቀሰ?ለዘመናት የሲዳማ ህዝብ እራስን በራስ ለማስተዳደር ሲታገል መክረሙ አይዘነጋም።የሲዳማ ህዝብ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር ካደረገው ትግል ይልቅ አ...
17/11/2025

የአህዳውያኑ ቅዠት በሀዋሳ ዳግም ለምን ተቀሰቀሰ?

ለዘመናት የሲዳማ ህዝብ እራስን በራስ ለማስተዳደር ሲታገል መክረሙ አይዘነጋም።የሲዳማ ህዝብ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር ካደረገው ትግል ይልቅ አጠገቡ ሆነው የሱ የሆነውን መዝብረው እሱን ግን በሚጠሉ ነጣቂ አህዳዊዎች ጋር ያደረገው ትግል ይልቃል።

ዛሬ ላይ ሲዳማ ክልልነቱን አረጋግጦ ወደ ልማት ጥያቄው ፊቱን ባዞረበት በዚህ ወቅት ዳግም የሀዋሳ ከተማን አጀንዳ ለማድረግ የሲዳማ ጠላቶች ህብረት ፈጥረው በየፊናቸው ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል።

ከዘሀበሻ እስከ ትናንሽ ፔጆች።አለፍ ሲልም ሀዋሳ ሆዱን ብቻ ሳይሆን ሱሱን አራግፋ ሰው ያደረገችው የካምፓላው ጥገኛ ምናሴ ሳይቀር በሀዋሳ እና በሲዳማ ላይ ያነጣጠረ ትግል ጀምረዋል።

በመሆኑም የሲዳማ ህዝብ አይቻልም ተብሎ የሚታሰበውን በአንድነት እንዳሳካ ለእነዚህ አህዳዊያን ነጣቂዎች በሚገባቸው ቋንቋ ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል።

ሰበር ዜናየአፋር ክልል ሚሊሻዎች ወደ ክልላቸው ሰብረው በገቡ የሕውሓት ታጣቂዎች ላይ የመልሶ ማጥቃት መክፈታቸው ተሰምቷል፡፡ ሚሊሻዎቹ ወደ ግንባር ሲንቀሳቀሱ የሚያስ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበ...
06/11/2025

ሰበር ዜና

የአፋር ክልል ሚሊሻዎች ወደ ክልላቸው ሰብረው በገቡ የሕውሓት ታጣቂዎች ላይ የመልሶ ማጥቃት መክፈታቸው ተሰምቷል፡፡ ሚሊሻዎቹ ወደ ግንባር ሲንቀሳቀሱ የሚያስ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተራጭቷል፡፡

ሰበር -ዜና ‼️  ከአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ ከጥፋቱ የማይመረው ጉጅሌው የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በማግባት 6 መንደሮችን በጉልበት በመቆ...
05/11/2025

ሰበር -ዜና ‼️

ከአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

ከጥፋቱ የማይመረው ጉጅሌው የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በማግባት 6 መንደሮችን በጉልበት በመቆጣጠር ንጹሃንን በሞርታርና በዙ-23 በመደብደብ የተለመደውን የሽብር ተግባሩን በግልጽ ጀምሯል።

በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 26/02/2018 ዓ/ም የአዛውንቶች የህወሓት ጉጅሌ በአፋር ክልል በዞን ሁለት በመጋሌ ወረዳ ቶንሳ ቀበሌ ዋራዓ እና ሚልኪ በሚባሉ ልዩ አካባቢዎች ወሰን ተሻግሮ በመግባት ከምሽቱ አንድ ሰአት አካባቢ በንጹሐን የአፋር አርብቶ-አደሮች ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በመክፈት የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግጭት አዋጅ በግልጽ አፍርሷል።

ይህ የህወሓት ጣብ-ጫሪ ቡድን በቶንሳ ቀበሌ ላይ ተኩስ በሚከፈትበት ወቅት ሰላም ወዳድ የአፋር ሽማግሌዎች እንድመለሱ ቢማፀኗቸውም ጉጅሌው ግን አሻፈረኝ በማለት ግጭቱን አስከትሏል። ይህ ከትናንት ጥፋቱ የማይማረው ተስፋ ቢሱ የህወሓት ጉጅሌ ቡድን ከድርጊቱ በአስቸኳይ ካልተቆጠበ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የዜጎች ደህንነትና የወሰኑን ክብር የማስጠበቅ፣ እንዲሁም ራስን ከማንኛውም ውጫዊ ጥቃት የመከላከል ኃላፊነቱን እንደሚወጣ እንገልፃለን።


#ሼር
#ሼር


በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓልበእናት ላይ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፈጸመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል::የሕግ አስከባሪ አካል አባል የነበረው እና በአንዲት እናት ላይ ...
25/10/2025

በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል

በእናት ላይ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፈጸመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል::

የሕግ አስከባሪ አካል አባል የነበረው እና በአንዲት እናት ላይ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ፈጽሟል የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

ይህ ድርጊት በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን እና መነጋገሪያን የፈጠረ ሲሆን፣ በፍትህ ላይ ያላቸውን እምነት ያናጋ መሆኑን ህብረተሰቡ እየገለጸ ነው።

የህብረተሰቡ ጥያቄ፦ ህዝቡ ፖሊሱ በፈጸመው አሳፋሪ ድርጊት የሚመጥን እና ለሌሎችም አስተማሪ የሚሆን ፍርድና ቅጣት እንዲያገኝ ጠይቋል።

የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እና መሰል በደሎች ዳግም እንዳይፈጸሙ እርምጃው አጥጋቢ መሆን አለበት ሲል አስተያየቱን እየሰነዘረ ይገኛል።

ፍትህ ይረጋገጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን!
ሀማራ ሚዲያ

ርዕሰ መስተዳድሩ በስራ ላይ ናቸው=======================አመሻሹን እየወጡ ባሉ መረጃዎች በብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ መድረክ ማጠናቀቅያ ላይ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ...
24/10/2025

ርዕሰ መስተዳድሩ በስራ ላይ ናቸው
=======================
አመሻሹን እየወጡ ባሉ መረጃዎች በብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ መድረክ ማጠናቀቅያ ላይ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰመስትዳድር ደስታው ሌዳሞ ከሀላፊነት ታገዱ ተብሎ የሚሰራጨው ዜና ሀሰተኛ መሆኑን ሚዲያችን አረጋግጣለች።

ከዚህ ርዕስ ጋር በተያያዘ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መድረክ የተነሳ ምንም ጉዳይ አለመኖሩን የገለጹልን ምንጫችን መረጃው ፍፁም ስህተት መሆኑን አክለው በመግለፅ ማህበረሰቡ እራሱን ከሀሰተኛ መረጃ እንዲጠብቅ ሀሳባቸውን ችረዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የተለየ መረጃ እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።

ሀማራ ሚዲያ

የጤና ባለሞያዎች ህይወት አለፈበምስራቅ ሸዋ ኦለንጪቲ  በቀን 12/02/2018 ዓም ከአርሲ ዞን  ከተለያዩ ወረዳዎች ከተወጣጡና ለትምህርት ወደ ሀረማያ ዩንቨርስቲ ሲጓዙ በነበሩ  የጤና ባለሙ...
22/10/2025

የጤና ባለሞያዎች ህይወት አለፈ

በምስራቅ ሸዋ ኦለንጪቲ በቀን 12/02/2018 ዓም ከአርሲ ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች ከተወጣጡና ለትምህርት ወደ ሀረማያ ዩንቨርስቲ ሲጓዙ በነበሩ የጤና ባለሙያዎች ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የብዙዎች ህይወት ተቀጥፏል።

የሙፍቲ የቀብር ስነስርአት በምክር ቤቱ ተወገዘ!መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል ...የቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር ኢድሪሰ በኑዛዜያቸው መሰረት ከሙስሊሞች መቃብር ውጪ በቤታቸው አጠገብ እንዲቀበሩ ...
21/10/2025

የሙፍቲ የቀብር ስነስርአት በምክር ቤቱ ተወገዘ!

መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል ...

የቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር ኢድሪሰ በኑዛዜያቸው መሰረት ከሙስሊሞች መቃብር ውጪ በቤታቸው አጠገብ እንዲቀበሩ የተወሰነው ውሳኔ በሀገራችን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ክስተት መሆኑን ነው።እኛም የተውሒድን ገጽታ ለመጠበቅ ስንል ይህንን ድርጊት አጥብቀን እንቃወማለን።

ድርጊቱ ለቀጣይ ትውልዶች ከጊዜ ሂደት በኋላ ወደ ሺርክና ወደ ቀብር አምልኮ የሚያመራ ሰበብ እና መንገድ እንዳይሆን እንሰጋለን። የዑለማእምክር ቤቱ ይህ ውሳኔ ሲወሰንና ተግባራዊ ሲደረግ ምንም አይነት ቅድመ-መረጃ እንዳልነበረው ሊታወቅ ይገባል።

በጉዳዩ ዙሪያ የጠቅላይ ምክር ቤቱን ክቡር ፕሬዝዳንት አነጋግረን የነበረ ሲሆን፣ ኑዛዜው እንዲሻርና ቀብሩ በሙስሊሞች መቃብር እንዲፈጸም ለማድረግ ከሸይኹ ቤተሰቦችና ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ሙከራ እንዳደረጉ ነገር ግን እንዳልተሳካላቸው ገልጸውልናል።

በመሆኑም፣ ምክር ቤቱ ከሸሪዓህ መንፈስ ጋር የሚጋጩ እንዲህ አይነት ተግባራትን በብርቱ የሚቃወምና የሚያወግዝ መሆኑን ይገልጻል።

በተጨማሪም፣ ሁሉም ዑለማዎች የተውሒድን ክብር ለመጠበቅና ከሺርክ ለማስጠንቀቅ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ መሰል ጉዳዮች ላይ ትክክለኛውን የሸሪዓህ ግንዛቤ እንዲያሰርጹና ግንዛቤ እንዲፈጥሩ አደራ ይላል።

ሸይኽ ዶ/ር ዐሊ ሙሐመድ
የኢትዮጵያ ዑለማእ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት

አሳዛኝ ዜና፡ በድሬዳዋ-ደወሌ ባቡር አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ!ከደወሌ ወደ ድሬዳዋ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ባቡር ላይ ትላንት ምሽት 8፡00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ ...
21/10/2025

አሳዛኝ ዜና፡
በድሬዳዋ-ደወሌ ባቡር አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

ከደወሌ ወደ ድሬዳዋ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ባቡር ላይ ትላንት ምሽት 8፡00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ አሰቃቂ አደጋ ደረሰ።

በዚህ አደጋ ምክንያት የ14 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ 29 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ከሺኒሌ ወረዳ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሺኒሌ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን፣ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

Via ድሬ ቲቪ

ነብስ ይማር ወገኖቻችን💔

ወልዲያ‼️በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ዙሪያ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎች ጠዋት ጀምሮ እስከዚህ ሰዓት ድረስ/5:40/ ጠንከር ያለ የተኩስ ልውውጥ እየተሰማ መሆኑን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋ...
27/09/2025

ወልዲያ‼️
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ዙሪያ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎች ጠዋት ጀምሮ እስከዚህ ሰዓት ድረስ/5:40/ ጠንከር ያለ የተኩስ ልውውጥ እየተሰማ መሆኑን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።
ይህ የተኩስ ልውውጥ ከሰሜኑ ጦርነት ወዲህ ያየነው ጠንከር ያለ ውጊያ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ የመድፍ ድምጽ እየሰማን ነው ብለዋል።
ተኩስ የሚሰማው ከመቻሬ መብራት ሀይል እስከ ጀነቶ በር-ጉቦ አዲሱ ማረሚያ ቤት አካባቢ ነው ብለዋል።

ሀማራ ሚዲያ

Address

EVERYWHERE
Awassa

Telephone

+251919798102

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሀማራ ሚዲያ - Hamara media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category