16/01/2025
ጀግናው መሪያችንን ሺህ አመት ኑርልን እወድሃለን አብርሽ 🙏
ጀግናው መሪ ክብር አቶ አብርሃም ማርሻሎ ከመሠረቱ ጀምሮ በሚዛናዊ ፖለቲካን የሚያራምድ የብሔር ብሔረሰቦች መብት እንዲከበር ነፃነትና ወንድማማችነት እንዲጠናከር ሁሌም የሚተጋ ከወጣነትነት ዕድሜ ጀምሮ ለዚህ መስዋዕነትን እየከፈለ የኖረ ህልም የሰው ልጆች በሰላምና በእኩልነት በምድር እንዲፀና ብሎም ምድር ለሰው ልጆች እንድትመች የሚተጋ ታማኝ እና ትልቅ ሰው ነው።
ከወረዳ አመራርነት እስከ ዞን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሲሰራ ህዝብን የሚጎዱ አመለካከትና ተግባር ውስጥ ሳይሳተፍ ህሊናውን ጠብቆ እጁና ልቡን ንጽህ በመሆን በታማኝነት ህዝብን ያገለገለ በዚህም ተግባሩ በቀድሞ ደቡብ ክልል በተለያዩ የመሪነት ቦታዎች ሲያገለግል በታማኝነት በትህትና ማንንም ሳይለያይ ወደ ሁሉም ዞኖች፤ ወረዳዎች እስከ ቀበሌ ድረስ እየወረደ ለህዝባች ልማት አንድነትና ሰላም ባለመታከት የሰራ መሆኑን የቀድሞ የደቡብ ክልል አመራሮች፤ ሠራተኞች ሁሉም በአንድ ቃል ስለ ክብር አቶ አብርሃም ማርሻሎ ይመሰክራሉ እስከ አሁንም በዚህ ተግባሩ ተመስጋኝ እንደሆነ እስካሁን ያወራሉ።
እጁና ልቡን ንጽሁ መሆኑን የሚታወቀው በተለያዩ ቢሮዎች እና በከፍተኛ ሃብት ባላቸው ተቋማት ውስጥ ሲመራ ህዝብን በድሎ፤ ለግሌ ጥቅም ልስራ ብሎ በብልሹ አሠራር ውስጥ የማይሳተፍ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው መሪ መሆኑን አብሮ በሲዳማ ክልል፤ በቀድሞ ደቡብ ክልልን በተለያዩ ተቋማት አብሮት የሰሩ ሁሉ በአግራሞት ይመሰክራሉ።
ክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ ሀገር ምድር የሚያውቃቸው ለሀገር አለኝታና ባለውለታ፥ ለሀገሩ ትልቅ መሰዋዕነት የከፈሉ፥ የሰላም አንባሳደር፥ የልማት ፊትአውራር፥ የለውጥ ሐዋሪያ፥ የተራማጅ አስተሳሰብ ባለቤት ከክልል አልፎ ለሀገር ልማት ትልቅ ዋጋ የከፈሉና እየከፈሉ ያሉ ባለምጡቅ አዕምሮ ባለቤት መሆናቸው ይታወቃል።
የህዝቦች አንድነትና ወንድማማችነት የሚያምን የህዝብ ልጅ ነው። ከሁሉም በላይ አብርሃም ማን እንደሆነ የኢትዮጽያ ህዝብ ብሎም የሲዳማ ህዝብ እና የወላይታ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል።
ክብር አቶ አብርሃም ማርሻሎ ላይ የተነሳውን ረብ የለሽ ወሬ ፍፁም ተቀባይነት የለውም።