Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau

Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau We deliver Government Information Door to Door
(2)

ጉባኤው ኢትዮጵያ ልምድ ያካፈለችበትና የመፍትሔ አካል ሆና የቀረበችበት ነበር - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትሆሳዕና ፣ ሐምሌ 22፣ 2017  ኢትዮጵያ ያስተናገደችው 2ኛው የዓለም የምግብ...
29/07/2025

ጉባኤው ኢትዮጵያ ልምድ ያካፈለችበትና የመፍትሔ አካል ሆና የቀረበችበት ነበር - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 ኢትዮጵያ ያስተናገደችው 2ኛው የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ ልምዷን ያካፈለችበትና ለምግብ ሥርዐት መስተካከል መፍትሔዎችን ያቀረበችበት ነው አለ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፡፡

አገልግሎቱ የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ እና የጣሊያን መንግሥታት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በመቀናጀት ያዘጋጁት የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ በርካታ መሪዎች፣ የግብርናዉ ዘርፍ ተመራማሪ ግለሰቦች እና ተቋማት እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በታደሙበት በአዲስ አበባ ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡ በጉባኤዉ ባለፉት ዓመታት በሥርዐተ ምግብ ለውጥ ረገድ የታዩ ስኬቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ተገምግመዋል፤ ቀጣይ አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ጉባኤዉን ከማስተናገድ ባሻገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሄደችበትን ርቀት በመልካም ተሞክሮነት አካፍላለች፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በየዓመቱ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የምትተክለዉን በቢሊዮኖች የሚቈጠር ችግኝ እና ከሥርዐተ ምግብ መረጋገጥ ባሻገር ያስገኛቸዉ ውጤቶች በልምድነት ቀርቧል፡፡

ጉባኤዉ የ2030 (እ.አ.አ) የዘላቂ ልማት ግብን ለማሳካት በሥርዐተ ምግብ ረገድ ስኬት ሊመዘገብ በሚችልበት አግባብ ላይ በስፋት የመከረ፣ በርካታ አማራጭ ተሞክሮዎችን የዳሰሰ እና ቀጣይ ትኩረቶችን ያመላከተ ኾኖ ተጠናቅቋል፡፡
በሌማት ትሩፋት፣ በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በከተማ ግብርና፣ በአረንጓዴ ዐሻራ … በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበችዉ ኢትዮጵያ ከጉባኤዉ ጎን ለጎን የኹለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነቶችን ለማጠናከር መድረኩን በእጅጉ ተጠቅማበታለች፡፡

በተጀመረዉ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም በግብርናዉ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን አሳይታበታለች፡፡
ባለፈዉ በጀት ዓመት ከ150 በላይ አህጉራዊ እና ዓለማቀፍ ጉባኤዎችን ያስተናገደችዉ ኢትዮጵያ በጀመረችዉ ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ የዓለም የኮንፈረንስ ቱሪዝም የትኩረት ማእከል ኾና ቀጥላለች፡፡

የከተሞችን ገጽታ በእጅጉ መለወጧና የአገልግሎት ዘርፉ እየጎለበተ መምጣት፣ የሕዝቧ እንግዳ ተቀባይነት ባህል የዳበረ መኾን፣ ተስማሚ የአየር ንብረት ያላት መዲና ባለቤት መኾን፣ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ዐቅም እየጎለበተ መምጣት መሰል ትልልቅ ጉባኤዎችን ለማስተናገድ ዕድሎችን እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

ለጉባኤዉ በስኬት መጠናቀቅ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የፀጥታ ተቋማት፣ አገልግሎት ሰጪ የንግድ ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም እንግዶች ለጉብኝት እና ለልምድ ለውውጥ በተንቀሳቀሱባቸዉ ኹሉ በክብር ላስተናገዱ ኢትዮጵያውያን ኹሉ መንግሥት የላቀ መስጋና ያቀርባል፡፡

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃ

በዌብሳይት https://www.cergcab.et/

በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB

በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL

በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678
በቲክቶክ tiktok.com/

በዩቲዩብ https://youtube.com/?si=Ipdg3R3A3hpPQEUV

በኢንስታግራም https://www.instagram.com/cergcab/profilecard/?igsh=MWNseXBlaW05dnM3MA==

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!

29/07/2025

የሌማት ቱርፋት መሶብን በምግብ የመሙላት ውጥን |ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በመትከል ለኢትዮጵያ ማንሰራራት ሀገራዊ ጥሪ እንሰለፍ - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት (ሆሳዕና፣ሐምሌ 22/2017)በአረንጓዴ ዐሻራ ልማት የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው...
29/07/2025

በመትከል ለኢትዮጵያ ማንሰራራት ሀገራዊ ጥሪ እንሰለፍ - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

(ሆሳዕና፣ሐምሌ 22/2017)በአረንጓዴ ዐሻራ ልማት የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጉዞ በሀገራችን የተረጋጋ ሀገርና ትውልድ ለመገንባት አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

በተለይም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አነሳሽነት መረሃ ግብሩ ከተበሰረ ወዲህ በተለያዩ ዘርፎችም መነቃቃት ተፈጥሯል፡፡ የሀገራችን የደን ሽፋን መጠንም በፍጥነት እየተቀየረ መጥቷል፡፡

በአረንጓዴ ዐሻራ መረሃ ግብር የታጀበው ሰባት ዓመታትን የተሻገረ የአትዮጵያ ብልጽግና ጉዞም በሀገራችን ከፍተኛ ውጤቶችን ከማሳየት ባለፈ በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ተቋማት ተጽኖ ፈጣሪነት ደረጃዋን ከፍ አደርጎታል፡፡

በመረሃ ግብሩ የዕድሜ፣ የፆታ፣ የብሔር፣ የሃይማኖትና ሌሎች ልዩነቶች ሳይስተዋሉ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት የሕብረተሰብ ክፍሎች በስፋት በመሳተፍ አይተኬ ተሳትፎ አደርጓል፡፡ በሂደቱም መላው ሕዝባችን መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ማሳደግና ለውጤት ማብቃት ባደረገው የጋራ ርብርብ ዘርፈ-ብዙ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በአረንጓዴ ዐሻራ ያሳካን እምርታ ኢትዮጵያዊያን በጋራ ከቆምንና ከተባበርን ታዓምራዊ ስራዎችን መከወን እንደምንችል ያሳዩ ናቸው፡፡

የኑሮ መሠረታችን አረንጓዴ ተክሎች መሆናቸውን ሕዝባችን ከመረዳት ባለፈ በተግባር አስመስክሯል፡፡ በተለይም ባለፉት ስድስት ዓመታት በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ከ40 ቢሊዬን የሚልቁ ችግኞችን እንደ ሀገር ታቅዶ ተተክሏል፡፡ በዘንድሮው ክረምትም 7.5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡

የተተከሉ ችግኞች የማህበረሰቡ የባለቤትነት ስሜትን እና ለአካባቢው ሃላፊነትን እየጎለበቱ በመምጣቱ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ፣ የአፈር መሸርሸርን ከመቀነስ፣ የደን ሽፋንን ከማሳደግ፣ ለአየር ሚዛን ጥበቃ እና ሕይወት ላለው ሁሉ ለመኖር ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ለአከባቢና ሀገር ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አበርክቶ እያደረገ ይገኛል፡፡

ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በአንድ ቀን ሰባት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል በዚህ ክረምት ለማሳካት የታቀደውን 7.5 ቢሊዮን ግብ እውን እንድናደርግ ዐሻራችንን እንድናኖር ለመላው ኢትዮጵያዊያን ጥሪ ቀርቧል። ስለሆነም መላ ሕዝባችን ከሁሉም ኢትዮጵያ ማዕዘናት ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ/ም በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዬን ችግኝ በመትከል የታቀደውን ግብ እንድናሳካ ሀገራዊ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በሁሉም ሀገራችን ክፍሎች በርካታ ዜጎች እንዲሳተፉ በማድረግ ለሀገራችን ማንሰራራት ዐሻራችንን ማኖር ይጠበቅብናል፡፡ ይህንን ስናደርግ የሀገራችን የተፈጥሮ ገጽታ ከመገንባት ባሻገር የምግብ ሉዓላዊነታችንን እናረጋግጣለን፡፡

ለቀረበው ታሪካዊና ሀገራዊ ጥሪ ተግባራዊነት በመዘጋጀትና ምላሽ በመስጠት የኢትዮጵያን መንሰራራት ጅምር እውን በማድረግና የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅበትን አስተዋጾኦ እንዲያበረክት መንግስት ዳግም ጥሪውን ያቀርባል።

በመትከል እናንሰራራለን!

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ለተጨማሪ መረጃ

በዌብሳይት https://www.cergcab.et/

በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB

በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL

በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678
በቲክቶክ tiktok.com/

በዩቲዩብ https://youtube.com/?si=Ipdg3R3A3hpPQEUV

በኢንስታግራም https://www.instagram.com/cergcab/profilecard/?igsh=MWNseXBlaW05dnM3MA==

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!

በመትከል ማንሰራራት !የፊታችን ሐሙስ ሐምሌ 24/2017 አይቀርም !     #አረንጓዴዐሻራ
29/07/2025

በመትከል ማንሰራራት !

የፊታችን ሐሙስ ሐምሌ 24/2017 አይቀርም !
#አረንጓዴዐሻራ

በ354 የነዳጅ የማደያ ባለቤቶች ላይ ክስ ተመስርቷል፡- የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን(ሆሳዕና ፣ሐምሌ 22/2017)በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት አድ...
29/07/2025

በ354 የነዳጅ የማደያ ባለቤቶች ላይ ክስ ተመስርቷል፡- የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን

(ሆሳዕና ፣ሐምሌ 22/2017)በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት አድርገዋል በተባሉ 354 ተጠርጣሪ የነዳጅ የማደያ ባለቤቶች ላይ ክስ መመስረቱን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲበራ ፉፋ ተናግረዋል፡፡

አቶ ዲበራ ፉፋ ከኢቢሲ ኤፍኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት፤ ባለስልጣኑ በማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት በርካታ ስራዎች እየሰራ ነው፡፡

በዚህም ማደያ ውስጥ ነዳጅ እያለ የለሚ ብለዋል በተባሉ እና ከማደያ ለተሽከርካሪዎች መሸጥ ሲገባቸው በጀሪካንና በበርሜል ሲሸጡ የተገኙ ተጠርጣሪዎች ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ከታሪፍ ማሻሻያ ፍላጎት ጋር በተያያዘ በወራት መጨረሻ ላይ በማደያዎች አካባቢ የሚታዩትን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሕግ ማስከበር ስራዎች በስፋት እየተሰሩ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

በተደረጉ ጠንካራ የቁጥጥር ስራዎችም በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በወራት መጨረሻ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ የተሸከርካሪ ሰልፎችን መቀነስ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

ከነዳጅ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች በኢትዮ ቴሎኮም በኩል የለማውን ጂፒኤስ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አቶ ዲበራ ጠቁመዋል፡፡

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ በነዳጅ ግብይትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት አዋጅ ማፅደቁ ይታወሳል፡፡

አዋጁ የነዳጅ ማከፋፋያ ማደያዎች የግብይትና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 13 63/17 የተደነገጉ አሰራሮችን አክብረው እንዲሰሩ ይደነግጋል ማለታቸዉን ኢቢሲ ዘግቧል።

በመትከል ማንሰራራት ...
29/07/2025

በመትከል ማንሰራራት ...

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ የ2017 በጀት አመት  ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማና የ2018 ዕቅድ ውይይት መድረክ በሆሳዕና  ከተማ እየተካሄደ ነው።(ሆሳዕና ሐምሌ 22/20...
29/07/2025

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ የ2017 በጀት አመት ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማና የ2018 ዕቅድ ውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።

(ሆሳዕና ሐምሌ 22/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ የ2017 በጀት አመት በክንፉ መሪነት የተሰሩ ስራዎች ማጠቃለያ ሪፖርት ግምገማና የ2018 ዕቅድ ተግባቦት መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።

በበጀት አመቱ በሁሉም ዘርፎች የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት የተሰሩ ስራዎች ስኬታማ ነበሩ ብለዋል የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ሽመልስ።

ወይዘሮ ኤልሳቤጥ እንዳሉት በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ በአደረጃጀት ተደራጅተዉ በመንቀሳቀስ ግንባር ቀደም ሆነው ሌሎች ሴቶችን በማሰለፍ የንቅናቄ ስራዎችና መደበኛ ተግባራትን ማከናወን ስለመቻሉ ተናግረዋል፡፡

ሴቶችን ወደ አመራርት እንዲመጡ በፓርቲው እየተሰራ እንደሆነ እና እነዲሁም በኢኮኖሚ ዘርፋ በሌማት ቱርፋት፣ በንብ ዕርባታ በዶሮ እርባታ በጓሮ አትክልት ውጤታማ ስራዎች መስራት ተችሏል ብለዋል።

በማህበራዊ ዘርፍም ሴቶች በጤና ተቋማት እንዲወልድ እንዲሁም የናቶች ማቆያ ምቹና ተስማሚ እንዲሆኑ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ስራዎች መሠራታቸውን ገልፀዋል።

በውይይቱ የተገኙት የስብሰባ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሴቶችን ብልጽግና ለማረጋገጥ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ወደ ውሳኔ ሰጭነት ለማምጣት ጠንካራ ስራ መሰራት እንዳለበት እንዲሁ የተጀመሩትን የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን ማስቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በመትከል ማንሰራራትየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሐምሌ 24 /2017 የተሟላ ዝግጅቱን አጠናቋል። በአንድ ጀንበር እንደ ሀገር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ክልላችን ...
29/07/2025

በመትከል ማንሰራራት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሐምሌ 24 /2017 የተሟላ ዝግጅቱን አጠናቋል።

በአንድ ጀንበር እንደ ሀገር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ክልላችን የተሟላ ዝግጅት አድርጓል።

ይህን ተከትሎም የፊታችን ሐሙስ ሐምሌ 24/2017 በክልላችን 6ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ተዘጋጅተናል።

የህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ተመላከተ (ሆሳዕና ፣ሀምሌ 22/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና...
29/07/2025

የህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ተመላከተ

(ሆሳዕና ፣ሀምሌ 22/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ከሆልት አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጀት ጋር በመተባበር በተሻሻለው በአዲሱ አማራጭ የህፃናት ድጋፍና ክብካቤ መመሪያ ላይ የተዘጋጀ በሆሳዕና ከተማ እየተሰጠ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አምሪያ ስራጅ እንዳሉት ህፃናት ላይ የሚሰራው ስራ ሀገር ላይ መስራት ነው።

የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በትኩረት መስራት ይገባቸዋል ያሉት ኃላፊዋ በህፃናት ላይ የሚደረገው ድጋፍና ክብካቤ ይበልጥ መጠናከር እንዳለበትም አመላክተዋል።

በአዲስ መልኩ ተሻሽሎ የወጣው አማራጭ የህፃናት ድጋፍና ክብካቤ መመሪያ በህፃናት ላይ የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችን ለመከላከልና ተጋላጭነታቸውን በመቀነስ ህፃናት ወደ ጎዳና እንዳይወጡ ለማድረግ በማለም የተዘጋጀ መመሪያ ስለመሆኑ አስገንዝበዋል።

መመሪያው የህፃናት መብትና ደህንነት እንዲረጋገጥና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲጎለብት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የገለፁት ወ/ሮ አምሪያ በመመሪያው የፈፃሚና የአስፈፃሚ አካላት ግንዛቤ ከፍ እንዲል በተለያዩ ማዕከላት ስልጠናው በተደራጀ መልኩ መሰጠቱን ገልፀዋል።

በህፃናት ላይ የሚሰራው ስራ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች በመተባበር ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

ስልጠናው በተደራጀ አግባብ እንዲሰጥ ሆልት አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ከፍተኛ አሰተዋጽኦ ማበርከቱን ከክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

በ2017 በጀት ዓመት ከ 9መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል - የገቢዎች ሚኒስቴር(ሆሳዕና፣ሀምሌ 22/2017)፣ በ2017 በጀት ዓመት ከ 9መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን...
29/07/2025

በ2017 በጀት ዓመት ከ 9መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል - የገቢዎች ሚኒስቴር

(ሆሳዕና፣ሀምሌ 22/2017)፣ በ2017 በጀት ዓመት ከ 9መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው ገቢው ከባለፈዉ በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ387 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለዉ።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያቀደውን ገቢ በመሰብሰብ በላቀ አፈፃፀም ማጠናቀቁን የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ እንዳሉት፤ ለእቅዱ አፈፃፀፀም ባለፈዉ በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተደረገዉ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና በመንግስት የተቋቋመዉ ብሔራዊ የታክስ ሪፎርም ጉልህ ሚና ነበራቸዉ።

አክለውም በገቢ አሰባሰቡ ወቅት ገቢን መደበቅ ፣ ግብይትን ያለደረሰኝ ወይም በሕገ ወጥ ደረሰኝ ማከናወን፣ ኮንትሮባንድ እንዲሁም የታክስ ማጭበርበር ያልተቀረፉ የታክስ አስተዳደሩ ተግዳሮቶች ናቸዉ ብለዋል።

ጥንካሬዎችን አስቀጥለን እንዲሁም ክፍተቶችን አርመን፤ በ2018 በጀት ዓመት የታቀደዉን 1.28 ትሪሊዮን ገቢ እዉን ለማድረግ ሁላችንም መረባረብ አለብንም ነው ያሉት።

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የተጠናቀቀውን እና አዲሱን በጀት ዓመት አስመልክቶ የጋራ የውይይት መድረክ ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ጀምረዋል።(EBC)

29/07/2025

ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ በጅማ

ሁለት ቀን ቀረው !የፊታችን ሀሙስ ሐምሌ 24/2017 በሀገር አቀፍ ደረጃ 700 ሚሊዮን ችግኞች በክልላችን ደግሞ 6 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ተዘጋጅተናል።   #አረንጓዴዐሻራ   ...
29/07/2025

ሁለት ቀን ቀረው !

የፊታችን ሀሙስ ሐምሌ 24/2017 በሀገር አቀፍ ደረጃ 700 ሚሊዮን ችግኞች በክልላችን ደግሞ 6 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ተዘጋጅተናል።
#አረንጓዴዐሻራ

Address

Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau:

Share