
10/12/2024
የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን መንገድ …..
የሀገራችን ቱሪዝም ካለበት ማነቆ አንዱ የአሰራር አለመዘመንና ዘለግ ያለ ዘልመዳዊ የቢሮክራሲ መንገዶች ይበልጥ ዘርፉን እንደ ካሮት የቁልቁል ጉዞ ላይ እንዲገኝ አድርጎታል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በዘርፉ ሌሎች ሀገራት ያደጉበትን መንገድ የመከተልና የመተግበር እሳቤዎች በጥቂቱም ቢሆን እየታየ ነው፡፡ በዚህም በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ መንግስታዊ መዋቅሮች ውስጥ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን አንዱ ነው፡፡
ኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን በመንግስት መዋቅር የሚገኝ ነገርግን ለአሰራር ያመች ዘንድ Autonomous ሆኖ የክልሉን የቱሪዝም ሀብት የመለየት፣ መዳረሻዎችን እንዲለሙ የማድረግ እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጪ ለሚገኙ ጎብኚዎች የማስተዋወቅና ገቢ እንዲገኝ የመሸጥ ስራዎችን ያስተባብራል፡፡ ለዚህም ይረዳው ዘንድ Visit Oromia (ኦሮሚያን ይጎብኙ) በተሰኘው ንቅናቄ የገበያ እና ማስተዋወቅ ስራዎችን በዋናነት ይሰራል፡፡
በአፍሪካ ውስጥ የዚህ ሞዴል ዋነኛ ተጠቃሽና ተጠቃሚ ሀገር ጎረቤት ሩዋንዳ ናት፡፡ Visit Rwanda
አሁን ላይ ያለውን የሩዋንዳ ከፍተኛ የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም እንቅስቃሴ በተለይ በቢዝነስ ቱሪዝም ያላቸውን ተመራጭነት ላስተዋለ ያለጥርጥር በዚህ ሞዴል ለአመታት ሳይታክቱ መስራት መልካም ውጤትን ለማየት አይነተኛ መንገድ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ባለፉት 10 ዓመታት የፖል ካጋሜዋ ሀገር በቪሲት ሩዋንዳ ንቅናቄ እጅግ እመርታዊ ለውጥ ከማምጣት ባሻገር በአለም ታሪክ ከምትታወቅበት የእርስበእርስ ጦርነት በላይ በቱሪዝሙ እየታወቀችበት ትገኛለች፡፡ የዚህ ንቅናቄ አካል በሆነው ከታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ የአለማችን ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በጋራ አብሮ ከመስራት እስከ አጋርነት ብሎም ዋነኛ የገበያ ምንጭ እስከመሆን ደርሳለች፡፡
አርሰናል፣ፒኤስጂ፣ባየርሙኒክ ሩዋንዳ በስፖርት ቱሪዝም ተመራጭ እንድትሆን ብቻ ሳይሆን ምርትና አገልግሎቷን በተለይም ቡና በእነዚህ ግዙፍ ስቴድየሞች በጨዋታው እንዲቀርብ አስችሏታል፡፡ የየቡድኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ሩዋንዳን መጎብኘት የቤት ስራቸው ካደረጉ ሰነበቱ፡፡ በዚህም በአፍሪካ ውስጥ በስፖርት በተለይ ቅርጫት ኳስ፣እግርኳስ እንዲሁም አሁን አሁን አለም አቀፍ የመኪና ውድድር በሩዋንዳ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ባለፉት 10 ዓመታት ከ800 በላይ አለም አቀፍ ኹነቶችን በሀገረ ሩዋንዳ እንዲካሄድ ከማስቻሉም በላይ በየአመቱ የትልልቅ ኹነቶች መዳረሻ በመሆን ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አስተዋፅዖ አድርጓል፡፡
ለዚህም የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ፖል ካጋሜ የቱሪዝሙ እንቅስቃሴ በመንግስታዊ መዋቅር ሆኖ ነገር ግን ቢሮክራሲ ያልበዛበት በቀጥታ ራሳቸው ፕሬዝደንቱ የሚመሩትና አቅጣጫ የሚሰጡበት በፋይናንስ ምክንያት ስራዎች የማይስተጓጎልበት የሀገሪቱ ትልቁ አምድ ዘርፍ እንዲሆን በማድረጋቸው ነው፡፡ Rwanda Development Board
እንመለስና …
የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽንም(OTC) ልክ እንደ ሩዋንዳ በኦሮሚያ ፕሬዝደንት ፅ/ቤት የሚመራ በተለመደው የመንግስት መዋቅርና አሰራር ያልተተበተበ በዚህም የክልሉን የቱሪዝም እምቅ ሀብት በመለየትና በማልማት፣ በተለያዩ ሀገራት በማስተዋወቅ፣የገበያ እድሎችን በመፍጠርና በንግድና መሰል አውደርዕዮች ላይ አግሬሲቭሊ በመሳተፍ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ለአለም እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር አጋርነት በመፍጠር ዘርፉ ይበልጥ ትኩረት እንዲያገኝ የሚደረገውን ጥረት በግሌ የማደንቀው ተግባር ነው፡፡
ከተለመደው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ባሻገር አማራጭ የቱሪዝም አይነቶችን እንደ ቡና፣ወይን እንዲሁም ሀላል ቱሪዝም ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑ ይበል ያሰኛል፡፡
ከዚህ በኃላ ምን እንዲሰራ ይጠበቅበታል ?
✍️መዳረሻን በመለየት ማልማት እንዲሁም የለማውን የማስተዋወቅ ተግባር ላይ በተሰራው ልክ የአገልግሎት ጥራት(Service Quality) ላይ በትይዩ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ጎብኚዎች(ገበያው) ሲመጣ በተዋወቀው ልክ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል አልያ የዘላቂነት(sustainability) ጥያቄ ብቻ ሳይሆን መልካም ያልሆነ ልምድ ይዘው ከሄዱ የገበያ ድግግሞሽ(Market Reputation) እንዳይኖር አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል፡፡
🔎ቱሪዝምን ከ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ (ዲጂታል ቱሪዝም) ከማስተሳሰር ፣ የሰው ሀብት ልማት ላይ ከመስራት አንጻር እንደ ጅምር ለሌሎችም ተመስሌታዊ መንገድ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡
#እንደ መውጫ
✔️የሌሎች ክልል ተመሳሳይ ተቋማትም ይህን መንገድ ቢከተሉ ከራሳቸው ክልል ባለፈ እንደ ሀገር በብዙ የሚጠቅም ይሆናል፡፡ ቪዚት ኦሮሚያ በክልሉ የሚገኙ መዳረሻ ቦታዎችን የሚያስተዋውቁበት መንገድ፣ የሚጠቀሟቸው ተስማሚ ገለጻዎች ከማራኪ ምስሎች ጋር እጅግ የሚደነቅ ነው፡፡
🔜አዳማ እና ቢሾፍቱ እንደ ቀዳሚ ተምሳሌታዊ ፕሮጀክት(Pilot Project) ተወስደው ትልቅ የቱሪዝም ስራዎች በተለይ በቢዝነስ ቱሪዝም ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉበትን አቅም መጠቀም ግን ግድ ይላል፡፡
#መደምደሚያ
በኢትዮጵያ የቱሪዝም እንቅስቃሴ በ ልክ መዳረሻዎችን በተገቢው መንገድ ያስተዋወቀ(Destination Marketing Org.) የመንግስትም ሆነ የግል ዘርፍ ተቋም የለም፡፡ በዚሁ መጠን የቱሪስት/ጎብኚ ቁጥርም በተሰራው ልክ መምጣትና ገቢ ማስገኘትም ያለበት ወቅት መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡
👍👍Thumbs Up Team Oromia Tourism Commission
Lelise Dhugaa 👏👏
Nega Wedajo Werete👍👍
Visit Oromia