Abush Mesele-አቡጁ

Abush Mesele-አቡጁ " አቤቱ፥ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅህ ምራኝ፤ መንገዴን በፊትህ አቅ�
Subscribe my YouTube channel
👉https://www.youtube.com/

03/07/2026

Worship

02/07/2026

Fy sound

last word from KG student
01/07/2026

last word from KG student

20/06/2026

🏆💚-እንኳን ደስ አላችሁ/እንኳን ደስ አለን!-🏆💚
ከጅምሩ መሪ፤ በፍፃሜው ሻምፒዮን!
ክለባችን ሲዳማ ቡና ከውድድሩ ጅማሬ ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በብርቱ ትጋት፣ በአንድነት፣ በጥራት እና በማይናወጥ ቁርጠኝነት እየመራ ሻምፒዮን በመሆኑ ከልብ እንኳን ደስ አላችሁ!

ይህ ድል ተጫዋቾቻችን የደከሙበት፣ የአሰልጣኞቻችን የጥረት ውጤት፣ የአመራሮቻችን የቁርጠኝነት ማሳያ እንዲሁም የደጋፊዎቻችን ያላቋረጠ ድጋፍ ፍሬ ነው። ሲዳማ ቡና በውድድሩ ሁሉ የሚያስደንቅ ብቃት በማሳየት ከጅምሩ ጀምሮ የመሪነት ቦታውን በክብር ጠብቆ በመጨረሻም የሻምፒዮንነትን ክብር ተቀዳጅቷል።

ይህ ድል ለክለባችን ብቻ ሳይሆን ለመላው የሲዳማ ሕዝብ የኩራትና የደስታ ቀን ነው። በየትኛውም ቦታ ሆናችሁ ክለባችንን በጸሎት፣ በማበረታታት እና በድጋፍ ከጎኑ ለነበራችሁ ደጋፊዎች ሁሉ ክብርና ምስጋና ይገባችኋል።

የሲዳማ ቡና ድል የአንድነት፣ የትጋት እና የእምነት ድል ነው። ይህ የዛሬ ስኬት ለነገው ታላቅ ስኬት መሠረት ይሁን።

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ለዚህ ታሪካዊ የሻምፒዮንነት ድል አደረሳችሁ! ሲዳማ ቡና ሁሌም የኩራታችን ምንጭ ።

🏆💚 ሲዳማ ቡና ሻምፒዮን! 💚🏆

13/06/2026

ወጥቶ ከመቅረት እግዚአብሔር ይጠብቀንየ5 ሰዎች ህይወት አለፈ😭በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቱላ ክፍለ ከተማ፣ "ገመጦ ጋሌ" ተብሎ በሚጠራው ልዩ ስፍራ (ወራንቻ ፍተሻ አካባቢ) በደረሰ የተሽከርካ...
03/04/2026

ወጥቶ ከመቅረት እግዚአብሔር ይጠብቀን
የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ😭

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቱላ ክፍለ ከተማ፣ "ገመጦ ጋሌ" ተብሎ በሚጠራው ልዩ ስፍራ (ወራንቻ ፍተሻ አካባቢ) በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ5 ሰው ሕይወት የ4 ወንዶች አና 1 ሴት በአጠቃላይ የአምስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል።

"ፊቼ ጫምባላላ የፍቅር፣የአንድነት፣የአብሮነትና የመተሳሰብ ባህላዊ እሴትነቱን ጠብቆ የዘለቀ የሲዳማ ብቻ ሳይሆን የመላው የዓለም ማህበረሰብ በመሆን በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኔስኮ የተመዘገበ ው...
14/03/2026

"ፊቼ ጫምባላላ የፍቅር፣የአንድነት፣የአብሮነትና የመተሳሰብ ባህላዊ እሴትነቱን ጠብቆ የዘለቀ የሲዳማ ብቻ ሳይሆን የመላው የዓለም ማህበረሰብ በመሆን በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኔስኮ የተመዘገበ ውብ ባህላዊ ሀብት ነው:-"አቶ አብርሃም ማርሻሎ

እንኳን ለሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ለሆነው የፍቼ ጫምባላላ በዓል አደረሰን/አደረሳችሁ!

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የፍቼ ጫምባላላ በዓል የሲዳማ አባቶች(አያንቶዎች) የስነ-ፈለክ ዕውቀት እና ጥበብ ላይ ተመስርተው ዘመንን በልዩ የወራት፣የቀናትና የሳምንታት ቀመር አስልተው ከትውልድ ወደ ትውልድ በክብር ያስተላለፉት የሀገራችን አኩሪ መገለጫ እና የዓለም ህዝቦች ውብ ቅርስ ሆነ በማይዳሰስ ቅርስነት በUNESCO የተመዘገበ ታላቅ በዓል ነው።

የሲዳማ ውብ ባህላዊ መገለጫ የሆነው የፊቼ ጫምባላላ በዓል ሰላምና መከባበር፣አብሮትና መቻቻል፣ይቅርባይነትና እርቅ በአንድ ላይ የተጋመዱበት የበጎነት እሴቶችን በውስጡ የያዘ ደማቅ ባህል ነው።

ቀደምት ጠበብት የሲዳማ አባቶች ፍቼ ጫምባላላ ባህላዊ ይዜቱን ሳይለቅ ከዓመት ዓመት እየተከበረ እንዲዘልቅ በማድረግ ረገድ ባህላዊ ይዜቱን ሳይለቅ ስርዓት አበጅተው በማቆየት በድንቅ እንክብካቤ፣ ጥበብና ክብር ለዛሬው ትውልድ ያሸጋገሩት ድንቅ ባህላችንን ነው። ይህንን ድንቅ ባህል ቀጣዩ ትውልድ በአንድነትና በፍቅር በመደመር እሳቤ ታግዞ እሴቶቹን እያጎለበተ ማስቀጠል ይገባዋልም ብለዋል።

ፊቼ በዓል በመደመር መተጋገዝን፣መተባበርን፣አንዱ ለአንዱ አቅም መሆንን፣ተባብሮና ተጋግዞ መሻገርን በፍቅርና በአብሮነት የያዘ ተፈጥሯአዊ ባህላዊ ቅርስ ሲሆን አባቶቻችን ከጥንት ጀምሮ በተፈጥሮ በተጎናፀፉት ዕውቀት በሰዎች መካከል በጎና ጠቃሚ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና የወንድማማችነት/እህትማማችነት እሴት መስተጋብሮች ተገንብተው እንዲዘልቁ ያስቻሉት ውብ ባህል ነው።

የፊቼ ጫምበላላን በዓል ስናከብር የበዓሉ እሴት በሆነው በመረዳዳት እና በመተጋገዝ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችንን የወትሮ አብሮነታችንን በማሳየት መሆን አለበት።

የፍቼ ጫምባላላ በዓል በፍቅር እና በይቅርባይነት ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲስ ዘመን መሸገሪያ በመሆኑ በዓሉ በውስጡ የያዛቸው እሴቶች መሰረት አድርገን በአዲስ ሃሳብ የሃገራችንን ብልፅግናን እውን የምናደርግበት እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጻለው።

በመጨረሻም በዓሉ የእርቅ፣የሰላም፣የደስታ፣የአብሮነት እና ብሩህ ተስፋ የሚሰነቅበት እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ብለዋል::

አቶ አብርሃም ማርሻሎ
በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

እንኳን ለፊቼ ጫምባላላ አደረሰን/አደረሳችሁ!
Ayidde Cambalaalla!

ተያዘ በወጣቷ ላይ የመግደል ሙከራ ወንጀል ፈፅሞ የተሰወረን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አውሎ ለአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ማስረከቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡በአማራ...
28/02/2026

ተያዘ

በወጣቷ ላይ የመግደል ሙከራ ወንጀል ፈፅሞ የተሰወረን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አውሎ ለአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ማስረከቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህር ዳር ከተማ ነዋሪ የሆነችና የግል ተበዳይ ወ/ሪት ትዕግስት አየነው የተባለች ወጣት ላይ የመግደል ሙከራ በመፈፀም በፖሊስ ክትትል ሲደረግበት የነበረው የቀድሞው ፍቅረኛዋ ኢዮብ ወይም ናትናኤል ጫኔ በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አባላት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

ተከሳሹ ከዚህ ቀድም በፍቅረኛው ላይ ወንጀሉን ፈፅሞ በሌለበት የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሌለበት በስምንት ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነበት ሲሆን ተፈላጊው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ተሰውሮ መቆየቱን ፖሊስ አረጋግጧል፡፡

ፖሊስ በተፈላጊው ላይ የወጣበትን የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ መሰረት በማድረግ ባደረገው ብርቱ ክትትል ተጠርጣሪውን የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 12፡00 ሠዓት አካባቢ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው ገርጂ ዱባይ ሞል አካባቢ በቁጥጥር ስር በማዋል ለአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስረክቧል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎች የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለጊዜውም ለመሰወር ሙከራ ቢያደርጉም ከፖሊስና ከህግ ማምለጥ እንደማይችሉ አውቀው ለህግ ተገዢ መሆን ይኖርባቸዋል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል፡፡

 shalomታሰረ ተብሎ እንደዝህ ደስ ያለህ ሌላ ነገር ቢሆን ምን ልትል ነበር....?
30/01/2026

shalom
ታሰረ ተብሎ እንደዝህ ደስ ያለህ ሌላ ነገር ቢሆን ምን ልትል ነበር....?

Address

Awassa
SIDAAMA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abush Mesele-አቡጁ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share