Aykel Express

Aykel Express ርስታችንን ለማስመለስ መስዋዕት ለመሆን ዝግጁ ነን!

ለነባሩ ጭልጋ ወረዳ አስተዳደር ም/ቤት   በወረዳዉ ማለትም በ16 ቀበሌ በሶስት ጤና ጣቢያ የማህበረሰቡን ሁለተናዊ የጤና ሁኔታ  ለማሻሻል አልሞ መስራት ይኖርበታል። ከ3 ጤና ጣቢያዎች 2ቱ ...
02/01/2023

ለነባሩ ጭልጋ ወረዳ አስተዳደር ም/ቤት
በወረዳዉ ማለትም በ16 ቀበሌ በሶስት ጤና ጣቢያ የማህበረሰቡን ሁለተናዊ የጤና ሁኔታ ለማሻሻል አልሞ መስራት ይኖርበታል። ከ3 ጤና ጣቢያዎች 2ቱ በደጋማዉ እና ወይናደጋዉ አካባቢ እንዲሁም 1 ቆላማዉ ቀጠና ይገኛል ።

በጤና ኤክስቴሽን የእናቶችን ፣የህፃናትን ጤና ለማስተካከል መስራት ሲገባዉ ፖለቲካዊ ሽርሙጥና በሆነ መንገድ ተጠምዶ ይገኛል።

ለአብነትም በአደዛ ጤና ጣቢያ ያለዉ የመሰረተ ልማት ግንባታ መጓተት ፣ ስርአት የለሽ የጤና ጣቢያ ሃላፊ እና ሙያተኛ ፣ 2 ካርቶን ኦሚፕራዞል መድሃኒት ማህበረሰቡ ሳይጠቀምበት ኤክስ አደርጎ የተገኘበት ተቋም እንዲሁም Under five የሚሰጠዉን የኩፍኝ(measle) ክትባት above 7 ለሆኑ ህፃናት ላዛ ትምህርት ቤት ላይ ተገኝቶ ክትባት የሰጠ ተቋም እና ሃላፊ ያለበት ጤና ነዉ ። ክትባቱን የሰጠዉ ሙያተኛም አሁን የጤና ጣቢያ ሃላፊ ሁን ተብሎ ተሸልሟል።

ይህ ብቻ አይደለም የዚህ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ነዉር ጫንድባ ጤና ጣቢያን ባዶ ያደረገ ልጅ መጥቶ በምክትልነት እንዲመራዉ ይሁንታ ሰጥቶታል። በዚህም የ 350 ሽ ብር በላይ የጤና መድን ኪሳራ ወረዳዉን አከናንቦታል ።

ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ማህበረሰቡ በየጊዜዉ የሚያወጣዉን የህክምና ወጭ በአመት አንዴ በመክፈል ራሱን ከወጭ የሚከላከልበት ስርአት ነዉ። በመሆኑም በዚህ ስርአት የሚታቀፍ ማንኛዉም ሰዉ አምኖበት ጠቀሜታዉን አዉቆ በራሱ ፈቃድ በጤና መድን (health insurance ) ይታቀፋል በእየ አመቱም ክፍያ ይከፍላል። ሁኖም ይህ ደካማ እና ልፍስፍስ ሃላፊዎች ያሉት ተቋም የዉባ ወረርሽኝን ለመከላከል የክልሉ ጤና ቢሮዉ ከለጋሽ አካላት ባገኘዉ ገንዘብ ያሰራጨዉን የዉባ መከላከያ አጎበር ለማህበረሰቡ Timely ከማድረስ ይልቅ የጤና መድን ካልከፈላቹህ አይሰጣቹህም የሚል ህግ የሚያወጣ ደካማ ስብስብ ነዉ።

ጤና መድን መግባት መብት እንጂ ግዴታ አይደለም ማነሽ ሲስተር ለምለም ። ይልቅ በሹፌር እና your former boss በነበረ አሁን ሙያተኛሽ በሆነዉ ሰዉ ሃሳብ እየተመራሽ ሙያተኛን ከማቧደን ፣ስራን ከማበላሸት ከቻልሽ ተቋሙን ምሪዉ ካልቻልሽ ልቀቂ ሃላስ!

የተከበሩ አቶ ዘለቀ እንቢ አለ ፣ወይዘሮ ካሳየ ስመኝ እና ፓርቲያቹህ ይህን ደካማ የአመራር ስምሪት ፣ሙያተኛን የሚያሸማቅ፣ ሌባን የሚያበረታታ ስብስብ ሃይማትሉት ከሆነ በእጃችን ያሉትን ከጫንድባ ጤና ጣቢያ ፣እስከ ዳንጉራ ብሉም በሸድ እስካለዉ አደዛ ጤና ጣቢያ ሙሉ የመድሃኒት፣ የጀኔሬተር፣ የፕላፕሌት እንዲሁም ሌሎች ዝርፊያዎች ለዞን ጤና መምሪያ የምናደርስ መሆኑን እንገልጣለን!
Change is Natural

14/10/2022

ሰላም ለሁሉም
12787 ይህ ቁጥር አይደለም ደቡብ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር ወይም ሶማሌ ክልል አቋርጦ የወጣ ተማሪ አይፈለም። የSuper stupidity አክቲቪስቶች መነሃሪያ የሆነዉ አማራ ክልል ፈተና አንፈተንም ብለዉ የወጡ ተማሪዎች ናቸዉ።

የእነዚህ ተማሪዎችን ማቋረጥ እንደትልቅ ድል እየቆጠሩ የሚዘግቡ እዉን ፊደል ቆጥረዋልን!

ትምህርት ሚኒስቴር ከዜሮ ተነስቶ የሰራዉ ስራ የሚያስመሰግነዉ ቢሆንም ይህን ያህል ሽ ተማሪ ያቆረጠበትን ምክንያት ሳሱር ሳያደርግ ያስተላለፈዉ ዉሳኔ በድንጋጤ የወጡ የድሃ ልጆችን እንዳይጎዳ መለስ ብሉ ቢመለከት!

ለተፈጥሮ ቀመር ሳይስ ተፈታኞች መልካም ፈተና!

ተረጋግታቹህ ተፈተኑ!

28/07/2022

አቶ ከፋለ ማሞ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ሊሸሽ ሲል ቴዎድሮስ ኤርፖርት ላይ በቁጥጥር ስር ዉሏል።

ይቀጥላል

20/06/2022

የአብይ መንግስ ባለፉት 4 የንግስና አመቱ የንፁሃንን ሞት ለምዶ ያስለመደን ድብርት መቸ ነዉ የሚለቀን?

መንግስት መንግት ለመባል ትንሹ ሃላፊነቱ የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ነዉ

ወለጋ ከ460 በላይ ለሞቱት ምስኪን አማሮች ማን ነዉ ተጠያቂዉ? አማራን የወከሉት ፓለቲከኞች ዛሬም በመደመር መንገድ ስልጠና ላይ ናቸዉ ወይስ ይህን ነዉረኝነት ለመታገል ይነሱ ይሆን?

ለማንም ለዚህ ጭፍጨፋ ኦህደድ መራሽ ስለሆነ ለዚህ ማካካሻ ሌላ ጥፈት የአማራ ክልል በተባለዉ ቦታ ሊሞክሩ ስለሚችል ትኩረት አድርጉ ሰለብሪቲዉን ቀነስ አድርጋቹህ

ለሞቱት ወገነቸ ነፍስ ይማር

Beyond financing ዐማራ ባንክ
18/06/2022

Beyond financing
ዐማራ ባንክ

በዚህ ወቅት ስለልማት ወይስ ስለ ብድር ማስመለስ መወራት ያለበት❗️ በማህበረ ኢኮኖሚዉ የተጎሳቆለ አርሶ አደር ካለበት የክልሉ አካባቢዎች አንዱ ጭልጋ ወረዳ ነዉ። ይህ አርሶ አደር በፓለቲከኞ...
07/06/2022

በዚህ ወቅት ስለልማት ወይስ ስለ ብድር ማስመለስ መወራት ያለበት❗️
በማህበረ ኢኮኖሚዉ የተጎሳቆለ አርሶ አደር ካለበት የክልሉ አካባቢዎች አንዱ ጭልጋ ወረዳ ነዉ።

ይህ አርሶ አደር በፓለቲከኞች (ethnic entrepreneur ) ምክንያት በርካታ መከራዎችን አሳልፏል፣ ከረጅነት ወደ ተረጅነት ተሸጋግሮ የሰዉ እጅ እየተመለከተ ይገኛል። አንፃራዊ ሰላም(በፓለቲከኞቹ አነጋገር) ስፍኗል እየተባለ ባለበት ወቅት ገበሬ ወደ ልማት ለመግባት ትልቅ የራስ ምታት የሆነዉ የመዳበሪያ ዋጋ አለመቀመስ ነዉ። የጭልጋ አንዱ ክፋይ የሆነዉ ( ጭልጋ ቁጥር2) ወረዳ በፀጥታ አመራሮቹ በኩል (በአቶ ሃሰን ሱሩር እና በዋ/ኢ ወንድም ) አማካኝነት በ2011አም ክፉኛ ቃጠሎ እና የኢኮኖሚ ድቀት ድጋሜ በ2014 መባቻ አካካቢ ቃጠሎ ያስተናገዱ ማህበረሰብ እስከ ሮብ ለመልሶ ማቋቋም የወሰዳቹህትን ብድር ካልመለሳቹህ እርምጃ እንወስዳለን በማለት የቀበሌ ተወካዮችን አስፈርሞ ልኳል ።

ለመሆኑ የወረዳዉ አስተዳደር የሚመራዉን ህዝብ ያለበትን የድህነት ሁኔታ ይረዳል ወይ? አብቁተ ማለቴ የአማራ ገበሬ አራቁተ እዉን ለልማት ነዉ የሚሰራዉ? 2011 አም በስማቸዉ የተሰበሰበዉ ያ ሁሉ ሚሊዮን ብር የት ገባ?

ለመሆኑ ብድር የመመለስ አቅም አለዉ ይህ ማህበረሰብ በእርዳታ እያደረ ያለ ምስኪን አቶ ዘለቀ ብታድቡ ምን አለ።

ህግ ማስከበር ብላቹህ የሰራቹህትን አሳፋሪ ትግባር እና ወርደት ዝም ያልነዉ ከእናንተ በላይ እኛ ስለ ተሳቀቅን ነዉ።

25/04/2022

መልካም የትንሳኤ በዓል ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ❗️

15/04/2022

ዘበር መግለጫ❗️
የቅማንት ኮሚቴ 6ኛ ጊዜ ምህረት ተደረገለት
ይህን በተመለከተ ሰፊ ሃተታ ይኖረናል
Stay tuned

09/04/2022

ጭልጋን At large ጎንደርን በተመለከተ የማዕከላዊ ጎንደር አስተዳደር ከሁለቱ ጭልጋ፣ ከሁለቱ የደንቢያ ወረዳዎች ፣ ላይ አርማጭሆ የተካተቱበት ደጋፊ ምክር ቤት አቋቁሟል።

ትላትም የዚሁ አካል የሆነ የሰላም ኮንፈረስ በአቶ ዳኛዉ የዞን ሰላም እና ደህንነት መምሪያ ሃላፊ፣ የተመራ ቡድን በአይከል ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች እና የወረዳ መስተዳድር አካላት ጋር ዉይይት አድርገዋል።

በዚህ ዉይይት ስለ አካባቢዉ ዘላቂ ሰላም ተሰብኳል፣ አቅጣጫም ተቀምጧል ። ነገር ግን let it clear to be is በርካታ የሆኑ peace conference እንዲሁም Arbitration ተደርገዋል ምን ዉጤት አመጡ? ካልመጣስ ምንድነዉ ክፍተቱ ? ዘላቂዉ ነገርስ የቱ ነዉ ብሎ መጠየቅ ብልሕነት ነዉ። በተመሳሳይ መንገድ እየተጓዙ የተለየ ነገር መጠበቅ just similar to lived in illusion that some one dreamed but not reached

ጎንደር የልማት ቀጠና እንደትሆን ከተፈለገ ጊዜዉን የሚመጥን የአመራር ስምሪት ፣ if peaceful resolution is possible for the conflict here in Chilga that extend to metema and Gondar must include the right stake holder on a firmed ground for both parties beyond the cadres.

Else we couldn.t restore what we dreamed and believed to Gondar

ወልቃይት❗️ወልቃይት የአማራን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣ ፋንታ የምትወስን ጅኦ እስትራቴጂካዊ ምድር ነች። በቀላሉ የአፍሪካ ስስ ተረከዝ ፣የወያኔ እስትፋስ የነበረች ምድር ናት ወልቃ...
02/04/2022

ወልቃይት❗️
ወልቃይት የአማራን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣ ፋንታ የምትወስን ጅኦ እስትራቴጂካዊ ምድር ነች።

በቀላሉ የአፍሪካ ስስ ተረከዝ ፣የወያኔ እስትፋስ የነበረች ምድር ናት ወልቃይት❗️

በመሆኑም ከሁሉም አካባቢ የተወጣጡ የአማራ ወጣቶች አካባቢዉን መጎብኘታቸዉ በሙዚቃ ቅኝት የሚያዉቋትን ወልቃይት ፣ከከፋኝ አማራ እስከ አሁን በርካታ ጀግኖች አጥታቸዉን የከሰከሱላት የአማራ ምድር መሆኗን ይጎበኛሉ፣ይቆጫሉ ፣ ነገን ጥሩ ለማድረግ ይተጋሉ❗️

የአማራ ብልፅግና ይህን ጉዞ ማዘጋጀቱ እያደነኩ ነገር ግን ከዚህ ከፍ ያለዉን ፖለቲካዊ መፍትሔዉን በማስቀመጥ ዞኑን ህጋዊ አድርጎ በጀት ከፌደራል መንግሱ ሊለቀቅለት ይገባል።

NB ጠላት ከመቀሌ እስከ ሞያሌ አማራን የሚገድለዉ በወሎየነቱ፣ በጎንደሬነቱ፣ በጎጃሜነቱ ፣በሽዋነቱ ፣ በክርስቲያንነቱ ወይም በእስልምና እምነቱ አይደለም ። አማራ በመሆኑ እንጂ❗️

ዛሬ በአይከል ካፍቴራ አዳራሽ የሙህራን መማክርት ጉባኤ😂 ድንቄም ሙህራን  መድረክ ተካሒዶ ነበር። ይህ መድረክ ለስሙ ከአይከል ከተማ አስተዳደር እና በሁለቱ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግሰት ሰራተ...
30/03/2022

ዛሬ በአይከል ካፍቴራ አዳራሽ የሙህራን መማክርት ጉባኤ😂 ድንቄም ሙህራን መድረክ ተካሒዶ ነበር።

ይህ መድረክ ለስሙ ከአይከል ከተማ አስተዳደር እና በሁለቱ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግሰት ሰራተኞች ተሳትፈዋል ይላል። እዉነት ነዉ የቅማንት ኮሚቴ ክፍለ ህዝብ ያዘጋጀዉ መድረክ ፣ሃሳቡን በክፍለ ህዝቡ በኩል ለዉዉይት ያቀረበበት መድረክ ነዉ። በዚህ መሰረት

1)በህገ መንግስቱ መሰረት ህዝብ የመረጠዉ ያስተዳድረን ኮሚቴዉ?
2) አሁን ያለዉ የመንግስት መዋቅር እኛን አይወክልም
3)ምዕራብ ጎንደር ዞን የተፈናቀሉ የመንግስት ሰራተኞች ፣ህዝቡ ይመለስ ፣አይከል ዘርፈዉ ያፈናቀሉትን ግን ትንፍሽ አይሉም
3) እኛ ማፈን ፣ማገት እና መግደል እንችላለን ነገር ግን አማራ ብድሩን መመለስ የለበትም ወቾ ጉድ
4) በምዕራብ ጎንደር በኩል ወደ ዉስጥ ያስገባነዉ የሳምሪ፣የግሙዝ ታጣቂ ለፅድቅ ነዉሰለዚህ ቲሃን እንደልብ እንፈጭባት ❗️
5) ኮሚቴዉ ህጋዊ የማንነት ወኪል ስለሆነ በምህረት ይግባ ወዘተ የሚሉ ነበሩ።

በዚህ መድረክ የተገኛቹህ ከ10 የማትበልጡ የነባሩ ጭልጋ ሙያተኞች የታሪክ አተላዎች ናቹህ ። ስማቹህንም መዝግበን ለታሪክ አስቀምጠናል። አስፈላጊ ከሆነ ማንነታቹህን እና ስማቹህን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን።

30/03/2022

የተንከልን አካባቢ ህዝብ በተመለከተ ህዝቡ ያነሳዉን መሰረታዊ የመሰረተ ልማት ጥያቄ በአግባቡ መመለስ እንጂ አጉል ፍረጃ መግባት Super stupidity ነዉ❗️

አቶ ዘለቀ እንቢአለ እና ካቢኒያቹህ የተንከል አካባቢ ተወላጅ የሆኑ አመራሮች ፣ሙያተኞች ችግር ሊኖርባቸዉ ይችላል ነገር ግን ህዝብ በጥቅሉ ችግር አይፈጥርም ። ህዝቡ በጠቅላላዉ ሮሮ ካሰማ ችግሩ ያለዉ ከእናንተ ነዉ እንጂ ከህዝቡ አይደለም። የትኛዉን የህዝቡን ጥያቄ ነዉ የመለሳቹህት? ህዝቡ የሚፈልገዉን ነገር፣የጠየቀዉ ጥያቄ በአግባቡ ካልተመለሰለት ሁሌ ግብር መክፈል ይሰለቻል እኮ ።

አሁንም ነባሩ ጭልጋ ወረዳ ያለዉ የአመራር ስምሪት 99% የህዝብን ችግር የመፍታት ሳይሆን የመረዳት አቅም የለዉም።

ስለዚህ መጀመሪያ ራሳቹን ተመልከቱ፣ ህዝብ አትናቁ ❗️

27/03/2022

የአማራ ክልል የቅማንት ልዩ ዞንን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ በእነ አበራ አለማየሁ እና ስማቸዉ በኩል ቢሮ ሰጦ ሲሰራ የኖረዉን አሁን ወደ መሬት ለማዉረድ ተፍ ተፍ ማለት ጀምሯል።

አቶ ወርቁ ሃይለማርያም የፀጥታዉ መሃንዲስ 😂 በዚህ መልኩ የጎንደር መከራ ያበቃል ብለዉ አስበዉ ከሆነ መሃዲስኖቶን😂እጠራጠራለሁ ።

ያ 69 ቀበሌ (:- በብዙ ዘንድ ያልታመነበት) ግን ደግሞ 3>ከ69 ብሎ በሰፈር ሸፍቶ አካባቢዉን በማተራመስ ላይ የሚገኘዉ ኮሚቴስ ምን ላይ ነዉ? የቅማንት ህዝብስ አልቀበልም ያለዉን 69 ቀበሌ እንዴት ተረከበ?

ለማንም አሁንም ሰከን በሉ በስኳር ኩፖን፣ በችሮታ የተመረቁ በርካታ ቀበሌዎች አሉ ❗️

27/03/2022

18/07/2014አም
መንግስት እና ህዝብ በተለያየ መንገድ❗️

በአሳለፍነዉ ሳምንት ብልፅግና ከህዝቡ ጋር ያደረገዉ ጉባኤ ላይ ያልጠበቁት በርካታ ጥያቄ እና ትችት በመድረኮቹ ተነስተዋል። ለአብነትም በጭልጋ ቁጥር2 ወረዳ ከተነሱት በርካታ ጥያቄዎች በሁለት ጎራ ይከፈላሉ
1 በሰላም እና ድህንነት ዙሪያ ከጫንድባ እስከ ቀይ አፈር በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል ከእነዚህ ዉስጥ ከአይከል ጫንድባ ፣ ከአይከል ዳንጉራ ያለዉ መንገድ በፀጥታ ችግር ዝግ በመሆኑ አገልግሉት ለማግኘት በጎንደር እየዞርን እየተገላታን ነዉ? በአጎራባች ቀበሌዎች አካባቢ ግጭት ፣አፈና እና ዘረፋ ስላለ ህዝቡ ተረጋግቶ መቀመጥ አልቻለም ። ይህ መቸ ነዉ የሚቆመዉ ? ለ8 አመት ይህ ችግር እየተባባሰ ዛሬ ላይ ብዙዎችን ለሞት፣ ስደት፣ ለአካል ጉዳት ዳርጓል ።አሁንም እየዳረገ ይገኛል። ይህ መቸ ነዉ መፍትሔ የሚሰጠዉ? ዳዋ ቀጠና ያለዉ የእገታ እና ወንብድና ተግባር መቸ ነዉ የሚቆመዉ ወዘተ የመሳሰሉ ችግሮች ተነስተዋል።

2) በመሰረተ ልማት እና መልሶ ግንባታ በኩል ደግሞ በጤናዉ ዘርፍ ከእናቶች ጋር በተያያዘ፣ ከጤና መድን አገልግሎት ጋር በተገናኘ ፣ የንፁህ መጠጥ ዉሃ ችግር፣ በትምህርት ጥራት፣ በ12ኛ ክፍል ፈተና በተመለከተ፣ በግብርና የግብአት እጥረት እና የአፈር ማዳበሪያን የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ላይ ጠጠር ያሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል። እንዲሁም በርካታ ሰዉ መኖሪያ ቀየዉ ተቃጥሎበት በየቀበሌዎች ተጠልለዉ የሚገኙት መቸ ነዉ መልሶ ማቋቋሙ ተሰርቶ ወደ የቀበሌቸዉ የሚመለሱት በማለት በምሬት ጠይቀዋል።

በመድረኩ የነበሩት የብልፅግና ካድሪዎች ግን መልስ መስጠት ተስኗቸዉ ሲተባተቡ ዉለዋል። በምትኩ ለመልሶ ማቋቋም 2011 አም በብድር መልክ የተሰጠን ብር መልሱ ሲሉ ተደምጠዋል። የሚበላዉ የእለት ምግብ የለለዉ ህዝብ ምኑን ሽጦ ነዉ የሚመልሰዉ? ደግሞስ ካለዉ የተቃጠለዉን ቤቱን ገንብቶ አይገባም ነበር ? አልተገናኝቶም ወገኔ
ትምህርት ፣ጤና ፣ዉሃ ፣ግብርና ላይ የተነሱ ጥያቄዎችን በወሬ እመልሳለሁ ብሉ በጀቱን ግን ለህንፃ ግንባታ አዙሬዋለሁ ብሎ እርፍ። ለመሆኑ ማን ነዉ መቅደም ያለበት ? የህዝቡን ችግር መፍታት ወይስ ማንን ለማገልገል ነዉ ህንፃ የሚገነባዉ? ደግሞ ክልሉ ወረዳዉ ሲከፈል አቶ ገዱ ቢሮ ገንብተን እንሰጣለን አላለም ነበር? ነዉ ደፍሮ የሚጠይቅ ጠፋ? ለማንም ብልፅግና ላይ በቅርቡ የህዝብ አብዪት የሚፈነዳ ይመስለኛል። እንደ ዶግማ ርዕዮተ የለለዉን ዲሪቶ ትታቹህ ባላቹህ ስልጣን እንደ ህዝቡ ጠያቂ ሳትሆኑ መልስ እና መፍትሔ ትለሙ።
በጠቅላላው መንግስት እና ህዝብ በተለያየ መንገድ እየተጓዙ ነዉ። ህዝብ ወደፊት መንግስት ወደ ሗላ ሽምጥ እየጋለቡ ነዉ።

Address

Aykel

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aykel Express posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category