Gojjam press

Gojjam press አብ ቀባዒ ወልድ ተቀባዒ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ትክክለኛው ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ነው፡፡
ተዋህዶ የሚያሰኝም ይህ ነው!

17/08/2026

ጎጃም ክርስትናን መቼ እንደተቀበለ ያውቃሉ ?

ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ክረስትናን ከተቀበለ ከአንድ ሺ አመት በኋላ ነው ጎጃም ክርስትናን የተቀበለ።

ማነው እንዲህ ያለ ካሉ ዝርዝሩን እነሆ ምንጩ ገድለ ተከስተ ብርሃን ነው።
እንደገድሉ ገለጻ ጎጃም እስከ 14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ክርስትናን አልተቀበለም ነበር ክርስትናን የተቀበለው በአባ ተከስተ ብርሃን ሰባኪነት በአጼ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት ነው የአጼ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት መቼ ነበር ከተባለ ከ1297-1327 እንደነበር በነገስታቱ ታሪክ የታወቀ ነው።

ሌላው ገድሉ ላይ የምንረዳው "አባ ሰላማ ለኢትዮጵያ ሰዎች የቃሉን ትምህርት ባስተማረ ጊዜ ከሳቴ ብርሃን ተባለ እንደዚሁም ሁሉ አባታችን በኪሞስ ለጎጃም ሰዎች ሐዲስ ሐዋርያ ነውና ተከስተ ብርሃን ተባለ"
የሚለውን ነው ። ቀጥሎም የጎጃም አብያተ ክርስቲያናት እናትና የመጀመሪያይቱ ከአድማራት ሁሉ የምትበልጥ ዲማ ናት ይላል ገድሉ እርስዎ እንዴት ያዩታል።
ለማነኛውም ገድሉን በግዕዝና በአማርኛ እናንበው

ወእምድህረ ተንስአ በኪሞስ ወኦደ ፈለገ ግዮስ ወበጽሐ ብሄረ ጉጃም እንዘ ይመርሆ መልአከ እግዚአብሄር ወሰበከ ስብከተ ወንጌል ዘመንግስተ ሰማያት ወአጥመቀ ጥምቀተ ወቀረበ ቁርባነ በርትእት ሃይማኖት ወአጥመቀ ብዙኃነ ሰብአ እንዘ ይትአመኑ ኃጢአቶሙ ወሰበረ ጣኦታቲሆሙ ወአብጠለ ምህራማቲሆሙ እስመ ሰብአ ጎጃም ኢአምኑ በክርስቶስ እስከኔሁ ።
ወኢያእመርዎ ለእግዚአብሄር ብሄረ ጎጃም ወአምኑ በስብከቱ በመዋእለ መንግስቱ ለአምደ ጽዮን ወልደ ይርአድ በከመሰበከ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ለብሄለ አግአዚ ሃይማኖተ ክርስቶስ በመዋእለ መንግስቶሙ ለአብርሃ ወአጽብሀ ነገስተ አክሱም ወአመ ሰበከ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ስብከተ ቃሉ ለኢትዮጵያ ብሄረ አግአዚ ተሰምየ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ወከማሁ አቡነ በኪሞስ ተሰምየ ተከስተ ብርሃን እስመ ሐዲስ ሐዋርያ ለብሄረ ጎጃም ።ወይቤሎ እግዚኡ ለበኪሞስ በደመና ሰማይ ኃረይኩከ ወሰመርኩከ ከመ ኤርምያስ ዘይቀድመከ ወከመ ጳውሎስ ንዋየ ኅሩየ ረሰይኩከ ወድህረ አጥመቀ ኩሎ ሰብአ ጎጃም
አድያሚሃ ወኩሎ ደወላ እምወሰና እስከ ወሰና ለግዮን ንበር ውስተ ክፍልከ ዘይእቲ ደብረ ድማህ ከመ ይሰባህ ስምየ በውስቴታ እስከ ለዓለመ አለም በእንቲአከ ።....ወጠነ አቡነ በኪሞስ በኪሞስ ሀኒፀ ቤተክርስቲያን ወቀረበ ቁርባነ
ወይእቲ ቀዳሚት እግዝእትነ ማርያም ዘደብረ ድማህ እምኩሎን አብያተ ክርስቲያናት ዘብሄረ ጎጃም ..ወዛቲ ደብረ ድማህ ተአቢ ወትትሌአል በስባሔ ወበክብር እምኩሎን አድባራት ።

በአማርኛ

አባ በኪሞስ ከዚያ ተነስቶ አባይን ተሻግሮ መልአከ እግዚአብሄር እየመራው ጎጃም ደረሰ ከዚያ መንግስተ ሰማይ የምታገባውን ወንጌልን ሰበከ ኃጢአታቸውን አምነው ብዙ ሕዝቦችን አሳምኖ አጠመቀ ጣኦታቸውን ሰበረ መስገጃቸውን አጠፋ የጎጃም ሰዎች እስከርሱ ድረስ እግዚአብሄርን አያውቁትምና በአምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት በእርሱ ስብከት የጎጃም ሰዎች አመኑ በአክሱም ነገስታት በአብርሃና አጽብሐ ዘመነ መንግስት የወንጌልን ሃይማኖት ለኢትዮጵያ ሰዎች አባ ሰላማ እንዳስተማረ የጎጃም ሰዎችን አስተማረ ።
አባ ሰላማ ለኢትዮጵያ ሰዎች የቃሉን ትምህርት ባስተማረ ጊዜ ከሳቴ
ብርሃን ተባለ እንደዚሁም ሁሉ አባታችን በኪሞስ ለጎጃም ሰዎች ሐዲስ ሐዋርያ ነውና ተከስተ ብርሃን ተባለ ጌታ በደመና ሆኖ አባ በኪሞስን ከአንተ እንደሚቀድም እንደ ነቢዩ ኤርምያስ መረጥሁህ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ምርጥ እቃ አደረግሁህ አለው ከአባይ እስከ አባይ ድረስ በአውራጃ እስከ አሉት ሰዎች ድረስ የጎጃምን ሰዎች ከአጠመቅህ በኋላ በተሰጠህ ቦታ ይህችውም ድማህ ናት ተቀመጥ አለው ። እስከ ዘላለሙ ድረስ በአንተና ከአንተ በኋላ የሚነሱ በልጆችህ በመነኮሳት ስሜ ይመሠገን ዘንድ ነው ።ልጆችህ መነኮሳት እንደ ሰማይ ኮከብ እንደ ምድር አሸዋ ይበዛሉ።
አስተምሮ ካሳመነ በኋላ ክፍሉ ወደ ሆነችው ወደ ድማ ታቦተ ማርያምን ይዞ ገባ በዚአም እንደ ተነገረ በውስጧ ተከላት አባታችን በኪሞስ ቤተክርስቲያን ይሰራ ዘንድ
ጀመረ ይህችውም የጎጃም አብያተክርስቲያናት እናት የሆነችው መጀመሪያይቱ ድማ ማርያም ናት።
ይህችም ደብረ ድማ ከሁሉም አድባራት በአገልግሎት ትበልጣለች

ምንጭ
ገድለ አቡነ ተከስተ ብርሃን ተርጓሚ
ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ የፈለገ ብርሃን ናዳ ቅድስት ማርያም እና የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም አስተዳዳሪ ገጽ ገጽ 2፤3፤4፣5

ጎጃም ክርስትናን እንዲቀበል ሐዋርያ ሆነው የመጡለት ሰው ለመምጣታቸው ምክንያት የሆነውን ታሪክ ደግሞ በሚቀጥለው እንነግርሃለን።
ጎጄ ስማ ከግብጾች በተወሰደ ሃይማኖታዊ የሸዋ ማደንቆሪያ ስልት ያልደነቆርህ ከሆንህ ሲሰራብህ የኖረው ሴራ ይገባህና ዛሬም ቅባት ተዋህዶ እያሉ ከሚከፋፍሉህ አደንቋሪዎች የማደንቆሪያ ስልት ተላቀህ ሊቁ መላከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ልጆች ናቸው በሚለው ገዚ ሀሳብ ተስማምተህ በግብጾች ስልት እየሄደ ያለውን የካራ ቡድን ከነሴራው አውልቀህ ጥለህ ተነጋግረህና ተወያይተህ አንድ ትሆናለህ። የካራ ማደንቆሪያ ስልት ሰለባ የሆነህ ከሆነ ግን ምንም ማድረግ አይቻልም በክፍል ሁለት ጠብቀኝ

22/07/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Getaneh Getaneh, Mastwal Sinshaw, Ashenafi Ethio Man

21/07/2026

With Bieza Mera Mera – I just got recognized as one of their top fans!

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gojjam press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share