GION Amhara-ግዮን አማራ

GION Amhara-ግዮን አማራ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from GION Amhara-ግዮን አማራ, Media/News Company, Bahir Dar.

11/05/2023

የዘመናችን ተመራጩና ገላግሌው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ቴሌብር ሁለተኛ ዓመቱን አስቆጥሯል፡፡
በነዚህ ፍሬያማ ዓመታት የቴሌብር ደንበኞች ብዛት ስንት ደርሷል?

የውድድሩን ደንብ እና ህጎች አስተያየት መስጫው ላይ ይመልከቱ፡፡

በደሴ ከተማ መላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጥቁር ልብስ  በመልበስ ሰልፍ አደረጉ!ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመው ኢመደበኛ መፈንቅለ ሲኖዶስ  እና ...
05/02/2023

በደሴ ከተማ መላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ጥቁር ልብስ በመልበስ ሰልፍ አደረጉ!

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመው ኢመደበኛ መፈንቅለ ሲኖዶስ እና መንግስት በድርጊቱ እያሳየ ያለውን ቸለልተኝነት በማስመልከት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የመጣባቸውን መከራ ጥቁር ልብስ በመልበስ መንግስትን አውግዘዋል።

በሰልፉ ላይ የተለያዩ መልዕክቶች የተላለፉ ሲሆን ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ፣ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን ማሰርና ማንገላታት ይቁም፣ የምንሞትለት ሃይማኖት እንጂ ብሔር የለንም፣ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ የመጨረሻውን ደወል አሰምተናል፣

መንግስታዊ አምባገነንነት እና አፍራሽነት ይቁም የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

ሰልፉም በሰላም ተጠናቋል።

ዘጋቢ ኤልያስ ደባሱ ከደሴ

የጎንደሩ አድባር ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በጥምቀት ዋዜማ በጎንደር!
17/01/2023

የጎንደሩ አድባር ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በጥምቀት ዋዜማ በጎንደር!

05/01/2023

የመጨረሻው ዙር ተጫውተው የሚሸለሙበት የገና ድግስ
በገና ጨዋታ ወቅት ከምንጫወትበት ሙዚቃ ላይ የተወሰደ ስንኝ ነው፡፡ ከስንኙ የጎደሉትና ቃላት ከሳጥኑ ፈልጉ፤ መልሱን በአስተያየት መስጫው በአጭሩ ይንገሩን፡፡

ታብሌት፤ ስማርት ስልክ፤ ስማርት ሰዓት፣ ኤርፖድ (የጆሮ ማዳመጫ) እና በርከት ያለ የአሻምቴሌ ነጥቦችን ለማሸነፍ ይሳተፉ፤ በመቀጠል ገፁን ይከተሉ(Follow)፤ ልጥፉን ይውደዱ(Like) እንዲሁም ያጋሩ (Share)
የገና ስጦታዎን ይውሰዱ!

04/01/2023

እነሆ በዚህ ገፅ የሚሸለሙበት ሁለተኛውን ጨዋታ ይዘን መጥተናል
ታኅሣሥ 29 ከሚከበረው የገና በዓል ጋር ተያይዞ ከነዚህ ውስጥ ሊካተት የማይገባው ሃገር የቱ ነው?
መልሱን በአስተያየት መስጫው ላይ ይንገሩን።
ታብሌት፤ ስማርት ስልክ፤ ስማርት ሰዓት፣ ኤርፖድ (የጆሮ ማዳመጫ) እና በርከት ያለ የአሻምቴሌ ነጥቦችን ለማሸነፍ ይሳተፉ፤ በመቀጠል ገፁን ይከተሉ(Follow)፤ ልጥፉን ይውደዱ(Like) እንዲሁም ያጋሩ (Share)
የገና ስጦታዎን ይውሰዱ!
በፌስቡክ እና ትዊተር ገፆቻችን ይሳተፉ

የውድድር ደንብ እና ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ናቸው

29/12/2022
ጥበብ እንቁአን አጣች!ዝነኛው እና ወጣቱ የብዙዎቻችን የሳቅ ምንጭ የምናውቀው እንቁ የጥበብ ሰው  #ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚች አለም ድካም አርፏል።ለቤ...
11/12/2022

ጥበብ እንቁአን አጣች!

ዝነኛው እና ወጣቱ የብዙዎቻችን የሳቅ ምንጭ የምናውቀው እንቁ የጥበብ ሰው #ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚች አለም ድካም አርፏል።

ለቤተሰቡ ፤ለጓደኞቹ፤ ለጥበብ አድናቂዎች መፅናናት እንመኛለን::

ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ተዋናይ

በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝናን አና በብዙዎች ተወዳጅነትን ያተረፈ ተዋናይ ነው። በጉዳዬ ፊልም ላይ ደግሞ በድርሰት ፣ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በትወና ተሳትፎበታል ፤ እጅግ በጣም ብዙ ፊልሞች ላይ ተውነዋል ።

▪️3+1
▪️300 ሺ
▪️አስነኪኝ
▪️ባላ ገሩ
▪️የፍቅር ABCD
▪️ብላቴና
▪️ቦሌ ማነቂያ
▪️እንደ ባል እና ሚስት
▪️ኢንጂነሮቹ
▪️እርቅ ይሁን
▪️ኢዮሪካ
▪️ጉዳዬ
▪️ሀገርሽ ሀገሬ
▪️ሕይወቴ
▪️ህይወት እና ሳቅ
▪️ከባድ ሚዛን
▪️ፍቅር እና ፌስቡክ
▪️ከቃል በላይ
▪️ላውንድሪ ቦይ
▪️ኮከባችን
▪️ማርትሬዛ
▪️ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2
▪️ሞኙ የአራዳ ልጅ 4
▪️ትዳርን ፍለጋ
▪️አንድ ሁለት
▪️ብር ርርር
▪️ወደው አይሰርቁ
▪️ወፌ ቆመች
▪️ወንድሜ ያዕቆብ
▪️እንደ ቀልድ
▪️ወቶ አደር
▪️አባት ሀገር
▪️የሞግዚቷ ልጆች
▪️ይዋጣልን
▪️ዋሻው
▪️ወሬ ነጋሪ
▪️ወጣት በ97

ነፍስህ በሰላም ትረፍ ወንድም 🙏😭

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ!*በሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት ዲሞክራሲያዊ ሥርአት ለመትከል ፣ እኩልነትን ለማረጋገጥ እና የኢትዮ...
09/12/2022

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ!
*
በሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት ዲሞክራሲያዊ ሥርአት ለመትከል ፣ እኩልነትን ለማረጋገጥ እና የኢትዮጵያን ሕዝብ የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ለማድረግ በርካታ መስዋዕትነት የተከፈለ እና በብዙ ውጣውረዶች ውስጥ ያለፍን ቢሆንም ፣ ትግላችን እና ጉዟችን ከድጡ ወደማጡ እየሆነ ፣ ሀገራዊ ፈተናዎቻችን እየበረቱ እና አዳዲስ ችግሮች እየተፈጠሩ በአሁኑ ወቅት ሀገራዊ ኅልውናችንን እና አንድነታችንን ላይ አደጋ የጋረጡ ፈተናዎች ከፊት ለፊታችን ተደቅነው ይገኛሉ፡፡ ባለፉት አምስት አስር ዓመታት ውስጥ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከተፈጠሩ ፖለቲካዊ የኃይል አሰላለፎች ውስጥ ዋነኛ ኃይል ሆኖ የወጣው “የነጻ-አውጭዎች” የኃይል አሰላለፍ የአማራን ሕዝብ በጠላትነት በመፈረጅ እድልና አጋጣሚ በፈቀደለት ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ሁሉ በሕዝባችን ላይ ተነግሮ የማያልቅ መከራ እና እልቂት ሲያደርስ ቆይቷል፡፡

ሀገር ለማፍረስ ተማምለው ጫካ የወረዱ እና በለስ ቀንቷቸው አራት ኪሎ እግር የጣላቸው “ነጻ-አውጭ” ድርጅቶች ያለሕዝብ ፈቃድ እና ይሁንታ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫኑት ሀገር-አፍራሽ ሕገ-መንግስታዊ ሥርአት እና አፓርታይዳዊ የአስተዳደር መዋቅር ስራ ላይ ከዋለበት ካለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ፖለቲካዊ ቀውሱ እና ምስቅልቅሉ ወደ ታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል እንዲወርድ እና በየእለቱ የወገኖቻችን ሕይወት የሚቀጠፍበት ፣ ከቀያቸው የሚፈናቀሉበት እና በማያቋርጥ የእልቂት እና የቀውስ አዙሪት ውስጥ ተዳርገን እንገኛለን፡፡ የቀውስ አዙሪቱ ተባብሶ ቀጥሎ ቀድሞ እያሰለሰ በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጸም የኖረው የዘር-ማጥፋት ወንጀል አሁን የዕለት ተዕለት ክስተት እና የተለመደ የአዘቦት ተግባር ወደመሆን ተሸጋግሯል፡፡ በዚህ የቀውስ አዙሪት ውስጥ ዋነኛው ገፈት ቀማሽ የአማራ ሕዝብ ቢሆንም የኦሮሞን ህዝብ ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የቀውስ አዙሪቱ ተጠቂ እና የግፍ ጽዋው ተቋዳሽ መሆናቸው አልቀረም፡፡

በሥራ ላይ ያለው ሀገር-አፍራሽ ሕገ-መንግስት እና አፓርታዳዊ የአስተዳደር መዋቅር ዋነኛ አርክቴክት እና አናጺ የሆነው አሸባሪው ትሕነግ በጦር ግንባር ተሸንፎ ትጥቅ ለመፍታት መፈረሙን ተከትሎ ፣ የሽብር ቡድኑ ይፋዊ አጋር የሆነው ኦነግ-ሸኔ እና በህቡዕ እና በይፋ ለቡድኑ ሥልታዊ እና ቀጥተኛ ድጋፍ ሲሰጡ የቆዩት የኦሮሚያ ክልልን የሚዘውሩ አንዳንድ ባለስልጣናት ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የወደቁ ሲሆን ፣ በአዲስ አበባ እና በፌዴራል መንግስቱ ውስጥ ያለውን መዋቅራቸውን በማንቀሳቀስ በኦሮሚያ ክልል ፣ በአጎራባች ክልሎች እና በአዲስ አበባ ከተማ ቀውስ ለመፍጠር እና ሀገር ለማተራመስ የመጨረሻውን አቅማቸውን አሟጠው በመጠቀም ወደለየለት የሽብር ስራ ገብተዋል፡፡ በውጤቱም በበርካታ የወለጋ ዞኖች በአማራ ተዋላጆች ላይ እያሰለሱ ሲፈጽሙት የቆዩትን የዘር ማጥፋት ወንጀል የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ያደረጉ ሲሆን ፣ በፌዴራል መንግስት መዋቅሮች ውስጥ በየደረጃው በተቀመጡ አስፈጻሚወቻቸው በኩል በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል መዝሙር ዘምሩ እና የኦሮሚያን ባንዲራን አውለብልቡ የሚል የማተራመሻ ስልት ይዘው በመግባት፣ በህጻናትና በመምህራኖች ላይ ነውረኛ ጫና በመፍጠር አዲስ አበባ ከተማን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ ያለ የሌለ አቅማቸውን አሟጠው እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡

በጫካ ያለውም ሆነ የመንግስት መዋቅርን የተቆጣጠረው ኦነግ-ሸኔ ወደ ለየለት የሽብር ተግባር ውስጥ ገብተው ንጹሃንን ዕለት በዕለት የሚጨፈጭፉት እና አዲስ አበባ ከተማ ድረስ ዘልቀው አዲስ የቀውስ ማዕከል ለመፍጠር እየተጣጣሩ ያሉት ፣ ተሸንፎ እጅ የሰጠውን የጥፋት አጋራቸውን እና አሸባሪውን ትሕነግ ከገባበት ቅርቃር ለማውጣት እና እነሱም የማይቀርላቸውን የሽንፈት ጽዋ ላለመጎንጨት የመጨረሻውን መንፈራገጥ እያደረጉ ለመሆኑ (The last kick of a dying horse) ማሳያ ከመሆን የሚያልፍ አይደለም፡፡ ከሁሉም በላይ አሸባሪው ኦነግ-ሸኔ እና የኦሮሚያ ክልልን የሚዘውሩት አንዳንድ ባለስልጣናት በአማራ ተወላጆች ላይ እየፈጸሙት ያሉት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፣ በኦሮሚያ ክልል እየፈጠሩት ያለው ፖለቲካዊ ምስቅልቅል እና አዲስ አበባን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ እየሄዱበት ያለው እርቀት የሚያረጋግጠው የስብስቡን ጥንካሬ ሳይሆን ፣ በሥራ ላይ ያለው አፓርታዳዊ የአስተዳደር መዋቅር ለሽብርተኝነት እና ሽብርተኞች መደበቂያነት የተመቸ መዋቅር መሆኑን ፣ ሥርአቱ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለቀ እና ሊጠገን በማይችል ስብራት ላይ የሚገኝ መሆኑን ነው፡፡

ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ሕዝብ ላይ የኅልውና አደጋ የደቀኑትን የፖለቲካ ኃይሎች ነጥሎ ሲታገል የቆየ ሲሆን ፣ ይህን የትግል መስመር አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ፓርቲያችን አብን የአማራ ሕዝብ የተደቀነበትን የኅልውና አደጋ ለመቀልበስ በሚችልበት የተሟላ አቋም ላይ እንደሚገኝ ይተማመናል! ሕዝባችን ሊሸነፉ አይችሉም የተባሉ ጠላቶቻችንን በአስደናቂ ተጋድሎ እያሸነፈ እና እጅ እያሰጠ በድል ግስጋሴ ላይ እንደሚገኝ ጠላትም ወዳጅም የሚውቀው ሃቅ ነው፡፡ ባልታጠቁ እና ራሳቸውን ለመከላከል በማይችሉ ህጻናት ፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች እና ሲቪል ወገኖቻችን ላይ በየእለቱ የሚፈጸመው ጭፍጨፋ እና እልቂት ሀዘን አጥንታችን ድረስ ዘልቆ ቢገባም ፣ እንደ ሕዝብ እየተፈጸመብን ያለው የማያባራ ጥቃት አንገታችንን አያስደፋንም! ለጠላቶቻችን እጅ አያሰጠንም! ኦነግ-ሸኔ እና በመንግስት የሲቪልና የጸጥታ መዋቅር ተሰግስገው በሕዝባችን ላይ ያለእረፍት ጭፍጨፋ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸሙ ያሉት እና አዲስ አበባ ከተማን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ እየተውተረተሩ ያሉት ሽብርተኞች ምኞት እንደማይሳካ እና ሽንፈታቸው የማይቀር ለመሆኑ ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል፡፡

ፓርቲችን አብን ለመላው የአማራ ሕዝብ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አንድነቱን እንዲያጠናክር ጥሪውን እያስተላለፈ ፣ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በግፍ እየተጠቃ ካለው የአማራ ሕዝብ ጎን እንድትሰለፉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ድል ለአማራ ሕዝብ! ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አዲስ አበባ ፣ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ
ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም

የአማራዉ ደም መፍሰስ እንዴት ይቁም? ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ምየአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ ሃገረ መንግስት ምስረታ ያደረገዉ አበርክቶ የአንበሳዉን ድርሻ የሚይዝ እና አገር በተደፈረች ወይም ...
04/12/2022

የአማራዉ ደም መፍሰስ እንዴት ይቁም?
ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም

የአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ ሃገረ መንግስት ምስረታ ያደረገዉ አበርክቶ የአንበሳዉን ድርሻ የሚይዝ እና አገር በተደፈረች ወይም ችግር ላይ በወደቀች ጊዜ ከማንም ቀድሞ ግንባር በመሰለፍ ደሙን የሚያፈስ ህግ አክባሪና ከማንኛዉም የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ለዘመናት በፍቅር አብሮ የኖረ ህዝብ ነዉ።ባህርዳር በአገራችን የስርዓት ለዉጥ ለማምጣትም ከፊት በመሰለፍ ከፍተኛዉን መስዋዕትነት የሚከፍለዉ አማራ ቢሆንም የመሪነቱን ሚና ለሌሎች አማራ ጠል ግለሰቦች በይሉኝታ አሳልፎ በመስጠት የራሱን ህዝብ ለተደጋጋሚ የህልዉና አደጋ እየዳረገዉ ይገኛል። በአገራችን የስርዓት ለዉጥ በመጣ ቁጥር ስርዓቱን የሚረከበዉ አካል የመጀመሪያ ጠላት አድርጎ የሚወስደዉ አማራዉን ነዉ። የደርግ መንግስት ለዉጥ በተረከበ ማግስት አማራዉን ለማዳከምና ለማጥፋት በማሰብ የአማራዉን የነቃ የህብረተሰብ ክፍል ማጥፋትና የአማራዉን ሃብት መቀራመት የመጀመሪያ ስራዉ አድርጎ እንደፈፀመ ይታወቃል። በመቀጠልም የአማራዉን ድጋፍ ተንተርሶ ወደ ስልጣን የመጣዉ የትህነግ/ህወሃት ዘረኛ መንግስት የሃሰት ትርክት በመፍጠር አማራዉ በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች እንዲጠላና እንደ ጠላት እንዲታይ በማድረግ ለ27 ዓመታት በመላዉ ኢትዮጵያ የሚገኘዉን አማራ ከኖረበት እና እትብቱ ከተቀበረበት ቀዬ ሃብቱንና ንብረቱን እየጣለ እንዲሰደድ እና በግፍ እንዲገደል አደረገ። በአሁኑ ሰዓትም የአማራዉን ቀናዒነት በመጠቀም የትግል አጋር አድርጎ ወደ ስልጣን የመጣዉ የኦሮሙማዉ ዘረኛ መንግስት የመጀመሪያ ስራ አድርጎ የወሰደዉ አማራዉ እረፍት አልባ እንዲሆን አማራዉ በሚኖርበት የአገሪቱ ክፍል በጅምላ እንዲገደልና እንዲፈናቀል ፕሮጀክት ቀርፆ ማስፈፀምን ነዉ። በኦሮሞ ዘረኞች የአማራ ደም እንደ ጅረት መፍሰስ የጀመረዉ በደርግ መንግስት ከአሶሳዉ ከ200 በላይ አማሮችን በአንድ ቤት ዘግቶ ከማቃጠል ጀምሮ እስከ አሁኑ የወለጋዉ የአማራ ደም እንደ ጅረት የሚፈስበት ጊዜ ነዉ። በተለይም የአማራዉ እልቂት በወለጋ ኦሮሚያ በክልሉ ልዩ ኃይልና በኦነግ ሸኔ ትብብር የሚካሄድና የማያባራ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን በየቀኑ የሚያልቀዉን የአማራ ህዝብ ለመቁጠር እስኪያስቸግር ድረስ በቶሌ ቀበሌ በሶስት ሰዓት ብቻ ከተጨፈጨፉት 1500 በላይ እስክ ሰሞኑ በመጠለያ ዉስጥ ታግተዉ እስከተቃጠሉት ክ200 በላይ አማራዎች ያለርህራሄ እየተጨፈጨፉ ይገኛሉ። አሁን በዚህ ሰዓት በአንገር ጉተን ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች በክልሉ ልዩ ኃይልና በኦነግ ሸኔ ትብብር በጅምላ እየተጨፈጨፉ ይገኛሉ። የቀጠለዉ ጭፍጨፋ ባለመቆሙ በህይወት የተረፉ አማራዎች ከዚህ የሞት መንደር (The Circle of Death) የሚያወጣቸዉ የነፍስ አድን ጥሪ ቢያሰሙም የሚደርስላቸዉ ሳይሆን ዘራቸዉ እንዳይተርፍ የሚጨፈጭፍ የክልሉ ገዳይ ኃይል ከቧቸዉ ይገኛል። እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ ጊዳ ያና ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች የሞት ቀለበት (Village of Death) ዉስጥ ገብተዉ የሞትን ፅዋ እየተጠባበቁ የሚገኝበት ሁኔታ ላይ ናቸዉ። በአሁኑ ወቅት ይህ ዘረኛ የኦሮሙማ መንግስት ስልጣኑን ተቆጣጥሮ በመንግስታዊ መዋቅር ታግዞ የሚፈፅመዉ አማራን የማጥፋት ተግባር በአጭር ጊዜ ዉስጥ የሚቆም አለመሆኑ እና የምዕራቡ ዓለም የአማራዉን እልቂት እያወቁም ለይምሰል እንኳን መግለጫ የማይሰጡበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። ለዚህም ምክንያቱ የምዕራቡ ዓለም በህወሃት አገዛዝ ዘመን የአማራ ህዝብ ለአገሩ ያለዉን ቀናዒነትና አርበኝነት መስበር ባይችሉም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መስበር የሚቻለዉ በዚህ ዘረኛ የኦሮሙማዉ መንግስት አማካኝነት መሆኑን በማመን ነዉ። በተጨማሪም አማራዉ እርስ በእርሱ እንዳይተማመን እና በአንድነት ራሱን እንዳይከላከል በጎጠኝነት አረንቋ ዉስጥ እንዲገባ ከፍተኛ በጀት ተመድቦና ፕሮጀክት ተቀርፆ በስራ ላይ ዉሏል። ይህ የሚያሳየዉ አማራዉ በምን ያህል የከፋ የህልዉና አደጋ ላይ እንደሚገኝ ነዉ። ይህን በመንግስታዊ መዋቅር እየታገዘ የሚፈፀም አማራዉን የማጥፋት ፕሮጀክት አሁን ላለዉ ዘረኛ መንግስት እንዲያስቆምልን መጠየቅ በሌላ አካል የተፈፀመ እንዲመስል ድጋፍ መስጠት ካልሆነ በስተቀር ዉጤቱን እንደማይቀይረዉ ድርጅታችን በጽኑ ያምናል። የአማራ ጀግኖች አደራ የሚከተሉትን ጥሪዎች ለአማራ ህዝብ ያስተላልፋል።
1. ማንኛዉም አማራ ከተቋቋመዉ የአማራ ፋኖ አንድነት ማህበር ጎን በመሰለፍ የሚጠበቅበትን አስተዋፆ እንዲያደርግ እንጠይቃለን
2. ለኦሮሙማዉ ዘረኛ መንግስት ተላላኪ በመሆን አማራዉን እጅ ተወርች አስሮ እንዳይደራጅና እራሱን እንዳይከላከል ያደረገዉን ነቀርሳ ብዓዴንን የአሁኑ የአማራ ብልፅናን ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ሁሉም አማራ በአንድነት እንዲነሳ እንጠይቃለን
3. በአሁኑ ወቅት አማራዉ በአገሩ እንደ ሌላ ዜጋ የሚታይበትና በየትኛዉም የኢትዮጵያ ክፍል የመንቀሳቀስ፤ የመኖር እና ሃብት ንብረት የማፍራት መብት የሌለዉ እና በመንግስታዊ መዋቅር ህልዉናዉ አደጋ ላይ የወደቀበት በመሆኑ አማራዉ ራሱን ከመጥፋት ለመታደግ የመጨረሻ አማራጭ የሆነዉን ስር ነቀል የስርዓት ለዉጥ ለማምጣት መላዉ አማራ ለሁለገብ ትግል ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ እንጠይቃለን
4. በመላዉ ዓለም የሚገኙ የአማራ ድርጅቶች በተናጠል በሚደረግ ትግል የሚመጣ ለውጥ አለመኖሩን በመገንዘብ የተቀናጀና ዉጤታማ ትግል ለማድረግ የጋር ግብ እና ርዕዮተ ዓለም በመንደፍ በአንድነት እንዲሰሩ እናሳስባለን
5. ለጊዚያዊ ጥቅም በነቀርሳዉ ብዓዴን ዉስጥ እና አማራን በጎጥ ለመከፋፈል በተቀረፀዉ ፕሮጀክት ስር ሆናችሁ የአማራዉን የህልዉና ትግል እያጨናገፋችሁ የምትገኙ የአማራ ልጆች አቋማችሁን በማስተካከል ከዚህ እኩይ ተግባራችሁ እንድትታቀቡ እናሳስባለን
6. የአማራዉ ጅምላ ፍጅት፤ መፈናቀል እና መሰደድ ባልደረሰባቸዉ አካባቢዎች የምትገኙ የአማራ ምሁራን፤ ባለሃብቶች እና የማህበረሰብ አንቂዎች አሁን በሌላ አካባቢዎች የሚታየዉ የህልዉና አደጋ በቅርብ ጊዜ በሁሉም አካባቢ የሚፈፀም መሆኑን አዉቃችሁ ለሚደረገዉ የአማራን ህልዉና የመታደግ ሁለገብ ትግል የበኩላችሁን አስተዋፆ እንድታደርጉ እንጠይቃለን !ክብር ዋጋ ለከፈሉ የአማራ ጀግኖች!
የአማራ ጀግኖች አደራ፣ ለንደን፣ ዩናይትድ ኪንግደም

ሰበር ዜና! #ከአማራ ክልል ወደ አዲስአበባ የተወሰዱ እስረኞች ዛሬ በ23/3/2015 ዓ.ም ከሰዓትም በልደታ ፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን  ፍ/ቤቱ እያንዳንዳቸዉ በ40ሺ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ተወሰ...
02/12/2022

ሰበር ዜና!

#ከአማራ ክልል ወደ አዲስአበባ የተወሰዱ እስረኞች ዛሬ በ23/3/2015 ዓ.ም ከሰዓትም በልደታ ፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ እያንዳንዳቸዉ በ40ሺ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ተወሰነ።

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GION Amhara-ግዮን አማራ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share