አሚኮ ስፖርት AMECO Sport

አሚኮ ስፖርት AMECO Sport Ameco Sport Provides Real-time Sport updates.

24/10/2025

የባሕር ዳር ሌላኛው ድምቀት

24/10/2025
በቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያውያን ለአሸናፊነት ታጭተዋል።ባሕር ዳር: ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ደረጃ ከተሰጣቸው የግማሽ ማራቶን ውድድሮች መካከል የ...
24/10/2025

በቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያውያን ለአሸናፊነት ታጭተዋል።

ባሕር ዳር: ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ደረጃ ከተሰጣቸው የግማሽ ማራቶን ውድድሮች መካከል የቫሌንሲያ ማራቶን ይገኝበታል፡፡

በፊታችን እሑድ ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም በሚካሄደው ፉክክርም በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ፡፡

በወንዶች የቦታው ክብረወሰን ባለቤት ዮሚፍ ቀጀልቻ ነው። አትሌቱ በ2024 ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ ያስመዘገበው ሰዓት 57 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ የወቅቱ የዓመቱ የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን ነበር፡፡

ይሁን እንጂ 2025 ላይ በባርሴሎና ግማሽ ማራቶን ጃኮብ ኪፕሊሞ የዮሚፍን የዓለም ክብረወሰን ሰዓት አሻሽሏል፡፡ ክብሩን ለማስመለስም የዓለም የ10 ሺህ ሜትር የብር ሜዳልያ ባለቤቱ ዮሚፍ ቀጀልቻ ቫልንሲያ ላይ የሚሰለፍ ይኾናል፡፡

ዮሚፍ የአሸናፊነት ቅድመ ግምቱን ያግኝ እንጂ ግማሽ ማራቶንን ከ59 ደቂቃ በታች የገቡ ሦስት አትሌቶች ተፎካካሪዎቹ ይኾናሉ፡፡

ቅድመ ግምት ካገኙት መካከል በዓለም ሻምፒዮና የነሐስ ሜዳልያ ባለቤቱ የስዊድኑ አንድሪያስ አልምግሬን አንዱ ነው፡፡ 2025 ላይ በተለያዩ ርቀቶች የተሳካ ጊዜ እና ፈጣን ሰዓት እያስመዘገበ ቫሌንሲያ የደረሰው አንድሪያስ የአውሮፓ የግማሽ ማራቶን ክብረወሰንን ለመስበር እያሰበም ይሮጣል፡፡ 59 ደቂቃ ከ23 ሰከንድም የራሱ ፈጣን ሰዓት ነው፡፡

ኬንያውያኑ ፓትሪክ ሞሲንግ እና ጌዲዮን ኪፕሮቲች እንዲኹም የቡሩንዲው ሮድርጊ ክዊዜራ የሚጠበቁ ሌሎች አትሌቶች ናቸው። ሳሙኤል ተፈራ እና ጌትነት ዋለ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በግማሽ ማራቶን ቫሌንሲያ ላይ አሐዱ ብለው ይጀምራሉ፡፡

በወንዶቹ በዚህ ውድድር ኬንያ 15 ጊዜ የበላይነት ስትወስድ በኢትዮጵያ በኩል ጀማል ይመር እና ዮሚፍ ቀጀልቻ ብቻ አሸናፊ ኾነዋል፡፡ የቫሌንሲያ ግማሽ ማራቶን አዘጋጆች ያለፈው ዓመት ከተወዳዳሪ አትሌቶች ውጭ 25 ሺህ ተሳታፊዎች መካፈላቸውን ያወጡት መረጃ ያመላክታል፡፡

አምናም 13 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ለውድድሩ ካወጡት 5 እጥፍ ገቢ ማግኘታቸውን በድረ ገጻቸው አሳውቀዋል፡፡

ታዲያ ዘንድሮ ከሌሎች ዓመታት የተሻለ ፈጣን ሰዓቶች እንዲመዘገቡ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል፡፡ይሄም ፉክክሩን እያጠናከረ የከተማዋን የስፖርት ቱሪዝም እድገት እያሳደገ ለመምጣቱ ማሳያ ነው፡፡

በሴቶች በ2021 በዚህ ቦታ የተመዘገበው 1ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን ኾኖ ተመዝግቧል፡፡ ይሄን ያደረገችው ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ናት፡፡

እሑድ በሚደረገው መድረክ ደግሞ ፎይተን ተስፋዬ ለዚህ ክብር ትጠበቃለች፡፡ ያለፈው ዓመት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት አትሌቶች ኬኒያዊቷ ኧግነስ ጀቤት ንጌቲች እና ኢትዮጵያዊቷ ፎይተን ተስፋዬ ነበሩ፡፡

በ2024 በተደረገው ውድድር በ21 ሰከንድ ልዩነት በንጌቲች ተበልጣ 1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ ያስመዘገበችው ፎይተን ፈጣን ሰዓት ለማስመዝገብ ትጠበቃለች፡፡

ኾኖም ኬኒያዊቷ አግነስ ጀቤት ንጌቲች የ10 ኪሎ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን ያሻሻለቸው በዚችው ከተማ ነበር፡፡

የሁለቱን ተፎካካሪዎች ፍጥጫ ተጠባቂ ካደረጉት ሌላኛው ምክንያት መካከል በ2024 እና 2025 የፈረንጆቹ ዓመት በተሳተፈችባቸው ወድድሮች ላይ ፎይተን ተስፋዬ ስኬታማ ናት፡፡

በ2024 ቫሌንሲያ ላይ በግምሽ ማራቶኑ ሁለተኛ ከወጣች በኋላ 2025 ላይ በዓለም አትሌቲክስ የነሐስ ደረጃ በሚሰጠው የበርሊን ግማሽ ማራቶን አሸንፋለች፡፡

በቀዳሚነት ከማጠናቀቋ በተጨማሪ የቦታውን ክብረወሰን 1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት ማሻሻል ችላለች፡፡

በዓመቱ ውስጥ ስኬታማ የኾኑት አግነስ እና ፎይተን በመጭው እሑድ የሚያደርጉት ፉክክርም ተጠባቂ ኾኗል፡፡ ሙላቴ ተክሌ ሌላኛዋ ተሳታፊ ኢትዮጵያዊት አትሌት ናት፡፡

ከኬንያ፤ ዩጋንዳ እንዲኹም ከአሜሪካ የተውጣጡት አትሌቶችም እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ ያለፈው ዓመት 5 ሴት አትሌቶች 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ በታች ገብተዋል፡፡

ዘንድሮም የተሸለ ሰዓት እንደሚጠበቅ አዘጋጆቹ ቅድመ ግምት አስቀምጠዋል፡፡

ዘጋቢ:- ሐናማርያም መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

24/10/2025

#ባለታሪኮቹ

#እሑድ 7 ሰዓት ይጠብቁን

የጣና ሞገዶቹ ነጥብ ተጋርተዋል።ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 14/2018ዓ.ም (አሚኮ) በሁለተኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሰባት ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ከአርባ ም...
24/10/2025

የጣና ሞገዶቹ ነጥብ ተጋርተዋል።

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 14/2018ዓ.ም (አሚኮ) በሁለተኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሰባት ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ከአርባ ምንጭ ጋር አንድ እኩል ተለያይቷል።

በአንደኛ ሳምንት ሀዲያ ሆሳዕናን አሸንፎ የጀመረው ባህርዳር ከተማ ነጥቡ አራት ደርሷል።

ከነጌሌ አርሲ ጋር አቻ የተለያየው አርባ ምንጭ በድጋሜ ነጥብ ተጋርቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

የጣና ሞገዶቹ ከአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋሉ።ባሕር ዳር: ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ሁለተኛ ቀን ዛሬ ሲቀጥል አራት ...
24/10/2025

የጣና ሞገዶቹ ከአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋሉ።

ባሕር ዳር: ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ሁለተኛ ቀን ዛሬ ሲቀጥል አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

በዛሬው ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ከአርባ ምንጭ ከተማ 7፡00 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረት አግኝቷል።

ዓመቱን በድል የጀመሩት የጣና ሞገዶቹ በድል ጉዟቸው ለመቀጠል ከአዞዎቹ ጋር ጥሩ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

አሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ከሀድያ ሆሳዕና ጋር በነበራቸው የአንደኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ላይ የተጠቀሙበት የቴክኒክም ኾነ የታክቲክ ጨዋታ ውጤታማ እንዳደረጋቸው ታይቷል።

በተለይም አሠልጣኙ 4-4-2 አሰላለፍን መምረጣቸው የግብ ክልላቸውን በመዝጋት በመልሶ ማጥቃት ተጨዋቾቻቸው እንዲጫዎቱ በማድረጋቸው ውጤት ይዘው እንዲወጡ አስችሏቸዋል።

በተለይም የመሐል ክፍሉ ጥንካሬ ለተከላካይ ክፍሉ እና ለአጥቂ መስመሩ የተሻለ እገዛ እንዲያደርግ እና ጫናውን እንዲሸከም ማድረጋቸው ቡድኑ ተረጋግቶ ሦስት ኳሶችን በተጋጣሚ መረብ ላይ አሳርፎ እና አሸንፎ እንዲወጣም አስችሎታል።

በተለይም ክንዱ ባየልኝ ከተከላካይ መስመር ተስፈንጥሮ በመምጣት ያስቆጠራት ግብ ቡድኑ ምን ያክል አሰላለፉ በነጻነት እንዲጫዎት እንዳደረገው አመላካች ነው።

በሌላ በኩል ከተቃራኒ ቡድን አሰላለፍ አኳያ በነጻነት ሲጫዎት የነበረው አማኑኤል ገብረሚካኤል ግብ ለማስቆጠር አልተቸገረም።

አሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው በዚህኛው ጨዋታ እጅግ የተዋጣለት ቅያሪ አድርገው በሴዝ ኦሴ ያገኟት ሌላ ግብ የአሠልጣኙን የጨዋታ ማንበብ ችሎታ ያሳየ ነበር።

ዛሬስ ከአርባ ምንጭ ከተማ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ አሸንፎ ለመውጣት ምን አይነት የአጨዋወት ስልት ይከተላሉ የሚለው ተጠባቂ ነው የሚኾነው።

አሠልጣኙ በዚህ ጨዋታ ፔፔ ሰይዶን፣ መሳይ አገኘሁን፣ ፍጹም ፍትሀለውን፣ ግርማ ዲሳሳን፣ ክንዱ ባየልኝን፣ በረከት ጥጋቡን፣ ፍቅረሚካኤል አለሙን፣ ሄኖክ ይበልጣልን፣ ወንድወሰን በለጠን፣ ዮሐንስ ደረጀን እና አማኑኤል ገብረሚካኤልን በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ያካትታሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ተጋጣሚያቸው አርባምንጭ ከተማም የተሻለ አቋም ላይ የሚገኝ በመኾኑ ለጣና ሞገዶቹ ቀላል እንደማይኾን ነው የሚጠበቀው። አርባ ምንጭ ከተማ በአንደኛ ሳምንት ጨዋታ ከነገሌ አርሲ ጋር ተጫውቶ 1ለ1 ነው መለያየት የቻለው።

በነገሌ አርሲው ጨዋታ ግብ ማስቆጠር የቻለው ታምራት እያሱ ዛሬም የቡድኑ ተጠባቂ ተጫዋች እንደሚሆን ይጠበቃል።

ሌሎች የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎችም ዛሬ ይደረጋሉ። በሶከር ኢትዮጵያ መረጃ መሰረት መቀለ 70 እንደርታ ከመቻል 9፡00

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀድያ ሆሳዕና 10፡00፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምድረ ገነት ሽረ 12፡00 እና የሚያደርጉት ሌላው ተጠባቂ ጨዋታዎች ናቸው።

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ፋሲል ከነማ አሸነፈ። ባሕር ዳር:ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2ለ0 አሸንፏል፡፡     ...
23/10/2025

ፋሲል ከነማ አሸነፈ።

ባሕር ዳር:ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2ለ0 አሸንፏል፡፡

ለፋሲል ከነማ የማሸነፊያ ግቦቹን በረከት ግዛው እና አቤኔዘር ዮሀንስ አስቆጥረዋል፡፡

በሊጉ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ነገሌ አርሲን አሸንፏል። አዳማ ከተማ እና ሸገር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ ያለ ግብ ተጠናቅቋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ሊዮኔል መሲ ውሉን አራዘመ።ባሕር ዳር: ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሊዮኔል አድሬስ ሜሲ በኢንተር ሚያሚ ለተጨማሪ ጊዚያት ለመጫወት ውሉን አራዝሟል። በውሉ መሠረት መሲ በአሜሪካው ክለ...
23/10/2025

ሊዮኔል መሲ ውሉን አራዘመ።

ባሕር ዳር: ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሊዮኔል አድሬስ ሜሲ በኢንተር ሚያሚ ለተጨማሪ ጊዚያት ለመጫወት ውሉን አራዝሟል።

በውሉ መሠረት መሲ በአሜሪካው ክለብ አንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ ታህሳስ 2028 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

23/10/2025

ስፖርት ዜና፡ ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም #አሚኮ #ዜና

ከእሱ የተሻለው የግራ መስመር ተከላካይ ማን ነው?ባሕር ዳር: ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፖርቱጋል ውስጥ በአንድ ትንሽየ እና የድሆች ሰፈር እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ሰኔ 19/2002...
23/10/2025

ከእሱ የተሻለው የግራ መስመር ተከላካይ ማን ነው?

ባሕር ዳር: ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፖርቱጋል ውስጥ በአንድ ትንሽየ እና የድሆች ሰፈር እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ሰኔ 19/2002 አንድ አፍሪካዊ ዝርያ ያለው ሕጻን ይህችን ዓለም ተቀላቀለ።

በዛ ጥቁሮች ክብር በማያገኙበት ሰፈር ውስጥ ድህነቱ ተጨምሮ በርካታ ውጣ ውረዶችን ለማሳለፍ ይህችን ዓለም የተቀላቀለው ኑኖ አሌክሳንደር ታቫሬስ ሜንዴስ አሁን የደረሰበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት ብዙ ተፈትኗል።

ኑኖ ሜንዴስ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ግራ ተከላካዮች አንዱ ከመኾኑ አስቀድሞ ብዙ ተጽዕኖን እያሳለፈ የአካባቢው ክለብ በኾነው ዴስፐርታር ኳስን ማንከባለል ጀምሯል።

ይህ ተጨዋች በነበረው ጠንካራ አቋም እና ጥረት ብዙም ሳይቆይ በፖርቱጋል ሦስት ታላላቅ ክለቦች ዐይን ውስጥ ገባ።

በ10 ዓመቱም የስፖርቲንግ ሲፒ ማሠልጠኛን ተቀላቀለ። መጀመሪያ ላይ እንደ አጥቂ አማካይ ይጫወት የነበረ ቢኾንም ወደ ግራ ተከላካይነት ተቀይሮ እዚያው ቦታ ላይ ስኬታማ መኾን ችሏል።

ከኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ የመጀመሪያ የሚባለውን ፕሮፌሽናል ጨዋታውን ለስፖርቲንግ ነው ማድረግ የቻለው። ማርኮስ ኩኛ ክለቡን ለቆ ሲሄድ ትኩረት ያገኘው ተጨዋቹ በግራ ተከላካይነት የመጀመሪያ የክለቡ ምርጫ እንዲኾን አስችሎታል።

ይህ ተጨዋች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2002 መስከረም ላይ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ቀጥሎ በክለቡ የመጀመርያው ተሰላፊ ትንሹ ተጨዋች ለመኾንም በቅቷል።

ከ2020 እስከ 2021 አስደናቂ ስኬት ላይ የደረሰው ኑኖ አሌክሳንደር ታቫሬስ ሜንዴስ የስፖርቲንግ ፕሪሜራ ሊጋን እና ታሳ ዳ ሊጋን በማሸነፍ የሀገር ውስጥ ድርብ ዋንጫዎችን ሲያነሳ ቁልፍ ተጨዋች ነበር።

ባሳየው ምርጥ ብቃቱም በፕራይሜራ ሊጋ የዓመቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል።

ነሐሴ 2021 ሜንዴስ ለአንድ የውድድር ዘመን በውሰት ወደ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን አቀና። ባሳየው ብቃት በ2022 በ38 ሚሊዮን ዶላር የግዢ ውል ለአራት ዓመታት በቋሚነት እንዲፈራረም አስችሎታል።

በፒኤስጂ በውሰት የቆየበት ጊዜም ክለቡ ለ10ኛ ጊዜ የሊግ አንድን ዋንጫ እንዲያሸንፍ ረድቷል። በ 2022/2023 የውድድር ዘመን ደግሞ ከክለቡ ጋር ዋንጫ በማንሳት የሊጉ የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች የሚለውን ሽልማት አሸንፏል።

ተጫዋቹ ከከባድ የጡንቻ ጉዳት ከተመለሰ በኋላም ሜንዴስ ፒኤስጂ ሊግ አንድን፣ ኩፕ ደ ፍራንስን እና የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ እንዲያነሳ አስተዋጽኦ ማድረግም ችሏል።

በዚህ አስደናቂ ብቃቱም በቻምፒዮንስ ሊግ የዓመቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ እንዲካተት ከማስቻሉም በላይ በ2025 የባሎን ዶር ሽልማት ምርጫ ላይ 10ኛ ደረጃን መያዝ ችሏል።

ሜንዴስ በወጣትነት ደረጃዎች ፖርቱጋልን ወክሎ ከተጫወተ በኋላ፣ በመጋቢት 2021 ለ2022 ፊፋ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የብሔራዊ ቡድን ሙሉ የመጀመሪያ ጨዋታውን አደረገ።

የኑኖ ሜንዴስ ፍጥነት፣ ቴክኒካዊ ችሎታ እና ብስለት ድምር ለፓሪስ ሴንት ዠርሜንም ኾነ ለፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን ወሳኝ ተጨዋች መኾኑን አሳይቷል።

ፒኤስጂ ባለፈው ዓመት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ ሜንዴስ ምርጥ ብቃቱን አሳይቷል። የወቅቱ የዓለም ምርጥ ከሚባሉት ያማል፣ ሳላህ እና ሳካን ከመሳሰሉ ተጫዋቾች ጋር ፊት ለፊት የተፋለመው ፖርቱጋላዊ የግራ ተከላካይ እኝህን ተጫዋቾች በማቆም ለፒኤስጂ ስኬት ትልቅ ድርሻ ነበረው።

አሁን ላይ የዓለማችን ምርጡ ተከላካይ እየተባለ የሚሞካሸው ሜንዴስ ባለፈው ዓመት በፒኤስጅ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ጨምሮ ሦስት ዋንጫዎችን አሸንፏል።

ከፖርቱጋል ጋር ደግሞ የኔሽንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ነው። ይህን ተከትሎም የ2024/2025 የባሎን ዶር ሽልማት ላይ 10ኛ ደረጃን ይዞም አጠናቅቋል።

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።ባሕር ዳር: ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ዛሬ ሲቀጥል አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡ ዛሬ...
23/10/2025

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ባሕር ዳር: ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ዛሬ ሲቀጥል አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡

ዛሬ ከሚካሄዱ ጨዋታዎች መካከል ፋሲል ከነማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

በዛሬው የፋሲል ከነማ ጨዋታ አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በአንደኛ ሳምንት ከኢትዮጵጵያ ንግድ ባንክ ጋር ካደረጉት የቴክኒክ እና የታክቲክ ጨዋታ በተለየ አሰላለፍ ይዘው እንደሚገቡ ነው የሚጠበቀው፡፡

አሠልጣኙ ባለፈው ጨዋታቸው 3-3-4 አሠላለፍ የተጠቀሙ ሲኾን ይህም የመከላከል ቦታውን በተወሰነ መጠን እንዲሳሳ በማድረግ መረባቸው እንዲደፈር አድርጓል፡፡

አሠልጣኙ ይህን ክፍተት በተቻለ መጠን ለማጥበብ የተከላካይ መስመሩን በተቻለ መጠን ለመዝጋት ይሞክራሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡

ቡድኑም በአቻ ውጤት እንዲጠናቀቅ የኾነበትን ሁኔታ ዛሬ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ይቀይሩታል ተብሎም ይታሰባል፡፡

ሞይስ ፓዋቲ፣ ምኞት ደበበ፣ አቤነዘር ዮሐንስ፣ ዋሳዋ ጃአፍሪ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ ሐብታሙ ተከስተ፣ ብሩክ አማኑኤል፣ ዳግም አወቀ፣ በረከት ግዛው፣ ቃልኪዳን ዘላለም እና ቢኒያም ጌታቸው በዛሬው ጨዋታ እንደሚሰለፉ ታውቋል፡፡

ባለፈው ጨዋታ ግብ ማስቆጠር የቻለው በረከት ግዛው በዚህኛው ጨዋታም የተሻለ እንደሚኾን ይጠበቃል፡፡ ጨዋታውም 9፡00 ላይ ይካሄዳል፡፡

በሌሎች የዛሬ መርሐ ግብሮች ኢትዮጵያ ቡና ከነገሌ አርሲ 7፡00፣ ሸገር ከተማ ከአዳማ ከተማ 10፡00 እና ወላይታ ዲቻ ከድሬዳዋ ከተማ 12፡00 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

ሪያል ማድሪድ፣ ሊቨርፑልና ቼልሲ ድል ቀንቷቸዋል።ባሕር ዳር: ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሦስተኛ ዙር በተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ አሸንፏል።ከእንግሊዝ...
23/10/2025

ሪያል ማድሪድ፣ ሊቨርፑልና ቼልሲ ድል ቀንቷቸዋል።

ባሕር ዳር: ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሦስተኛ ዙር በተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ አሸንፏል።

ከእንግሊዝ ቡድኖች ደግሞ ቼልሲ እና ሊቨርፑል ሲያሸንፉ ቶተንሃም ያለ ጎል አቻ ተለያይቷል።

ሪያል ማድሪድ ጁቬንቱስን በጁዲ ቤሊንግሃም ብቸኛ ጎል ነው ያሸነፈው።

ቸልሲ አያክስን እና ሊቨርፑል ፍራንክፈርትን በተመሳሳይ 5ለ1 ነው ያሸነፉት።

በሌሎች የምሽቱ ጨዋታዎች፦
👉 ባየርሙኒክን ክለብ ብራግን 4 ለ 0

👉 ስፖርቲንግ ማርሴይልን 2 ለ 1 ሲያሸንፉ
👉 አታላንታ ከ ስላቭያ ፕራግ ያለ ጎል አቻ ተለያይተዋል።

ዘጋቢ፦ ዋሴ ባየ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Address

Bahirdar
Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አሚኮ ስፖርት AMECO Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አሚኮ ስፖርት AMECO Sport:

Share