አሚኮ እውነታ ማጣሪያ AMECO Fact Check

አሚኮ እውነታ ማጣሪያ  AMECO Fact Check Ameco Fact check your ubiquitous platform to check facts.

ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር ባሕር ዳር፡ መስከረም 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከቴክኖሎጂ መዘመን ጋር ተያይዞ ዋና የመገናኛ እና የመረጃ መለዋወጫ የኾነው ማኅበራዊ ሚዲያ የሰው ልጅን ሕይ...
15/09/2025

ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር

ባሕር ዳር፡ መስከረም 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከቴክኖሎጂ መዘመን ጋር ተያይዞ ዋና የመገናኛ እና የመረጃ መለዋወጫ የኾነው ማኅበራዊ ሚዲያ የሰው ልጅን ሕይወት እያቀለለ ነው።

በአንጻሩ ለጥላቻ እና ጥፋትም ይውላል። በተለይም የሚዲያ ግንዛቤ አነስተኛ በኾነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት የሚዲያው አገልግሎት ለጥፋት ሲጋለጥ ይስተዋላል።

ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ፣ በስፋት ጥቅም ላይ የመዋላቸውን ያህል ጠቃሚ ሃሳቦችን በማንሸራሸር ችግርን ለመቅረፊያ ከመጠቀም ይልቅ ጥላቻን የሚሰብኩ እና ከባሕል እና ሥነ ምግባር ያፈነገጡ ልምምዶች ሲስተናገዱባቸው ይስተዋላሉ።

በማኅበራዊ ሚዲያ የሚንሸራሸሩ የጥላቻ መልዕክቶች፣ የግጭት ጥሪዎች፣ አሰቃቂ ወንጀሎችን የሚያሳዩ ምስሎች እና ሌሎችም ከስብዕና ያፈነገጡ መልዕክቶች ፈተና ኾነዋል።

በአንጻሩ ደግሞ ባይበዙም ማኅበራዊ ሚዲያን ለዕውቀት ልውውጥ፣ ለሰላም፣ ለመደጋገፍ እና ለችግር መቀረፍ ዓላማ የሚያውሉም አሉ።

መምህር ሞሀመድ አሚን ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ ከሚጠቀሙት መካከል ይጠቀሳሉ። መምህሩ ማኅበራዊ ሚዲያን በተለይም ፌስ ቡክን ችግረኛ ተማሪዎችን በትምህርት ቁሳቁስ ለመርዳት ይጠቀሙበታል።

መምህር ሞሀመድ የኅብረተሰቡ የመከባበር፣ የመተዛዘን እና የመረዳዳት እሴትን በማኅበራዊ ሚዲያ ለማስቀጠል እና ለመጠቀም እንዲቻል ያስተምራሉ። በጎ ሥራዎችን በመተግበርም ንቁ ተሳታፊ ናቸው።

እንደማሳያ በ2016 የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ ከ40 ሺህ በላይ ሰዎችን አስተባብረዋል። ለበርካታ ተማሪዎችም ድጋፍ በማድረግ ያለ ችግር እንዲማሩ አድርገዋል። አሁንም በጎ ሥራዎችን አስቀጥለዋል።

ማኅበራዊ ሚዲያ አሉታዊም ኾነ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳለው የጠቀሱት መምህር ሞሀመድ አጠቃቀሙ እንደ ሰዎች እንደሚወሰንም ገልጸዋል።

ማኅበራዊ ሚዲያ የተራራቁ እና የተረሳሱ ሰዎችን ለመልካም ሥራ በማገናኘትም አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው። ሁሉም ለበጎ በመጠቀም መተጋገዝ እና ሕይወትን ቀለል ማድረግ ይገባል ነው ያሉት መምህሩ።

መምህር ሞሀመድ በከፈቷቸው የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን አፍርተዋል። በጎ፣ ትምህርታዊ እና የንግድ ሥራ ትምህርትንም ያስተላልፉባቸዋል። ይህን በጎ ተግባርም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የተናገሩት።

"ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የማገኛቸውን በጎ ሃሳቦች ለጓደኞቼ እና ተከታይቼ አጋራለሁ፤ በጎ ላልኾኑት ደግሞ ምንም ዓይነት ምላሽ አልሰጥም፤ ይልቁንም ለካምፓኒው ሪፖርት በማድረግም ተቃውሞየን እገልጻለሁ፤ መልዕክቱ ሪፖርት ከበዛበትም ካምፓኒው እንዲጠፋ ያደርገዋል" ነው ያሉት።

ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ከሚጠቀሙት መካከል ሌላኛው ደግሞ የባሕር ዳር ነዋሪው አቶ ታዘባቸው ጣሴ ናቸው።

አቶ ታዘባቸው አሁን ላይ ሁሉንም ማኅበራዊ ሚዲያዎች ይጠቀማሉ። ለመማማር፣ ለመቀራረብ እና ለበጎ እየተጠቀመባቸው መኾኑን ገልጸዋል።

"አንዱ በሌላው ላይ ከመነሳሳት እና ከጥላቻ ይልቅ ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ ብናውል ተጠቃሚ እንኾናለን" ነው ያሉት አቶ ታዘባቸው። የተሳሳቱ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀሞችን አይቶ ማለፍ ብቻ ሳይኾን ተገቢ አለመኾኑን ማስተማር እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።

ከዚህ በፊትም በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች ላይ ይሳተፉ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ታዘባቸው ዘንድሮም በፌስ ቡክ የመማሪያ ቁሳቁስ በማሠባሠብ ለ100 ተማሪዎች አድርሰዋል።

ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በተራራቀ ቦታ የሚኖሩ ሰዎችን በማስተባበር መሥራታቸውንም ጠቁመዋል። ለመቄዶንያ ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ለማገዝ እንደተጠቀሙበትም ነው ለአሚኮ የተናገሩት።

የማኅበራዊ ሚዲያው አየር ወንድም ከወንድሙ ለማጋደል እና ለማጨራረስ ተጨናንቆ በነበረበት ጊዜ ይህን ስሜት ወደ ሰላማዊ እና መረዳዳት ለመቀየርም መሥራታቸውን አብራርተዋል።

በቀጣይ ማኅበራዊ ሚዲያን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም መረዳዳትን ማስቀደም እንደሚገባም አስገንዝበዋል። አረጋውያንን በየጊዜው ከመመጽወት ቋሚ ገቢ የሚያገኙበትን ዕቅድ ከጓደኛቸው ጋር በመኾን እየሠሩ እንደሚገኙም አብራርተዋል።

ሰው አፍራሽ እና አሉታዊ ነገሮች ላይ የመሳብ አዝማሚያ እንደሚታይበት የገለጹት አቶ ታዘባቸው ለሰላማዊ እና ለበጎ ዓላማ የሚለቀቁ መረጃዎችን የማበረታታቱ ሁኔታ ደካማ መኾኑን ነው ያነሱት።

ይህንን የተሳሳተ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን ማስተካከል ያለበት ራሱ ማኅበረሰቡ ነውም ብለዋል። ከአፍራሽ መልዕክቶች መታቀብ ብቻ ሳይኾን በመቃወም ጭምር የማኅበራዊ ሚዲያ ልምድን ማስተካከል እንደሚቻል ነው የመከሩት። ኀላፊነት መውሰድ እና ቁርጠኛ መኾን እንደሚገባም ነው አቶ ታዘባቸው የገለጹት።

በጎ በጎውን ማሰብ እና መሥራት በማኅበራዊ ሚዲያው ሲለመድ ለሀገር ሰላም እና መረዳዳትን ያተርፋል ብለዋል።

ብዙም ወጭ የማያስወጣውን ማኅበራዊ ሚዲያ ለበጎ ዓላማ በመጠቀም ኅብረተሰቡ ከድህነት ለመላቀቅ ያለበትን ውጣ ውረድ ማቅለል የተማረ ሰው መገለጫ ስለመኾኑም ነው የተናገሩት። የወገኑ ችግር የሚያሳስበው ሰው በሀሰተኛ እና የጥላቻ መረጃ ግጭቶችን እየቆሰቆሰ እልቂትን አያባብስም፤ የአቅማቸውን ያህል ለበጎ የሚሠሩ ሰዎችንም ማበረታታት ኀላፊነት እና ሰብዓዊነት የሚሰማው ዜጋ ሥራ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ዋሴ ባየ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

"አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ስሌት ነው በሚል የሚዘዋወረው መረጃ ስህተት ነው" የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽኝ ባሕር ዳር: ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የተፈቀደው አዲሱ የደመወዝ እስኬል ይ...
20/08/2025

"አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ስሌት ነው በሚል የሚዘዋወረው መረጃ ስህተት ነው" የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽኝ

ባሕር ዳር: ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የተፈቀደው አዲሱ የደመወዝ እስኬል ይህን ይመስላል የሚሉ ሐሰተኛ መረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያ እየተለጠፉ መኾኑን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ.ር) የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ስኬል በሚል በአንዳንድ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚናፈሱ አሳሳች መረጃዎች ሐሰተኛ ናቸው ብለዋል።

በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አማካኝነት ብቻ የሚለቀቁ መረጃዎች በመንግሥት እና በተቋሙ የሚተገበሩ መረጃዎች መኾኑን መገንዘብ ጥሩ ነው ማለታቸውን ከኮሚሽኑ ማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ መረጃዎችን ከመጠቀም በፊት በተገቢው መንገድ ማጣራት ይገባል።ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የማኅበራዊ ሚዲያ ሰዎች ሀሳባቸውን የሚለዋወጡበት እና...
12/08/2025

በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ መረጃዎችን ከመጠቀም በፊት በተገቢው መንገድ ማጣራት ይገባል።

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የማኅበራዊ ሚዲያ ሰዎች ሀሳባቸውን የሚለዋወጡበት እና መረጃ በቀላሉ ተደራሽ የሚኾንበት የመገናኛ አማራጭ ነው። ይህ የመገናኛ አማራጭ በርካታ ጥቅሞችን የሚሰጥ ቢኾንም ያልተገደበ አጠቃቀም ይስተዋልበታል። ያልተረጋገጠ መረጃ የሚሰራጭበት እንደኾነም ይነሳል። ከዚህ አንጻር የማኅበራዊ ሚዲያ የላቀ ጥቅም ቢኖረውም በአግባቡ መጠቀም ካልተቻለ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በርካታ የተሳሳቱ መረጃዎች ሲሰራጩ ይስተዋላል። የተዛቡ መረጃዎች በመሠራጨታቸውም አደገኛ ውጤቶችን እያስከተለ ይገኛል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ መረጃዎችን ተጠቅሞ የመረጃ ምንጭ አለመጥቀስ እና ለመጀመሪያ ደረጃ ምንጭ ዕውቅና ወይም ዋጋ አለመስጠት ከሚዲያም ኾነ ከጋዜጠኝነት መርህ ያፈነገጠ ድርጊትም ነው።

በቅርቡ ካጋጠሙ የሀሰት የመረጃ ስርጭቶች መካከል እንኳን ብናነሳ ከሰሞኑ በሰው ሠራሽ አስተውሎት በተቀነባበረ መልኩ ጣናነሽ ቁጥር ፪ ወደ ጣና ሐይቅ ሳትገባ "ገባች"፣ "ሥራ ጀመረች" የሚሉ መረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩ እየተመለከትን ነው። ይህ መረጃም የተሳሳተ መረጃ ነው።

እነዚህን ለአብነት አነሳን እንጂ ሌሎችም በዚህ ዘገባ ያልተካተቱ የተሳሳቱ መረጃዎች ሲዘዋወሩ መመልከት በማኅበራዊ ሚዲያ መንደር የተለመደ ክስተት እየኾነ መጥቷል።

በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል መምህርት ሕይወት ዮሐንስ ሀሰተኛ መረጃዎች በሰው ሠራሽ አስተውሎት እየተቀናበሩ የሚሰራጩ መረጃዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ከሩቅ በመኾን የግለሰቦችን ፍላጎት ብቻ ለማስረጽ ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት መኖራቸውንም አመላክተዋል። የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት የጋዜጠኝነት ሙያንም ጥያቄ ውስጥ የሚከት እየኾነ መምጣቱንም አንስተዋል።

ጉዳዩ ማኀበረሰቡን ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ለሥነ ልቦና ቀውሶች እንደሚዳርግ መምህር ሕይወት ተናግረዋል።

ተቋማትም ይሁን ግለሰቦች የመረጃ ምንጭ ሳይጠቅሱ መረጃ ማሰራጨት ተገቢው የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ክህሎት ካለመኖር የመነጨ እንደኾነ ገልጸዋል።

ተቋማት ለሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች መረጃ የማጣራት፣ የማደራጀት እና ማጋራት በተመለከተ በቂ ግንዛቤ መፍጠር ብሎም መተግበር እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

የመረጃ ምንጭ መጥቀስ መረጃው እንኳን ስህተት ኾኖ ቢገኝ ኀላፊነቱን የሚወስደው መጀመሪያ ያጋራው ሚዲያ በመኾኑ ከተጠያቂነትም እንደሚያድን ጠቁመዋል።

መረጃዎችን ከማሠራጨት እና ከማጋራት በፊት የመረጃውን ምንጭ ማጣራት፣ መረጃውን መተንተን፣ ማደራጀት እና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ መጠቀም እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል።

ማኅበረሰቡም ዘመን ያመጣውን ቴክኖሎጅ ብቻ አምኖ ከመቀበል ይልቅ በአካባቢው ስላለው ሁኔታ በቅርበት ማጣራት እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል።

በመንግሥት በኩል ቁጥጥር ከሚደረግባቸው እና ተጠያቂ ከሚኾኑ የሚዲያ ተቋማት መረጃዎችን መውሰድ እንደሚገባ መምህርት ሕይወት አስገንዝበዋል።

የእውነት ማጣራት ባለሙያ እና አሠልጣኝ አብነት ቢኾነኝ ማኅበራዊ ሚዲያ ለሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ምቹ አማራጭ እየኾነ መምጣቱን ተናግረዋል።

ሀሰተኛ መረጃ በሦስት ምክንያቶች እንደሚሰራጩ አቶ አብነት አስረድተዋል። መረጃን በማሳሳት (Mis information)፣ መረጃን በማዛባት(Dis information)፣ እና መረጃን በማደፍረስ ወይም በመበከል(Mal information) ሀሰተኛ መረጃ እንደሚሰራጭም ነው የጠቆሙት።

ማኅበረሰቡ ሐሰተኛ መረጃን በሁለት መልኩ ማጣራት እንደሚችል አንስተዋል። በመጀመሪያ መረጃውን ከተለያዩ ምንጮች በማየት ማረጋገጥ ይገባል።

በመረጃው ውስጥ የተጠቀሱትን የመረጃ አይነቶች፣ ተጓዳኝ የመረጃ አማራጮችን በማየት፣ ዝርዝሮችን እና ሕጋዊ ሰነዶች የተካተቱበት መኾኑን ማረጋገጥ አንዱ መንገድ መኾኑንም አንስተዋል።

በሁለተኛ ደረጃ የእውነታ ማጣሪያ ቴክኖሎጅዎችን እና መተግበሪያዎችን በመጠቀም ማጣራት እንደሚቻልም አስረድተዋል።

በተለይም በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተቀነባበሩ ፎቶዎችን እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ተጠቅመው የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በእውነታ ማጣሪያ መተግበሪያዎች መለየት እንደሚቻል ነው የተናገሩት።

ተቋማትም ለየራሳቸው የእውነታ ማጣሪያ አማራጮችን በመዘርጋት ትክክለኛ መረጃን ለማኀበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሩሲያ አውሮፕላን ሊያከራይ ነው የተባለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው።ባሕር ዳር: ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሩሲያ አየር መንገዶች...
06/08/2025

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሩሲያ አውሮፕላን ሊያከራይ ነው የተባለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው።

ባሕር ዳር: ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሩሲያ አየር መንገዶች አውሮፕላኖችን በኪራይ ውል እንደሚያቀርብ እንዲሁም የአውሮፕላን መለዋወጫዎችን እንደሚያቀርብ በማኀበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር የነበረው ዜና ከእውነት የራቀ መኾኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከማንኛውም ወገን ጋር ምንም አይነት ጥያቄም ኾነ ውይይት እንዳላደረግን ለሚመለከታቸው ሁሉ ለማሳወቅ እንወዳለን ብሏል አየር መንገዱ።

በተጨማሪም ከተባለው የሀሰት መረጃ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ለማከናወን ምንም አይነት እቅድም ኾነ ፍላጎት የለንም ሲል አየር መንገዱ ግልጽ አድርጓል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራውን የሚያከናውነው የሚመለከታቸውን ዓለም አቀፍ ሕጎችን፣ ደንቦችን እና የውል ግዴታዎችን ሙሉ በሙሉ በማክበር መኾኑን ማረጋገጥ እንወዳለን ማለቱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል ምን ይደረግ?ባሕር ዳር፡ ሐምሌ30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሀሰተኛ መረጃ ዜጎች በዕውቀት ላይ የተመሠረቱ ውሳኔዎችን የመወሰን አቅማቸውን በማቀጨጭ የዕለት ከዕለት እ...
06/08/2025

ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል ምን ይደረግ?

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሀሰተኛ መረጃ ዜጎች በዕውቀት ላይ የተመሠረቱ ውሳኔዎችን የመወሰን አቅማቸውን በማቀጨጭ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴያቸውን ያዛባል።

በአካባቢያዊ እና ሀገር አቀፍ ምርጫዎች በሚኖራቸው ተሳትፎ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳርፋል፤ እንዲኹም በማኅበረሰቦች መካከል መከፋፈልን እና መካረርን በማስፋት ለግጭት በር ይከፍታል።

በዜጎች የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ እና በማኅበረሰቦች መስተጋብር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድረውን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት መረጃ አጣሪዎች ጥረት የሚያደርጉ ቢኾንም ችግሩ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ እና ዘለቄታዊ መፍትሄ ለመስጠት የሲቪክ ድርጅቶች፣ የማኅበረሰብ ትስስር መድረኮች እና መንግሥት ተቀናጅተው የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል።

ዜጎች ስለሚዲያ እና ስለመረጃ ያላቸውን ንቃት እና ግንዛቤ ማሳደግ ሀሠተኛ መረጃ የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት ለመግታት አይነተኛ መፍትሄ ነው። ንቃት እና ግንዛቤ ያላቸው ዜጎች ትክክለኛ መረጃ ከየት ማግኘት እንዳለባቸው ያውቃሉ።

ለሀሠተኛ መረጃ ያላቸውን ተጋላጭነት ይቀንሳሉ። ይህም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲወስኑ ያስችላቸዋል። በዚህ ረገድ የሲቪክ ድርጅቶች ጉልህ ሚና መጫወት ይችላሉ።

የሲቪክ ድርጅቶች የተለያዩ ስልቶችን በመንደፍ እና ከተቋማት ጋር በመቀናጀት ዜጎችን የማንቃት እና የማስተማር ሥራ መከወን እንዲኹም ሀሠተኛ መረጃን የተመለከቱ ይዘቶች በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት ግፊት በማድረግ፣ የነቃ እና ግንዛቤ ያለው ትውልድ እንዲፈጥር የበኩላቸውን ሚና መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

ፊንላንድ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2014 ጀምሮ ሀሠተኛ መረጃን የተመለከቱ ይዘቶችን በሥርዓተ-ትምህርቷ በማካተት እና የተቀናጀ የንቃት እና የግንዛቤ ዘመቻዎችን በማካሄዷ፣ የሀሠተኛ መረጃ ተጽዕኖን በመቋቋም ረገድ በብዙዎች ዘንድ በምሳሌነት ትጠቀሳለች።

በሌላ በኩል እንደ ፌስቡክ፣ ጉግል፣ ቴሌግራም እና ትዊተርን የመሳሰሉ የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው ይታወቃል።

እነዚህን መድረኮች ትክክለኛ መረጃ የሚያሰራጩ ገጾች እና ቻናሎች በቅድሚያ የመታየት ዕድል እንዲያገኙ በማስቻል፤ ዜጎች ሀሠተኛ መረጃን ሪፖርት የሚያደርጉበትን አካሄድ ቀላል እና በሚረዱት ቋንቋ እንዲኾን በማድረግ እንዲኹም ሪፖርቶችን እና ይዘቶችን የሚከታተሉ በቂ ባለሙያዎችን በመመደብ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭት እንዲቀንስ ኅላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

በተመሳሳይ ሚዲያዎች በተቋማቸው ውስጥ መረጃ የሚያጣራ ክፍል በማቋቋም እና ጋዜጠኞቻቸው ስለ መረጃ ማጣራት ሂደት በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸው በማሠልጠን ሀሠተኛ መረጃ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን መወጣት ይችላሉ።

መንግሥት የሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል ያወጣውን ሕግ በአግባቡ እንዲፈጸም የማድረግ ኅላፊነት አለበት፡፡

ከሲቪክ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ዜጎች ስለ ሚዲያ እና መረጃ በቂ ንቃት እና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማገዝም ይጠበቅበታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

30/07/2025

የትጋት ምልክት!

የጥንቃቄ መልዕክት፦ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሀሰተኛ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች።ካናዳን ጨምሮ ሕጋዊ የሥራ ስምሪት የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተገባባቸው የ...
27/07/2025

የጥንቃቄ መልዕክት፦

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሀሰተኛ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች።

ካናዳን ጨምሮ ሕጋዊ የሥራ ስምሪት የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተገባባቸው የተለያዩ ሀገራት ለሥራ እንልካለን የሚሉ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተዘዋወሩ ይገኛል፡፡

ይህም ገንዘብ ከማጭበርበር ባለፈ ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የጉልበት ብዝበዛ፣ ፆታዊ ጥቃትና መሰል የከፋ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚዳርግ ነው። በመኾኑም ሁሉም ጥንቃቄ እንዲያደረግ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሳስቧል።

በዚህ መሠረት፦

👉ኢትዮጵያ ካናዳን ጨምሮ ከየትኛውም የአውሮፓ ሀገር ጋር የሁለትዮሽ የሥራ ስምሪት ስምምነት የላትም።

👉የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለየትኛውም የጉዞ ወኪል ወይም ኤጀንሲ የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተገባባቸው ሀገራት ዜጎችን ለሥራ እንዲያሰማራ የሰጠው ውክልናም ኾነ ፍቃድ የለም፤

ሕጋዊ ሥራ ስምሪት የሚሰጥባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሕጋዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ለመዘርጋት ባደረገው ጥረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሀገራት ጋር ሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

እነዚህም 👇

👉ሳዑዲ አረቢያ
👉የተባበሩት አረብ ኤሚሬት
👉ዮርዳኖስ
👉ሊባኖስ
👉ኳታር እና
👉ኩዌት መኾናቸው ተጠቅሷል።

ሀሰተኛና አጭበርባሪ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች ዋነኛ መለያቸው ምንድን ነወ?

👉የቅድሚያ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ ይጠይቃሉ (ለቪዛ፣ ለሥራ ማስኬጃ፣ ለህክምና እና ሌሎች በሚል።

👉ለቀላል ሥራዎች አማላይ ጥቅማ ጥቅም እና በከፍተኛ የደመወዝ መጠን እንደሚያስቀጥሩ ቃል ይገባሉ።

👉ፈጣን ውሳኔዎችን እንዲያደርጉ ግፊት ያደርጋሉ።

👉ሀሰተኛ የሆነና ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተሰጠ ፈቃድ ወይም ውክልና አለን በሚል ሰነዶችን ያሳያሉ።

👉በተለያዩ የውጭ ሀገር ቁጥሮች እየደወሉ አጭበርባሪነታቸው እንዳይታወቅ ጥረት ያደርጋሉ።

👉ወጥመዳቸው ውስጥ ያስገቧቸውን ዜጎች በአካውንት ብር እንዲያስገቡ ካደረጉ በኋላ አድራሻቸውን ይሰውራሉ።

ሕጋዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት እንዴት ማግኘት ይቻላል?

👉በየትኛውም ሀገር ሕጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመኾን በመጀመሪያ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት lmis.gov.et መመዝገብ።

👉የሚሰጠውን ሥልጠና መውሰድና ብቃትዎን በምዘና ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

ለጥንቃቄ፦ በድምጽ ጥሪ አማካኝነት የሚፈጸም የሳይበር ጥቃት፦ባሕር ዳር: ሐምሌ09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቪሺንግ(Vshing) መረጃ በማጥመድ ከሚፈጸሙ የጥቃት አይነቶች አንዱ ነው። በድምጽ...
16/07/2025

ለጥንቃቄ፦

በድምጽ ጥሪ አማካኝነት የሚፈጸም የሳይበር ጥቃት፦

ባሕር ዳር: ሐምሌ09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቪሺንግ(Vshing) መረጃ በማጥመድ ከሚፈጸሙ የጥቃት አይነቶች አንዱ ነው። በድምጽ ጥሪ አማካኝነት የሚፈጸም የጥቃት ዓይነት ነው።

አጭበርባሪዎች ሕጋዊ አካል መስለው ስልክ በመደወል የግለሰቦችን የግል መረጃዎች፣ የይለፍ ቃሎች፣ የክሬዲት ካርድ ቁጥሮችን እና ሌሎች መሰል ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመመንተፍ ይህን የጥቃት አይነት ይጠቀማሉ።

የዚህ አይነት ማጭበርበር በእውነተኛ ሰዎች ወይም አስቀድሞ በተቀዳ ሮቦ-ኮሎች (robocalls) የሚፈጸም ነው።

በመኾኑ ከማያውቁት አካል ለሚደረግ የስልክ ጥሪ የትኛውንም መረጃ ከመስጠት መቀጠብ እንደሚገባ ከኢንሳ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

እየተስፋፋ ያለዉ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን የሀ...
19/06/2025

እየተስፋፋ ያለዉ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው።

ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን የሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግርን አስመልክቶ ለሦስተኛ ጊዜ በተቋሙ በወጣዉ ጥናታዊ ሪፖርት ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አማካሪ ታምራት ደጀኔ በሀገሪቷ እየተስፋፋ ያለዉ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብለዋል።

በመኾኑም የአገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች የአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገዋል።

ኩባንያዎች የሚሰጧቸዉን አገልግሎቶች የሀገሪቷን ብሔራዊ ጥቅም ባማከለ መልኩ ሊኾን እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ማኅበራዊ ሚድያ ማንኛውንም ይዘት በአነስተኛ ዋጋ፣ በፍጥነት እና በቀላሉ አዘጋጅቶ፣ ማንነትን ሳያሳውቅ ለማሰራጨት ዕድል የሚፈጥር በመኾኑ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ጥናቱ አመላክቷል፡፡

በመግለጫዉ ላይ በሕግ አውጭው ክፍል የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የሚረዳ የፖሊሲ እና ማኅበራዊ ሚዲያን የሚመራ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ መኾኑ ተነስቷል።

የማኅበራዊ ሚዲያ አቅራቢ ኩባያዋች በሀገሪቱ ለሚሰጡት አገልግሎት ለተጠቃሚዎች የአቅም ግንባታ ሥራ መሥራት እንዳለባቸው እንዲኹም በሀገሪቱ ቅርንጫፎቻቸውን መክፈት እንዳለባቸው ተነስቷል።

የሀሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች ዋነኛ ምንጮች ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፤ የመገናኛ ብዙኅን እና ግለሰቦች፤ የሃይማኖት ተከታዮች እና ፖለቲከኞች መኾናቸው ጥናቱ ማረጋገጡም ተነስቷል።

ጥናቱ አምስት የማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መሰረት በማድረግ የተጠና መኾኑን የገለጹት አማካሪዉ በጥናቱ ከ2000 በላይ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ ይዘቶች ላይ የናሙና ግምገማ ተደርጓል።

ከነዚህ ውስጥ 1995 መረጃዎች ተተንትነዋል፤ በቀጣይ ሁሉንም የመገናኛ ብዙኅን አዉታሮችን ተደራሽ የሚያደርግ ጥናት እንደሚጠና ተናግረዋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

ምንም ዓይነት የነፃ ትምህርት ዕድል እየሰጠ አለመኾኑን የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። ባሕር ዳር:ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምንም ዓይነት የነፃ ትምህርት ዕድል እየሰጠ አለመኾኑን...
24/04/2025

ምንም ዓይነት የነፃ ትምህርት ዕድል እየሰጠ አለመኾኑን የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።

ባሕር ዳር:ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምንም ዓይነት የነፃ ትምህርት ዕድል እየሰጠ አለመኾኑን የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ባወጣው መረጃ በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ነፃ የትምህርት ዕድል እንሰጣለን በማለት በሀሰተኛ መረጃ ገንዘብ የሚሰበስቡ እንዳሉ ማወቁን ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው ምንም ዓይነት የነፃ ትምህርት ዕድል እንደሌለ አውቃችሁ በተሳሳተ መረጃ ገንዘባችሁን ያለአገባብ እንዳታባክኑ በጥብቅ እናሳውቃለን ነው ያለው በማሳሰቢያ መልዕክቱ።

ከሀሰተኛ መረጃ መጠንቀቅ እንደሚገባ ዩኒቨርሲቲው አሳሳስቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

ከውስጥ አዋቂዎች ጋር የተያያዙ ዋና ዋና  የሳይበር የጥቃት ስጋቶች:- ባሕር ዳር: ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ከውስጥ አዋቂዎች ጋር የተያያ...
24/04/2025

ከውስጥ አዋቂዎች ጋር የተያያዙ ዋና ዋና የሳይበር የጥቃት ስጋቶች:-

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ከውስጥ አዋቂዎች ጋር የተያያዙ ዋና ዋና የሳይበር ጥቃት ስጋቶች ያላቸውን ጉዳዮች አጋርቷል።

ተቋማት ብዙውን ጊዜ ጠቃሚ ሀብቶችን ከጥቃት ለመጠበቅና በአግባቡ ለማሥተዳደር ለተወሰኑ አካላት ሚስጥራዊ መረጃዎችን የማግኘት እድል ለውስን ሠራተኞች ይሰጣሉ።

ይህን መብት ያገኘ አንድ ሠራተኛ ግልጽ ባልሆነ የሥራ ምክንያት ከተሰጠዉን መብት በላይ ለመጠቀም ከሞከረ፣ ይህ አይነቱ ሁኔታ ምናልባት የውስጥ አዋቂ ስጋት ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል። የውስጥ አዋቂዎች ጋር የተያያዙ የጥቃት ስጋቶች ያላቸውንም የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር አሳውቋል።

👉የመረጃ ምዝበራና ጥሰት

👉የአዕምሮአዊ ንብረት ስርቆት

👉የተቋምን መረጃና የመረጃ ሥርአትን ማበላሸት

👉የገንዘብና ተያያዥ ጉዳዮች ማጭበርበር

በውስጥ አዋቂዎች እንዲህ አይነት ችግሮች እንዳይፈጠሩ ጥንቃቄ ማድረግ እና መከታተል ይመከራል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ለጥንቃቄ፦ በድምጽ ጥሪ አማካኝነት የሚፈጸም የሳይበር ጥቃት፦ባሕር ዳር: ሚያዝያ/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቪሺንግ(Vshing) መረጃ በማጥመድ ከሚፈጸሙ የጥቃት አይነቶች አንዱ ነው። በድምጽ ...
22/04/2025

ለጥንቃቄ፦ በድምጽ ጥሪ አማካኝነት የሚፈጸም የሳይበር ጥቃት፦

ባሕር ዳር: ሚያዝያ/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቪሺንግ(Vshing) መረጃ በማጥመድ ከሚፈጸሙ የጥቃት አይነቶች አንዱ ነው። በድምጽ ጥሪ አማካኝነት የሚፈጸም የጥቃት ዓይነት ነዉ።

አጭበርባሪዎች ሕጋዊ አካል መስለዉ ስልክ በመደወል የግለሰቦችን የግል መረጃዎች፣ የይለፍ ቃሎች፣ የክሬዲት ካርድ ቁጥሮችን እና ሌሎች መሰል ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመመንተፍ ይህን የጥቃት አይነት ይጠቀማሉ።

የዚህ አይነት ማጭበርበር በእውነተኛ ሰዎች ወይም አስቀድሞ በተቀዳ ሮቦ-ኮሎች (robocalls) የሚፈጸም ነው።

በመኾኑ ከማያዉቁት አካል ለሚደረግ የስልክ ጥሪ የትኛዉንም መረጃ ከመስጠት መቀጠብ እንደሚገባ ከኢንሳ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Address

Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አሚኮ እውነታ ማጣሪያ AMECO Fact Check posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አሚኮ እውነታ ማጣሪያ AMECO Fact Check:

Share