Shola Media

Shola Media እንኳን ወደ Shola Media በሰላም መጣችሁ።ሰበር እና ወቅታዊ መረጃዎችን ማዳመጥ ከፈለጋችሁ ቤተሰብ ይሁኑ ስለመጣችሁ እናመሠግናለን። subscribe and hit the bell button to be our channel member.

እንኳን ወደ Shola Media በሰላም መጣችሁ። በዚህ ቻናል ላይ በአገራችን ኢትዮጵያና በሌሎች ሀገራት የሚሠሙትን ሰበር አና ወቅታዊ መረጃዎችን ማዳመጥ ከፈለጋችሁ ሰብስክራይብ በማድረግና የደውል ምልክቱን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ ስለመጣችሁ እናመሠግናለን።
በያላችሁበት የአለም ክፍል ሰላማችሁ ይብዛ።

Well, Come to Shola media. On this channel, you'll find the latest news updates and breaking news about Ethiopia and other countries around the globe.

አስፋዉ መሸሻ አረፈጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ትላንት ማታ ማረፉ ተስምቷል::ለዘመድ ወዳጅና ለአድናቂወቹ መፅናናትን እንመኛለን።
14/01/2024

አስፋዉ መሸሻ አረፈ

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ትላንት ማታ ማረፉ ተስምቷል::

ለዘመድ ወዳጅና ለአድናቂወቹ መፅናናትን እንመኛለን።

በዲማ ወረዳ በእሳት ቃጠሎ 42 የንግድ ቤቶችና እንስሳት ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱ ተነገረ በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ ቻሞ ቀበሌ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ በ42 የንግ...
30/12/2023

በዲማ ወረዳ በእሳት ቃጠሎ 42 የንግድ ቤቶችና እንስሳት ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱ ተነገረ

በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ ቻሞ ቀበሌ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ በ42 የንግድ ቤቶችና እንስሳቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል ።

አደጋው ያጋጠመው ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ላይ ሲሆን መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት የእሳት ቃጠሎ እንደተከሰተ ተገልጿል ።

በእሳት ቃጠሎው ሆቴሎችን ጨምሮ በአጠቃላይ በ42 የንግድ ቤቶች ላይ ውድመት ሲደርስ 12 ፍየሎች ደግሞ በእሳት መቃጠላቸውን የዲማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ሃላፊ የሆኑት አ/ቶ ኡመድ ኦቶው ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በዚሁ የእሳት አደጋ የሁለት ግለሰቦች ብቻ የተቀመጠ 270 ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ ተቃጥሏል ተብሏል ። እሳቱን በቀበሌው ማዕድን ስራ የተሰማራው ኢትኖ ማይኒንግ ኩባንያ እና ፌዴራል ፖሊስ ከህብረተሰብ ጋር በመሆን ባያጠፉት ከዚህ የከፋ ጉዳት ያደርስ ነበር ተብሏል ።

የቻሞ ቀበሌ አስተዳደር ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማሰባሰብ ከማህበረሰቡ የተውጣጣ ኮሚቴ ለማዋቀር በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

https://youtu.be/VAbSOW0l2xE
30/12/2023

https://youtu.be/VAbSOW0l2xE

#ፋኖ አማራፋኖ ሰበር ዜናፋኖ ፋኖ ሙዚቃየአማራ ድምጽ,the voice of amhara,amharic daily news,ethiopia,a...

https://youtu.be/2UUw9XjnBGw
29/12/2023

https://youtu.be/2UUw9XjnBGw

#ፋኖ አማራፋኖ ሰበር ዜናፋኖ ፋኖ ሙዚቃየአማራ ድምጽ,the voice of amhara,amharic daily news,ethiopia,a...

  የቱሪዝም ሚኒስቴር አንድ ካልሲ በ450 ብር መግዛቱ በፓርላማ አስወቀሰው።የቱሪዝም ሚኒስቴር በተጋነነ ዋጋ የሚያከናውነው ግዢ መታረም እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ...
28/12/2023



የቱሪዝም ሚኒስቴር አንድ ካልሲ በ450 ብር መግዛቱ በፓርላማ አስወቀሰው።

የቱሪዝም ሚኒስቴር በተጋነነ ዋጋ የሚያከናውነው ግዢ መታረም እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የቱሪዝም ሚኒስቴርን የ2014 በጀት ዓመት ሂሳብ ኦዲት ሪፖርት መነሻ በማድረግ ይፋዊ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የመንግስትን የፋይናንስ ስርዓት በመጣስ የተለያዩ ስህተቶችን ስለመፈጸሙ ተናግረዋል፡፡

ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊዎች ሶስት ሾፌሮች
ሙሉ ልብስ የአንዱ ዋጋ 32,500 ብር
የሱፍ ጨማ የአንዱ ዋጋ 13,500 ብር
ሸሚዝ የአንዱ ዋጋ 1,350 ብር
ከርቫት የአንዱ ዋጋ 1,750 ብር
ቀበቶ የአንዱ ዋጋ 1,950 ብር
ካልሲ የአንዱ ዋጋ 450 ብር

በተጋነነ ዋጋ ግዢ በመፈፀም ክፍያ መፀፈሙ ተነግሯል።

በተጨማሪም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ለሚመሩት ከቤቶች ኮርፖሬሽን የተሰጣቸውን ቤት ለማደስ ከ400ሺ ብር በላይ መውጣቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ህግን ያልተከተለ ነው ሲሉ ተችቷል።

ምንጭ Fast Mereja page

የድሮን ጥቃት ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ተፈጽሞ ሰዎች ተገደሉ መባሉን ሮይተርስ ዘገበ!ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን ምዕራብ 200 ኪሎ ሜትር ግድም በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን  ...
28/12/2023

የድሮን ጥቃት ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ተፈጽሞ ሰዎች ተገደሉ መባሉን ሮይተርስ ዘገበ!

ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን ምዕራብ 200 ኪሎ ሜትር ግድም በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የባሮ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ሰኞ ዕለት የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዛሬ ዘገበ።

በጥቃቱ አምስት መቁሰላቸውንም የዜና ምንጬ አክሏል ። ዶይ ቸቬለ (DW) በዞኑ ልዩ ስሙ ባሮ በሚባል ስፍራ ሰኞ እለት የእምነት ተቋም ላይ ተፈጸመ በተባለ የሰው አልባ ጢያራ (ድሮን) ጥቃት በትንሹ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ማስታወቁን ትናንት ዘግቦ ነበር።

የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው በቤተክርስቲያኑ ቅጽር ግቢ ከመስክ ላይ በቆሎ በሚሰበስቡ ሰዎች ላይ መሆኑን ሮይተርስ ሁለት የዐይን እማኞች እና አንድ የፖለቲካ ፓርቲን ጠቅሶ ዛሬ ዘግቧል። ስለ ጥቃቱ የተጠየቁት የመንግስት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ «ፍጹም ሐሰት» ማለታቸውን የዜና ምንጩ አክሏል። በሰው አልባ ጢያራ ተገደሉ ከተባሉት ስምንት ሰዎች መካከል ሁለቱ ዲያቆናት፤ ሁለቱ የቤተክርስቲያኒቱ ኪቦርድ ተጨዋቾች እና አንድ ዘማሪ ይገኙበታል ብሏል ሮይተርስ።

«አንዳች እንግዳና አስፈሪ ድምፅ ሰማሁ» ሲሉ ለሮይተርስ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የዐይን እማኝ፦ «በበቆሎ ማሳው ውስጥ የተበጣጠሱ ሰውነቶች እና ሥጋዎችን ተበታትነው ዐየሁ» ብለዋል ። ሮይተርስ ለጠቅላይ ሚንሥትር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ሥዩም፤ ለኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ ኃይሉ አዱኛ እና ለመከላከያ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄ ቢያቀርብም ወዲያው ምላሽ አለማግኘቱን አትቷል ።

ኦሮሚያ ክልል በቾ ወረዳ በርካታ ተሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተቃጠሉ‼️(17/04/2016)ከምሽቱ 5:30  ጀምሮ ሰበታ ከተማን ወጣ ብሎ በሚገኘው በቾ ወረዳ አዋሽ ቡኔ ቀበሌ ዋና መንገድ ወደ ...
28/12/2023

ኦሮሚያ ክልል በቾ ወረዳ በርካታ ተሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተቃጠሉ‼️
(17/04/2016)ከምሽቱ 5:30 ጀምሮ ሰበታ ከተማን ወጣ ብሎ በሚገኘው በቾ ወረዳ አዋሽ ቡኔ ቀበሌ ዋና መንገድ ወደ አዲስ አበባ እና ወሊሶ አቅጣጫ ሲጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ሰባቱ ተቃጥለዋል።

በኮድ 2 ፒካፕ ወደ ጅማ አቅጣጫ ይጓዙ የነበሩ 4 ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የዋሱ መሀመድ ቴሌግራም ቻናል ቤተሰቦች ከስፍራው መረጃውን አድርሰዋል።

በቅርብ የነበሩ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ከጥቃቱ በኋላ በቦታው ላይ መድረሳቸውን እና መንገዱ አሁን ላይ ክፍት መሆኑን ገልፀዋል። አሽከርካሪዎች የመንገዱን ደህንነት የበለጠ አረጋግጣችሁ ብትጓዙ እመክራለሁ።
Wasu

የአምባው ኦፕሬሽን በሻለቃ ሀብቴ ወልዴ የሚመራው ቴዎድሮስ ብርጌድ የተሳካ ኦፕሬሽን አካሂዷል። በኦፕሬሽኑም በወገራ አንባጊዮርጊስ ከተማ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ታጉረውበት የነበረው ፖሊስ ...
28/12/2023

የአምባው ኦፕሬሽን

በሻለቃ ሀብቴ ወልዴ የሚመራው ቴዎድሮስ ብርጌድ የተሳካ ኦፕሬሽን አካሂዷል።

በኦፕሬሽኑም በወገራ አንባጊዮርጊስ ከተማ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ታጉረውበት የነበረው ፖሊስ ጣቢያ ተሰብሮ ታጉረው የነበሩት ተለቀዋል። 200 ክላሺንኮቭ እና አንድ ብሬን ከበርካታ ተተኳሽ ጋር ገቢ ተደርጓል። በዚህ ኦፕሬሽን እጅ አንሰጥም ያሉ 5 ፖሊሶች እና አንድ ሚሊሻ እርምጃ ተወስዶባቸዋል። ይህ ኦፕሬሽን እንዲሳካ ትብብር ያደረጉ የሚሊሻ እና የፖሊስ አባላት ስላደረጋችሁት ሁለንተናዊ ትብብር ፋኖ አመስግኗችኃል።

ኦፕሬሽኑ 15 ደቂቃ የፈጀ ሲሆን። ኦፕሬሽኑ የተካሄደው ከሌሊቱ 8 ነው። በአሁኑ ሰዓት ነበልባሎቹ ቦታቸውን ይዘዋል። በሌላ በኩል ወደ እንቃሽ በመውረድ በህዝብ ላይ ሽብር የፈጠረው የጠላት ሀይል መውጫ መግቢያ ጠፍቶታል። እንቃሽና አጅሬ ጃኖራ መልካ ምድሩ ለወገን ሀይል ሁሌም እንደ ወገነ ነው። ዝርዝር ከብርጌዱ አመራሮች ይቀርባል።

ድል ለህዝባችን‼️

https://youtu.be/b8PAOlXTR_A
28/12/2023

https://youtu.be/b8PAOlXTR_A

#ፋኖ አማራፋኖ ሰበር ዜናፋኖ ፋኖ ሙዚቃየአማራ ድምጽ,the voice of amhara,amharic daily news,ethiopia,a...

ብልጽግና በአዲስ አበባ መርካቶና አካባቢው ከፍተኛ የጅምላ አፈሳ እያካሄደ መሆኑን የማዋከቡ ሰለባዎች ተናገሩ።የአገዛዙ ብረት ለበስ ፖሊሶች ሰሞኑን በመርካቶ፤ ተክለሃይማኖት፤ አሜሪካን ግቢ፤ ...
27/12/2023

ብልጽግና በአዲስ አበባ መርካቶና አካባቢው ከፍተኛ የጅምላ አፈሳ እያካሄደ መሆኑን የማዋከቡ ሰለባዎች ተናገሩ።

የአገዛዙ ብረት ለበስ ፖሊሶች ሰሞኑን በመርካቶ፤ ተክለሃይማኖት፤ አሜሪካን ግቢ፤ ጎጃም በረንዳና አካባቢው ባሉ ሰፈሮች ከፍተኛ የሆነ የጅምላ አፈሳ እያካሄዱ መሆኑን በአገዛዙ ታጣቂዎች መዋከብ የደረሰባቸው የከተማ ነዋሪዎች ለሮሃ አረጋግጠዋል፡፡
በተለይም የንግዱ ማህበረሰብ አካላት የሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በእነዚህ የንግድ እንቅስቃሴ በሚበረታባቸው ሰፈሮች በድንገት ከበባ የሚፈጽሙ የብልጽግና የጸጥታ ሃይሎች እስካሁን ለምን እንደሆነ ግልጽ ባልተደረገ ምክንያት የጅምላ አፈሳ እያደረጉ ሰዎችን ወደ እስር እየወሰዱ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡

አንድ መርካቶ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ለሮሃ በሰጠው ቃል ‹‹ድንገት የሰፈሮቹን መውጫና መግቢያ መንገዶች ይዘጋሉ፤ ከዚያ እዚያ አካባቢ እንቅስቃሴ የሚያደርግን ሰው ሁሉ አፍሰው ጭነው ይወስዳሉ›› ብሏል፡፡

‹‹ባለፈው ሀሙስ በድንገት ፖሊሶች መጥተው እኔና አጠገቤ የነበሩትን ነጋዴዎች ወሰዱን›› የሚለው አስተያየት ሰጪው ‹‹ከዚያ በኋላ ንግድ ፈቃድ አድሰሃል ወይ፡ ቲን ነምበር አለህ ወይ እያሉ አዋከቡኝ፤ አለኝ ላሳያችሁ ብልም ቀኑን ሙሉ አሰሩኝ›› ሲል አብራርቷል፡፡
ይህ እስርና ማዋከብ ሁሉ ነገሩ ከእጁ የወጣበት ብልጽግና በአዲስ አበባው ነዋሪ ላይ እየወሰደው ያለው የመጨረሻ የማስፈራሪያ እርምጃ መሆኑን የሚገልጹት የጥቃቱ ሰለባዎች የመንግስትነት አቅሙ የተገፈፈው ብልጽግና በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ቅቡልነት ለማግኘት ሲል የተጠቀመው ስልት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

‹‹ነጋዴው ለቢዝነሱ እንደሚጨነቅ ስለሚያውቁ ብልጽግናን በግልጽ ከተቃወመ አስከፊ ነገር እንደሚደርስበት ለማስፈራራት የሚጠቀሙት ዘዴ ነው›› ብለዋል አንድ አስተያየት ሰጪ ለሮሃ በሰጡት ቃል፡፡
ብልጽግና ከአዲስ አበቤው ልብ ውስጥ ከወጣ ዓመታት ቢቆጠሩም ግማሹን በእስርና በማዋከብ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለውን ደግሞ በጥቅም ለመደለል በመሞከር ዕድሜውን ለማራዘም እየጣረ ይገኛል፡፡
ምክንያቱም አዲስ አበባ ላይ የሚነሳ ህዝባዊ ተቃውሞ መጨረሻውን እንደሚያፈጥንበት ተገንዝቧል፡፡

https://youtu.be/gLAjhL6XFkI
27/12/2023

https://youtu.be/gLAjhL6XFkI

#ፋኖ አማራፋኖ ሰበር ዜናፋኖ ፋኖ ሙዚቃየአማራ ድምጽ,the voice of amhara,amharic daily news,ethiopia,a...

 በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን...
27/12/2023



በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን በክልሉ ያለው የጸጥታ ችግር በተማሪዎች ምዝገባ ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል ብለዋል።

ክልሉ 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማር ሲገባው ያን ማድረግ አለመቻሉን ኃላፊው ተናግረዋል።

ከሁለት ሚሊዮን በላይ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች መኖራቸውን የገለፁት ኃላፊው ፤ መማር የሚገባቸው ተማሪዎች የትምህርት ዕድል እንዳያገኙ መደረጉን አመልክተዋል።

በጸጥታው ችግር ምክንያት ሁለት ሺህ በሚጠጉ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ከመማር ማስተማር ሥራ ውጪ መሆናቸውን ገልፀዋል። ይሁን እንጂ መምህራኑ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ ባለው ግጭት "ወደ 42 ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዳቸውንም" ጠቁመዋል።

[ዘገባው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ነው]

Address

Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shola Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Shola Media:

Share