22/05/2026
ሶስቱ እነሴዎች በጎጃም‼️
~~~~~~~~~
ጎጃም ካሉት 35 ያህል ወረዳዎች በምስራቁ ክፍል የሚገኙት የዳዊት ዘር የእሴ ዘር ናቸውና እነብሴ ሳር ምድር፣ጎንጃ ሲሶ ነሴ እና ሁለት እጁ እነሴ ይባላሉ፡፡
-------
ጎዛሞ፣ጎዣም፣ጎጃም ሀይማኖትን ቀድም የተቀበለ ህዝብ ማለት ነው- የግዕዝ ሰዋሰው ሲረባ፡፡ምክኒሃቱም በመርጡለ ማርያም፣በጣና ቂርቆስ እና በፈለገ ጊዮን (የአባይ መነሻ) የሀይማኖት መጀመሪያ፣የቅዱሳን መናሃሪያ፣የትውፊት ና የስራዓት መፈፀሚያ ሁኖ አገልግሏል ፡፡ገነት የአባይ ምንጭ ናት፡፡ገነት ጣና ገዳማት ውስጥ ነው የሚሉት የመፅሐፍ ቅዱስ ተመራማሪዎች ለዚህ ይመስላል።
-------
ጎጃም ቅድስት ድንግል ማርያምን በጣና ቂርቆስ፣ የሙሴ ህግን፣ትዕዛዘ ሰንበትን ቀድሞ ተቀብሏል፡፡በእርግጥ የኤርትራን ባህር የከፈለው እስራኤላዊው ሙሴ ሚስቱ ጎጃሜ ነበረች፡፡አማቱም ካህኑ ዮቶር የስልጣን እርከን በማውጣት ሀይማኖት ና ሃገር እንዴት እንደሚመራ ለሙሴ ምክር ለግሶ እንደነበርም ድርሳናት ይመሰክራሉ፡፡
------------
ቅድስት ድንግል ማርያምም አማኑኤል ይዛ በጣና ገዳማት አርፋለች፡፡ ደሸት የሚባለው የዘር ግንድም ምንጩ ጎጃም አባይ ና ጣና አካባቢ ነው፡፡የደሸት የልጅ ልጅ ማራ ይባላል፡፡ማራ የአማራን ነገድ ይወክላል፡፡በሱባ ማራ(አ) ቋንቋ "እውነተኛ ብርሃን" ማለት ነው፡፡ለዚህም ከደሸት ዘር በመነሳት ሃማራ፣አህማራ፣አማራ ነፃ ህዝብ፣ሩህሩህ ህዝብ፣የእውነተኛ የብርሃን ምንጭ..... ተብሎ ይተረጎማል - ዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ፡፡ምናልባትም ለዚህ ሳይሆን አይቀርም አንዳንዶች አማራን እንደ ሀይማኖት፥ የሚቆጥሩት፡፡
------------
አማራ የሚለው የትልቅ ነገድ መጠሪያ ደምቆ
በብዛት መጠራት የጀመረው ከ 1270 ዓም አፄ ይኩኖ አምላክ ንጉሰ አማራ ብሎ ከነገሰ በኃላ ነው፡፡ይሁን እንጂ፣ከንጉስ ይኮኖአምላክ ቀድሞም ይሁን ዘግይቶ የአማራ ንጉስ ሁኖ የወጣ መሪ በታሪክ የለም፡፡
ነገስታቱ ከአማራው ቢገኙም ከየመን እስከ
እየሩሳሌም፣ከኩሽ ሱዳን) እስከ ሊቢያ ድረስ ኢትዮጵያውያን ማስፋት የፖለቲካ እሳቤያቸው መዳረሻ ነበር፡፡
-------
አማራ አማኝ ቢሆንም የሀይማኖት መጠሪያ ሳይሆን ከ 3ሺ ዓመት ቀድሞ የቆየ ነባር፣ሀይማኖተኛ እና ጦረኛ ነገድ (ብሄር) ነው - (የአማራ ባህል በዶክተር አንተነህ አወቀ) የአማራው አንድ አካል የሆነው ጎጃም እንደ ሩቅ ምስራቅ እስያ የሃይማኖት መካን (ቦታ) ነው፡፡
------
መርጡለ ማርያም ገዳም
----------
ከህገ ኦሪት ጀምሮ ሀይማኖታዊ ግልጋሎት ሰጥቷል፡፡ በ 333 ዓም በሁለቱ አክሱማዊ ወንድማማቾች በአብርሃ እና በአፅብሃ በወርቅ እና በእንቁ ተገነባ፡፡ በመጀመሪያው ጳጳስ በአቡነ ከሳቴ ብርሃን ተባርኮ ፣ከአክሱም ፅዮን ቀጥሎ የኢትዮጵያ ዕድሜ ጠገብ ገዳም ነው--ርዕሰ ሩዕሳን መርጡለ ማርያም ገዳም፡፡
መርጡለ ማርያም (የማርያም አዳራሽ) ገዳም የሃይማኖት መንበር ብቻ አይደለም፡፡ከአብርሃ እና አፅብሃ እስከ የይሁዳው አንበሳ ንጉስ ሀይለ ስላሴ ድረስ የነገሱ ነገስታት ያበረከቱት ስጦታ፣ ዕንቁ፣ አልባስ....በክብር ቦታውን ይዞ ይገኝበታል፡፡አፄ ሚኒሊክ ከጎጃሙ ንጉስ ተክለሃይማኖት ጋር የተፃፃፏቸው
ደብዳቤዎችን ጨምሮ ሌሎች የነገስታት ማስታወሻዎችም በመርጡለ ማርያም ገዳም ተሰንደዋል፡፡
--------
የአባይን ምንጭ ለአውሮፓ ያስተዋወቀው ጀምስ ብሩስ መፅሀፈ ሄኖክን ወደ አውሮፓ በድብቅ አስወጥቶታል፡፡ይህ መፅሐፍ ግን ዋናው መርጡለ ማርያም ገዳም ውስጥ አለ፡፡ኢትዮጲያ ከ 6 በላይ የሀይማኖት መፅሀፍትን በዮኔስኮ አስመዝግባለች፡፡ 6ቱም መርጡለ ማርያም ገዳም ውስጥ ይገኛሉ፡፡ለአብነት፣መፅሀፈ ሄኖክ፣ግብረህማማት፣መፅሀፈ ቅዳሴ፣አርባይቱ ወንጌል።
መርጡለ ማርያም ገዳም በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ከአዲስ አበባ 336 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቆ ይገኛል፡፡
የእነሴ ወረዳዎች እነብሴ ሳር ምድር፣ጎንጃ ሲሶነሴ እና ሁለት እጁእነሴ ናቸው።
Source፥የመርጡለ ማርያም ገዳም ታሪክ