E-Tech Media

E-Tech Media | የትምህርት መጨረሻው የጠፋብንን ማንነት ማግኘት ነው !

ጌትሽ ማሞ (ተቀበል ቁ.1 & 2) ለአዲስ አበቤ የደረሰው ቅኔእንዴው መላ መላ መላው ሳይጠፋሽአየሁሽ ለሸገር ግራ ሲገባሽስታውቂው መንገዱን የአዲስን ጎዳናግራ መጋባትሽ አይመስልም የጤናአሞሻል...
12/08/2022

ጌትሽ ማሞ (ተቀበል ቁ.1 & 2) ለአዲስ አበቤ የደረሰው ቅኔ

እንዴው መላ መላ መላው ሳይጠፋሽ
አየሁሽ ለሸገር ግራ ሲገባሽ
ስታውቂው መንገዱን የአዲስን ጎዳና
ግራ መጋባትሽ አይመስልም የጤና
አሞሻል ሰማሁኝ እግዜር ይማርሽ
አንቺ ሰው አታጭም የሚያስታምምሽ
አይዞሽ ይተውሻል በአንቺ ብቻ አይደለም
ዘንድሮ ያልተነካ ያልታመመ የለም
አንቺ እጅሽ ሰፊ ነው የለም ሚጎልሽ
ለእኛ ህልም እንጀራ ወግ እየጋገርሽ

አንቺ ግፍ አትፈሪም በእኛ ቤት ሆነሽ
ዳንቴል ትሰሪያለሽ ለዚያኛው ቤትሽ
ሐገር ትሰሪያለሽ ለዚያኛው ቤትሽ

ድገምልኝ ድገምልኝ....
.. አለ ጌትሽ ማሞ

እንኳን ደስ አለሽ እማማ ኢትዮጵያ !!በዚህ ደስ የማይለው ሰይጣን ብቻ ነው።
12/08/2022

እንኳን ደስ አለሽ እማማ ኢትዮጵያ !!

በዚህ ደስ የማይለው ሰይጣን ብቻ ነው።

ዛሬ በሶስቱ መንግስታት (መንግስቱ ሐ/ማርያም፣ መለስ ዜናዊና ዶ/ር አብይ አህመድ) ጊዜ ህዝብ የተናገራቸውን ስነ ቃሎችን እንካችሁ ብለናል🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴⛏ በጓድ መንግስቱ ኃይለ...
02/08/2022

ዛሬ በሶስቱ መንግስታት (መንግስቱ ሐ/ማርያም፣ መለስ ዜናዊና ዶ/ር አብይ አህመድ) ጊዜ ህዝብ የተናገራቸውን ስነ ቃሎችን እንካችሁ ብለናል
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

⛏ በጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም ጊዜ

መንጌ ኃይለማርያም የብረት ምሰሶ፤
የጠፋውን ሀገር አቀናው መልሶ።

ስንደው በሄሊኮፕተር በቆሎው በጀት፤
መንጌ ኃይለማርያም የድሆች አባት።

መንጌ ኃይለማርያም አይሙት አይበላሽ፤
ለተራበው ስንዴ ለጠገበው ክላሽ።

📌 በጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ጊዜ

ደርግ ፋሽስት ነው ከወያኔ አይከፋም፤
ስልጣን ቢጥመውም ሀገር አያጠፋም።
ወያኔ እንደ ትል ነው ውስጥ ውስጡን ይበሳል
ሰርስሮ ሰርስሮ ወናውን ያስቀራል።

ስማችን ወያኔ ስድባችን ቅማላም፤
የደርግን ወታደር ነዳነው እንደ ላም።

እነ ውስኪ እራቱ እነ ክትፎ ቁርሱ፤
አሙሲት ሲተኮስ ባህርዳር ደረሱ።

ወልቃይት ታረሰ በጥቋቁር በሬ፤
እራያም ታረሰ በጥቋቁር በሬ፤
በቆሎ ብንዘራው በቀለ በርበሬ።

ኸረ ምን ታሰበ ምን ተጠረጠረ፤
ራያ ከመሀሉ በሽቦ ታጠረ፤
አላማጣ ወዳ ቆቦ ወድህ ቀረ።

🌶 በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ ጊዜ

ሙሴ መጣ ብለህ መለከት ስትነፋ፤
የመጣልህ አዳኝ ከፈርዖን ከፋ!

ኢህአዴግ ሄደና መጣ ብልፅግና፤
ኑሮም ተወደደ ረከሰ ዝምድና!

ባባቴ ቤት ጮማ እንዳልቆረጥኩበት፤
በእናቴ ቤት ጠጁን እንዳልጠጣሁበት፤
ብልፅግና መጥቶ ሹሮም አጣሁበት!

ምንጭ:- ከፌስቡክ መንደር

የቀረ ካለ ጨምሩበት

ተጻፈ በክርስቲያን ታደለ (ክሪስ)«ነገን ማየት…እጓጓለሁ!»****[ትናንት]«ኧረ ደርጉ ደርጉ ደርጉ የበለለው፣በአንድ መለኪያ አረቄ ወንድሙን ገደለው።»[ዛሬ]በጭብጨባ ብዛት ልቡ የቀለጠው፣በሰ...
31/07/2022

ተጻፈ በክርስቲያን ታደለ (ክሪስ)

«ነገን ማየት…እጓጓለሁ!»
****
[ትናንት]
«ኧረ ደርጉ ደርጉ ደርጉ የበለለው፣
በአንድ መለኪያ አረቄ ወንድሙን ገደለው።»

[ዛሬ]
በጭብጨባ ብዛት ልቡ የቀለጠው፣
በሰባራ ወንበር ወንድሙን ለወጠው።

[ለነገ ሩብ ጉዳይ]
እየጠራ ሄደ ኩል እየመሰለ፣
ነኝ እንጂ ጨዋታው ነበርሁ እንዳይደለ።

 #ሼር በማድረግ ለመልካም ሰዎች በማድረስ ተባበሩ  /Hiwetበነገራችን ላይ  #ሼር ስናደርግ መረጃው መርዳት ለሚፍልጉ ሰዎች በቶሎ ይደርሳል፣ ለድርጅቶችና ለማህበራትም ይደርሳል። በዉጭ ሃገ...
31/07/2022

#ሼር በማድረግ ለመልካም ሰዎች በማድረስ ተባበሩ /Hiwet
በነገራችን ላይ #ሼር ስናደርግ መረጃው መርዳት ለሚፍልጉ ሰዎች በቶሎ ይደርሳል፣ ለድርጅቶችና ለማህበራትም ይደርሳል። በዉጭ ሃገር ለሚኖሩ መልካም ሰዎች ይደርሳል። ታዲያ ይሔን ማድረግ ከቻልን ወንድማችንን ታደግነው ማለት አይደልም?

ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ጸሎተኛ በጻለቱ፣ በየሚዲያው ተደራሽ በማድረግ ልንረዳው ይገባል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን እነብሴ ሳርምድር ወረዳ መርጡለ ማርያም ዙሪያ ተወልዶ ያደገውና በጅማ ዩኒቨርስቲ Biomedical Engineering ተመርቆ በስራ ላይ የሚገኘው በብዙ መልካም ስራዎች ለአብነትም #መርጡለ ማርያም ካቴድራል ግንባታ #ደሴ፣ወልድያና ኮምቦልቻ ለወደሙ ተቋማት በቅርቡ በህመም ላይ እያለም #ለወይብላ ማርያም ቤተክርስቲያን ገንዘብ በማሰባሰብ እና በቦታው እየተገኘ በመደገፍ የምናውቀው ወንድማችን Temesgen GebreHiwot "የሀሞት ጠጠርና የጉበት ካንሰር አለብህ" ተብሎ በጸና ታሟል። ሆኖም #ተመስገን አሁን በባህርዳር ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምናዉን እየተከታተለ ይገኛል።

ሰዎች አይደለን በቃ ለሰው የሚኖረውን ሰው እናድነው! ከፈጣሪ በታች አለንልህ እንበለው።

ተሙን/ወልደ ሰንበትን/ ስላመመዉ ህመም በተመለከተ ባለኝ መረጃ መሰረት ህመሙ ከሀሞት ፊኛ የተነሳ ካንሰር/ክፉ እጢ/ ሲሆን ወደ ጉበቱና ወደ ሆዱ ሊምፍ ኖዶች ተዛምቷል። እናም የአልትራ ሳውንድ ምርመራ ፣የሲቲ ስካን ምርመራ የደም ምርመራ እንዲሁም ከእበጡ ተወስዶ ምርመራ ተረጋግጧል። ይሄውንም የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስቶችና ሰብ ስፔሻሊስቶች ፣የራዲዮሎጂ ስፔሻሊስቶች፣የካንሰር ስፔሻሊስቶች በሐዋሳ በአዲስ አበባ እና በባህርዳር ሆስፒታሎች አይተው ውጤቱን አረጋግጠዋል። እናም የባለሙያዎች ውሳኔ እንዲደሚከተለው ነው።
አሁን ባለበት ደረጃ ቀዶ ጥገና ለመስራት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ነው። ስለዚህ አማራጩ የካንሰር መድሃኒት/chemotherapy/ መውሰድ በመሆኑ እንዲጀምር ተወስኗል:: ነገር ግን አዲስ ግኝት በውጭ ሀገር ካለ ከሰዎች ጋር ንግግር እየተደረገ ነው። ያም ሆነ ይህ የ ኬሞትራፒ መድሃኒት ዋጋው ውድ ስለሆነ በቶሎው ብር ብናዋጣና እርሱንም ቢጀምር መልካም ነው። በእኛ ደሞዝ መታከም እንደማንችል ሁላችንም እናውቃለን። ስለዚህ ሁላችንም እንረባረብ። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ፈጣሪ እጁን እንዲዘረጋለት "ወልደ ሰንበት" እያላቹህ በፀሎታቹህ አስቡት።"

ተሙዬ ህመምህ የትዕግስትና የጽናትህን መለኪያ ፈተና አድርጎልህ ቆመህ ለምስክርነት ያብቃህ። ወላዲተ አምላክ ፈጥና ትድረስልህ። ወንድሜ እግዚአብሔር ተዓምራት ሰርቶ ወንድማችን ቆሞ ለመመስከር ያብቃው እመብርሃን የምህረት እጆቿን ትዘርጋለት።

ከታች ያለዉ የባንክ ቁጥር ለወንድማችን #ተመስገን ተብሎ የተከፈተ ጣምራ አካውንት ነው። የቻላቹህትን /የቻልነዉን እንርዳ።

CBE: 1000489167623

አሁን ባለው መረጃ የታላቋ ሃገር ኢትዮጵያ መሪ፣ የአለም የሰላም አምባሳደር ፣ የንፁሐን ጠበቃ፣ የደህንነታችን ጠበቃ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በአሁኑ ሰዓት ሚስጢራዊ በሆ...
30/07/2022

አሁን ባለው መረጃ የታላቋ ሃገር ኢትዮጵያ መሪ፣ የአለም የሰላም አምባሳደር ፣ የንፁሐን ጠበቃ፣ የደህንነታችን ጠበቃ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በአሁኑ ሰዓት ሚስጢራዊ በሆነ ሆስፒታል ህክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተሰምቷል ።

ክቡርነታቸው በሰላም ወደ ቤተ-መንግታቸው ይመለሱ ዘንድ መልካም ምኞታቹህን በጨዋ ደንብ እስኪ ተመኙላቸው...

ችግኟን ግን እየተከላቹህ

  to Stop    Day 5
24/07/2022

to Stop


Day 5

Marathon again ! ወርቁ ገቢ ሆኗል ።   ! የአለም ሪከርድም ተሰብሯል።
18/07/2022

Marathon again ! ወርቁ ገቢ ሆኗል ። ! የአለም ሪከርድም ተሰብሯል።

የ 10,000 ሜ ወንዶች ፍፃሜ አልተሳካም ። ቢሆንም ግን ጥሩ የሚባል ፍልሚያ ነበር። አይዞን በርቱልን።ለኡጋንዳስ ማን አላት?  አንድ ወርቅ ታግኝጅ። ያው ወርቁ ከአፍሪካ አልወጣም።
17/07/2022

የ 10,000 ሜ ወንዶች ፍፃሜ አልተሳካም ። ቢሆንም ግን ጥሩ የሚባል ፍልሚያ ነበር። አይዞን በርቱልን።

ለኡጋንዳስ ማን አላት? አንድ ወርቅ ታግኝጅ። ያው ወርቁ ከአፍሪካ አልወጣም።

17/07/2022



ኢትዮጵያ ዛሬም ከፍ ብላለች
በወንዶች ማራቶን ወርቅ አስገኝቷል
ሞስነት ገረመው የብር ሜዳልያ
🥇🥈
🇪🇹
እንኳን ደስ አለን!!
ይህን አስደናቂ ድል ተመልከቱ !!

1ኛ እና 2ኛ ወጥተናል ። እልልልልልልል ነው።ወይ ሰንበት
17/07/2022

1ኛ እና 2ኛ ወጥተናል ። እልልልልልልል ነው።

ወይ ሰንበት

እስኪ ሁላቹህም ቶላ ቶላ በሉ
17/07/2022

እስኪ ሁላቹህም ቶላ ቶላ በሉ

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when E-Tech Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share