Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን Amhara Media Corporation Strives for the Betterment of the Life of the People.
(1267)

የአሚኮን ሞባይል መተግበሪያ ፕሌይ ስቶር ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
���
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.AMECO.AMECOapp

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት https://www.ameco.et
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ
+251582265018

ገበያ ልማትና ደንበኞች አገልግሎት
0941272206

በኩር ጋዜጣ
0582265018

አማራ ራዲዮ
0583209919

አማራ ባሕር ዳር ኤፍ ኤም 96.9
0583208314

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም ዋና ዋና ዜናዎች፦ 👉"ዕቅዱን ማሳካት የምርጫ ጉዳይ አይደለም" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ https://www.facebook.com/share/...
24/08/2025

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም ዋና ዋና ዜናዎች፦

👉"ዕቅዱን ማሳካት የምርጫ ጉዳይ አይደለም" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

https://www.facebook.com/share/p/1CR9GTKLw8/

👉የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

https://www.facebook.com/share/p/1F8LwxXYF2/

👉ኢኮኖሚያዊ ወንጀል የፈጸሙ አካላት ጉዳያቸው ወደ ፍትሕ ቀርቦ ውሳኔ እየተሰጠ ነው፡፡

https://www.facebook.com/share/p/19xtNGgU6q/

👉በሀገራዊ ምክክሩ አካል ጉዳተኞችን በስፋት ለማሳተፍ እየተሠራ ነው።

https://www.facebook.com/share/p/1GWfZFbQW5/

👉አሚኮ ለትምህርት ዘርፉ ዐይን እና ጆሮ ኾኖ አገልግሏል።

https://www.facebook.com/share/p/1D4ArMxA54/

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

24/08/2025

፡ "ለተማሪዎች ምዝገባ ውጤታማነት ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል" የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

24/08/2025

፡ "ወደ ልማትና ዕድገት ለመሸጋገር የልማት ዕቅዱን በቁርጠኝነት መፈጸም ይገባል" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

24/08/2025

፡ "የኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎችን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን በተሠራው ሥራ ውጤት ተገኝቷል" ፍትሕ ቢሮ

24/08/2025


ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም
#አሚኮ #ዜና

"ዛሬ ፈተናዎቻችንን ተቋቁመን ልጆቻችንን ካላስተማርን ነገ የተማሩ ዜጎችን ማፍራት ሕልም ይኾንብናል" ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)  ባሕር ዳር: ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልሉን ሕዝብ የ...
24/08/2025

"ዛሬ ፈተናዎቻችንን ተቋቁመን ልጆቻችንን ካላስተማርን ነገ የተማሩ ዜጎችን ማፍራት ሕልም ይኾንብናል" ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

ባሕር ዳር: ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልሉን ሕዝብ የቆየ ታሪክ በአግባቡ እና በወጉ የሚመረምር ከተገኘ ለትምህርት ያለው አዎንታዊ አመለካከት ዘመን ተሻጋሪ የሚባል ነው፡፡ ጥንታዊ ቅርሶቹ እና ታሪካዊ ሰነዶቹ ከእውቀት አፎት የፈለቁ ለመኾናቸው ዛሬም ድረስ ሕያው ምስክሮች ናቸው፡፡

የክልሉ ሕዝብ ቱባ ባሕል እና ነባር እሴቶች የአማራ ሕዝብ የቀደመ የትምህርት እርሾ እንደነበረው ያመላክታሉ፡፡ ምሳሌያዊ ንግግሮቹ፣ አፈ ታሪኮቹ እና የትውልድ ቀረጻ ዳራዎቹ የእውቀት አሻራ የጎበኛቸው ናቸው፡፡

"የተማረ ይግደለኝ" በሚል ቀደምት ብሂሉ የሚታወቀው የክልሉ ሕዝብ ለዕውቀት ያለውን ቅርበት እና በተማረ ሰው ያለውን እምነት አጉልቶ ያሳያል፡፡ በጥንታዊ የትምህርት ሥርዓቱ ልጆቹን ገና በሕጻንነታቸው ቀያቸውን ለቅቀው እና ከወላጆቻቸው ርቀው ትምህርት እንዲቀስሙ መላኩ ከዛሬ ይልቅ በነገ ላይ የነበረውን ጽኑ እምነት አጉልቶ ያመላክታል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ የተፈጠሩ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ ችግሮች በተለይም የትምህርት ዘርፉን ክፉኛ ጎድተውት አልፈዋል፡፡ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት የነበረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በክልሉ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ የከፋ የሚባል ጉዳት አድርሰውበት አልፈዋል፡፡

በቅርቡ ደግሞ በክልሉ የተፈጠረው የእርስ በእርስ ግጭት እና ጦርነት በመማር ማስተማር ሥራው ላይ ብቻ ሳይኾን በትምህርት ተቋማት ላይም ጉዳት አድርሷል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ ኾነዋል፡፡ በርካታ የትምህርት ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ መምህራን፣ ርእሳነ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የትምህርት ዘርፉ መሪዎች ውድ የሚባል ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ይህም ወደ ኋላ ላይ ከስሜት ወደ ምክንያታዊነት፣ ከግጭት ወደ ቁጭት ለተመለሱ ሁሉ አንገት የሚያስደፋ ስህተት ኾኗል፡፡

የ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት አጀማመርን አስመልክቶ ዛሬ በቢሯቸው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ባለፉት ሁለት ዓመታት የትምህርት ዘርፉ መክፈል የማይገባውን ዋጋ ከፍሏል ይላሉ፡፡

በ2016 እና 2017 የትምህርት ዘመናት የበርካታ ሀገራትን ዜጎች ቁጥር የሚስተካከል ተማሪ ከትምህርት ገበታ እንዲርቅ ተገድዷል ነው ያሉት፡፡ በ2016 የትምህርት ዘመን 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን እና በ2017 የትምህርት ዘመን ደግሞ 4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ተማሪዎች ሳይማሩ ቀርተዋል፡፡

ለበርካታ ዓመታት የትምህርት ሥርዓታችን ስብራት በዘርፉ ምሁራን ተደጋግሞ ሲነገር ቆይቷል ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ ዛሬ ለደረስንበት ምስቅልቅል እና ፈተና የዳረገንም ትናንት መሥራት የሚገባንን በአግባቡ ባለመሥራታችን ነበር ይላሉ፡፡

ዛሬ ላይ በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚፈጠር ትንሽ ስንጥርም ዳፋው ምናልባትም ነገ ከነገ በኋላ የሚስተዋል እንደኾነ ጠቁመዋል፡፡

በ2018 የትምህርት ዘመን 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተማሪዎችን በመመዝገብ ለማስተማር ታቅዷል ያሉት ቢሮ ኀላፊዋ እቅዱ ክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ያሳለፈውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ በመኾኑ ምክንያታዊ ነው ብለዋል፡፡

ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ወደ ትምህርት ቤት ያልመጡ ነገር ግን እድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ሕጻናት እና ላለፉት ሁለት ዓመታት ፈተና ያልወሰዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ከተማሪ ቁጥር በላይ ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት እንደተሰጠም ተነስቷል፡፡ በዚህ ዘመን ተማሪዎች ቢቻል የቴክኖሎጂ ፈጣሪ መኾን ይኖርባቸዋል፤ ካልተቻለ ደግሞ ከቴክኖሎጂ ጋር በቀላሉ ተላምደው ማላመድ የሚችሉ መኾን ይጠበቃል ነው ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ፡፡ ለዚህ የሚያግዝ የተፋጠነ የትምህርት ሥርዓት እየተዘረጋ መኾኑን አንስተዋል፡፡

ክልሉ ያቀደውን የተማሪ ቁጥር እና የትምህርት ጥራት ለማሳካት በጋራ መሥራት ያስፈልጋል ያሉት ቢሮ ኀላፊዋ ወላጆች ቅድሚያ ልጆቻቸውን ለማስተማር ሥነ ልቦናዊ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

አስፈላጊውን የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት፣ የልጆቻቸውን ትምህርት መከታተል፣ ትምህርት ቤቶችን ለልጆች ትምህርት ምቹ ማድረግ፣ መምህራንን፣ ርእሳነ መምህራንን እና ሱፐርቫይዘሮችን መደገፍ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 19-30/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 12 ቀናት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች እንደሚካሄድ ቢሮ ኀላፊዋ ጠቁመዋል፡፡ የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ሥራ መስከረም 5/2018 ዓ.ም በክልሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ይጀመራል ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ ወላጆች በትምህርት ቤቶች ተገኝተው የልጆቻቸውን ትምህርት በድምቀት እንዲያስጀምሩም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

"ዛሬ ፈተናዎቻችንን ተቋቁመን ልጆቻችንን ካላስተማርን ነገ የተማሩ ዜጎችን ማፍራት ሕልም ይኾንብናል" ያሉት ዶክተር ሙሉነሽ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን ሀገራዊ እና ታሪካዊ ኀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡

በሙከራ ምዝገባው እና በሕዝባዊ ውይይቶች ተስፋ ሰጪ ቁጭቶችን አይተናል፤ በጋራ ከቆምን እና በጋራ ከሠራን እቅዱን ማሳካት እንደምንችል ባለሙሉ ተስፋ ነኝም ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

አሚኮ እሴት እና ባሕል ግንባታ ላይ የራሱን ሚና ተጫውቷል።ደሴ: ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አሚኮ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት በተለያዩ መርሐ ግብሮች እያከበረ ነው። ይህንንም ተከትሎ...
24/08/2025

አሚኮ እሴት እና ባሕል ግንባታ ላይ የራሱን ሚና ተጫውቷል።

ደሴ: ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አሚኮ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት በተለያዩ መርሐ ግብሮች እያከበረ ነው። ይህንንም ተከትሎ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋጡማ ሞላ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ባስተላለፉት መልዕክት አሚኮ ብሔረሰብ አሥተዳደሩ በቋንቋው ባሕሉን እና እሴቱን እንዲያስተዋውቅ የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል በማቋቋም ትልቅ ሥራ እየሠራ ያለ ተቋም ነው ብለዋል።

ከነጣጣይ ትርክት በመውጣት ብሔራዊ ገዥ ትርክት ለመፍጠር የሚሠሩ ሥራዎችን አጉልቶ በማውጣት ሀገራዊ አንድነትን ለማስጠበቅ ሲሠራ መቆየቱንም ገልጸዋል።

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሚሠሩ የሰላም ሥራዎች ሕዝቡ ጋር እንዲደርስ በማድረግ ረገድ አሚኮ ትልቁን ድርሻ ተወጥቷልም ብለዋል አፈ ጉባኤዋ።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ባሕል፣ እሴት እና አብሮነት እንዲጠናከር ከማድረግ ባሻገር ከአጎራባች ዞኖች ጋር ያለው ወንድማማችነት እንዲጠናከር በማድረግ ውስጥም ሚናውን እየተወጣ ያለ ተቋም መኾኑን አስረድተዋል።

አሚኮ በቀጣይ የሕዝብ ድምፅ መኾኑን በማስቀጠል በክልሉ የሚሠሩ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን ለሕዝቡ ለማድረስ በትኩረት ሊሠራ ይገባልም ብለዋል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

‎ኢኮኖሚያዊ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች ...‎ባሕር ዳር: ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ‎የአማራ ክልል ምርትና ግብይት፣ የገበያ አረጋጊ፣ የሕገ ወጥ ንግድ እና ፀረ ኮንትሮባንድ ጥምር ግ...
24/08/2025

‎ኢኮኖሚያዊ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች ...

ባሕር ዳር: ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ‎የአማራ ክልል ምርትና ግብይት፣ የገበያ አረጋጊ፣ የሕገ ወጥ ንግድ እና ፀረ ኮንትሮባንድ ጥምር ግብረ ኀይል የወንጀል ጉዳዮች ቴክኒክ ኮሚቴ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።

የቴክኒክ ኮሚቴው የፍትሕ ቢሮ፣ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ፣ ገቢዎች ቢሮ፣ የፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን እና ሌሎች የፌደራል እና የክልሉን ተቋማትን ያቀፈ ኮሚቴ ሲኾን በፍትሕ ቢሮ ሰብሳቢነት የሚመራው ነው፡፡

‎‌መድረኩ የቴክኒክ ኮሚቴው በ2017 በጀት ዓመት በየተቋማቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ያካተተ ሪፖርት ቀርቧል። ከነዚህም መካከል ለፈጻሚ አካላት ሥልጠና መሰጠቱ እና ወደ ተግባር መገባቱ ተነስቷል፡፡ ለማኅበረሰቡ በሕገወጥ ንግድ እና ጉዳቶቹ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች መከናወኑም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

‎በምግብና መድኃኒቶች ላይ የተደረገ ቁጥጥር፣ ሕገ ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር በንግድ ድርጅቶች የበር ከበር ጉብኝት፣ የሕገ ወጥ ደረሰኝ ክትትልና ቁጥጥር፣ የኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር እና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች መሠራቱ ተጠቅሷል።

በ‎‌ዚህም ለጤና ጠንቅ የኾኑ የተበላሹ የምግብ ሸቀጦች፣ የታሸጉ ምግቦች እና መጠጦች ተገኝተው መወገዳቸው ተነስቷል። በክትትል እና በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ሕገወጦች ላይ አሥተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱ ተነግሯል።
‎አማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር ሙሉጌታ አሻግሬ የቴክኒክ ኮሚቴው የ2017 በጀት ዓመት በንግዱ ማኅበረሰብ ላይ በሚደረጉ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች በሚገኙ ሕገወጥ ድርጊቶች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡

ተበላሽተው የተገኙ 121 ሚሊዮን ብር በላይ የሚወጡ ምግብና ምግብ ነክ እቃዎች መወገዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ከአሥተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ ክስ የተመሰረተባቸው መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡

‎በበጀት ዓመቱ 971 ኢኮኖሚነክ መዝገቦች ለዐቃቢ ህግ ቀርቦ 946 በዐቃቢ ሕግ ውሳኔ ያገኙ ሲኾን 287 ክርክር ተደርጎ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል ብለዋል፡፡ በዚህም ከገንዘብ መቀጫ እስከ እስራት ተቀጥተዋል፡፡ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ቅጣት ተወስኗል ነው ያሉት፡፡ ከ76 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የንግድ ዕቃዎች በመንግሥት ተወርሰዋል፡፡ በጥቅሉ በቅጣትና በውርስ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመንግሥት ገቢ ተደርጓል ብለዋል፡፡

መድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኀላፊ አያሌው አባተ (ዶ.ር) ባስተላለፉት መልዕክት ኮሚቴው ኢኮኖሚነክ ወንጀሎችን ለመከላከል ውጤታማ በኾነ መንገድ ለመምራት እና ተጠያቂነትን ለማረገጋገጥ የተቋቋመ ነው ብለዋል፡፡

‎ዓላማውም ሕጋዊ በኾነው የንግዱ ማኅበረሰብ እና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ነው ብለዋል፡፡ በኢኮኖሚ ላይ የሚፈጸም ወንጀል አስቸጋሪ ባሕሪ ያለውና ተግዳሮቱ ሰፊ ነው ያሉት ምክትል ኀላፊው ምክንያቱ ደግሞ የወንጀሉ ፈጻሚ አካላት ወንጀሉን የሚፈጽሙት ሥልጣን ካላቸው እና ሕግ ከሚያስከብሩ አካላት ጋር በመኾኑ ነው ብለዋል።

‎ሌላው ምክንያት ሕገ ወጦች ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም እና ቁጥር ያላቸው በመኾኑ ካለው የባለሙያ ስብጥር አኳያ ተጠያቂነትን በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻሉ ከባድ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

‎በሰው ሠራሽ ችግሮች ምክንያት ያለንን ምርት ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ አለመቻል እና ኾን ተብሎ የምርት እጥረት እንዲከሰት የሚያደርጉ አካላት በመኖራቸው ገበያው እንዲራቆት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች በተለያዩ ምክንያቶች ለተጠቃሚዎች አለመድረሱ ገበያው ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩንም አንስተዋል፡፡

‎ሕገ ወጥነትን ለመቆጣጠር በተከናወኑ ተግባራት በኢኮኖሚ ወንጀል ላይ በተሰማሩ አካላት ጉዳያቸው ወደ ፍትሕ ቀርቦ ውሳኔ እየተሰጠ መኾኑን አንስተዋል፡፡ የበለጠ አመርቂ ሥራ ለመሥራት ከማኅበረሰቡ ጋር በትብብር መሥራት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

‎አማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ፈንታው ፈጠነ በበኩላቸው ለሕገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ጥምር ግብረ ኀይል የቴክኒክ ኮሚቴው የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል በየደረጃው ካሉ የሸማቾች ማኅበራት ጋር በመተባበር በመሰረታዊ እና ፍጆታ ምርቶች አቅርቦት ላይ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን አንስተዋል፡፡

‎‌‌በቀጣይም ከደመወዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ ሕገ ወጦች ምርቶችን በማከማቸት በኑሮ ውድነቱ ጫና እንዳይፈጥሩ በትኩረት እና በትብብር መሥራት እንደሚገባ በመድረኩ ማጠቃለያ መልዕክት ተላልፏል።
‎ዘጋቢ፡- ፍሬሕይወት አዘዘው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን


በሀገራዊ ምክክሩ አካል ጉዳተኞችን በስፋት ለማሳተፍ እየተሠራ ነው።ደሴ: ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአካል ጉዳተኞች በሀገራዊ የፖለቲካ ውሳኔዎች ላይ የመሳተፍ መብት አላቸው። "የአካ...
24/08/2025

በሀገራዊ ምክክሩ አካል ጉዳተኞችን በስፋት ለማሳተፍ እየተሠራ ነው።

ደሴ: ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአካል ጉዳተኞች በሀገራዊ የፖለቲካ ውሳኔዎች ላይ የመሳተፍ መብት አላቸው።
"የአካል ጉዳተኞች ሚና እና አስተዋፅኦ ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ" በሚል መሪ መልዕክት የአካል ጉዳተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ በደሴ ከተማ ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ አካል ጉዳተኞች ተሳትፈዋል።

በግጭት ወቅት አካል ጉዳተኞች ይበልጥ ተጋላጭ ይኾናሉ ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የአካል ጉዳተኞች ድርሻ ከፍተኛ መኾን አለበትም ብለዋል።
በሀገራዊ ምክክር ሂደት አካል ጉዳተኞች አጀንዳ በማጋራት፣ ሀሳብ በመስጠት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያረጉ ተመላክቷል።

የሀገሪቱን የፖለቲካ ሥርዓት ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ የአካል ጉዳተኞች ድምፅ ወሳኝ ነው ያሉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድኅን
በተለይም የአካል ጉዳተኞችን ፍላጎት እና ችግር የሚረዱ ተወካዮች በሕግ አውጪ አካላት ውስጥ ሚና እንዲኖራቸው መደረግ አለበት ነው ያሉት።

በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ አካል ጉዳተኞችን በስፋት ለማሳተፍ እየተሠራ መኾኑንም ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድህን
ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፦ ሰልሀዲን ሰይድ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም ይጀመራል።ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 19/201...
24/08/2025

የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ2018 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 19/2017 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንደሚካሄድ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በትምህርት ዘመኑ 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱም ተገልጿል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 የትምህርት ዘመን አጀማመርን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ለትምህርት ዘመኑ የተማሪዎች ምዝገባ በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።

በክልሉ በተመረጡ አካባቢዎች ነሐሴ 15 እና 16/2017 ዓ.ም የሙከራ ምዝገባ መካሄዱን ያነሱት ዶክተር ሙሉነሽ በበርካታ ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ዘመኑ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ታይተዋል ብለዋል።

በሙከራ ምዝገባው የታየውን ተስፋ ሰጪ መነሳሳት በመድገም ባለፉት ዓመታት የተፈጠሩ ክፍተቶችን ማካካስ እንደሚገባም ቢሮ ኀላፊዋ አንስተዋል። የማኅበረሰቡ ቁጭት፣ የአጋር አካላት ድጋፍ እና በየደረጃው የነበረው ቅድመ ዝግጅት የታቀደውን ውጤት ለማሳካት አቅም ይሆናል ብለዋል።

የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ሥራ መስከረም 5/2018 ዓ.ም እንደሚጀምርም ቢሮ ኀላፊዋ አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

24/08/2025

"በሐረሪ ክልል በነበረን ቆይታ ከአመራሮች ጋር በምሽት ያደረግነው የእግር ኳስ ጨዋታ" ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ሑሉንም ከአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ  #አሚኮ30  #አሚኮኢትዮጵያ  #አሚኮኅብር
24/08/2025

ሑሉንም ከአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ
#አሚኮ30 #አሚኮኢትዮጵያ #አሚኮኅብር

#አሚኮ30ሑሉንም ከአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ

Address

Bahir Dar, Ethiopia P. O. BOX 955
Bahir Dar
6000

Website

https://www.ameco.et/

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን:

Share