ዙታሊ ሚዲያ- Zutalie Media

ዙታሊ ሚዲያ- Zutalie  Media ዙታሊ ሚዲያ-የኑሮዎ ምርኩዝ! !

አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል - የልጃገረዶች የነጻነት በዓልበነሐሴ ወር አጋማሽ መከበር የሚጀምሩት አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል ልጃገረዶች አምረውና ተውበው በነጻነት የሚያከ...
22/08/2025

አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል - የልጃገረዶች የነጻነት በዓል

በነሐሴ ወር አጋማሽ መከበር የሚጀምሩት አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል ልጃገረዶች አምረውና ተውበው በነጻነት የሚያከብሯቸው በዓላት ናቸው።

አሸንዳ በትግራይ፣ ሻደይ በሰቆጣ፣ አሸንድዬ በላሊበላ፣ ሶለል በቆቦ ሲከበሩ፤ ከሕጻን እስከ አዋቂ የበዓላቱ መገለጫ በሆኑ አልባሳትና መዋቢያዎች አጊጠው የሚታዩባቸው ናቸው።
ልጃገረዶቹ ጥልፍ ቀሚስ፣ ሹፎን እና ጀርሲ ለብሰው፤ ፀጉራቸውን አልባሶ፣ ግልብጭ፣ ጋሜ፣ ቁንጮ፣ ሳዱላ እና ቅርድድ ተሠርተው፤ በሕንቆ፣ አልቦ፣ ድሪ፣ ድኮት፣ ጉትቻ፣ ማርዳ፣ እና መስቀል አጊጠው ለጭፈራ አደባባይ ይወጣሉ።

የበዓላቱ አከባበር የሚጀምረው በመንደር፣ በጎጥ ወይም በደብር ደረጃ ከ12 እስከ 20 ወይም ከዚያ በላይ ሆነው በሚደራጁ ልጃገረዶች ባህላዊ ጨዋታ ነው።

በዚህ ባህላዊ ጨዋታ ወጣት ወንዶች ልጃገረዶችን በማድነቅ፣ በማጀብ፣ በማሽኮርመምና ከአላስፈላጊ ትንኮሳዎች በመጠበቅ ትልቅ ሚና እና ተሳትፎ እንዳላቸው ይወሳል።
የአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓላት ስያሜ በክብረ በዓሉ ወቅት ልጃገረዶች በወገባቸው ዙሪያ ከሚለብሱት ከታች ነጭ፣ ከላይ አረንጓዴ የሆነ ረጅም ሳር ወይም ተክል የተወሰደ ስለመሆኑ ይነገራል።

በዓላቱ መቼ እና እንዴት መከበር እንደ ጀመሩ የተካሄደ ጥናት ባይኖርም፤ አፈ-ታሪክ እና አንዳንድ ሊቃውንት ክብረ በዓሉ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሙሴ ዘመን መከበር እንደጀመረ ይገልፃሉ።

ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ልጃገረዶች በበዓላቱ ላይ የሚያሰሙትን ግጥም ነው፦
“አሸንድዬ አሸንዳ ሙሴ ፍስስ በይ በቀሚሴ፣
አበ ሙሴ፣ ወርቅ አበ ሙሴ ፍስስ በይ በቀሚሴ።"

የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አሸናፊ ሙሉጌታ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ነሐሴ ወር ላይ በአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓላት ምክንያት የቱሪስት ፍሰቱ እንደሚጨምር ነው የገለፁት።

በዓላቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን የመሳብ አቅም እንዳላቸው ጠቅሰው፤ በዚህ ወቅት በርካታ ቱሪስቶች መዳረሻቸውን ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እንደሚያደርጉ አክለዋል።
ኢትዮጵያ በተለያዩ ባህሎቿ እና እሴቶቿ ሀብታም ናት ያሉት አቶ አሸናፊ፤ ከእነዚህ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማሳደግ ይቻል ዘንድ አብዝቶ ማስተዋወቅ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

"የሻደይ ቄጤማ የምህረት፣ የደስታ እና የሰላም  ተምሳሌት ናት" ብፁዕ አቡነ በርናባስ የሻደይ በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በሰቆጣ ከተማ ደብረ ፀሐይ ወይብላ ቅድስት ማርያም ካቴድራል እ...
22/08/2025

"የሻደይ ቄጤማ የምህረት፣ የደስታ እና የሰላም ተምሳሌት ናት" ብፁዕ አቡነ በርናባስ

የሻደይ በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በሰቆጣ ከተማ ደብረ ፀሐይ ወይብላ ቅድስት ማርያም ካቴድራል እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ በርናባስ ሻደይ የሰላም እና የፍቅር ምልክት ነው ብለዋል።

በኖኅ ዘመን የነበረው የውኃ ሙላት መጉደሉን ለማብሰር እርግብ የሰላም ቄጤማ እንዳመጣች ሁሉ ዛሬም ደናግል ዘማርያን የሻደይ ቄጤማ ይዘው እየዘመሩ ይውላሉ ነው ያሉት።

በኖኅ ዘመን ቄጤማ ሰላምን፣ ደስታን፣ ፍቅርን እንዳበሰረ ሁሉ ዛሬም የሻደይ ቄጤማ የምህረት የደስታ፣ የሰላም ተምሳሌት ኾኖ በቤተክርስትያኗ እየተከበረ መምጣቱን አንስተዋል።
ዛሬም ሀገራችን ሰላም እና ፍቅር ያስፈልጋታል ያሉት ብፁዕነታቸው በዓሉን ስናከብር ለሀገር ሰላም በመስበክ እና በመተባበር ሊኾን ይገባል ብለዋል። የተቸገሩትን ወገኖች በመርዳትና በመደገፍ በዓሉን ማክበር እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል  የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል በዓል በተለያዩ አካባቢዎች በተለያየ ስም ይጠራ እንጅ የስያሜው መሰረት ተመሳሳይ ነው፡፡ ይሄም በክብረ-በዓሉ ወቅት ልጃገረዶች በወገባቸዉ...
22/08/2025

ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል

የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል በዓል በተለያዩ አካባቢዎች በተለያየ ስም ይጠራ እንጅ የስያሜው መሰረት ተመሳሳይ ነው፡፡ ይሄም በክብረ-በዓሉ ወቅት ልጃገረዶች በወገባቸዉ ከሚያስሩት ረጅምና ስሩ ነጭ ሌላዉ አካሉ አረንጓዴ ከሆነዉ ቅጠል የመጣ ነው፡፡ ሻደይ በኽምጠኛ አረንጓዴ ወይም ለምለም ማለት ነው።

የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል በዓል መቸ እና እንዴት መከበር እንደጀመረ በጥናት የታወቀ ባይሆንም አፈ-ታሪኮች እና አንዳንድ ሊቃውንት ክብረ በዓሉ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሙሴ ዘመን መከበር እንደጀመረ ይናገራሉ፡፡ ለዚህም እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ልጃገረዶች ለዘመናት ለበዓሉ የሚያሰሙትን ግጥም ነው፡፡

“አሸንድዬ አሸንዳ ሙሴ
ፍስስ በይ በቀሚሴ፡፡
አበሙሴ፣ ወርቅ አበሙሴ
ፍስስ በይ በቀሚሴ፡፡”

በዓሉ ከኖህ ዘመን የጥፋት ውሃ መጎደል እና ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋርም በቀጥታ እንደሚገናኝ በርካታ ማስረጃዎች አሉ።

የሻደይ፣ አሸንድዩ፣ ሶለል ባህላዊ ጨዋታ አከባበር የሚጀምረው በመንደር፣ በጎጥ ወይም በደብር ደረጃ ከ12 እስከ 20 እና በላይ በሚደራጁ የልጃገረዶች ተሳትፎ ነው፡፡ የባህላዊ ጨዋታው ተሳታፊዎች በየዕድሜ ደረጃው ያሉና በቡድን የሚሰበሰቡ ሕፃናት፣ ልጃገረዶችና እናቶች ቢሆኑም የጨዋታው ባለቤቶች በዋናነት ልጃገረዶች/ያላገቡ እንስቶች/ ናቸው፡፡
በባህላዊ ጨዋታው እንደ ዕድሜ ክልላቸው የተሰባሰቡ የሻደይ/አሸንድዩ/ሶለል ተጫዎች ቡድኖች የየራሳቸው መሪ አላቸው፡፡ በዚህ ባህላዊ ጨዋታ ወጣት ወንዶች ልጃገረዶችን በማድነቅ፣ በማጀብ፣ በማሽኮርመምና ከአላስፈላጊ ትንኮሳዎች በመጠበቅ ከፍተኛ ሚናና ተሳትፎ አላቸው።

አባቶች ደግሞ በመመረቅና የጨዋታውን ስርዓት በማስጠበቅ፣ ቤት ለቤት ተዘዋውረው ለሚጫወቱት ተጫዎች ቡድኖች በዓይነትና በገንዘብ ሽልማት መስጠት፣ መመረቅ፣ ለቀጣይ ዓመት ቃል መግባት ሆኖ ጨዋታው ከትልቅ አባት/ከሃይማኖት መሪ ወይም ከኃላፊ/ተጀምሮ እስከተራው ቤት ድረስ እየተዘዋወሩ አበባ በመጣል የሚጫወቱት የልጃገረዶች ክብረ በዓል/ ባህላዊ ጨዋታ ነው፡፡


እንኳን አደረሳችሁ!

የደብረ ታቦር በዓል በደብረታቦር ከተማ ተከበረ።የደብረ ታቦር ዓመታዊ በዓል በዛሬው ዕለት በደብረታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ተከብሯል፡፡በዓሉ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ነሐ...
19/08/2025

የደብረ ታቦር በዓል በደብረታቦር ከተማ ተከበረ።

የደብረ ታቦር ዓመታዊ በዓል በዛሬው ዕለት በደብረታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ተከብሯል፡፡

በዓሉ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ነሐሴ 13 የሚከበር ሲሆን÷ በደብረታቦር ከተማ ርዕሰ አድባራት ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሐይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

ከበዓሉ አከባበር ጎን ለጎን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በደብረታቦር ኢየሱስ ሙዚየም ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል።

የዝነኛዋ ድምፃዊት ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ አዲስ አልበም ሊወጣ ነው::ድምፃዊት ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ አዲሱን አልበሟን ማጠናቀቋ ተሰምቷል። አልበሙ "ደህና ሰው" የሚል መጠሪያ ተሰጥቷታል ። ፍቅር...
19/08/2025

የዝነኛዋ ድምፃዊት ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ አዲስ አልበም ሊወጣ ነው::

ድምፃዊት ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ አዲሱን አልበሟን ማጠናቀቋ ተሰምቷል።

አልበሙ "ደህና ሰው" የሚል መጠሪያ ተሰጥቷታል ።

ፍቅርአዲስ ነቃ ጥበብ በ2008 ዓ/ም ለመጨረሻ ጊዜ ለህዝብ ያደረሰችው "ምስክር" የተሰኘ አልበሟን እንደሆነ ይታወሳል።

የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑ ተገለጸ።የገንዘብ ሚኒስቴር በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ...
19/08/2025

የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑ ተገለጸ።

የገንዘብ ሚኒስቴር በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል አለ፡፡

ነባሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከምጣኔ ውጭ ሌሎች ማሻሻያዎችን በማካተት ከ3 አስርት ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ በ2017 በጀት አመት ስራ ላይ መዋሉን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከነበረው ከ12 በመቶ በላይ ድርሻ በየዓመቱ በተከታታይ እየቀነሰ ከ7 በመቶ በታች መድረሱን ጠቅሶ፥ ከዚህ ጠቅላላ ቅናሽ 44 በመቶው የተጨማሪ እሴት ታክስ ድርሻ እንደሆነ አመልክቷል፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ ህጉን አሁን ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ የቀጣይ ዓመታት ለውጦች ጋር እንዲጣጣም በማድረግ በመካከለኛ ዘመን የገቢ ስትራቴጂው መሰረት ተሻሽሎ በ2017 በጀት ዓመት ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል ብሏል፡፡

በማሻሻያው መሰረት በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን ነው የገንዘብ ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡

ትራምፕ ዩክሬን የኔቶ አባል እንደማትሆን ተናገሩ።በዋይት ሃውስ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ለመቀበል እየተዘጋጁ ያሉት ትራምፕ ዩክሬን የኔቶ አባል እንደማትሆን ተናግረዋል።የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናል...
18/08/2025

ትራምፕ ዩክሬን የኔቶ አባል እንደማትሆን ተናገሩ።

በዋይት ሃውስ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ለመቀበል እየተዘጋጁ ያሉት ትራምፕ ዩክሬን የኔቶ አባል እንደማትሆን ተናግረዋል።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬን ፕሬዝዳንት " ከፈለገ" ከሩሲያ ጋር ሚደረገውን ጦርነት መቋጨት እንደሚችል፤ በሚደረሰው የሰላም ስምምነት አማካኝነት ግን "ዩክሬን ወደ ኔቶ እንደማትገባ" አሳውቀዋል፡፡

ትራምፕ፤ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪን በዋይት ሃውስ ከመቀበላቸው ከጥቂት ሰዓታት በፊት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሞስኮ ከስምንት ዓመት በፊት እ.አ.አ በ2014 በህገወጥ መንገድ ቆርጣ የወሰደችውን የክሬሚያ የባህር ሰርጥ መሬት "መመለስ አይቻልም" ብለዋል።

ትራምፕ ይህንን የተናገሩት በአላስካ ከሩስያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ ነው። ይህ ስብሰባ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ሲያቀርቡ የነበሩትን የተኩስ አቁም ጥያቄ በመተው በምትኩ ዘላቂ የሰላም ስምምነት እንዲደረግ ጥሪ እንዲያቀርቡ ያደረገ ነው።

ዜሌንስኪ እሁድ ምሽት ወደ አሜሪካ ከገቡ በኋላ ዩክሬን ውጤታማ የደህንነት ዋስትና እንድታገኝ አጋር ሀገራት በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

አንድ የአሜሪካ ልዑክ እሁድ ዕለት እንደተናገሩት ፑቲን ለዩክሬን የኔቶ አይነት የደህንነት ስምምነት ሊኖር እንደሚችል ተስማምተዋል።

ለመንግሥት  ሰራተኞች ደሞዝ ተጨመረ፡፡"መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው" ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን  የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን መንግ...
18/08/2025

ለመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ ተጨመረ፡፡

"መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው" ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን መንግሥት የመንግሥት ሰራተኛውን ሕይዎት ለማሻሻል የሚያስችል እርምጃዎችን መውሰዱን ተከትሎ መግለጫ አውጥቷል፦

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት የገጠሟትን የኢኮኖሚ ስብራቶች ለመጠገንና ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ግስጋሴ ለማፋጠን አዲስ የኢኮኖሚ ልማት ዕይታ እና መንገድ እየተከተለች ትገኛለች። በተያዘው ብዝኀ ዘርፍ፣ ብዝኀ ተዋናይ እና ብዝኀ ተጠቃሚ የኢኮኖሚ ዕድገት አቅጣጫ፣ ጥራት ላለው እና አሳታፊ የኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡

እንደሚታወቀው፣ ሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን በመሠረታዊነት ለመፍታት ልዩ ልዩ ሪፎርሞችን ጀምራ በሰኬት ጎዳና ላይ ትገኛለች፡፡ የእነዚህ ሪፎርሞች ዓላማ ሁለት ነው፡፡ በአንድ በኩል ነባር ሀገራዊ ስብራቶችን መጠገን እና የተንከባለሉ ዕዳዎችን ማቃለል ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የዛሬን እና የነገን ትውልድ ጥያቄዎች በመመለስ፣ የኢትዮጵያን ብልጽግና በአስተማማኝ መሠረት ላይ መገንባት ነው፡፡

ሪፎርሙን በመተግበር በተገኙ ውጤቶች እና ትሩፋቶች፣ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች እንዲሁም የቢዝነስ አንቀሳቃሾች እና በግል ክፍለ ኢኮኖሚ የተሠማሩ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የገቢ ሁኔታ ከኢኮኖሚ ዕድገቱ ጋር አብሮ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በዚህ ሂደት ግን የቋሚ ደመወዝተኞች በተለይም የመንግሥት ሠራተኞች ገቢ በተገቢው መጠን ሊጨምር አልቻለም፡፡

በየጊዜው እየጨመረ በመጣው ሰፊ የመንግሥት ሠራተኛ ቁጥር (በዓመት ወደ 100 ሺህ) ምክንያት የመንግሥት አጠቃላይ የደመወዝ ወጪ ድርሻ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መጥቷል። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ለደመወዝ የሚያውለው ወጪ ከአጠቃላይ የመንግሥት ወጪ አንጻር ያለው ድርሻ ከ30 እስከ 32 በመቶ ይደርሳል፡፡

በአንጻሩ ደግሞ ለእያንዳንዱ የመንግሥት ሠራተኛ የሚከፈለው ደመወዝ በሚፈለገው መጠን መጨመር ባለመቻሉ አሁንም የሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ አነስተኛ ነው፡፡ ይሄንን በመረዳት እና በየጊዜው በመንግሥት ሠራተኛው በተለይም ዝቅተኛ ተከፋይ በሆነው ላይ እየደረሰ ያለውን የኑሮ ጫና ለማቃለል፣ መንግስት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት 91 ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ እንዲሻሻል ተደርጓል። ያለፈው የበጀት ዓመት እንደ ሀገር ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የገባንበት እና በመንግሥት ወጪ ላይ ከፍተኛ ጫና የነበረበት ዓመት ቢሆንም፣ መንግሥት ባለው ቁርጠኛ ሰው ተኮር አቋም፣ የዝቅተኛ ተከፋይ ሠራተኛውን ደመወዝ ትርጉም ባለው ሁኔታ አሻሽሏል።

ደመወዝ ከመጨመር ባለፈ ቋሚ ገቢ ያለውን ሠራተኛ የመግዛት ዐቅም ለማሳደግ፣ መንግሥት ከ1994 ዓም ጀምሮ ሥራ ላይ በቆየው የቁርጥ ገቢ ግብር ዐዋጅ ውስጥ በተካተቱት የግብር ማስከፈያ ምጣኔ እና በተለያየ ደረጃ ግብር በሚጣልበት የገቢ ቅንፍ (income bracket) ላይ ማስተካከያ አድርጓል፡፡ በዚህም ሰፊ ማሻሻያ የተደረገ ሲሆን፣ በተለይም ከታክስ ነጻ የሆነውን የተቀጣሪ ገቢ ከብር 600 ወደ ብር 2000 ለማሳደግ ተችሏል።

መንግሥት ለዘመናት ሲንከባለል የመጣውን የመንግሥት ሠራተኛ ዝቅተኛ የክፍያ ሁኔታ እና ተያይዞ የመጣውን የኑሮ ጫና በአንድ ጊዜ በሚደረግ የደመወዝ ማሻሻያ ሊቀርፈው እንደማይችል ይገነዘባል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግሥት ከእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ብልጽግና ምዕራፍ ሁሉም ለልማቱ አዎንታዊ ሚና የተጫወተ ዜጋ ተጠቃሚ መሆን አለበት ብሎም ያምናል። ስለሆነም ከሚወሰዱ ሌሎች ማሻሻያዎች በተጨማሪ፣ ከመስከረም 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡ በዚሁ ማሻሻያ መሠረት፦

1. ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4,760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ እንዲያድግ ይደረጋል፡፡
2. የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11,500 ይሻሻላል።
3. ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ ይደረግበታል፡፡
4. ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000 እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቋል፡፡ ይህም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል። ይህ የደመወዝ ጭማሪ ካለን የልማት ፍላጎት አንጻር አገልግሎቶችና መሠረተ ልማት ለማስፋፋት የሚያስፈልገንን ሀብት የሚሻማ ቢሆንም፣ የመንግሥት ሠራተኛውን ኑሮ ማሻሻል ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ የተወሰነ ነው። ከዚህም ባሻገር የመንግሥት ሠራተኛው ችግር በደመወዝ ማሻሻያ ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ በቀጣይ የቤት አቅርቦትን እና የጤና መድን ሽፋንን ጨምሮ በተከታታይ መፍትሄ እንዲበጅላቸው ይደረጋል፡፡

መንግሥት ይሄንን የደመወዝ ማሻሻያ ሲያደርግ ጭማሪው በቂና የመጨረሻ ነው ብሎ በማመን አይደለም፡፡ በቀጣይነት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ማሻሻያው እየተተገበረ ሲሄድ ብቃትና ውጤትን መሠረት ያደረጉ ማሻሻያዎች ይደረጋሉ፡፡ በተጨማሪም የጀመርነው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ይበልጥ ውጤት እያስመዘገበ በሄደ ቁጥር፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የትሩፋቱ ተቋዳሽ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም በተገቢ ደረጃና መጠን ለመክፈል ከተፈለገ፣ ያንን የሚሸከም ሀገራዊ ኢኮኖሚ መገንባት አለብን፡፡ ኢትዮጵያ ለአገልጋዮቿ ተገቢውን ክፍያ እንድትከፍል የሚያስችላትን ኢኮኖሚ የመገንባት ኃላፊነት ደግሞ፣ በመንግሥት ሠራተኛው ላይ ጭምር የተጣለ ብሔራዊ ግዴታ ነው፡፡ ካልተከልነው ዛፍ ፍሬ፣ ካልዘራነው ሰብል ምርት ልናገኝ አንችልምና፡፡

ኢኮኖሚያችን ካላደገ፣ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ሊያድግ አይችልም፡፡ ለአብነት የታክስ ገቢያችንን በአንድ በመቶ ብናሳድግ እንኳን፣ ከብር 3ዐዐ ቢሊዮን በላይ ተጨማሪ ሀገራዊ ገቢ እናገኛለን፡፡ ይሄንን ለማሳካት ደግሞ በየመስኩ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ከፍተኛውን ሚና ይጫወታሉ፡፡

በአጠቃላይ ዘላቂና ትርጉም ያለው የኑሮ ደረጃ መሻሻል እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ዓይናችንን ለአፍታም ቢሆን ከሀገራዊ ሕልማችን ሳንነቅል መረባረብ አለብን። በዚህ ሂደት ውስጥ ኢትዮጵያውያን የሚከፍሉት የውዴታ መሥዋዕትነት አለ፡፡ ይህ መሥዋዕትነት ለነገ ሲባል የሚከፈል መሥዋዕትነት ነው፡፡ ለተሻለ ነገ ስንል የተወሰኑ ፍላጎቶቻችንን እንተዋለን፡፡ ውድ ዕውቀታችንን፣ ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን እንሠዋለን፡፡ ያደጉ ሀገራት ሁሉ የከፍታ ማማ ላይ የደረሱት በአንድ ወቅት መሥዋዕትነት በከፈሉ ትውልዶቻቸው ትከሻ ላይ መሆኑን ሁላችንም ይህንን ዘወትር በማስታወስ አገራችንን ከፍ ወዳአለ ደረጃ ለማድረስ ከእኛም ተመሳሳይ መሰጠት የሚጠበቅ መሆኑን መረዳት አለብን፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን በነጻነት የምንኖረው፣ ከመኖር ለሚበልጥ ሀገራዊና ሕዝባዊ ክብር ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን በሠው ዐርበኞቻችን ምክንያት ነው፡፡ የኢትዮጵያ የመንግሥት ሠራተኞች የድካማቸውን ያህል ክፍያ እንደማያገኙ ይታወቃል፡፡ ይሄም ለተሻለች ኢትዮጵያ እየተከፈለ ያለ መሥዋዕትነት እንደሆነ መንግሥት ዕውቅና ይሰጣል። ስለሆነም በዚሁ አጋጣሚ፣ በአነስተኛ ክፍያ ሕዝብና መንግሥት የሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነት በመወጣት ላይ ለሚገኙ አገልጋዮች መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

የመንግስት ሠራተኛው ያለውን የኑሮ ውድነት ተቋቁሞ ለመላው የንግዱ ማህበረሰብ ተገቢውን አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ የንግዱ ማህበረሰብ መንግስት ለሚወስዳቸው የሪፎርም እርምጃዎች አጋዥ እየሆነ መጥተዋል። ይሄው ተግባር አሁንም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ይሁንና እንዳንድ የንግዱ ህብረተሰብ አካላት ከእዚህ ቀደም በተለምዶ የደመወዝ ጭማሪ ተደረገ በሚል በሸቀጦች ዋጋ ላይ እንደሚጨምሩ ይታወቃል፡፡ በሰሞኑ በሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ አስታኮ እና ለኑሮ ውድነቱ መቋቋሚያ ተብሎ በተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ ዜና በመስማት ህገወጥና ምንም ምክንያት በሌለው መንገድ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉት ላይ መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ አድርገው በሚገኙት ላይ ደግሞ መንግሥት አስተማሪ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በቅድሚያ ያሳውቃል፡፡

በመጨረሻም ሕዝባችንን በንጽሕናና በትጋት በማገልገል፤ ከሚገባንና ከሚጠበቅብን በላይ በመሥራት፤ ሙስናና ብልሹ አሠራርን በመታገል፤ ከዕቅዶቻችን በላይ በማከናወን፤ የኢትዮጵያን ብልጽግና እንደምናረጋግጥ መንግሥት ጽኑ እምነት አለው፡፡ የብልጽግና ጉዟችን በቀጠለ መጠን፣ በየምዕራፉ ሁላችንም የብልጽግናን ትሩፋት መቋደሳችን አይቀሬ ነው፡፡ ለዚያ ደግሞ ሁላችንም ወገባችንን አጥብቀንና ታጥቀን መትጋት አለብን፡፡ ይህ ሲሳካ ነጻነታችንን በደማቸው እንዳጎናጸፉን ቀደምት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሁሉ፣ እኛም ሀገራቸውን ለማበልጸግ ዋጋ የከፈሉ ትውልዶች ተብለን ታሪክ ሲዘክረን ይኖራል።

የትራምፕ እና የፑቲን  የፊት ለፊት የአላስካው ውይይት፤ትራምፕ ከፑቲን ጋር ባይስማሙም በውይይታቸው 'ለውጥ እንደታየ' ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት...
16/08/2025

የትራምፕ እና የፑቲን የፊት ለፊት የአላስካው ውይይት፤

ትራምፕ ከፑቲን ጋር ባይስማሙም በውይይታቸው 'ለውጥ እንደታየ' ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በአላስካ ባደረጉት ውይይት ከስምምነት ላይ ባይደርሱም "ለውጥ መታየቱን" ገልጸዋል።

"ስምምነት ላይ እስከሚደረስ ድረስ ስምምነት የለም። እዚያ ላይ አልደረስንም" ብለዋል። ለሦስት ሰዓታት ሁለቱ መሪዎች ከተወያዩ በኋላ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል። ከጋዜጠኞች ጥያቄ ግን አልተቀበሉም።

ፑቲን የዩክሬንን ጦርነት ለመግታት "በጣም እንደሚፈልጉ" ከመግለጽ ባለፈ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። በውይይቱ ያልተጋበዙት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ "ስምምነት እንዲፈርሙ" ትራምፕን ጠይቀዋል።

ትራምፕ እና ፑቲን ሊገናኙ ቀነ ቀጠሮ የያዙባት አላስካ ማለት፦✔️ አላስካ ማለት ታላቋ ምድር ማለት ነው።✔️ ከሩሲያ 82 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።✔️ አሜሪካ ለሩሲያ 7.2 ሚሊዮን ዶ...
13/08/2025

ትራምፕ እና ፑቲን ሊገናኙ ቀነ ቀጠሮ የያዙባት አላስካ ማለት፦

✔️ አላስካ ማለት ታላቋ ምድር ማለት ነው።

✔️ ከሩሲያ 82 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

✔️ አሜሪካ ለሩሲያ 7.2 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል ነበር አላስካን እ.አ.አ በ1867 የግሏ ያደረገቻት።

✔️ የአላስካን ሰንደቅ ዓላማ ዲዛይን ያደረገው የ13 ዓመቱ ቤኒ ቤንሰን እንደሆነ ይነገራል።

✔️ በውሻዎች እየተጎተቱ በበረዶ መንሸራተት አላስካ የምትታወቅበት የስፖርት አይነት ነው።

✔️ አሁን ላይ በአላስካ ምድር ከአሜሪካ ሰንደቅ ጎን የነበረው የሩሲያ ባንዲራ በቦታው የለም።

"በጎንደር የከፍታ ዘመን ላይ ይታዩ የነበሩ ምልክቶችን አሁን እያየን ነው" አቶ ቻላቸው ዳኘው የጎንደር ከተማ ከንቲባ ከቀበሌ ጀምረው በተለያዩ የሥልጣን ደረጃዎችና ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋ...
12/08/2025

"በጎንደር የከፍታ ዘመን ላይ ይታዩ የነበሩ ምልክቶችን አሁን እያየን ነው"

አቶ ቻላቸው ዳኘው የጎንደር ከተማ ከንቲባ

ከቀበሌ ጀምረው በተለያዩ የሥልጣን ደረጃዎችና ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል፡፡ የጎንደር ከተማ አካባቢ ጥበቃ ፅዳትና ውበት ኃላፊ፣ የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዋና ኃላፊ፣ የባህልና ቱሪዝም መምርያ ኃላፊ፣ የጎንደር ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ አሁን ደግሞ 37ኛው የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

አቶ ቻላቸው ዳኘው በከተማዋ ተወልደው ማደጋቸው፣ አካባቢውን በደንብ ማወቃቸውና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ማገልገላቸው ከተማዋን በከንቲባነት ለመምራት እንዳገዛቸው ይናገራሉ፡፡ ጎንደር ከተማን ለማስተዳደር ሕልም ስለነበራቸው ለዚህም የሚሆኑ የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውንም ያወሳሉ፡፡

"አመራርነት (Leadership) አንድ ቦታ የሚቆም ሳይሆን በየወቅቱ የሚማሩበት ነው ይላሉ፡፡ ‹‹የቆየ ችግር ሲፈታ በአንተ ጊዜ የተፈታ ተብሎ የታሪክህ አካል ሆኖ ይጻፋል፡፡ በመሆኑም ችግር ሲያጋጥመኝ ብዙም የማማርር ሰው አይደለሁም፡፡ ምክንያቱም በኃላፊነት ቦታ ላይ ሳለሁ ችግሮችን በመፍታት የታሪክ አካል መሆን እፈልጋለሁ" ይላሉ አቶ ቻላቸው፡፡

የፌደራል ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርማ (logo) ለመቀየር የሄደበትን መንገድ በፍጥነት ማስቆማቸው ተሰማ። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አርማ በመቀጠል እጅግ ልዩ የሆነ ዲዛይን ያለ...
11/08/2025

የፌደራል ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርማ (logo) ለመቀየር የሄደበትን መንገድ በፍጥነት ማስቆማቸው ተሰማ።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አርማ በመቀጠል እጅግ ልዩ የሆነ ዲዛይን ያለው እና ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ ያገለገለውን አርማ ምስሉ ላይ በሚታየው አርማ ባለፈው ሳምንት ለመቀየር ታስቦ እንደነበር ሰራተኞቹ መረጃ ሲያደርሱኝ ነበር፣ ለአዲሱ አርማ በሚገርም ሁኔታ 600 ሚልዮን ብር እንደወጣበትም ሪፖርተር ዘግቧል።

በርካታ አለም አቀፍ ባንኮችም ሆኑ ሌሎች ተቋማት አርማ ሲቀይሩ የቀደመውን ተንተርሰው ይቀይራሉ፣ አገልግሎቱንም ያስታውሳሉ/ይዘክራሉ።

ከሰማንያ ዓመት በላይ ታሪክ ያለው ባንክን በዚህ መልኩ በአንዴ መቀየሩ የባንኩን እሴት፣ ታሪክ (heritage) አውጥቶ ይጥላል። አንድ የብራንድ ዲዛይን ባለሙያ "አዲሱ ሎጎ የአንድ የቴክ ስታርትአፕ ወይም አንድ የትኛውም አለም ላይ የሚገኝ ድርጅት አርማ ሊሆን ይችላል። ክቡ አርማ ግን ልዩ ነው፣ በዛን ወቅት ኮምፒውተር ሳይኖር እንዴት ሰሩት ብዬ ሳስብ ይደንቀኛል" ብሏል። ሌላኛው ደግሞ 'Always reliable bank' የሚለው ራሱ የ grammar ችግር አለበት

Address

BahirDar-Ethiopia
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዙታሊ ሚዲያ- Zutalie Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዙታሊ ሚዲያ- Zutalie Media:

Share