Amhara Tube

Amhara Tube አስተማሪና አዝናኝ እንዲሁም ተከታታይ ልብ ወለድ ፅሑፎች እንዲደርሷችሁ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ

"አባቴ ጥሪ ሲኖርበት ልብስ የለኝም ይላል፤ ህልሜ ለአባቴ ቆንጆ ሱፍ መግዛት ነው" 🔥አንዲት ታዳጊ በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) ተከታዮቿ ጥያቄ ጠይቀዋል መልስ ትሰጣለች። ከቀረቡላት ጥያቄዎች...
15/07/2026

"አባቴ ጥሪ ሲኖርበት ልብስ የለኝም ይላል፤ ህልሜ ለአባቴ ቆንጆ ሱፍ መግዛት ነው" 🔥

አንዲት ታዳጊ በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) ተከታዮቿ ጥያቄ ጠይቀዋል መልስ ትሰጣለች። ከቀረቡላት ጥያቄዎችም አንዱ "ህልምሽን ንገሪን" የሚል ነበር።

የእሷ ምላሽ ግን ብዙሃንን አሳዝኗል። አባቷ ጥሩ ልብስ እንዲኖረው ትሻለች። "ለእሷ ሲል" አያቶቿ ቤት ለመኖር ተገዷል። እንዲህ ትላለች፦

"ህልምሽ ምንድን ነው ተብያለሁ። ህልሜ ለአባቴ ሱፍ መግዛት ነው። ጥሪ ሲኖርበት ልብስ የለኝም ይላል። ደግሞም ለአባቴ ከዚህ ተሻለ ቤት መሥራት። ለእኔ ብሎ አይደል አያቶቼ ጋር የሚኖረው? በቃ ለእሱ ትልቅ ቤት መሥራት"

ይህ ምላሿ ብዙሃኑን አሳዝኗል። የእንርዳሽም ጥያቄ እየቀረበላት ይገኛል።

ዶች ኤችዲ

ለአርቲስት መኮንን ላፅከ ከዩቶፒያ ቴክኖሎጂ (Utopia Technology) የተሰጠ ይፋዊ መግለጫጉዳዩ፦ ለአርቲስት መኮንን ላእከ የመኪና ስጦታን ለማመቻቸት በተደረገው ስምምነት ዙሪያ የተሰጠ...
14/07/2026

ለአርቲስት መኮንን ላፅከ ከዩቶፒያ ቴክኖሎጂ (Utopia Technology) የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ

ጉዳዩ፦ ለአርቲስት መኮንን ላእከ የመኪና ስጦታን ለማመቻቸት በተደረገው ስምምነት ዙሪያ የተሰጠ ማብራሪያ ።

መግቢያ

ዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ለባለድርሻ አካላት ሁሉ ካለው ክብር የተነሳ ይህንን ጉዳይ በዝምታና በግል መፍታት መርጦ የነበረ ቢሆንም፤ ከተለያዩ ግለሰቦችና መገናኛ ብዙሃን የቀረቡልንን ጥያቄዎች ተከትሎ ይህንን ይፋዊ ማብራሪያ ለመስጠት ተገድደናል።

ሰሞኑን አርቲስት መኮንን ላእከ በመገናኛ ብዙሃን ቀርቦ በሰጠው ቃለ-መጠይቅ፤ ኩባንያችን የገባውን ቃል እንዳልጠበቀ አድርጎ በማቅረብ ህዝብን የሚያሳስት እና አጠቃላይ የነበረውን እውነታ ያላካተተ መረጃ አስተላልፏል። በመሆኑም እውነታውን ግልጽ ለማድረግ ሙሉ ዝርዝሩንና የስምምነቱን ሁኔታዎች እንደሚከተለው እናቀርባለን።

የጉዳዩ ዳራ እና የተደረገው ስምምነት

በአርቲስት መኮንን ላእከ የልደት በዓል አከባበር ላይ፣ የልደቱ አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት የዩቶፒያ ቴክኖሎጂን ማኔጅመንት ደጋግመው በመቅረብ ለአርቲስት መኮንን ላእከ መኪና እንዲገዛለት ድጋፍ እንድናደርግ ጠይቀው ነበር። በመጨረሻም ኮሚቴው በባንክ ብድር መኪና እንዲመቻች ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን፤ ስምምነቱም በሚከተሉት ቅድመ-ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነበር፦

* ቅድመ-ሁኔታ 1፦ አዘጋጅ ኮሚቴው ለመኪናው የሚያስፈልገውን ቅድመ-ክፍያ (Advance Payment/Down payment) ያዘጋጃል።
* ቅድመ-ሁኔታ 2፦ ኮሚቴው ወይም አርቲስቱ በባንክ በኩል የሚሰሩትን የብድር ሂደቶች እንድንጨርስላቸው ህጋዊ ውክልና (Power of Attorney) ይሰጡናል።

* ቅድመ-ሁኔታ 3፦ ኮሚቴው የገባው ቃል፤ አርቲስት መኮንን ለአቀ እና የኮሚቴው አባል የሆኑት ሌሎች አርቲስቶች የኩባንያችንን ስም ያስተዋውቃሉ እንዲሁም የኩባንያችን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ይሆናሉ።
* ቅድመ-ሁኔታ 4፦ ከላይ የተጠቀሱት ቅድመ-ሁኔታዎች በሙሉ ሲሟሉ፣ ኩባንያችን መኪናውን በባንክ ብድር እንዲመቻች የሚያደርግ ሲሆን፤ ቀስ በቀስ ግን ባንኩ የሚጠይቀውን ብድር ሙሉ በሙሉ በኩባንያችን በኩል ይከፈላል።

ስምምነቱ ምን ያህል ግልጽ እንደነበር ለማሳየት፣ በወቅቱ በቪዲዮ እንደተመዘገበው የኩባንያችን ማኔጅመንት በክብረ በዓሉ ላይ የተናገረው ቃል ይህንን ይመስላል፦

"ምንም እንኳን በኮሚቴው በኩል መደረግ ያለባቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም፣ በጋራ መኪናውን እናመቻቻለን።"

ይህ የሚያሳየው ኩባንያችን መኪናውን በነጻ ስጦታ አድርጎ ይሰጣል ሳይሆን፤ ከላይ በተገለጹት ቅድመ-ሁኔታዎች መሠረት መኪናውን በጋራ እንደምናመቻች በግልጽ መናገሩን ነው።

ሂደቱ የተስተጓጎለበት ምክንያት

ዩቶፒያ ቴክኖሎጂ የገባውን ቃል በታማኝነት በመጠበቅ መኪናውን አዘጋጅቶ ነበር። ነገር ግን አዘጋጅ ኮሚቴው እና አርቲስቱ የሚጠበቅባቸውን መሠረታዊ ግዴታዎች ሳይወጡ ቀርተዋል፦

1. የውክልና (Power of Attorney) እጥረት፦ አርቲስቱን ወክለን በባንክ በኩል የብድር ሂደቱን ለመጨረስ የሚያስችለንን ትክክለኛ ህጋዊ ውክልና ሊሰጡን አልቻሉም።
2. የቅድመ-ክፍያ አለመፈጸም፦ ለባንክ መግባት ያለበትን የቅድመ-ክፍያ ማስገባት አልቻሉም።

3. ምንም ዓይነት የማስተዋወቅ ሥራ አለመኖሩ፦ ምንም እንኳን ኩባንያችን ይሄንን ጉዳይ አጥብቆ ባይገፋበትም፤ በአርቲስቱም ሆነ በኮሚቴው በኩል የተደረገ አንድም የማስተዋወቅ (PR) ሥራ አልነበረም።

እነዚህ ሁሉ ጉድለቶች እያሉበት እንኳን፣ ዩቶፒያ ቴክኖሎጂ አርቲስቱ እና ኮሚቴው ውክልናውንና የተዘጋጀውን ቅድመ-ክፍያ ይዘው ይመጣሉ ብሎ በመጠበቅ መኪናውን ከ4 ወራት በላይ በሾውሩማችን (Showroom) ውስጥ አቁሞት ቆይቷል። ሆኖም ግን ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላም ምንም ዓይነት ምላሽ ባለማግኘታችን ስምምነቱን ለመሰረዝ ተገድደናል።

ለህብረተሰቡ ያለን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ

ዩቶፒያ ቴክኖሎጂና ባለቤቶቹ ባለፉት አሥርት ዓመታት ላደረጓቸው የበጎ አድራጎት ሥራዎችና ለህብረተሰቡ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ይታወቃሉ። ከእነዚህም መካከል፦

* ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) መኪና በስጦታ ማበርከታችን።
* በምናዘጋጃቸው ታላላቅ ኤግዚቢሽኖችና ዝግጅቶች ላይ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን በነጻ በማስተናገድ የመጀመሪያው በመሆን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ወጪ ማድረጋችን ይጠቀሳሉ።

ለኢትዮጵያ የጥበብ ማህበረሰብና ለአገራችን የጥበብ ፈርጦች ትልቅ ክብር አለን። በአሁኑ ወቅት ከአርቲስት መኮንን ላእከ ጋር የነበረው ስምምነት በሌላኛው ወገን ግዴታዎችን ባለመወጣቱ ምክንያት የቆመ ቢሆንም፤ ዩቶፒያ ቴክኖሎጂ የማህበራዊ ኃላፊነቱን (CSR) መወጣቱን ይቀጥላል። ወደፊትም ለኪነ-ጥበቡ ማህበረሰብ እንደምናደርገው ድጋፍ፣ ይገባቸዋል ለምንላቸው የማህበረሰቡ አባላት ድጋፎችንና የመኪና ስጦታዎችን የማመቻቸት ሥራችንን አናቋርጥም።

ለሚዲያ አካላት

የአርቲስት መኮንን ላእከ ቃለ-መጠይቅ ያስተላለፋችሁ፣ ያሰራጫችሁና ያጋራችሁ ማናቸውም መገናኛ ብዙሃን፣ ጋዜጠኞች እና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች፤ የጋዜጠኝነት የሙያ ስነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ የእኛንም ምላሽ በተመሳሳይ ደረጃና ስፋት ለህዝብ እንድታቀርቡልን በአክብሮት እንጠይቃለን። ተመልካቾቻችሁና አንባቢዎቻችሁ ትክክለኛውንና ሚዛናዊነቱን የጠበቀ መረጃ ማግኘት እንዲችሉ ይሄንን ይፋዊ ማብራሪያ ሙሉ በሙሉ እንድታስተላልፉልን እንጠይቃለን።

ለደንበኞቻችን፣ ለባልደረቦቻችን እና ለጠቅላላው ህዝብ ስለሰጡን እምነትና ድጋፍ እናመሰግናለን።

ከአክብሮት ጋር
የዩቶፒያ ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት

እኔን በመተዉ ሌላ ሴት ሊያገባ ነዉ በሚል በበቀል የፍቅረኛዋን እናት የገደለችዉ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣች የ35 ዓመቷ መሠረት ወርቅነህ ነዋሪነቷ በምዕራብ አርሲ ዞን ነገሌ አርሲ ከተማ ሲሆን...
14/07/2026

እኔን በመተዉ ሌላ ሴት ሊያገባ ነዉ በሚል በበቀል የፍቅረኛዋን እናት የገደለችዉ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣች

የ35 ዓመቷ መሠረት ወርቅነህ ነዋሪነቷ በምዕራብ አርሲ ዞን ነገሌ አርሲ ከተማ ሲሆን ከዚህ ቀደም በነበራት ትዳር ሑለት ልጆች ብታፈራም በፍቺ ትዳሯ መፍረሱን የዞኑ ፖሊስ ዋና መምርያ የወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ከድር ጅቦ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡በ2014 ዓመት መሠረት ልጆቿን የቀድሞ ባለቤቷ ጋር በማስቀመጥ በተለያየ የንግድ ስራ ላይ ተሠማርታ በነገሌ አርሲ ከተማ 01 ቀበሌ መጃ ቂልጦ የተባለ አካባቢ ቤት ተከራይታ መኖር ጀምራለች፡፡ በሂደት ጉተማ ሒርዾ ከተባለ በእድሜ ከእርሷ ከሚያንስ ወጣት ጋር መግባባት ትጀምራለች፡፡

በ2014 የተጀመረው ይህ ትዉዉቅ ወደ ፍቅር ግንኙነት ተቀይሮ ለአራት አመት አብረዉ ይቆያሉ፡፡በድንገት ግን ጉተማ ሌላ ልጅ ሊያገባና ሰርጉ በወላጆቹ ቤት እየተደገሠ መሆኑን እንደሠማች በጣም በመናደድ ክሕደት ፈፅሞብኛል የምትለውን ጉተማን ለመበቀል ትዘጋጃለች።ሚያዚያ 22 ቀን 2018 ዓም ምሽት 12 ሠዓት ላይ የጉተማ ሠርግ አንድ ሣምንት ሲቀረው መሠረት በቀጥታ ወላጅ እናቱ ቤት በመሔድ የስልሣ አመት ወይዘሮ ሚኒሉ ሴፉ አግኝታ በሠላማዊ መንገድ አናግራ ቡና ተፈልቶ እየጠጡ እያለ፣ ወይዘሮዋ ለሰርጉ የሚሆን በርበሬ አነሰኝ ብለው እንደ ወዳጅ ሲያናግሯት ፣ መሠረትም ምን ችግር አለው፣ እኔ ጋ አንድ ኩንታል በርበሬ አለ እንውሰድ ብላ ለእቅዷ መንገድ እንዳመቻቸች በሠጠችው የእምነት ቃል አረጋግጣለች፡፡

ወይዘሮ ምኒሉ ሴፉ በቀጥታ የተባለውን በርበሬ ለመውሰድ ከመሠረት ጋር ወደ ቤቷ ይሔዳሉ።እዚያም ሲደርሱ ምግብ ቀርቦላቸዉ ከበሉ በኃላ ልጆት እኮ እኔን አገባሻለሁ ብሎ ለአራት አመታት አብሮኝ ነበረ ፣ዛሬ ደግሞ ሌላ ሊያገባነው ስትላቸው እናት በርበሬውን ሣይወስዱ ተነስተው ሊወጡ ሲሉ ከኃላ ጭንቅላታቸውን በብረት ዘነዘና በመምታት ከጣለቻቸው በኋላ ደጋግሞ በብረት ዘነዘናው በመምታት ሕይወታቸው እንዲያልፍ በማድረግ በር ዘግታ ዞር ትላለች።

ምሽት ላይ ታናሽ ወንድሟን በመጥራት አስክሬኑን ተባብረው አራት መቶ ሊትር የሚይዝ የውኃ ማከማቻ ውስጥ በመክተት ያድራሉ።በነጋታው መሠረት አባቷን ኮንትሮባንድ እቃ እዚህ ዉሃ ማከማቻ ውስጥ ስላስቀመጥን አንተ ቤት ጓሮ ተሸሽጎ ይቀመጥ ጋሪ ይዘሕ ና በማለት አባቷ ኮንትሮባንድ ነው የተባለው አስክሬን ጭነው ከጓሮ ያስቀምጣሉ።በዚያን እለት ማታ መሠረት ከታናሽ ወንድሟ ጋር በመሆን ጓሮ ውስጥ በመቆፈር አስክሬኑን ይቀብራሉ። ሚያያዝያ 29 ልጃቸውን የሚድሩት ወይዘሮ ድንገት መሠወር ተከትሎ በቤተሠብ ድንጋጤ ፈጥሮ ባለበት ሠዓት ከመሠረት ጋር ተያይዘው ከቤት መውጣታቸው ለልጃቸው ጉተማ ሒርዻ መረጃ ይደርሰውና ለፖሊስ ያመለክታል።ፖሊስም መረጃው እንደደረሰው መሠረት ወርቅነህ እና ታናሽ ወንድሟን ዳንኤል ወርቅነሕን በቁጥጥር ስር ያውላቸዋል።ተከሳሾቹ ድርጊቱን መፈፀማቸውን አምነው ቃላቸውን በመስጠት አስክሬኑን ቆፍረው የቀበሩበትን ቦታ ያሳያሉ፡፡

ፖሊስ አስክሬኑን ለምርመራ ወደ ኩዬራ ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል በመመላክ የምርመራ መዝገቡን ይልካል። አቃቢ በከባድ የሠው መግደል ወንጀልና የተሠራ ወንጀል በመሸሸግ በእሕትና ወንድም ላይ ክስ ይመሠርታል።ክሱን የተመለከተው የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት፣1ኛ ተከሣሽ መሠረት ወርቅነሕ፣ አስቀድማ ሰው ለመግደል አስባ ፣ተዘጋጅታ በብረት ዘነዘና ደጋግማ በመምታት ከገደለች በኃላ የፈፀመችው ድርጊት እንዳይገለፅና እንዳይታወቅባት በማለት በውሐ ማጠራቀሚ ውስጥ አስክሬንን በማስቀመጥና ክብር በሌለው ሑኔታ መቅበሯ ጨካኝ፣ ነውረኛና አደገኛ ነዉ በማለት በሑለት የክስ ማቅለያዎች በሐያ ሶስት አመት እስራት እንድትቀጣ ሲወሠን፣

2ኛ ተከሳሽ ታናሽ ወንድሟና ተባባሪዋ ዳንኤል ወርቅነሕ፣ ወንጀል መፈፀሙን እያወቀ ወንጀል አድራጊው ከተጠያቂነ ለማዳን የረዳ በመሆኑ በአንድ አመት ከዘጠኝ ወራት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ፣ምክትል ኮማንደር ከድር ጅቦ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል። በተጨማሪ ይሕንን ዘገባ በተጠናከረ መንገድ እንድንሰራ የተባበሩንን የነገሌ አርሲ ከተማ ፖሊስ ፅፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ሐላፊ ኢንስፔክተር ወርቁ ሑሪሣና መርማሪ ፖሊስ ዋና ሣጅን ፍቃዱ ጉደታን ብስራት ሬዲዮ ያመሰግናል፡፡

©ዳጉ ጆርናል

በእምነት ተቋም በመግባት ውድመትና ዝርፊያ የፈጸሙ 21 ተጠርጣሪዎች ተያዙ!የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ...
22/06/2026

በእምነት ተቋም በመግባት ውድመትና ዝርፊያ የፈጸሙ 21 ተጠርጣሪዎች ተያዙ!

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አያት 49 ቁጥር-2 የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒም) አካባቢ ነው።

በተጠቀሰው አካባቢ የሚገኝው ባዶ ቦታ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የመንግስተ ሰማይ እንደራሴዎች ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የተወሰነ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑም ግንባታ አድርጎ አገልግሎት እየሠጠበት ይገኛል።

ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሠዓት ላይ ቁጥራቸው 21 የሆኑ የጋራ መኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች በቡድን በመደራጀትና ቦታው የእኛ ነው በማለት የቤተክርስቲያኑን ግቢ በኃይል ሰብረው በመግባት 10,132000 (አስር ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ) ብር የሚገመት ንብረት የመዝረፍና የማውደም ወንጀል ፈጽመዋል።

የወንጀል ድርጊቱ መፈጸም መረጃ የደረሰው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያም በወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑ ግለሠቦች ምንም እንኳን ከአካባቢው ቢሠወሩም ከያሉበት በቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።

በቀጣይ በወንጀሉ ተሳታፊ ናቸው ያላቸው ግለሠቦች ላይ ክስ እንደሚያስመሠርት የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሠል ድርጊቶች የኃይማኖት ግጭት የሚቀሰቅስና ተከባብሮ የኖረውን ህዝብ በጥርጣሬ እንዲታይ የሚያደርግ በመሆኑ ሁሉም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባውም አሳስቧል።!

ፓኪስታናውያን አጋቾች በአዲስአበባ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎችን በመያዣነት በመጠቀም ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የጠየቁ ሦስት ፓኪስታናውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ። የፓኪስታን...
22/06/2026

ፓኪስታናውያን አጋቾች በአዲስአበባ

ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎችን በመያዣነት በመጠቀም ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የጠየቁ ሦስት ፓኪስታናውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የፓኪስታን ዜግነት ያላቸው ዝሻን ካሊድ፣ ፍርዝ መሃመድ እና መሀመድ ጀናይድ የተባሉ ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሰኔ 4 እና ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ አትሌቶች መንደር ነው።

ተጠርጣሪዎቹ በተከራዩት የመኖሪያ ቤት ውስጥ የህንድና የባንግላዴሽ ዜግነት ያላቸውን ግለሰቦች በመያዣነት በመጠቀም የግል ተበዳዮችን በገመድ በማሰርና በፕላስተር በማፈን ከ15 እስከ 30 ሚሊየን ብር በመጠየቅ ጥቃት አድርሰውባቸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በዚህ ብቻ ሳያበቁ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት የገቡ 4 የህንድ ዜጎችን በማሰርና በመደብደብ ከ15 እስከ 25 ሺህ የህንድ ሩፒ አስልኩ በማለት ድብደባ ሲፈጽሙባቸው እንደነበር የግል ተበዳዮች ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

የወንጀሉ መፈጸም መረጃ የደረሰው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ተገቢውን የፍርድ ቤት መያዣና የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ባከናወነው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን ለወንጀል ድርጊት ሲጠቀሙበት ከነበረው ቢላዋ፣ ገመድና ፕላስተር እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገር ገንዘቦች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠርጣሪዎቹ እንዲያዙ መረጃ በመስጠት ላደረጉት ቀና ትብብር ምስጋናውን ያቀረበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙም ለፖሊስ መረጃ መስጠት እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል።

(ዘገባ፦ ዋና ሳጅን አዳነ ደስታ - አ/አ ፖሊስ)

በአክሱም ከተማ የ2 ዓመት ህፃን ልጅ አግተው 7 መቶ ሺህ ብር የተቀበሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ ሰለሞን ግደይ የተባለው ህፃን ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 አካባቢ በአክሱ...
22/06/2026

በአክሱም ከተማ የ2 ዓመት ህፃን ልጅ አግተው 7 መቶ ሺህ ብር የተቀበሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሰለሞን ግደይ የተባለው ህፃን ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 አካባቢ በአክሱም ከተማ አባይ ጸሃይ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በሁለት ወጣቶች በምስጢር ተጠልፎ ተወስዷል።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተባባሪዎቻቸውን ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎችን በዓድዋ ከተማ በቁጥጥር ስር በማዋል መደበኛ ምርመራ መጀመሩን ገልጿል።

ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የመኖሪያ አድራሻቸው ጭላ፣ ማይቅነጣል፣ ዓድዋ እና እንጮ በሆኑት በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ የማጣራት ስራ መከናወኑን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

በተደረገው ማጣራት መጀመሪያ ላይ ወርቅ ለማውጣት እንሄዳለን በሚል ምክኒያት ለአምስት ቀናት ቤት ተከራይተው የቆዩ መሆናቸው ታውቋል። ይሁን እንጂ ተጠርጣሪዎቹ በሂደት ሌላ የወንጀል እቅድ በመንደፍ ህፃኑን ከቤቱ ደጃፍ መጥለፉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ።

የምስክር መረጃ ለማጥፋት ምንም ዓይነት የትራንስፖርት አማራጭ ሳይጠቀሙ በጀርባቸው አዝለውት በጫካ በመጓዝ ዓድዋ ከተማ ውስጥ ደብቀውት እንደነበር የዞኑ ፖሊስ አብራርቷል።

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን በጥንቃቄ ከፈጸሙ በኋላ ለህፃኑ ማስለቀቂያ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ጠይቀዋል።ከዚህም ውስጥ 750 ሺህ ብር ተልኮላቸው የነበረ ቢሆንም የአክሱም ከተማ ፖሊስ ባደረገው ስኬታማ ክትትል ህፃኑን በሰላም ለቤተሰቦቹ ማስረከብ ችሏል።

ከተላከው ገንዘብ ውስጥ 40 ሺህ ብር ብቻ እንደጎደለ ተገልጿል።ከ710 ሺህ ብር በላይ የሚሆነው ገንዘብም ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ኤግዚቢት ሆኖ መያዙን የገለጸው የፖሊስ መምሪያው በአሁኑ ወቅት በአምስቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ሙሉ ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተናግሯል ።

Via በሰብል አበበ
©️ዳጉ_ጆርናል

ጉርሻ Page

🌴🌴🌴

ታዳጊዉን ሙሉ ወጭ በመሸፈን የምታስተምረው ደግ ተገኘች ! በተለያዩ በጎ ስራዎች የምናዉቃት ሊሊ በላይ  የእናቱን አስክሬን ቤት አስቀምጦ የእናቱን ቃል ለማክበር የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ.... ...
22/06/2026

ታዳጊዉን ሙሉ ወጭ በመሸፈን የምታስተምረው ደግ ተገኘች !

በተለያዩ በጎ ስራዎች የምናዉቃት ሊሊ በላይ የእናቱን አስክሬን ቤት አስቀምጦ የእናቱን ቃል ለማክበር የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ....

ፈተና ከቀብር በፊት እና በኃላ ለፈተና የተቀመጠው ካሊድን ሙሉ ወጭ በመሸፈን ማስተማር እንደምትፈልግ ገለፀች ።

ሊሊ በማህበራዊ ሚዲያ በኩል ባስተላለፈችዉ መልዕክት ይሂን ልጅ አፋልጉኚ እራሳቸዉን እስኪችሉ የትምህርት ቤት የቤትክራይ ከፋዬ ሰራተኛ ቀጥሬ ከግል ትምህርት ቤት ላስተምረዉ ። ስትል ገልፃለች ።

እህት ሊሊ በላይ ሀገሯን አብዝታ የምትወድ እና ፍቅሯንም በተግባር የምትገልጽ መሆኗን የሚያሳዩ ስራዎችን ህያው ምስክር ናቸው ።

ለምሳሌ ባለፉት ዓመታት በአዘዞ ቀበሮ ሜዳ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጋለች ከአልማ ጋር በመተባበር በጎንደር ከተማ ደረጃውን የጠበቀ ት/ቤት ገንብታ አስረክባለች።

በተለያዩ ማህበራዊና የኢኮኖሚ ችግር ለገጠማቸው ለተማሪዎች የህክምና ወጭ ለሚያስፈልጋቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያለመሰልቸት ለሰብአዊ አገልግሎት ለምና ሳይሆን ካካበተችው ከራሷ ሃብት ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ።

የሊሊ በላይ የተሰኘ የልጆች የእግር ኳስ ቡድንም አላት ። እነዚህንና ሌሎችም ሰብዓዊ ተግባር ላይ የተሰማራችው ሊሊ በቅርቡ በርካታ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ ራሳቸውን የሚችሉበት በተለይም ወጣቶች የስራ እድል የሚያገኙበት ግዙፍ ፕሮጀክት ይዛ እየመጣችም መሆኑን ስምቻለሁ ።
Via፦ ታዴ የማመይ ልጅ

ዕድሜ ያበስላል ብሩክታዊት ሽመልስ በሰለች! 👌🏾❤️ ግን ላጥ እያሉ ዱባይና ሲሼልስ ሻይ ቡና ብለው ስለሚመለሷት ነገር ሲጠየቁ "እኔ ኦንላይን ቢዝነስም እሠራለሁ" የሚሏት አማርኛ "የማይመስል...
22/06/2026

ዕድሜ ያበስላል ብሩክታዊት ሽመልስ በሰለች! 👌🏾❤️

ግን ላጥ እያሉ ዱባይና ሲሼልስ ሻይ ቡና ብለው ስለሚመለሷት ነገር ሲጠየቁ "እኔ ኦንላይን ቢዝነስም እሠራለሁ" የሚሏት አማርኛ "የማይመስል ነገር" ነው። በተለይ ወንድ አርቲስቶች ሚዲያ ላይ ወጥተው ተራብን በሚሉበት አገር፣ አርቱ screensaver መሆኑ ግልጽ ነው። የገንዘብ ምንጫቸውን ባይናገሩ እንኳን ምናለ ደህና መሸፈኛ ቢፈልጉለት? የለም.... የሆነ static websiteም ሊሆን ይችላል እኮ። የእሷን ይዘን እናውራና፣ ቢ ብራይዳል የተባለውን የዘጋችውን ቢዝነስ ሊንክ ፕሮፋይሏ ላይ አድርጋዋለች። እንዴት ነው ታዲያ የኦንላይን ቢዝነሷን የማታስተዋውቀው? ሰው ቢያንስ ደንበኛ ፍለጋ፣ ለሥራ ብሎ አያስተዋውቅም ወይ፥ ኣንድ ሚሊዮን ተከታይ ይዞ? 🤨

ያስደነገጠኝ ትናንቷን የረሳችበት ፍጥነት እና ወደ ኋላ ማስታወስ የማትፈልግበት ጥንካሬ።

Molla

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category