
08/01/2025
አቤት የጃውሳ ጉድ
አስረስ ማረ የውባንተ አባተ ባለቤት ላይ የግድያ ዛቻ እያደረሰ ነው!
ዉባነተ አባተ የተባለ የጃውሳ አመራር በመከላከያ ሰራዊቱ በተወሰደበት እርምጃ መሸኘቱ የሚታወቅ ሲሆን ዉባንተ ከመገደሉ በፊት ከዘመነ ካሴ እና ከአስረስ ማረ ጋር ለግድያ ሲፈላለግ እንደነበር በየጊዜው ከቡድኑ አፈትልኮ የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ዘመነ እና አስረስ በውባንተ መገደል ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የደስታ ስሜት ሲያንፀባርቁ እንደነበረም የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
እነዚህ ዉባንተን ለመግደል ብዙ ሲያሴሩ የቆዩት የቡድኑ አመራሮች ሰሞኑን የዉባንተን ባለቤት ሊገድሏት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነም የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ምክንያታቸውም የዉባንተ አባተ ባለቤት አስረስ እና ዘመነ ልጆቼን የማሳድግበትን መኪና አዘርፈውኛል በማለት ለሃብታሙ አያሌው መረጃ በመስጠቷ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ከዚህም የተነሳ አስረስ ሃብታሙ መረጃውን ሚዲያ ላይ የሚያውለው ከሆነ እንገድልሻለን በማለት የዉባንተን ባለቤት እያስፈራራት እንደሆነ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።