All About Bahir Dar

All About Bahir Dar News, Business Directory & Entertainment Portal. Email: [email protected]

Welcome to All About Bahir Dar page. ‘Allbahirdar.com is an innovative site where fresh and amazing things can be found about Bahir Dar, Ethiopia & beyond. We have created a platform that caters to a wide audience by providing up to date information on restaurants, hotels, arts, music, resorts and much more. There are various features that make ‘Allbahirdar.com a unique website, we invite you to read further and discover all that ‘Allbahirdar has to offer.

ያለ ማህፀን ነው ያደገው የሰው ፅንስ እውነት ሰው ነው። በሳይንስ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል የሚገኘው የዊዝማን የሳይንስ ተቋም ተመራማሪዎች ሙሉ በሙሉ ሰው ሰራሽ የሆነ የሰው ል...
05/06/2025

ያለ ማህፀን ነው ያደገው የሰው ፅንስ እውነት ሰው ነው።

በሳይንስ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል የሚገኘው የዊዝማን የሳይንስ ተቋም ተመራማሪዎች ሙሉ በሙሉ ሰው ሰራሽ የሆነ የሰው ልጅ ፅንስ በተሳካ ሁኔታ ማሳደግ ችለዋል:: ከወንድ ዘር እና እንቁላል ሳይሆን ሙሉ በሙሉ እንደገና ከተዘጋጁ ግንድ ሴሎች። ያለ ማህፀን ነው ያደገ ነው::

በልዩ የሚሽከረከር ጠርሙስ ኢንኩቤተር ውስጥ ያደገው የፅንስ ሞዴል፣ አንጎል የሚመስል መዋቅር፣ የልብ ቀዳሚ፣ እርጎ ከረጢት እና ሌላው ቀርቶ የአካል መፈጠር የመጀመሪያ ምልክቶችን ፈጠረ ሁሉም በ14 ቀናት ውስጥ ነው። አንድም ሰው ሰራሽ ፅንስ ከዚህ በፊት ይህን አላደረገም። ሳይንቲስቶች በኬሚካል የተቀናበሩትን ሁሉንም ዋና ዋና የፅንስ ቲሹዎች ለመመስረት የተጠቀሙት የሰው ግንድ ሴሎችን ብቻ ነው:: ምንም አይነት የዲኤንኤ ማስተካከያ እና ክሎኒንግ ሳይኖራቸው።

ይህ አዲስ ዘዴ ከቀደምት ኦርጋኖይድ ወይም ከፊል አወቃቀሮች የበለጠ በትክክል የተፈጥሮ እድገትን ያስመስላል። እውነተኛ ፅንስ እንዴት እንደሚፈጠር፣ እስከ ሲሜትሪ፣ የሕዋስ ግንኙነት፣ እና የአካል ክፍሎች እና እግሮች መፈጠር ድንገተኛ ክፍል መፈጠርን እንደገና ይፈጥራል።

ይህ ማለት የሚያስደነግጥ ነው። የሳይንስ ሊቃውንት የመጀመሪያዎቹን ሁለት ሳምንታት የሰው ልጅ እድገት በትክክል የሚከታተሉበት መንገድ አላቸው - ይህ ደረጃ በማህፀን ውስጥ የማይታይ ነው። ይህ ቀደም ባሉት ጊዜያት የፅንስ መጨንገፍ፣ የመትከል ውድቀት እና የትውልድ በሽታ መንስኤዎችን ሊገልጽ ይችላል፣ ይህም ቀደም ባሉት ጊዜያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ሊያድን ይችላል።

ግን ጥልቅ ጥያቄዎችን እንድንጋፈጥም ያስገድደናል። እነዚህ ገና ወደ ሕፃናት ሊያድጉ የሚችሉ እውነተኛ ሽሎች አይደሉም። ግን እነሱም ሙሉ በሙሉ ሰው ሠራሽ አይደሉም. ችላ ለማለት ተፈጥሮን በጣም በቅርበት ይመስላሉ። በህይወት እና ሞዴል መካከል ያለው ድንበር የት ነው? በስነምግባር እና በአስፈላጊነት መካከል?

የሰው ልጅ ይህንን ግኝት ለመፈወስ - ወይም ህይወትን ለመቆጣጠር ይጠቀምበት - የወደፊቱን ክፍለ ዘመን ይገልፃል።

 #ዋጋችንን ልያሳጡ የሚችሉ ጉዳዮች❗1.ከልክ በላይ መለማመጥ ❗2.ምንም አማራጭ የለኝም ማለት ❗3.ለሰው ጆሮ መሆን ❗4.ሳይጋበዝ መገኘት ❗5.ሀሉንም አውቃለሁ ማለት❗6.በተደጋጋሚ ምሰጥር ...
28/05/2025

#ዋጋችንን ልያሳጡ የሚችሉ ጉዳዮች❗
1.ከልክ በላይ መለማመጥ ❗
2.ምንም አማራጭ የለኝም ማለት ❗
3.ለሰው ጆሮ መሆን ❗
4.ሳይጋበዝ መገኘት ❗
5.ሀሉንም አውቃለሁ ማለት❗
6.በተደጋጋሚ ምሰጥር ማባከን❗
7. ሁል ጊዜ በሰው ጉዳይ ጣልቃ መግባት ❗
8.ሁል ጊዜ የሚታወቀውንም በቸልተኝነት መተው❗
9.ንቀት
10.የሁሉንም ሰው ምክር መቀበል ❗
12.ሁል ጊዜም ቀልደኛ መሆን❗
13.በአደባባይ መሳደብ ❗
14.ሁል ጊዜ ማድነቅ ❗
15.አግዘኝ ሳይባል አዘውትሮ ለሌላ ማገልገል❗
16.ሁል ጊዜ ጋባዥ መሆን❗
17.ሁል ጊዜም ተጋባዥ መሆን ❗
18.ከሴት ጋር መደባደብ፣ ❗
19.በሴት ቁጥጥርና ውሳነ ሁል ጊዜ መጓዝ ❗
20.ባለ ትዳር ሆኖ ያለ ምክንያት ሁል ጊዜ ከውጪ መመገብ ❗
21.በተደጋጋሚ መጣላት በተደጋጋሚ መታረቅ ❗
22.ከአማች በተደጋጋሚ መበደር ❗
23.በውሸት መመሰከር ❗
24.ሁል ጊዜ የሰውን መናገር ❗
25.ወልዶ አለማሳደግና መተው ❗
26.ዘማዊ መሆን❗
27.ከምሰትየው እጅ መብላትና መሰረቅ❗
28.የሰውን ችግር አለመካፈል ❗
29. ለራስ ከፍተኛ ግምት በመስጠት መቆለል❗
30.የቤት ውሰጥ ሥራውን መምረጥ❗
31.ልጆቹን አለመቅጣት ❗
32.ንቀትና ፍራሃት❗
33.የሰውን አለማዳመጥ፣የራሱን ብቻ መናገር ❗
34.ቃል መግባት ❗
35.ደረጃውንና ውሎውን አለመምረጥ❗
36.ቁማርተኛ መሆን፣ትርፍና ዋናውን መብላት ❗
37.ገጣገጥ ሽቶ እና ኮተቴ ላይ ገንዘብን ማፍሰስ❗
38.ለሠርግ ቤትንና መሬትን መሸጥ➤ታሪካዊ ሰህተት እና የሚያሰንቅ ነው።
39.ንብረትን ለአላሰፈላጊ ጉዳይ ተያዥ ማድረግና መበደር❗
40. .....................................................❗..ወዘተ ናቸው ❗
page
ከተመቸ ለሌሎች አጋሩ ?
Next topic,loading....❗

Are you interested in reading my story on   in the Blue Nile River and the efforts to combat it? I've witnessed firsthan...
21/08/2024

Are you interested in reading my story on in the Blue Nile River and the efforts to combat it? I've witnessed firsthand the power of solutions journalism in addressing this critical issue. I would love to hear your thoughts and feedback. Your comments are invaluable as we continue to raise awareness and drive change

Communities around the River Nile and Lake Tana still rely on the river to wash clothes and bathe — some who also depend on raw water for drinking face increasing waterborne diseases. Studies show plastic pollution is the biggest threat to the Lake’s biodiversity.

I am a journalist, managing content and Ethiopian stories for Africa News Channel (an English media outlet) and EMMA NEW...
21/08/2024

I am a journalist, managing content and Ethiopian stories for Africa News Channel (an English media outlet) and EMMA NEWS (an Amharic media language outlet). Journalism isn't just my profession; it's my calling and passion—I was born to tell stories that matter. You can find my work everywhere, from investigative pieces to in-depth analyses that resonate globally. I regularly contribute articles that capture the essence of Ethiopian life, culture, and pressing issues. I am a media educator who loves to teach journalism with visible examples. Stay connected to my latest stories and insights, which you can read regularly here😍🥰 :

Injustice for Heaven: The Brutal R**e and Murder of a Seven-Year-Old Sparks Outcry for Child Protection in Ethiopia

18/08/2024

The Brutal R**e and Murder of a Seven-Year-Old Sparks Outcry for Child Protection in Ethiopia
Heaven's mother, a dedicated surgical assistant nurse with over seven years of experience, was on duty when she received the devastating news that her young daughter had died. The details of Heaven's final moments are too horrifying to comprehend fully. While her mother was away at work, the perpetrator, a man with no previous criminal record, lured Heaven into his home under the guise of friendliness. Once inside, he forced sand mixed with pebbles into her mouth, held her down, and violently assaulted her. It was too late when Heaven's younger sister discovered what was happening. Despite attempts to save her, Heaven succumbed to the injuries inflicted upon her.
"Heaven was just an innocent child, full of life and dreams," her mother said in a tearful interview. "No mother should have to bury their child, especially not like this. Where is the justice for my daughter? How can someone who committed such a brutal act walk free after just a few years?"

https://www.africanewschannel.org/female/injustice-for-heaven-the-brutal-rape-and-murder-of-a-seven-year-old-sparks-outcry-for-child-protection-in-ethiopia/
https://www.africanewschannel.org/female/injustice-for-heaven-the-brutal-rape-and-murder-of-a-seven-year-old-sparks-outcry-for-child-protection-in-ethiopia/

ኢንተርኔትን እንደጦር ሜዳ መጠቀመው የሚቀለው መንግስት፤ ከአንድ አመት አፈና በኃላ Internet: The New Weapon of War and Battleground for Control, Infor...
16/07/2024

ኢንተርኔትን እንደጦር ሜዳ መጠቀመው የሚቀለው መንግስት፤ ከአንድ አመት አፈና በኃላ Internet: The New Weapon of War and Battleground for Control, Information, and Freedom Ethiopia
የወቅቱ ገዥ ፓርቲ በአማራ ክልል ለአንድ አመት ኢንተርኔትን ዘግቶ ፣ የዜጎችን ሀብት አባክኖ፣ የሰበዓዊ መብት ጥስቶች፣ የንፁሀን እምባ እና ጩኸት እንዳይሰማ ያለውን የአፈና አቅም ሲጠቀም ከርሟል፡፡ በእርግጥ ዴሞክራሲ በልመና የሚመጣ፣ እድገት በአፈና የማይሳካ ቢሆንም ሀገሪቱን ወደ ድሪቶነት በመቀየር፣ የዜጎችን ማህበራዊ እረፈት በመንሳት በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርተው እንዳይወስኑ የሀሳብ ሚዛን እንዳይኖራቸው አድርጎ ቆይቷል፡፡ ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን በቅርቡ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ ሀገራት በኢንተርኔት አፈና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን መረጃ የማግኘት መብት ነፍጓል። የሰዎች መረጃ የማግኘት መብት ከሰብዓዊ መብቶች ውስጥ አንዱ በመሆኑ መረጃን ማገድ ሰብዓዊ መብትን ማገድ ነው። በዚህ ረገጣም በመላው አማራ ለጆሮ የሚቀፉ ጅምላ ግድያዎች የአለመምነን አይንና ጀሮ ሳያገኙ ታፍነዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሚሊዮኖች የሚኖሩባቸው የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከኢንተርኔቱ ዓለም እንዳይገናኙ ከተዘጋባቸው ሰነባብተዋል። ሌላው ቀርቶ የቀጥታ ስልክ መስመር አገልግሎት የማያገኙ አካባቢዎች እና ከተሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ። በኢትዮጵያ አንዳች ነገር ኮሽ ሲል የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ማቋረጥ መንግስት ቀድሞ የሚመጣለት የስልጣን መጠበቂያ ስልቱ ነው፡፡ መረጃን እና ሃሳብን የሚፈራ መንግስት ኢንተርኔት በመዝጋት ወይስ ለጥያቄዎች መፍትሄ ማበጀት ይበጀው ይሆን የሚለውን ለመመለስ ለአቅም አደም የደረሰ አይመስልም።

አውራ መንገዶችን ዘግቶ፣ ግንኙነትን አቋርጦ ፣ የሀሳብ ሙግቶችን ሸሽቶ፣ የራሰን የሚዲያን ልሳን ብቻ ከፍቶ፣ ሸሚዝ ቀንፎ እየፎክሩ ከድሮን እየተጠቀመ፤ ድረ ገፅ እያፈነ፡- መረጃ እያቀበ ፣ ሃሰብ እያፈነ፣ ኢንተርኔት እና ግበዓት እየከለከለ የወውገጊየያ ስልት እንደነደፈ ከረመ፡፡ እኔን ካላመለካችሁ … እኔን ብቻ ካልሰማችሁ የሚሉ መንግስታት ኢንተርኔትን እንደጦር ሜዳ ይዋጉበታል፡፡ ቴክኖለጅዎችን ለስለላ ፣ አልሳካ ሲልም ለእቀባ እና ክልከላ ለአፈና መጠቀም መለያቸው ነው፡፡
የኢንተርኔት መዘጋት ጫናዎቹ ከምንም ጊዜ በላይ በምርጫ እና በተቃውሞ ወቅት እንደሚበረታ ሂዩማን ራይት ዎች የገለፀው ድርጅቱ ፤ ከዚህ ዓመት መጀመሪያ አንስቶም ኢትዮጵያን ጨምሮ ዋና ዋና የኢንተርኔት መዝጋቶች መመዝግባቸውን አክሰስ ናው Access Now እና ከተባሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መረጃ ማግኘቱን ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን Reporters sans frontières / Reporters Without Borders / RSF አመልክቷል። በእርግጥ በሽዎች እንደዜ ለአንድ አመት የከፈልነው ፓኬጅ በመንግስታዊው ኢትዮቴሌኮም Ethio telecom ያለአገግባብ ተበላ፡፡ ሀገሪቷንም በኢንተርኔት አፈና ምክንያት መንግስት ሚልዩን ዶላሮችነን እያሳጣት እንደሆነ Access Now ይገልፃል፡፡ ቡድኑ አያይዞም የእነዚህ ሃገራት መንግሥታት የተለያዩ አጋጣሚዎችን የፕሬስ ነፃነትን እና የመረጃ ተደራሽነትን ለመገደብ እንደ መሳሪያ እንሚጠቀሙ ገልጿል።
ሃሳቡ የማይሳካ ፣ ሳንሱሩ የማይሰምር ቢሆንም አሁን የኢንተርኔት ሳንሱር፡ የስልጣን መቆጣጠሪያ መሳሪያ ሁኗል፡፡ በዚህ የዲጂታል ዘመን በይነመረብ ላይ የተካሄደው ቁጥጥር፣ የመረጃ እና የነጻነት ፊልሚያ የጦር ሜዳ ሁኖ እንድንመለከተው ሆኗል። በአለም ላይ ያሉ ፈላጭ ቆራጭ መንግስታት የኢንተርኔት ሳንሱርን እንደ ሃይለኛ መሳሪያ በመጠቀም የሀሳብ ልዩነትን ለመጨፍለቅ፣ የራሳቸውን ብቻ ትረካዎችን ለማሰተጋባት እና በስልጣን ላይ ያላቸውን ቁጥጥር ለማስቀጠል የሚጠቀሙበት ሰልት ነው።
«በኢትዮጵያ ግጭትም ይሁን አለመግባባትም ይሁን ወይም የህዝብ ተቃዉሞ በተነሳ ቁጥር የመጀመሪያው በመንግስት ጥቃት የሚፈፀምበት የመገናኛ ዘዴ ኢንተርኔት ነው።በፊት የተለመደ ወይም ብዙ የሚወራለት ራዲዮ እና ቴሌቪዥን የመሳሰሉትን ጃም ማድረግ ወይም እዚያ አካባቢ እንዳይሰማ ማድረግ ነበር።አሁን ግን የመንግስት እርምጃ ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰራጭ ስልክም ጭምር መዝጋት ነው።ቀደም ሲል በምዕራብ ኦሮሚያ ወለጋ አካባቢ ጥቃት እና ግጭት ደረሰ ሲባል ኢንተርኔት ስልክም ጭምር ተዘግቶ ነበር።» ከዚያ ቀጥሎ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል የተከሰተውን አለመግባባት ተከትሎ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተዘጋ።ከዚያ ቀደም ብሎ ደግሞ«የሰሜን ኢትዮጵያ በምንለው ጦርነት ውጊያ በነበረባቸው አካባቢዎች በተለይ በትግራይ የስልክ መገናኛ ሁሉ ተቋርጦ ነበረ።
የኢንተርኔት አፈና በመጠቀም ህዝብን ከመረጃ ውጭ ያደረገው መንግስታዊ ዘዴ የመናገር ነፃነትን ከማፈን ባለፈ የዲሞክራሲ መርሆችን እና ሰብአዊ መብቶችን ጥሰዋል። የዲጂታል ፈላጭ ቆራጭነት መነሳት የኢንተርኔት ሳንሱር አዲስ ክስተት አይደለም፣ ነገር ግን አተገባበሩ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ደረጃ ላይ ደርሷል። እንደ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ኢራን እና ሰሜን ኮሪያ ያሉ መንግስታት የመስመር ላይ ይዘትን ለመቆጣጠር፣ ለመገደብ እና ለመቆጣጠር የተራቀቁ ዘዴዎችን ፈጥረዋል።

የመረጃ ተደራሽነትን ከመገደብ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የመረጃ አቅራቢ ጋዜጠኞችን ማሰርም ሌላው የጥቃት ገፅታ ነው። «ሰዎች መረጃ የማግኘት መብት መንፈግ ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኞችም በአጠቃላይ የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎች ስራቸውን እንዳይሰሩ ነው የተደረገው።በነገራችን ላይ ኢንተርኔት በመዝጋት ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞችን ወይም ነፃ ነን ብለው በየ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰሩ ወይም መረጃ የሚያሰራጩ ሰዎችን ማሰር ጭምር አለ። መንግስት ሀሳብ ይፈራል የሚሉት አሰተያየት ሰጭዎች በጣም እንዳሳሰባቸው ይገልፃሉ። የሰዎችን መረጃ የማግኘት መብትን መንፈግ ከሰብዓዊ መብት አንዱ ነው።ሰብዓዊ መብትን ከመርገጥ የሚቆጠር ነው።ይህም በጋዜጠኞች አቅም ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ህዝቡ መጠየቅ አለበት። የወደፊቱ ሂደት እንዴት ሊቀጥል ይችላል የሚለውም ብዙ ሊያነጋግር ይችላል።»
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) Ethiopian Human Rights Commission Ethiopian Human Rights Council Ethiopian Human Rights Defenders Center-EHRDC Center for Advancement of Rights and Democracy - CARD ለእሥር ከተዳረጉት ውስጥ አብዛኛዎቹ የተያዙት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሆኑን ማረጋገጣቸውን በተለያየ ጊዜ ያወጡት ሪፖርት ያሳያል፡፡ ተጠርጣሪዎች በሚያዙበት ወቅትም ሆነ ከተያዙ በኋላ ሰብዓዊ መብታቸው በተጠበቀ መልኩ ሕግን ተከትሎ እንዲሠራ «በአገር ውስጥ ያሉ ሚዲያዎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዳይችሉ የሚደረጉ ጫናዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ» ጠይቀዋል ።
ፍሪደም ሃውስ Freedom House የተሰኘው በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የክትትል ድርጅት እንዳለው ከሆነ ላለፉት አመታት ኢትዮጲያ የኢንተርኔት ነፃነት የሌላት ሀገር ናት ይላል፡፡ የፍሪደም ሃውስ የቴክኖሎጂ እና ዲሞክራሲ ዳይሬክተር አድሪያን ሻባዝ "ወንጀሉን እየመሩ ያሉት አምባገነን መንግስታት ባለስልጣናት የኢንተርኔት ሳንሱርን በመጠቀም ተቺዎችን ዝም ለማሰኘት እና የመረጃ ፍሰትን ለመቆጣጠር እየሰሩ ነው" ብለዋል። "ይህ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ እና መረጃ የማግኘት መሰረታዊ መብቶች ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ነው፡፡"
የሳንሱር ቴክኒኮች በአምባገነን መንግስታት የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች ይለያያሉ ነገር ግን አንድ አይነት አፋኝ ናቸው፡፡ የኢትዮጲያ መንግስትን ድህረ ገጽን ማገድ እና ማጣራት፣ የዲጅታል ሰራዊት በማሳተፍ የሚዲያ ታጋይ ፣ የግበረ መልስ ተፋላሚ ሃይላትን ማደረጃት፣ የሃሳብ ልዩነትን ወይም ገለልተኛ ዜናን የሚያቀርቡ ድረ-ገጾችን የሀሰት ሪፖርት አድራጊ ቡድኖችን በማደራጀት ከማዘጋት እስከ እንዳይጎበኙ ማገድ የሚደረሱ ርምጃዎች ታይተዋል።
በኢትዮጲያ ቦዘኔ የወቅቱን ገዥ ሃሳብ ከምክንያታዊነት ይልቅ ፣ በጥቅማ ጥቅም ታፍነው ‹‹ከማች ተዋጊዎች›› ሀሰተኛ ሪፖርት ለካምፓኒዎች በማቅረብ አካውንቶችን ለማሰለብ ይሰራሉ፡፡ ነፃ ሃሳብ አቅራቢዎች ለማሽማቀቅ ይዘምታሉ፡፡ ጠንካራ ትችት ያላቸው የይዘት ሃሳቦችን ለማስወገድ፡ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ክትትል ያደረጉባቸዋል፣፡ ነፃ ሃሳብ አቅራቢዎች በዚህም ክትትል እና ማስፈራራት፡ የሚዲያ ላይ እንቅስቃሴዎች በቅርበት ክትትል የሚደረግባቸው ሲሆን ግለሰቦች በዚያው የሚዲያ አይነት በመግለጻቸው ምክንያት ትንኮሳ ወይም እስራት ደርሶባቸዋል።
የወቅቱ ገዥ ፓርቲ የሚመራው መንግስትን ተኮረ ትችት በማህበራዊ ሚዲያ የሚፅፉ ዜጎች በፅሁፎቻቸው ምክንያት ዜጎች እንደታስሩ ይታወቃል።
በማህበረሰቡ ላይ ያለው ተጽእኖ
የኢንተርኔት ሳንሱር ተጽእኖ ጥልቅ እና ሰፊ ነው። ምን መረጃ ተደራሽ እንደሆነ በመቆጣጠር አምባገነናዊ ገዥዎች የህዝቡን ግንዛቤ በመቆጣጠር፣ አንድ ገፅ ብቻ እንዲቀርብ በማድረግ ራሳቸውን የህጋዊ ሌላውን የህገወጥ ገጽታ ለማስጠበቅ ይሰራሉ። ይህም ተቃውሞን ከማፈን ባለፈ በዜጎች መካከል የፍርሃትና ራስን በዝምታ እንዲሸበቡ ሳንሱርን ፈጥሯል።
ማጠቃለያ
የኢንተርኔት ሳንሱር ፈላጭ ቆራጭ ገዥዎች ቁጥጥርን ለመጠበቅ ምን ያህል ጊዜ እንደሚሄዱ የሚያሳይ ትልቅ ማስታወሻ ነው። ቴክኖሎጂ እያደገ ሲሄድ የአፈና ዘዴዎችም እየጨመሩ ናቸው።

የወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር የሽለመው ሚዲያዎችን ወይስ ራሱን? ተሸላሚ  ? Silenced Voices: How Politics Chokes Ethiopian Media? ተሸለሙ የተባሉት ሚዲያዎች ከሚሰ...
12/07/2024

የወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር የሽለመው ሚዲያዎችን ወይስ ራሱን? ተሸላሚ ? Silenced Voices: How Politics Chokes Ethiopian Media? ተሸለሙ የተባሉት ሚዲያዎች ከሚሰሯቸው ዜናዎች እና ፕሮግራሞች የህዝብ ድምፅ የሌላቸው፣ ሳቢነት፣ ማራኪነት፣ ችግር ፈችነት፣ የሁሉንም ድምፅ ማሰማት የጎደላቸው ናቸው፡፡ በፍጥነትና በጥራት ተዘጋጅተው የሚቀርቡ አይደሉም። ሳቢነት ይጎድላቸዋል። ጥልቀት ያንሳቸዋል። ዜናዎቹ ተከታታይነት የላቸውም። በዳራ የበለፀጉም አይደሉም። ተሸላሚ ተቋማት የሚያቀርቧቸው ዜና ሀተታ፣ ፊቸርና ዜና ትንታኔዎች በጅምር ያሉና ሙያው በሚፈልገው መጠን ያልበሰሉ ናቸው። እያዋዙ የሚያስተምሩ ፣ ዝርዘር መረጃ የማይሰጡ ፣ የማያሳውቁና የማያዝናኑ ናቸው።
እንደአንድ የሚዲያ መምህር ዘርፈ ብዙ ጥቃት በተነጣጠረበት ሁኔታ ውስጥ ሁነን የመንግስትን ብረት ለበስ እጆች ፈርተን ዝም ማለት አንችልም፡፡ we should reveal what is going on "Behind the Curtain: Ethiopian Media's Struggle with Political Intrigue" ሙያውን ቢያንስ ማራከሱ መቆም አለበት፡፡ እነዚህ ሁሉ ሚዲያዎች ለኢትዮጱያ ህዝብ ምኑ ናቸው? አንዳቸውም ለመሸለም ፣ የቀረቡት የሚዲያ መሪዎች መሪውን ስለሚፈርቱ እንጅ በስራቸው ኮርተው እንደማይሆን እርግጠኛ ሁኖ መናገር ይቻላል፡፡ እውነትን እየሸፈኑ ፤ ሐቅን እያዳፈኑ፣ ሙያዊ ክህደት እየፈፀሙ ራሱን ያመመውን እግርህን ነው ብለው እንደሚከራከሩ ያላዋቂ ባለሙያ መፍትሄ የጠፋቸው የፅህፈት ሚንስትሮች ተሸለምን ቢሉ ፣ የተሸለሙት ለህዝብ በሰጡት አገልግሎት ሳይሆን ለመንግስት አሸርጋጅነታቸው ብቻ እንደሆነ ሀቅ ነው፡፡
እስኪ የትኛውም ስራችሁም እንደማያሸልም የማህበራዊ ሚዲያ የአሰተያየት መስጫ ሳጥናችሁን ከፍታችሁ አንብቡ፡፡ This is Ethiopia's Media Battleground: Where Politics Wields the Pen. እርግጠኛ መሆን የሚቻለው ከዚህ ሽልማት መንግስት የህዝብ የሆኑ ሚዲያዎችን ወደባላቤቱ መመለስ እንደማይፈልግ ነው፡፡ በዴሞክራሲ እጦት የታፈነን ፣ ሰበዓዊ መብቱ የተገፈፈን ፣ በኢኮኖሚ አዘቅት ውስጥ የወደቀን፣ በግጨት አፈሙዝ የተከፈተባት ሀገርን የመረጃ ስርዓት እየመሩል ፣ ሀሳብን እየሸመገሉ ሳይሆን እየሸነገሉ የሚጓዙ ሚዲያዎችን መሸለም ለመረጃ መዛባት ፣ ለመረጃ መሳሳት፣ ለመረጃ መበከል እውቅና እንደመስጠት ነው፤፤
የሀገራችን ሚዲያዎች የዜናዎችን አሠራር፣ አደረጃጀትና አቀራረብ በትንሹ እንኳን ብናይ ተሸላሚ ሚዲያዎቻችን በአሰልችነታቸው፣ የህዝብ ድምፅ የሌላቸው፣ ጥበብ እና የእውቀት መረጃ ቀረፃ የተሳናቸው ዜናዎቻ እና ፕሮግራሞች ምን ያሸልማል? የተለያዩ ድምፃችን የማንሰማበት ፣ ጉዳያችንን ቢቢሲ፣ አልጀዚራ እና ሲኤን ኤን እስኪዘግበው ምንጠብቅበት፣ የተቀራኖ ድምፆች የማይሰሙበት፣ የሀሳብ ልዩነት የማይሰተናገድበት አይደሉም እንዴ? የሰለቹ የዜና መዋዕል (የውሎ ዜና) ዘገባዎች እና የህዝብ ግንኙነት ስራ ባህሪ የተዋረሳቸው፣ ጋዜጠኞች ቢናገሩ የልብ አያደርሱም ተብለው መሪዎች ጋዜጠኛ የሆኑበት ፕሮግራም ብቻ ናቸው። ምን? የት? መቼ? እንዴት? እና ማን? የሚሉትን ጥያቄዎች በአግባቡ የማይመልሱ፣ አውዱን ፍራቻ፣ እውነትን ሽሽት፣ ከታመመው ይልቅ ለጤናማው መጨነቅ፣ ከጎደለበት ይልቅ ለሞላለት ማለቅለቅ አይደለም እንዴ ሰራችሁ?
እናንተ ሰትሸለሙ፣ መሪዎች በአፍሪካ ተሸለሙ እያለ የሚቀልድብንን የናይጀሪያ ጋዜጠኛ ነበር ያስታወስኩት፣ በዜና እና ፕሮግራሞቻችሁ አንድም የተቃርኖ ድምፆች የማንስማበት፣ ፍትሃዊነት፣ እና ሚዛናዊነት የነጠፈበት ዘገባ ካሸለመ እንኳንም እያፈረን ተሸለማችሁ።
የመንግስት አክቲቪስት ሲሸለም እኛም የሰበዓዊ መብት ተሟጋቾችን መሸለም ግዴታ ይሆንብናል፡፡ ምክንያቱም እንባችን የሚገዳቸው፣ ሞታችን የሚያማቸው የማህበረሰብ አንቂዎች፣ የእውት አርበኞች እስር ቤትም ሆነው የህዝብ ድምፅ ናቸው፡፡
እነዚህ ከአንድ ግለሰብ የማህበረሰብ አንቂ ታማኝነት ያነሰ አቅም ያላቸው ሚዲያዎች በሽዎች ሰራተኛ ይዘው፣ በሳንሱር ተሸብበው፣ እውቀታቸውን ለመጠቀም የታፈኑት በነዚህ ሸላሚዎች ነው፡፡ እንቁ ብቁዎች አፃፃፋቸው ውበትም፣ እውነትም ያጣው መንግስትን ስለሚፈሩ ነው። በግል አስተያየት የታጀቡና የፖለቲካ ጉንፋን ያጠቃቸውና ሳይንሳዊ እሳቤ የራቃቸው ሙያዊ አሰተያየት የተለያቸው ዘጋቢ ሚዲያዎች ናቸው።
የእነዚህ ችግሮች መነሻ ራሱ አፈናውን ያበረታው መንግስት ለነፃ ሚዲያ መስራት እና የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ባህሎ የሞተ በመሆኑ ነው። ጋዜጠኞችን ነፃ ቢያደርጋቸው በዜና አመራረጥ፣ አፃፃፍና አቀራረባችው ላይ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ።
ለዚህ ሃሳብ ማሳደጊያ ያነጋገርኳቸው ጋዜጤኞች ‹‹መንግስትን በመፍራት የማይናገረውን የማያስጠይቀውን የልማት ስራ ብቻ የመዘገብ ተልዕኮ የወሰዱት መንግስት በመፍራት ነው፡፡›› ስለዚህ ‹‹የህዝብ ግንኙነት ዜና›› ዘጋቢ ሁነናል የሚለው የጠቅላይ ሚንስትሩ ተሸላሚ የሚዲያ ተቋም ጋዜጠኛ፣ በሚዲያ ኩረጃ ፣ ዜና ግልበጣ ውስጥ ወድቀናል በማለት እጁ እና ህሊናው እንደታሰረ ይናገራል።
አሁን የመንግስት ስብሰባ፣ የስልጠና፣ የወርክሾፕ ዜናዎች ላይ ነን የምትለው ዘጋቢ እንደ ወረደ ዜና መስራት የወቅቱ መሻሪያ መስመር ነው በማለት ታረጋግጣለች። በነዚህ ቦታዎች ላይ የምንሠራቸው ዜናዎች በአጀንዳው ላይ የተነሱ ቁልፍ ጉዳዮችና አከራካሪ ነጥቦች በመለየት ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የስብሰባ ተሳታፊዎች /የስብጥሩን ሚዛናዊነት በመጠበቅ/ እዛው (on the spot) በዕረፍት ሰአት ልዩ (excultive) ቃለ መጠይቅ በመስራት ማቅረብ፤ /የዕለቱ ክብር እንግዳ የሚያስተላልፈው መልዕክት እንደ አስፈላጊነቱ መጠቀም/ እና ለትርጉም የሚጋለጡ ሀሳቦችን ዘግተናል በማለት ትናገራለች፡፡
የጋዜጣዊ መግለጫዎች ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው ሌላ የተሸላሚ ሚዲያ ባለሙያ- ከጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከአፈጉባኤ፣ ከፕሬዝዳንቱና በተለየ መልክ ከሚሰጡ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ውጪ ያሉ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን አንዘግብም፡፡ ስለዚህ እኛ የጋዜጣዊ መግለጫ ጋዜጠኛ ነን፡፡ የምርመራ ዘገባ ስልቶች የሉም፡፡ ሲል ይጠቅሳል፡፡
እኛ የዜና ተቀባይ ሳጥን ጋዜጠኛ እንጅ ተጓዥ መንገደኛ አይደለንም፡፡ የሚለው ሌላው አሰተያየት ሰጭ - በተለምዶ ዜናዎቹ ናቸው ወደኛ እየመጡ ያሉት እኛ ወደዜናዎች ሂደን አናውቅም። ዜናዎች ወደኛ የሚመጡት ደግሞ በመጡበት አግባብ መስተናገድ ስለሚፈልጉ ነው። ይህን አቅጣጫ የሰጠን መንግስት ነው ይላል።
እያንዳንዱ ጋዜጠኛ /ከዋና - አዘጋጁ እስከ ሪፖርተሩ/ የራሱ የወሬ ምንጮች፣ /ቲፕ የሚሰጠንና መረጃ የሚያቀብሉ/ ሊኖሩት ይገባል። ከሚኒስትሩ እስከ በር ጥበቃው ድረስ /በተለምዶ በጋዜጠኝነት ት/ቤቶች እንደሚባለው ወዳጆቹ ሆነው የጥቆማና “ይህቺንስ ሰምተሃታል?” ብለው የሚያዋሩት ሰዎች ግንኙነት መመስረት በፍርሃት መመስረት አልቻለም። ስለዚህም ዜናን ቁጭ ብሎ ከመጠበቅ ዜናውን ማደን፣ መቆፈርና አሽትቶ ወደ መፈለግ አልተሻገረም። ተቋማዊ ህልውና ወይም መለያ የሚመሠረተው ተቋሙ ትርጉም ያላቸው ትኩስ፣ ሚዛናዊ፣ እውነታና የሚጣፍጡ ዜናዎች ማቅረብ ሲችል ብቻ ነው። የማይጣፍጥ ዜና ማንም አይቀምሰውም። ጣፋጩን ዜና ለማምረት “ዜናን የማደን” ወይም “የማሽተት” ተግባር የሁሉም ጋዜጠኛ መለኪያ፣ መገምገሚያ ይሆናል። ወደ ዜና መሄድ የዜናዎቻችንም የአቀራረብ ድምፀት ይለውጠዋል።
የዜናችን አፃፃፍ መለወጥ፦ ዜናችን በችኮ ቃላት፣ በፖለቲካ ጃርገን፣ በ”ብለዋል” ፣ በ”አሳውቀዋል”፣ በ”ገልፀዋል” እና “አመልክተዋል” ገለፃዎች የተሞሉ ናቸው። አፃፃፉ አይስብም። የሚሰማው የአንድ ወገን /የአንድ ተቋም ወይም ዘርፍ/ ድምፅ ነው። ይህ ድምፅ ደግሞ ያው “የተለምዶ” ነው በሚል ተመልካች - አድማጭ አይይዝም።

የወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር የሽለመው ማንነው ካልን ሚዲያዎችን ሳይሆን ራሱን ነው፡፡ ብለን እንደመድማለን፡፡ Ethiopian Media: Trapped in a Political Tug-of-War! በአየለ አዲሰ by Ayele Addis
Photo Center for Ethiopian Studies and French National Library free consultation

የ2025 የአውስትራሊያ የትምህርት እድል ኢትዮጲያን ጨምሮ በአውስትራሊያ ውስጥ ለጥናት (ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ) አቅርቧል፡፡ የማመልከቻ ገደብ፡ 30 ሚያዚያ 2024 https://australia...
02/02/2024

የ2025 የአውስትራሊያ የትምህርት እድል ኢትዮጲያን ጨምሮ በአውስትራሊያ ውስጥ ለጥናት (ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ) አቅርቧል፡፡ የማመልከቻ ገደብ፡ 30 ሚያዚያ 2024 https://australiaawardsafrica.org/awards/apply/
የአውስትራሊያ የሽልማት ስኮላርሺፕ በአውስትራሊያ መንግሥት ለቀጣዩ ትውልድ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ ለሚኖሩ የሚሰጡ ዓለም እድሎች ናቸው ናቸው። በጥናት እና በምርምር፣ ከአውስትራሊያ ጋር ዘላቂ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ለመገንባት የሚረዱ ክህሎቶችን እና እውቀቶችን ያዳብራሉ። አመልካቾች የሚገመገሙት በሙያቸው እና በግላዊ ብቃታቸው፣ በአካዳሚክ ብቃታቸው እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ብቁ በሆኑ አገሮች ውስጥ ባሉ የልማት ተግዳሮቶች ላይ ተጽእኖ የመፍጠር አቅማቸው ነው። ማመልከቻዎች ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለሌሎች የተገለሉ ቡድኖች በጥብቅ ይበረታታሉ።
IELTS እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና ውጤት ለኢትዮጲያውያን ከፍተኛ ትምህርት ለተመረቁ ፣ የመማሪያ ቋንቋው እንግሊዘኛ በመሆኑ ከሪጅስትራር በሚቀርብ ደብዳቤ ሳይፈተኑ ማመልከት ይችላሉ፡፡ ጥቅሞች የአውስትራሊያ የሽልማት ስኮላርሺፕ ግለሰቡ በአውስትራሊያ የትምህርት ተቋም የተገለጸውን የአካዳሚክ መርሃ ግብር እንዲያጠናቅቅ ለሚያስፈልገው ዝቅተኛ ጊዜ ይሰጣል፣ ማንኛውንም የመሰናዶ ስልጠናን ጨምሮ። የስኮላርሺፕ ተቀባዮች የሚከተሉትን ይቀበላሉ: የአየር ጉዞ ደርሶ መለስ፣ የአንድ ጊዜ ማቋቋሚያ አበል፣ ሙሉ የትምህርት ክፍያዎች ለኑሮ ወጪዎች፣ የመግቢያ ትምህርታዊ ፕሮግራም ለስኮላርሺፕ ቆይታው የውጭ አገር ተማሪዎች የጤና ሽፋን ተጨማሪ የትምህርት ድጋፍ ለምርምር ተማሪዎች የመስክ ሥራ አበል እና በኮርስ ሥራ የግዴታ የመስክ ሥራ ወጭን ይሸፍናል።
and and your friends that needs this list.
የልብዎን መሻት ፈጣሪ ይሙላ፡፡ ዋናው ማመልከቻ https://australiaawardsafrica.org/awards/apply/
ተጨማሪ የስኮላሽፕ መረጃ ከፈለጉ ለእርስዎ በቅንነት ለማገዘ የተከፈተ የቴሌግራም ገፅ ነው እሱን ይከተሉት፡፡ ለሌሎቸም ያስተዋውቁት እኛንም ያበርቱን ፤ https://t.me/Ethopianmedia
አልያም በግል የፌስቡክ ገፄ ፎሎው ማድረግ ይችላሉ፡፡ https://www.facebook.com/ayele.addis
ዮቱዩብ ሳብስክራይብ ቢያደርጉ በቅርቡ ላይቭ ውይይቶችን እና በድምፅ እና ምስል ፎርም አሞላሎችን ያገኛሉ፡፡ https://www.youtube.com/channel/UC_dGEm33v59ugUhha0R6jDw

https://australiaawardsafrica.org/awards/apply/

አሜሪካ የሚገኙ በአነስተኛ ግሬድ ማመልከት የሚቻልባቸው ዩኒቨርስቲዎች ዝረዝር ናቸው፡፡ 1. Albany State University: 2.0 2. Arkansas State University: 2.7...
02/02/2024

አሜሪካ የሚገኙ በአነስተኛ ግሬድ ማመልከት የሚቻልባቸው ዩኒቨርስቲዎች ዝረዝር ናቸው፡፡
1. Albany State University: 2.0
2. Arkansas State University: 2.75
3. California State University at Channel Islands: 2.5
4. California State University at East Bay: 2.5
5. California State University at Fresno: 2.75
6. California State University at Fullerton: 2.5
7. California State University at Long Beach: 2.7
8. California State University at Northridge: 2.5
9. California State University at San Bernardino: 2.5
10. DePaul University: 2.5
11. Fort Hays State University: 2.0
12. Grand Canyon University: 2.8
13. Jackson state University: 2.5
14. North Carolina State University: 2.0
15. Univ. of Maryland Eastern Shore: 2.93
16. Univ. of Minnesota at Twin Cities: 3.0
17. University of Maine: 2.0
18. University of Mississippi: 3.0
19. Univ. of Maine at Presque Isle: 3.0
20. Univ. of Arkansas at Little Rock: 3.21
and and your friends that needs this list.
የልብዎን መሻት ፈጣሪ ይሙላ፡፡
ተጨማሪ የስኮላሽፕ መረጃ ከፈለጉ ለእርስዎ በቅንነት ለማገዘ የተከፈተ የቴሌግራም ገፅ ነው እሱን ይከተሉት፡፡ ለሌሎቸም ያስተዋውቁት እኛንም ያበርቱን ፤ https://t.me/Ethopianmedia
አልያም በግል የፌስቡክ ገፄ ፎሎው ማድረግ ይችላሉ፡፡ https://www.facebook.com/ayele.addis
ዮቱዩብ ሳብስክራይብ ቢያደርጉ በቅርቡ ላይቭ ውይይቶችን እና በድምፅ እና ምስል ፎርም አሞላሎችን ያገኛሉ፡፡ https://www.youtube.com/channel/UC_dGEm33v59ugUhha0R6jDw

ነጻ የውጭ የትምህርት እድል፣ ውድ ቤተሰቦች፡- ይህ ሳትሞክሩት ካመለጣችሁ እከፋባችኃለሁ። 500 አመልካቾች MA/MSC ማስተርስ ወይም PHD ፒኤችዲቸውን እዚህ ለመከታተል ሙሉ ስፖንሰር ይደረ...
02/02/2024

ነጻ የውጭ የትምህርት እድል፣ ውድ ቤተሰቦች፡- ይህ ሳትሞክሩት ካመለጣችሁ እከፋባችኃለሁ። 500 አመልካቾች MA/MSC ማስተርስ ወይም PHD ፒኤችዲቸውን እዚህ ለመከታተል ሙሉ ስፖንሰር ይደረጋሉ። ዋናው ማመልከቻ ሊንክ ይሄ ነው፡፡ https://ic.ustc.edu.cn/en/v7info.php?Nav_x=9 ምንም ወጭ የለብዎትም፡፡ በዝቅተኛ ውጤት 2:2 GPA ቢኖራችሁ ማመልከት ይችላሉ። ማንኛውንም ፕሮፌሰር ማነጋገር አያስፈልግም፣ ቀጥተኛ ማመልከቻ ብቻ። የ ANSO ስኮላርሺፕ የድህረ ምረቃ ትምህርት ለመከታተል 200 ማስተር ተማሪዎችን እና 300 ፒኤችዲ ተማሪዎችን በየዓመቱ ሙሉ ወጭ ችሎ ይደግፋል። ጥቅሞች ሙሉ የትምህርት ክፍያ፣ ወርሃዊ ክፍያ አንድ የበረራ ትኬት፣ የጤና መድህን የማመልከቻ ክፍያ ይከፍልላችኃል፡፡ የአንድ ጊዜ ቪዛ አበል ተመላሽ ያደርጋል።
ይህ የነፃ ትምህርት (ስኮላርሺፕ) ሙሉ በሙሉ በገንዘብ የተደገፈ እና የሚያስቡትን ሁሉንም ነገር ይሸፍናል ፣ የመተግበሪያ ክፍያ የለም፣ IELTS አያስፈልግም HND ማመልከት ይችላል, ተቆጣጣሪ አያስፈልግም ፣ በረራ ይሸፍናሉ። ለጓደኞችዎ ያካፍሉ ፡፡ ጥሩ ማመልከቻ ካስገቡ ይህ የነፃ ትምህርት ዕድል ለማግኘት በጣም ቀላል ነው. የህልም መድረሻዎ ባይሆንም አሁንም እንደ ተለዋጭ እቅድ አስበው ያመልክቱ። https://ic.ustc.edu.cn/en/v7info.php?Nav_x=9
ዋናው ማመልከቻ ይሄ ነው፡፡ https://ic.ustc.edu.cn/en/v7info.php?Nav_x=9
የልብዎን መሻት ፈጣሪ ይሙላ፡፡
ተጨማሪ የስኮላሽፕ መረጃ ከፈለጉ ለእርስዎ በቅንነት ለማገዘ የተከፈተ የቴሌግራም ገፅ ነው እሱን ይከተሉት፡፡ ለሌሎቸም ያስተዋውቁት እኛንም ያበርቱን ፤ https://t.me/Ethopianmedia
አልያም በግል የፌስቡክ ገፄ ፎሎው ማድረግ ይችላሉ፡፡ https://www.facebook.com/ayele.addis
ዮቱዩብ ሳብስክራይብ ቢያደርጉ በቅርቡ ላይቭ ውይይቶችን እና በድምፅ እና ምስል ፎርም አሞላሎችን ያገኛሉ፡፡ https://www.youtube.com/channel/UC_dGEm33v59ugUhha0R6jDw

The International College of the University of Science and Technology of China (USTC) was established in 2017 to better develop the international education of the university, connect with domestic and foreign high-quality science and education resources, and build a crucial platform for internationa...

I discussed with the BBC Amharic about "access to information suppression, citizens' right to information, and sources o...
26/01/2024

I discussed with the BBC Amharic about "access to information suppression, citizens' right to information, and sources of information due to conflicts." የመረጃ ማፈን መገናኛ ብዙኃን እንዳይግባቡና ውይይትና ማሰላሰል እንዳይፈጥሩ እንቅፋት ሆነዋል። Suppression of information by the public and government officials has hindered the media from communicating and creating dialogue, discussion, and meditation.

Especially as stated in the discussion, Journalists have difficulty getting information due to the conflicts in Ethiopia; even the reports that come out are based on anonymous sources. This calls into question the credibility of the media. Regarding the situation in the Amhara region, the efforts of journalists to go to the place to get information and report are challenging, given the threat. Apart from the fact that the government does not provide formal details, there is absolutely no willingness to confirm or deny the events related to the war.

In Ethiopia, freedom of information and the right to access information are separated on paper and in practice. Government institutions established to provide information are blamed for neglecting their duties and responsibilities.

As I told the BBC, there is a general culture of "information apathy." Information will be suppressed from the government structure to society for "fear of the government."

This prevents the distribution of timely, accurate, and balanced information, especially the spread of false, disinformation, misinformation, and distorted information, which has a high impact.

The denial of access to information violates the constitution, which is the supreme law of the country, international human rights, and the declaration of freedom of the media and the right to access information.

In the age when information is said to be power, the mass media did not get information, which means that the people were denied the right to obtain information and to know.

Journalists censor themselves. According to the journalists, the lack of proper media coverage of the ongoing conflicts and injuries "may account for the violations and abuses that are not being committed" and thereby lose accountability.

Failure to report abuses and rights violations can result in stories that need to be told being suppressed. The effect is that "human rights abuses" will spread.

When information sources withhold information and withhold information, the door is opened for oppression and abuses to spread. But I understand the concerns that forced them to do this; there is no question about mobile recording. Sound recording is a challenging hour.
The "cover-up stifles the voices of the victims, and the failure of the war and its impact to be appropriately documented by the media deprives an opportunity for research and history to avoid evidence.

In addition, Suppression of information by the public and government officials has hindered the media from communicating and creating dialogue, discussion, and meditation.

በአገሪቱ ውስጥ ሚካሄዱ ግጭቶች ምክንያት በሰላማዊ ሰዎች እና በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው። በተለይ የመብት ጥሰቶች እና እንግልቶች በስፋት እንደሚፈጸሙ ይነገራል። እነዚህን ክ.....

አይስላንድ ነፃ የትምህርት እድል አለ። ዋናው ማመልከቻ ይሄ ነው፡፡ https://study.iceland.is/ ለማስተርስ ትምህርት ከነሙሉ ቤተሰብ መሄድ ይችላሉ። የባችለር ፕሮግራም የዕድሜ ገ...
25/01/2024

አይስላንድ ነፃ የትምህርት እድል አለ። ዋናው ማመልከቻ ይሄ ነው፡፡ https://study.iceland.is/ ለማስተርስ ትምህርት ከነሙሉ ቤተሰብ መሄድ ይችላሉ። የባችለር ፕሮግራም የዕድሜ ገደብ የለውም፡፡ የምስራች፡ ምንም የትምህርት ክፍያ አያስፈልግም፡፡ የስራ ሰዓት 25 ሰአት. የደመወዝ ክልል €800 ~ €2500 ያቀርባሉ። ተማሪዎች ሥራ ለማግኘት ምን ያህል ጊዜ ይፈጅባቸዋል ካላችሁ(ከ1 ሳምንት እስከ 3 ወር)። #እባክዎ #ሼር ያድርጉ በዚህ ላይ ፍላጎት አለዎት? የሚከፍሉት ወጪዎች፡- የአይስላንድ ዩኒቨርሲቲ ብዙ የእንግሊዝኛ ፕሮግራሞች ካላቸው ነፃ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው።
በታህሳስ ውስጥ ይከፈታል ስለዚህ አሁን መዘጋጀት ያስፈልግዎታል።
ለነዋሪነት ፈቃድ ማመልከቻ የሚያስፈልጉዎት ሰነዶች;
1፡ ቅድመ ሁኔታ የሌለው የመግቢያ ደብዳቤ
2፡ የፖሊስ ባህሪ ሰርተፍኬት
3፡ የጉዞ ጤና መድን (ሙሉውን Schengen.12months መሸፈን አለበት)
4፡ ፓስፖርት
5፡ የፓስፖርት ፎቶ
በአይስላንድ ዝቅተኛ ደመወዝ የለም ስለዚህ ክፍያው ጥሩ እና ለድርድር የሚቀርብ ነው። 5: አይስላንድ በጣም ቀዝቃዛ ነው 6፡ ሰዎች እንግሊዘኛ ቢናገሩም የአይስላንድ ቋንቋ አስቸጋሪ ነው።
7፡ የአይስላንድ ህዝብ ብዛት ወደ 320,000 አካባቢ ነው ነገር ግን ጥሩ የተማረ ህዝብ አለው። ምን ይመስልሃል? ለአይስላንድ ዩኒቨርሲቲ ለባችለር ፕሮግራም እንዴት ማመልከት እንደሚቻል! 1፡ መግቢያ ታህሳስ 12 ተጀመረ፡ በአይስላንድ ላሉ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰርተፍኬትዎን ብቻ ይዘው ማመልከት ላይችሉ ይችላሉ። የአንድ አመት የዩኒቨርሲቲ ትራንስክሪፕት ማቅረብ አለቦት። ስለዚህ OND ወይም ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ የተደረገ ዲፕሎማ። ለማስተርስ 1: በቀጥታ ማመልከት ይችላሉ። https://lnkd.in/dCTm9nqc ስኮላርሺፕም አለ። ሌሎች፡- ማስተርስ ወይም ቢኤስሲ ለመስራት ካልፈለጉ ለአይስላንድኛ ቋንቋ ዲፕሎማ ብቻ ማመልከት ይችላሉ።
ዝቅተኛ GPA ማመልከት ይችላል። አዎ ግን ዝቅተኛ GPA ካሎት፣ ለቢኤስሲ እንዲያመለክቱ እመክርዎታለሁ፣ ቀደም ሲል የኮርሱ እውቀት ስላሎት የመቀበል እድሉ ከፍ ያለ ነው። ማስተርስ 2አመት ነው ፣ቢኤስሲ 3አመት ነው ፣ይህ 3 አመት ለመቸኮል እና ለማቀድ የበለጠ ጊዜ ይሰጣል። በአይስላንድ 🇮🇸 የዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር ይኸውና የአይስላንድ ዩኒቨርሲቲ https://lnkd.in/dCTm9nqc
የአገሪቱን ልዩ መስፈርቶች ያረጋግጡ. https://lnkd.in/dJHwYJeN # እባኮትን #ጓደኞችዎን ወደዚህ ግሩፕ ይጋብዙ እና በቀና ልብ እድሎችን እናጋራቸው እና # ለጓደኞችዎ እና በኔትወርክዎ ውስጥ ያካፍሉ።
ዋናው ማመልከቻ ይሄ ነው፡፡ የልብዎን መሻት ፈጣሪ ይሙላ፡፡ https://study.iceland.is/
አልያም በድረገፃችን
https://am.africanewschannel.org/
ተጨማሪ የስኮላሽፕ መረጃ ከፈለጉ ለእርስዎ በቅንነት ለማገዘ የተከፈተ የቴሌግራም ገፅ ነው እሱን ይከተሉት፡፡ https://t.me/Ethopianmedia

Iceland offers great opportunities for higher education in seven highly qualified international academic programs across various fields. Icelandic institutes of higher education welcome applications sent by qualified students from all over the world.

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when All About Bahir Dar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to All About Bahir Dar:

Share