Miskaye Hizunan/ ምስካዬ ሕዙናን የበጎ አድራጎትና መንፈሳዊ ጉዞ

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • Miskaye Hizunan/ ምስካዬ ሕዙናን የበጎ አድራጎትና መንፈሳዊ ጉዞ

Miskaye Hizunan/ ምስካዬ ሕዙናን የበጎ አድራጎትና መንፈሳዊ ጉዞ The purpose of this page is help very poor person who can't eat one time per aday & go monastry places

05/03/2025

ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ሰላማችሁ በያላችሁበት ይብዛልኝ የዚህ ገፅ አባል በሙሉ ለመቅዶንያ 10 /አስር ብር እናዋጣ ስለትብብራችሁ ከወዲሁ አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏

24/01/2025
04/05/2017 ዓ.ም 30
12/01/2025

04/05/2017 ዓ.ም 30

የለቡ መርጡለ አርሴማ ወአቡነ አዳም ገዳም ሕንጻ ቤተመቅደስ በቅዱስ ፓትርያርኩ ተባርኮ መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።       ------------------------------------...
17/02/2024

የለቡ መርጡለ አርሴማ ወአቡነ አዳም ገዳም ሕንጻ ቤተመቅደስ በቅዱስ ፓትርያርኩ ተባርኮ መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
-------------------------------------------
የካቲት 9/2016 ዓ.ም ሐተሚ ( አዳማ - ኢትዮጵያ )

በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሥር መጋቤ ሀብታት ስማቸው ከበደ እና ወለተሃና የተባሉ በጎ አድራጊ ምእመናን በ ወራት ጊዜ ውስጥ የታነጸውና ውብ በሆነ መንገድ ግንባታው የተጠናቀቀው የለቡ መርጡለ አርሴማ ወአቡነ አዳም ገዳም ሕንጻ ቤተመቅደስ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጸሎት ተባርኮ መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ለረዥም ዓመታት በአነስተኛ የቆርቆሮ መቅደስ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውን የገዳሙን ሕንጻ በአዲስና ባማረ መልኩ እንዲሠራ መልአከ ጽዮን አባ እስጢፋኖስ ይርጋ የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ የሁለቱ አጥቢያዎች ዋና አስተዳዳሪ ከላይ የተገለጹትን የመነንፈስ ልጆቻቸውን በማሳሰብ እንዳሳነጹ በዕለቱ በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል። በገዳሙ ያለው ጸበል ለበርካታ ምእመናን እና የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች የፈውስ ቦታ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

በቡራኬ ሥርዓቱ ላይ ቅዱስነታቸውን በመከተል ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤ ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌና የምሥራቅ ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና መተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስየዳውሮ-ኮንታ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸው ምእመናን ተገኝተዋል። ሲል የዘገበው የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት ነው፡፡

ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ( አዳማ - ኢትዮጵያ)
የካቲት 9/2016 ዓ.ም

እኛም ብለናል በወጣው ይተካ 🙏🙏🙏🙏

ደጋፊ ብቻ ሳይሆን ጠያቂም ትሻለች!እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን "ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው" እህታችንን አቅማችን በፈቀደ መጠን የዛሬን ቡና ትተን ቢያንስ በቡና የምናወጣውን 1...
06/02/2024

ደጋፊ ብቻ ሳይሆን ጠያቂም ትሻለች!
እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን "ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው" እህታችንን አቅማችን በፈቀደ መጠን የዛሬን ቡና ትተን ቢያንስ በቡና የምናወጣውን 10/20 ብር እንርዳት "አምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ"፤ለአምሳ ሰው ጌጡ" እንዳሉ አባቶቻችን
| ቤተሰቦቿ ሆስፒታል ውስጥ ጥለዋት ሂደው በኩላሊት ህመም እየተሰቃየች ያለችውን የ26 ዓመቷ ወጣት ደጋፊ ብቻ ሳይሆን ጠያቂም በብርቱ ትሻለች!

(ይትባረክ ዋለልኝ)

እመቤት ታርቦሼ አድነው ትባላለች:: የ 26 ዓመት ወጣት ናት:: ተወልዳ ያደገችው ባሌ ሮቤ ውስጥ ነው:: የቤተሰቦቿ የመጅመሪያ ልጅ ናት:: ቤተሰቦቿ በግብርና የሚተዳደሩ ናቸው:: እመቤት የቤተሰቡ የመጀመሪያ ልጅ በመሆኗ ለቤቱም ትልቅ ሃላፊነት ነበረባት:: የልጅነት ህልሟም ትምህርቷን ተምራ ወላጆቿንና ቤተሰቡን መርዳት ነበር::

በዚህም ትምህርቷን እንደጨረሰች ባሌ ህዳሴ ቴሌኮም ውስጥ ተቀጥራ መስራት ጅመረች:: ቤተሰቧንም በትለይ ገበሬ አባቷን እየደገፈች ለሁለት ዕመታት እንደሰራች ታመመች:: ባሌ ሆስፒታል ሄዳ ስትታከም ሁለቱ ኩላሊቷ ችግር ውስጥ እንዳሉ ተነግሯት በሪፈር አዲስ አበባ ጳውሎስ ሆስፒታል መጥታ መታከም ጀመረች ::

ጳውሎስ ሆስፒታልም ሁለቱ ኩላሊቶቿ ከአገልግሎት ውጭ ስለሆኑ ኩላሊት የሚሰጣት ሰው ካግኝች ንቅለተከላ እንድታደርግ ይነግሯታል:: እመቤትም ኩላሊት የሚሰጣት ሰው ስለሌላት የዲያሌስስ ህክምና ጳውሎስ ጀመረች:: አባቷና ቤተሰቡም ነገሩ ከአቅም በላይ ሲሆንባቸው ልጃቸውን ሆስፒታሉ ውስጥ እንደትኛች ጥለዋት ይሄዳሉ::

አንድ አባትም የልጅቷን ችግር ተረድተው ከስዎች ጋር ተባብረው ቤት ተከራይተውላት ከሆስፒታል አወጧት:: ቤተሰቦቿ ጥለዋት ከሄዱ ስምንት ወር ሆኗቸዋል:: እንኳን መጥተው ሊጠይቋት መደወልም የለም::እመቤት ዛሬም ቆማ መሄድ አትችልም:: በደም ማነስና በድካም ትሰቃያለች::

የደም ስሮቿ በክንዷ ላይ ስላልተገኝ ዛሬ ዲያሊስስ የምትወስደው ከጡቷ ጎን ብብቷ ስር በሚገኝው ደምስሯ ነው:: ላይ በሚገኝው የምትኖረው በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው::እመቤት ላለፉት ስምንት ወር ቤት ተከራይተው በሳምንት ሶስት ቀን ለምትወስደው የዲያሌስስ ክፍያን እንዲሁም ምግቧን ሰዎች እየከፈሉላት ነው ህይወቷን ዛሬ ድረስ ታድገውላት እየኖረች ያለችው::

ውድ ኢትዮጵያውያን የዚህችን ወጣት ህይወት ለመታደግ የአቅማችሁን ድጋፍ አድርጉላት:: በተለይ በተለይ ከድጋፉ በላይ ደውላችሁ እንደቤተሰብ አይዞሽ እግዚአብሔር ይማርሽ በሏት:: እኔ ቤቷ ድረስ ሰው ወስዶኝ አይቻታለሁ:: በጣም አዝኜና የአቅሜን ድጋፍ አድርጌ ነው የተመለስኩት:: አደራ ደውሉላት ድጋፋችሁንም እድርጉላት::

ድጋፍ ለማድረግ የ ምትሹ የባንክ አካውንትንና

ሙሉ ስም:- እመቤት ታርቦሼ አድነው
የባንኩ ስም :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የባንክ ሂሳብ ቁጥር:-1000192221602

በዚህ ስልክ ቁጥር እየደወላችሁ እመቤትን እግዚአብሔር ይማርሽ በሏት :- +251952105282

# ይህንን መረጃ ሌሎቻችሁ በማድረግ ትብብር አድርጉላቸው::

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ረድኤት በረከት ምልጃ ፀሎት አይለየን   ✟⛪💚💛♥⛪✟
31/01/2024

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ረድኤት በረከት ምልጃ ፀሎት አይለየን
✟⛪💚💛♥⛪✟

እንኳን ለእናታችን ለመድኃኒታችን ለቅድስት ድንግል ማሪያም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ 🙏🙏🙏🙏"የጥሯ ሙሽራ" አስተሪዮን በመርጡ ለማሪያም❤❤❤❤❤❤***እናቴ የነገርኩሽን አ...
29/01/2024

እንኳን ለእናታችን ለመድኃኒታችን ለቅድስት ድንግል ማሪያም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ 🙏🙏🙏🙏
"የጥሯ ሙሽራ" አስተሪዮን በመርጡ ለማሪያም❤❤❤❤❤❤
***እናቴ የነገርኩሽን አደራ !!!***

28/01/2024

ውድ የተዋሕዶ ልጆች እንኳን ለአብሳሪው መልአከ ለቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🙏🙏🙏
⛪️✍እኔ በእግዚአብሔር #ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች #እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤”
(ሉቃስ ፩፥፲፱)🙇‍♀❤️🙏

#እንኳን አደረሳቹ ( #፲፱🕯)

ገብርኤል ማለት " #እግዚእ ወገብር”፦ #የእግአብሔር #አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር #በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ #ተሰወራቸው መላእክትም “መኑ ፈጠረነ፦ማን ፈጠረን” ሲሉ #ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “የፈጠረንን #አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል።

🍃⛪️ቅዱስ #ገብርኤል 🙏

የሰለስቱ ደቂቅ መጠሪያ ስማቸው
ሳትመራመረው #በእውነት ልጆች ናቸው
በእሳት ሲጫወቱ ከገብርኤል ጋራ
ንጉሡ ተደንቆ #ለአራተኛው ፈራ
የሰለስቱ ደቂቅ ቁመት በማነሱ
ከፍ ከፍ ብለው እላይ እንዲደርሱ
ተቀጣጠሉ ሲል አዘዘ ንጉሡ
የሰለስቱ ደቂቅ ፀባይ መጠንከሩ
ወደ ፍቅር ጌታ ሄዱ በረሩ
እንደ ንጉሡ ፍርድ እንዳነጋገሩ
የጠብ ሰው ነውና ተጠብሰው በቀሩ
#ናቡከደነጾር እዩት ሐሳቡን
ከምስል ቢጣሉ በዚያ ቀውጢ ቀን
የሠለሰስቱ ደቂቅ ገላጋይ ሊሆን
ይልቅ የእርሱ አሽከሮች መልካም ገላጋይ
መላ ቢስ ነው ለካ ፍጹም ወላዋይ
ከላይ ወረደ እንጂ መና ከሰማይ
ናቡከደነጾር በቁጣ ተናዶ
በሰለስቱ ደቂቅ #በመሳሳት ፈርዶ
ገብርኤል ነህና ታዳጊ ለሁሉ
እስከ ሰራዊትህ ላትነጣጠሉ
ከጧት እስከ ማታ ለአምላክህ ባለሟል
እናት #ኢትዮጲያን ቅዱስ ገብርኤል
እንደባቢሎን ተአምረኛ ገድል
ከአለማውያን እሳት የጦር ነበልባል
ጠላቷን አጥፋላት በበትረ መስቀል
ሲድራቅን ሚሳቅን አብድናጎን ሶስቱን
ቅድስት #እየሉጣን ቂርቆስን ሁለቱን
እንደታደግሀቸው አጥፍተህ እሳቱን
ኢትዮጲያን ታደጋት አደራ
ካሰከረው ከጠላት ወረራ
ቀልድ አይወድም ሲባል ቅዱስ ገብርኤል
#በዘካርያስ ላይ አፍ ይዟል በቃል
ድንግል ሀርና ወርቅ ፈትላለች በአዋጅ
ለወልድ ሙሉ ልብስ ሆኖ ሊዘጋጅ
መንፈስ #ቅዱስ ነበር ድርናማግ አዋሀጅ
ገብርኤልን ልኮ አብስር አለው እንጅ

🥀 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❤🙏🍃

#ቅድስ ገብርኤል ወቶ ከመቅርት
ይጠብቀን ምልጃው አይለየን❤🙏
#መልካም ቀን ❤🙏

ውድ የተዋሕዶ ልጆች እንኳን አደረሰን፤አደረሳችሁ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
25/01/2024

ውድ የተዋሕዶ ልጆች እንኳን አደረሰን፤አደረሳችሁ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ውድ የተዋሕዶ ልጆች እንኳን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏
19/01/2024

ውድ የተዋሕዶ ልጆች እንኳን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏

ውድ የተዋሕዶ ልጆች እንኩዋን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏🙏
19/01/2024

ውድ የተዋሕዶ ልጆች እንኩዋን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏🙏

Address

Bahir Dar

Telephone

+251955172269

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Miskaye Hizunan/ ምስካዬ ሕዙናን የበጎ አድራጎትና መንፈሳዊ ጉዞ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Miskaye Hizunan/ ምስካዬ ሕዙናን የበጎ አድራጎትና መንፈሳዊ ጉዞ:

Share

Category