Doch HD

Doch HD •No Racism •No Hate •No Distortions Doch HD ገና በጅምር ላይ ያለ የመረጃና የመዝናኛ ሚዲያ ነው። በዚህም መረጃ ሰጪ ቪዲዮ እና ምስል እንዲሁም ፅሁፍ በየቀኑ በየሰዓቱ ከእኛ ይመልከቱ። ዶች

የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች ሰርቪስ የሚውሉ 2 ዘመናዊ ባሶችን በ44 ሚሊዮን ብር ገዛ።‎የጌዴኦ ዞን አስተዳደር 44 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸውን ለመንግስት ሰራተኞች ሰር...
08/07/2025

የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች ሰርቪስ የሚውሉ 2 ዘመናዊ ባሶችን በ44 ሚሊዮን ብር ገዛ።

‎የጌዴኦ ዞን አስተዳደር 44 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸውን ለመንግስት ሰራተኞች ሰርቪስ የሚውሉ ሁለት ዘመናዊ ባሶችን አስገብቷል።

የህንድ ስሪት የሆኑና EICHER የሚል ስያሜ ያላቸው እነዚህ ዘመናዊ የህዝብ ማመላለሻ ባሶች 61 ወንበር ያላቸው ሲሆን የመንግስት ሰራተኞችን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።

የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን

ዶች

በካፋ ዞን የዴቻ ወረዳ አስተዳደር ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት በደረጃ ዕውቅና ሰጠ።በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን የዴቻ ወረዳ አስተዳደር "አገልጋይነት ክብር ነው"...
08/07/2025

በካፋ ዞን የዴቻ ወረዳ አስተዳደር ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት በደረጃ ዕውቅና ሰጠ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን የዴቻ ወረዳ አስተዳደር "አገልጋይነት ክብር ነው" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የዕውቅና እና ሽልማት መረሃ ግብር በአፈፃፀማቸው ላቅ ያለ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማትና ሠራተኞች የዋንጫና የሰርቲፊኬት ሽልማት ሰጠቷል።

በዚህም :-

1ኛ). የወረዳው ፍርድ ቤት
2ተኛ). የወረዳው ፍትህ ፅ/ቤት
3ተኛ). የወረዳው ንግድና እንዱስትሪ ፅ/ቤት

በመሆን ሽልማታቸውን ተረክበዋል። የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ዘገባ👉https://telegra.ph/Decha-07-08

ዶች

የዳውሮ ባህል ማዕከል ግንባታ ቀሪ ሥራዎችን በ1 ዓመት ጊዜ ወስጥ ማጠናቀቅ የሚያስችል ስምምነት ላይ ተደረሰ። የዳውሮ ባህል ማዕከል አዳራሽ ግንባታ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ የመንግሥት ልማት...
08/07/2025

የዳውሮ ባህል ማዕከል ግንባታ ቀሪ ሥራዎችን በ1 ዓመት ጊዜ ወስጥ ማጠናቀቅ የሚያስችል ስምምነት ላይ ተደረሰ።

የዳውሮ ባህል ማዕከል አዳራሽ ግንባታ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ የመንግሥት ልማት ድርጅት ከሆነው ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ጋር አሰራሩን ጠብቆ ቀሪ ሥራ እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል።

ግንባታው አሁን ያለበት ደረጃ 22.9 በመቶ ብቻ በመሆኑ የግንባታው ቀሪ ስራዎች የምህንድስና ግምት ዋጋ 3 መቶ 85 ሚሊዮን 5 መቶ 09 ሺህ 26 ብር ሲሆን በምህንድስና ግምቱ ዋጋ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ግንባታውን እንዲያጠናቅቅ የሚያስችል የውል ስምምነት ተደርሷ።

የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ እንደገለጹት የዳውሮ ዞን የባህል ማዕከል አዳራሽ ግንባታ የዳውሮ ልማት ወዳድ ማኅበረሰብ እና አጋሮቹ በልዩ ትኩረት የበኩላቸውን ድርሻ እያበረከቱ መቆየታቸውን ገልፀዋል ።

ይህ የተቋረጠው ግንባታ እንደገና እንዲጀመር የዳውሮ ልማት ማህበር የበላይ ጠባቂ ፣ የቦርዱ አባላትና በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላት ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም ገልጸዋል። የዳውሮ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ዝርዝር ዘገባ👉https://telegra.ph/DCCH-07-08

ዶች

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ 79 በመቶ የደረሰ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ወደ ሥራ ይገባል።የኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) የሚዛን አማን አው...
08/07/2025

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ 79 በመቶ የደረሰ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ወደ ሥራ ይገባል።

የኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው አሁን ላይ 79 ከመቶ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን እስከ ቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር ድረስ ግንባታው ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

አሁን ግንባታው የ1.1 ኪሎሜትር የአውሮፕላን መንደርደሪያ ኮንክሪት አስፓልት ንጣፍና 2.3 ኪሎ ሜትር የውሃ መስመር የመቀየር ሥራ መሰራቱም ተገልጿል።የቤንች ሸኮ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ዝርዝር ዘገባ👉https://telegra.ph/BSZGC-07-08

ዶች

"ካፊ-ኖኖ የሥራ ቋንቋ ነው ቢባልም በሚገባው ልክ ጥቅም ላይ አይውልም"ቋንቋው አከባቢ እሰራለሁ ያሉ የዶች ቤተሰብ ይህንን ፅፈው ልከዋል፦"Kaffi noonoo kaffi maccoochi shu...
08/07/2025

"ካፊ-ኖኖ የሥራ ቋንቋ ነው ቢባልም በሚገባው ልክ ጥቅም ላይ አይውልም"

ቋንቋው አከባቢ እሰራለሁ ያሉ የዶች ቤተሰብ ይህንን ፅፈው ልከዋል፦

"Kaffi noonoo kaffi maccoochi shuunee noonoo tuneebe getaa bi maachetooche kotti meeti gaacoon immi toommooch danehe.

Macco ebi malloon gaachoona bi noonoona bi iritoon yibbaatoona tuneba kooroona biriyee bi gaachemmoocho meeti heenoon kaachite.

Beshet keelli agenooch giyiti paanale ihatiyoona kaffi noonoo beet daqqoona bekket tollena'o toommooch gamini iihatiyoo giyaa bari baree kaatteena'o koteteete.

Ebi ihaatiyee goorooch bekket tolleena'o geta giddetina'o daggooche 1nno kaffi noonoo guudee shuunee noono tunebeeta meeti aaboon baribare iinjooch giddebeet sanedena'o amaari noonoona tuno.

2 baribaree taatecho tuneba qelli goreena'och macco gaacoon danoyich bi waammona bi noonoona iibbiyoo qajjichi amaari noonooch baach koonjo imoona shaahimmina'o iritena'one getaa tiyitina'o dagooche daneheete.

Tunebaani andoona tunegaata ebi iriteena'on biishooch gamini koonjo icheta ciichiyaache .

Ebi mooshoon ciinnimmi kuxina'o ebina ebin shaahee mooshena'on koonjo imi boono shuunemmoch shalligicho shunnehon.

Galletehon!"

አጅግ ተውቦ ዳግም የተደራጀው ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (SBC)ድንቅ ሥራ ነው። ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያም መሠል አይነግቡ የሚዲያ ተቋም እንደምትገነባ እናምናለን። በደንብም ታስቦበት ሊ...
08/07/2025

አጅግ ተውቦ ዳግም የተደራጀው ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (SBC)

ድንቅ ሥራ ነው። ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያም መሠል አይነግቡ የሚዲያ ተቋም እንደምትገነባ እናምናለን። በደንብም ታስቦበት ሊሰራ የሚገባው ትልቅ የጊዜው ወሳኝ ተቋም ነው።

ያሉንንም ተቋማት ይበልጥ ማደራጀትና ዘመኑን ወደሚመስል ተቋም ማሸጋገር ይጠይቃል። በአንድ ጀንበር የሚከወን ተግባር ባይኖርም ከታች ጀምሮ ጥሩ መሰረት መጣልና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻሉ የክልሉን ህዝብ በሚመጥን መልኩ መሥራት ያስፈልጋል።

በሥራ ላይ የሚገኙና ገና በመደራጀት ላይ ያሉ የክልላችን የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም ከዚህ ተቋም ልምድ ቢወስዱ፤ ከዚያም በቀሰሙት በጎ ልምድ ራሳቸውን መቃኘት ቢችሉ መልካም ነው።

ዶች

ባለስልጣኑ ወደ ቴፒ ከተማ የማይቋረጥ የበረራ አገልግሎት እንዲሰጥ ዋና አስተዳዳሪ አበበ ማሞ ጠየቁ።የቴፒ ከተማ አነስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያ የኢፌዴሪ የትራስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒ...
08/07/2025

ባለስልጣኑ ወደ ቴፒ ከተማ የማይቋረጥ የበረራ አገልግሎት እንዲሰጥ ዋና አስተዳዳሪ አበበ ማሞ ጠየቁ።

የቴፒ ከተማ አነስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያ የኢፌዴሪ የትራስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት ተደርጓል።

በዚህም ንግግር ያደረጉት ሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ዞኑ ዕምቅ የተፈጥሮ የደን ሽፋን ያለበትና ለቡናና ሻይ ልማት ስራዎች ተመራጭ ያደርገዋል ብለዋል።

መንግስት የየብስና የምድር ትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ በአካባቢው ያለውን ብዝሃ የኢኮኖሚ ዘርፍ ወደ ተሻለ የገበያ አማራጭ በማቅረብ ከኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

87 ሺህ ሄክታር የሚሆን ቡና በዞኑ አንደሚገኝም እና 17 ሺህ ሄክታር መሬትም በቅመማ ቅመም ሰብሎች እየለማ ይገኛልም ብለዋል ።

የኢትዮጵያ ሲቪላይዜሽን ባለስልጣን ሳይቋረጥ የበረራ አገልግሎት እንዲሰጥ አቶ አበበ ጠይቀዋል ።

በዕለቱም የፌደራል፣የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ዶች

በክልሉ ከተሞች በሚዛን አማን፣ ቦንጋና ቴፒ የተጀመሩ የአየር ማረፊያዎች ይበልጥ ተጠናክረው ወደ ሥራ ይገባሉ።የቴፒ መለስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያና የቡና ቅምሻ ማዕከል ተመረቅዉ ለአገልግሎት ...
08/07/2025

በክልሉ ከተሞች በሚዛን አማን፣ ቦንጋና ቴፒ የተጀመሩ የአየር ማረፊያዎች ይበልጥ ተጠናክረው ወደ ሥራ ይገባሉ።

የቴፒ መለስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያና የቡና ቅምሻ ማዕከል ተመረቅዉ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በዚህም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የቴፒ አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ በይፋ ስራ መጀመሩ ለኢትዮጵያ የመንሰራራትና የከፍታ ምሳሌ ነው ብለዋል።

ብልጽግና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ይህንን ውጤታማ ለማድረግ የክልሉ መንግስት የድርሻውን ይወጣል ብለዋል።

በክልሉ በቦንጋ፣በሚዛን አማንና በቴፒ ከተማ የተጀመሩት የአውሮፕላን ማረፊያ ልማት ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው ወደ ስራ እንዲገቡ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ።

በታርጫና በማጂ ቱም ከዚህ ቀደም አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ለዘመናት በመቋረጣቸው በህብረተሰቡ ዘንድ የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ በመሆናቸው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዳግም ወደ ስራ እንዲገቡ ያደርግ ዘንድ ጠይቀዋል።

ዶች

ፍትህ ያለ ምስክር ሳይዛነፍ የሚሰጥበት በካፋ ዞን የሺሾኢንዴ ወረዳው "አጂ-ጉዶ"በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች አንዱ የካፋ ህዝብ ነው።የካፋ ህዝብ የራሱ ጥ...
08/07/2025

ፍትህ ያለ ምስክር ሳይዛነፍ የሚሰጥበት በካፋ ዞን የሺሾኢንዴ ወረዳው "አጂ-ጉዶ"

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች አንዱ የካፋ ህዝብ ነው።

የካፋ ህዝብ የራሱ ጥንታዊ የባህል ሥርዓት ያለው ሲሆን ከነዚህ አንዱ በ" አጂ-ጉዶ" የሚሰጠው የዳኝነት ሥፍራ ባህላዊ የፍህት ሥርዓት ነው።

በዞኑ ሺሾኢንዴ ወረዳ መዲና ሺሺንዳ በ7 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አጋሮ ቀበሌ በዚህ "አጄ-ጉዶ" ምስክር ሳይፈለግ በእምነት እና በቃል ብቻ ፍትህ ለዘመናት ሲሰጥ ቆይቷል።

ይህ እጅግ የተከበረና የተፈራ ስፍራ ላይ ተገኝቶ በትዳሩ ያልታመነ፣ የዋሸና የሰረቀ እንዲሁም ካለ ምስክር እኩይ ነገር አድርጎ የሸሸገና ተበድሮ የከዳ ሁሉ ሊዋሽ የማይችልበት ቃልና እምነት የሚፈራበት የተከበረ ቦታ ነው።

ቦታው በ"አጋራኖ" እግርሥር የተቀመጡ ሰዎች ለገጠሟቸው በመደበኛው የህግ ሥርዓት ሊፈቱ የማይችሉ ነገሮች ሁነኛ መፍትሔ የሚያገኙበትም ነው።

በዚህ ሥፍራ ከከበሩ አባት መጥተው እጣንና ሌሎች ነገሮችን የወሰዱ ሰዎች በብዙ እንደሚሳካላቸውና ከተቸገሩበትም ነገር እንደሚያርፉ እንደሚታመን የቀዬው ሰዎች ይናገራሉ።

አንዱ መንፈሱ የተጨነቀበት ሰው ከአባት መጥቶ ችግሩን ተናግሮና ምርቃት ተቀብሎ ብቻ ከዚያ ካስጨነቀው ነገር እንደሚያርፍ ከ"ኦጋራኖ" ምርቃት የተቀበሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በትዳራቸው ያልታሙኑ፣ ተበድረው የከዱ፣ ሳይታይ በስውር አንዳች ነገር አድርገው የሸሸጉና ያልተገባ ነገር የተደረገባቸው ሁሉ እዚህ መፍትሔ ያገኛሉ።

በዚህ ሥፍራ በየዓመቱ በዓል የሚከበር ሲሆን የዓመቱ ክንውኖች ይነሱበታል፤ ባህላዊ ጭፈራና ደስታም የዚሁ ኩነት አካል ናቸው። የቀዬው ነዋሪው ያከብራል በነቂስ ይገኝበታል።

ይህንን ባህል የወረዳው መንግሥት ይበልጥ ለማጠናከር የመንገድ መሰረተ ልማት ሥራዎችን ለመስራት ማቀዱና በዚህ ሥፍራ የተሰጠውም ፍትህ እንዳይሻር ከመንግሥት ጋር እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች እንዳሉ መብራራቱን ዶች ተመልክቷል።

ዶች

ወላይታ ሶዶ ከተማ የመጀመሪያ ሴት ከንቲባ ሾመች።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾሞላታል።በዚህም ወ/ሮ እታገኝ ሀ/ማሪያም የወላይታ ሶዶ ከተማ ...
08/07/2025

ወላይታ ሶዶ ከተማ የመጀመሪያ ሴት ከንቲባ ሾመች።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾሞላታል።

በዚህም ወ/ሮ እታገኝ ሀ/ማሪያም የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።

ከንቲባ እታገኝ በከተማዋ ታሪክ የመጀመሪያ ሴት ከንቲባ ናቸው ተብሏል።

ዶች

08/07/2025

"ስለ ኮንታ ምን ልንገርህ...ተአምር ነው የተሰራው...ህዝቡ ቀድሞ ባይሰለጥን ጠብቆ አያቆይም ነበር"

በሃገራችን የሚገኙ እውቅ አርቲስቶች ኮንታን ተመልክተው ነበር። በዚህም የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ያነጋገርናቸው የጥበቡ አለም ፊታውራሪዎቹ በኮንታ ውበት ተደንቀዋል። ሃሳባቸው ከቪዲዮ ተያይዟል።

ዶች

የክልልና ፌደራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ ቴፒ ገባ።የክልልና ፌደራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ገብ...
08/07/2025

የክልልና ፌደራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ ቴፒ ገባ።

የክልልና ፌደራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ገብቷል።

የሥራ ኃላፊዎቹ በሸካ ዞን በሚኖራቸው ቆይታ የቴፒ አየር ማረፊያ ዳግም ሥራ የማስጀመር እና የቴፒ የቡና ቅምሻ ማዕከል ይፋዊ ስራ የሚያስጀምሩ ይሆናል።

በኢፌዲሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)ና የኢፌዲሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ያሉት ልዑክ ነው።

ልዑኩ ቴፒ ከተማ ሲደርስም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ከሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአከባቢው ማኅበረሰብፐጋር ደማቅ አቀባበል ማድረጋቸውን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቦት ዶች ተመልክቷል።

ዶች

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Doch HD posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Doch HD:

Share