19/07/2025
♦በድጋሚ ለቅሶ ሆነ የሁሉም ልብ ተነካ የአርባምንጭ እና የኢትዮጵያ ልጅ የኔ በሚላቸው ሰዎች እጅ ህይወቱ አለፈች!
"በሚስቱ እና በሚስቱ እህት ባል እንደተገደለ ፍርድ ቤት አረጋገጠ" ! በጣም ያማል 🥺💔🥺
የአርባምንጭ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊያን ደግሞ
"ስርዓተ ፍትሃት እንዲደረግለት እንጠብቃለን" አልን!
ይህ ልጅ በህይወት ዘመኑ ላይ በተገለጡ ስኬት እና ድሉ ላይ ሁሉ ቅድስት ቤተክርስቲያን አብራው እንድትገለጥ አድርጎ አልፏል።
ህገወጥ ጵጵስና ወቅት እንደ ታዋቂ ተጫዋች ሳይሆን እንደ ተራ ምዕመን " ለምን?" ብሎ ተሟግቷል። በእዛ በገነነበት ዘመኑ እንኳን እርሱ ለቤተክርስቲያን ምንም እንደሆነ አምኖ በጥምቀት በዓል ወቅት ለታቦት ምንጣፍ እያነጠፈ በታናሽነት ያገለግል ነበር።
ኳስ ለመመልከት ብቻ አስቦ በመጣ ህዝብ መሃል ከክብረ ቅዱሳን እስከ ክብረ ማርያምን አግዝፎ ስብኳል።
ወጣቶች በውድቀታቸው ሰዓት ሱስ ውስጥ ሳይሆን ቅድስት ቤተክርስቲያን አጸድ ውስጥ ሄደው መውደቅ እንዳለባቸው እርሱ በደከመበት ሰዓት ተመላልሶ አሳይቶ አርዓያ ሆኗል። ትዳር በዳንኪራ ሳይሆን በአርምሞ በቅዱስ ቁርባን እንደሚከብር ሆኖ አሳይቷል።
ነገር ግን ድራማ በበዛበት ትርዒት ነፍሱ በሰዎች እጅ ተነጠቀ። በህይወት እያለ ያከበራት እና የገለጣት ቤተክርስቲያን እንኳን በትርዒቱ ተዘናግታ ስርዓተ ፍትሃት ሳትፈጽምለት እንደ ኢአማኝ ተቀበረ። በህይወት ዘመኑ ካልተለያት ቅድስት ቤተክርስቲያን እንኳን ሞቱን ለዩ።
ወጣቶች በቤተክርስቲያን አውደ ምህረት እርሱን ለመዘከር አስበው ስርዓት ስለማይፈቅድ እየተቃጠሉ እንባቸውን ወደ ውስጥ አፍስሰው አለፈ።
ዛሬ ይህ ሁሉ የተሸፋፈነ ድራማ ተገልጦ የሀገር እና የቤተክርስቲያን ድንቅ ልጅ በተቀነባበረ መልኩ በሚስቱ እና በሚስቱ እህት ባል እንደተገደለ ፍርድ ቤት አረጋገጠ። በጣም ያማል።
ይህቺ ነፍስ ድጋሚ ሐዘን እና ለቅሶ ይገባታል? አይገባትም። ምክንያቱም ይህ ልጅ ሞቶ የሚበሰብስ የሰዶቃውያን ዘር ሳይሆን በየምስራች ቃል በክብር የሚነሳ በሥጋ ወደሙ የታተመ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ነው።
ነፍስ ይማርልን!
አሌ የቤተክርስቲያን ልጅ ነበረ በጣም አዝነናል ነፍስ ይማር
Andualem Degefu