Ethio Today News

Ethio Today News Ethio News

10/04/2024
09/04/2024

Check out abenezer’s video.

10/08/2021

Wud Ye Hagere Lijoch Kemechem Gze Bebelete Kurtignineten Miteyk Gze Lay Dersenal. Hulachinim Betebabere Kid Yhnin Fetenan Malef Alebin Mengst Bchawun Mnm Madireg Aychilm Hulachinm Le Hagerachn Le Wud Ethiopia Zeb Mekom Alebn. Ketetebabern And Kehonin Yemanalifewu Ngr Yelem . ኢትዮጵያ በልጆቷ ታፍራና ተከብራ ለዘለአለም ትኑሪ!!

25/06/2021

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የልማት እንጅ የፀጥታ ጉዳይ ባለመሆኑ ሱዳን ጉዳዩን ወደ ፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷ ተቀባይነት የለውም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሱዳን እና ግብፅ የህዳሴውን ግድብ ድርድር ወደ ፀጥታው ምክርቤት እንውሰደው ማለታቸው የህብረቱን ጥረት ለማደናቀፍ በማሰብ ስለሆነ ፣ኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እጁን ያስገባ የሚለውን የሱዳንና የግብፅን አቋም ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ገልጻለች ።

ግብፅና ሱዳን በአፍሪካ ህብረት የተጀመረውን ድርድር ከ9 ጊዜ በላይ አቋርጠው አሁን ደግሞ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት እንሂድ ማለታቸው ህብረቱን ብቻ ሳይሆን የሶስቱን አገራት ቀጣይ ግንኙነት እንሚሸረሽረውም የውጭ ጉዳይ በመግለጫው አንስቷል። ከዚህ በተጨማሪም ጉዳዩ የአፍሪካውያን ሆኖ ሳለ ግብፅና ሱዳን ግን ወደ ማይመለከተው የአረብ ሊግ በመውሰድ እያወሳሰቡትና አሁንም ድረስ የቅኝ ዘመን ሀሳብን እያንፀባርቁ እንደሆነም አመልክተዋል ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤትም ሱዳንና ግብፅ የአፍሪካ ህብረትን ድርድር እንዲያከብሩ ግፊት ያድርግ ስትል ኢትዮጵያ ጠይቃለች።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የልማት እንጅ የፀጥታ ጉዳይ ባለመሆኑ ሱዳን ጉዳዩን ወደ ፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷ ተቀባይነት የለውም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሱዳን እና ግብፅ የህዳሴውን ግድብ ድርድር ወደ ፀጥታው ምክርቤት እንውሰደው ማለታቸው የህብረቱን ጥረት ለማደናቀፍ በማሰብ ስለሆነ ፣ኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እጁን ያስገባ የሚለውን የሱዳንና የግብፅን አቋም ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው ገልጻለች ።

ግብፅና ሱዳን በአፍሪካ ህብረት የተጀመረውን ድርድር ከ9 ጊዜ በላይ አቋርጠው አሁን ደግሞ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት እንሂድ ማለታቸው ህብረቱን ብቻ ሳይሆን የሶስቱን አገራት ቀጣይ ግንኙነት እንሚሸረሽረውም የውጭ ጉዳይ በመግለጫው አንስቷል። ከዚህ በተጨማሪም ጉዳዩ የአፍሪካውያን ሆኖ ሳለ ግብፅና ሱዳን ግን ወደ ማይመለከተው የአረብ ሊግ በመውሰድ እያወሳሰቡትና አሁንም ድረስ የቅኝ ዘመን ሀሳብን እያንፀባርቁ እንደሆነም አመልክተዋል ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤትም ሱዳንና ግብፅ የአፍሪካ ህብረትን ድርድር እንዲያከብሩ ግፊት ያድርግ ስትል ኢትዮጵያ ጠይቃለች።

25/06/2021

ኢንጂነር እምብዛ ታደሰ በታጣቂዎች ተገሎ መገኘቱን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ!

በመቐለ ከተማ ከሁለት ቀናት በፊት በግምት ከቀኑ ሰባት ሰዓት በኃላ ባለው ግዜ ፣ ከቢሮ ወደ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ የአየር ማረፊያ ለመጓዝ በተዘጋጀበት፣ ለግዜው ማንነታቸው ባልታወቁ አፋኞች በሐይል ተወስዶ ደብዛው መጥፋቱ ሲነገርለት የቆየው ወጣቱ እንጅነር እምብዛ ታደሰ ፤ በጨካኝ የከተማ ሽብር ተልእኮዎች አስፈፃሚ ወንጀለኞች ተገድሎ ፤ በፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ሐይሎች በተከናወነ አሰሳ ፣ በትላንትናው እለት ከረፋዱ አምስት ሰዓት በዓይደር ልዩ ስሙ ማረምያ ቤት በተባለ ስፍራ ተገድሎ ብቻ ሳይሆን ለጅቦች ከተጣለበት ስፍራ ቁርጥራጭ የሰውነት አካላቱን በመለየት በተጨማሪ ምርመራም፤ በአረመኒያዊ አፈፃፀም በጭካኔ መገደሉን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ገዳዮች ይህንን መሰል ወንጀላቸውን ከመፈፀማቸው በፊትና በኃላ ያለ ህፍረትና መሸማቀቅ በሞትና መከራ ወኪል ልሳኖቻቸው በግልፅ በድፍረት የሚናገሩ ከመሆናቸውም በላይ፤ በሐሳብና ተግባራቸውም በትግራይ ወጣቶች ሞትና መከራ የመነገድና የመደመጥም ተልእኮ እንዳላቸውም አጥፊው ቡድን እና ደጋፊዎቹ ሃላፊነት ወስደው በአደባባይ ሽንጣቸውን ገትረው መስክረዋል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ በየትኛውም የተግባርም ሆነ በህግ የተቀመጠ የተልእኮ ወሰን መለኪያዎች በተለይ ባለፋት ጥቂት ሳምንታት የተሻሻሉ የአደጋ ጊዜ አመራር መርህዎችን በተከተሉና ሀላፊነት እና ወገናዊነት በሚሰማቸው የህዝብ ልጆች ፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትና የተቋረጡ አስፈላጊ ማህበራዊ አገልግሎቶችን የማስቀጠል ፣ነፍስ አድን ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግና ለህዝቡ ጊዜያዊ እፎይታ ለመስጠት በሚያስችሉ የዘመቻ ስራዎች ተሳትፎ፣ አንፃራዊ የህብረተሰብ ተሳትፎ መሻሻል ባገኘበት በአሁኑ ጊዜ መፈፀሙ ፣ የጥፋት ሀይሎቹ እኩይ አላማቸውን ከህብረተሰቡ የህልውና ጉዳይ በላይ ያስቀደሙ መሆናቸውን በግልፅ የሚያሳይ፤ ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ እነዚህን የመከራ ነጋዴዎች በቃ ሊላቸው የሚገባበት የመጨረሻው ደቂቃ ላይ እንደምንገኝ በጥብቅ የሚያመላክት ሀቅ ነው።

በዚህ አጋጣሚ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በእንጅነር እምብዛ እና በአጠቃላይ ባለፋት ተከታታይ ወራት በንፁሐን አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶች በጥብቅ እየኮነነና እያወገዘ ፤ ለሟች እንጅነር አርቲስት እምብዛ ታደሰ እና ሌሎች በለጋ እድሜያቸው የተቀጠፉ የጊዜያዊ አስተዳደር አባላት ቤተሰቦች ፣ የስራ ባልደረቦችና አፍቃሪዎቹ በሙሉ ፈጣሪ መፅናናት እንዲሰጥልን እየተመኝን ፣ በወንድማችን እንጅነር እምብዛ ታደሰ አሰቃቂ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን።
------ETHIO-MEREJA-----
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot

25/06/2021

#ሳዑዲአረቢያ

በእስር ላይ ያሉ ዜጎችን ለመርዳት ከትላንት በስቲያ በይፋ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።

በማህበራዊ ሚዳያ ላይ የቀረበውን ተከትሎ እጅግ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ክፍተኛ ርብርብር እያደረጉ ይገኛሉ።

ወገኑን ወዳድ የሆነው የኢትዮጵያዊ ችግር ላይ ለሚገኙት ዜጎች ደከመኝ ፤ ሰለቸኝ ሳይል የአቅሙን ሁሉ እያበረትከተ ነው።

እየተደረገ ካለው የቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪም ከኤምባሲው ሰራተኞች ውጭ ያሉ ዜጎች በጉልበት ድጋፍ እያደረጉ ነው።

በጅዳና አካባቢው ያለው ኢትዮጵያዊ በእስር ቤት ውስጥ ያሉና የተቸገሩ ወገኖቹን ለማገዛ ከድሮ በበለጠ የአንድነት ስሜት እየተረባረበ ይገኛል።

እየተደረገ ያለው ድጋፍ ፦
- ለህፃናት የሚሆን ወተት
- የህፃናት ዳይፐር /ሃፋዛ/
- ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎች የሚሆኑ ደረቅ ምግቦች - ለሴቶች እና ለሕፃናት የሚሆኑ የመፀዳጃ ቁሳቁሶች በተለይ ዋይፕና ሞዴስ
- የሚጠጣ ውሃ
- ፍራሽ የመሳሰሉት ነው።

NB : የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ\ቤት ጅዳ፥ የጄዳና የአካባቢው ማህበረሰብ (ኮሚዩኒቲ) ጽ / ቤት ጥሬ የገንዘብ ዕርዳታ ለዚሁ አላማ አይቀበልም።

08/03/2021

በየመን በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በደረሰ እሳት አደጋ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በየመን በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በደረሰ እሳት አደጋ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ የእሳት አደጋው በመዲናዋ ሰንዓ ሳዑዲ ዓረቢያ ካደረሰችው ጥቃት በኋላ የተከሰተ ነውቅ ተብሏል፡፡ በአደጋው ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ ከ170 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውንም የተመድ የፍልሰተኞች ድርጅት አስታውቋል፡፡ ምንጭ፦ ቢቢሲ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ…

08/03/2021

ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ እየተከበረ ነው፡፡ እለቱ ዓለም ላይ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረም ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያም “ጀግኖቻችንን እወቋቸው፤ አድንቋቸው” በሚል መሪ ቃል በመከላከያ ሚኒስቴር ተከብሯል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ እና የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ፊልሰን አብዱላሂ ተገኝተዋል። ወቅታዊ፣ትኩስ…

14/01/2021

አቦይ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ትናንት በቁጥጥር ስር የዋሉ የሕወሓት አመራሮች ከነበሩበት ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል

25/12/2020

የሶማሌ ክልል በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው የህይወትና የአካል ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለፀ።

ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ለፍቶ አዳሪ ንጹሃን ዜጎችን በማጥቃት ሀገርንና ህዝብን ወደ ትርምስ ለማስገባት ተቀናጅተው የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶ የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ የክልሉ መንግሥተ የሚታገል መሆኑን ይገልፃል፡፡

የክልሉ መንግስት የፌደራል መንግስት በአጥፊዎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ህብረተሰቡም አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ እያቀረበ ሕይወታቸውን ላጡት ለቤተሰቦችና የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Address

Bonga

Telephone

0917770976

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Today News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share