Otona Times

Otona Times Otan love

02/02/2024
 ከ3 ሚሊዮን በላይ መራጮች ሰኔ 12 በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ለመምረጥ በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተሰማሰኔ 12 በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ከ3 ሚሊዮን በላይ መራጮች ለመምረጥ በጉጉት እየተ...
31/05/2023



ከ3 ሚሊዮን በላይ መራጮች ሰኔ 12 በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ለመምረጥ በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተሰማ

ሰኔ 12 በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ከ3 ሚሊዮን በላይ መራጮች ለመምረጥ በጉጉት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተሰምቷል፡፡

ምርጫ ቦርዱ መራጭ ህዝቡ በወላይታ ዞን አንድ ሚሊዮን የሚደርስ መራጭ ህዝብ የለም ያለውን ስምተው ቁጭትና በወኔ ተላብሶ ሰኔ 12 ቀን በጉጉት እየጠበቁ ይገኛል፡፡

ሰኔ 12 የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ለወላይታ ህዝብ የማንነትና የህልውና ጉዳይ መሆኑን በማገንዘብ በነቂስ ወጥተው ነጭ ርግብን እንደሚመረጡ ታማኝ መንጮች አረጋገጡ፡፡

ልዩነታችንን አክብረን፤ ለወላይታ ህዝብ ጥቅም ለማስከበር በጋራ መቆም እንደሚያፈልግም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ የሚጦዙ ሀሰተኛና የተቀነባበሩ መረጃዎችን ህዝቡ ወደ ጎን በማለት ለወላይታ የሚበጀውን በነቂስ ወጥተው ነጭ ርግብን ይመርጣል፡፡ በዚህም መላው የወላይታ ህዝብ ታላቅ ድል እንደሚጎናጽፍም ይጠበቃል፡፡

06/01/2023

ከወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ዮሐንስ በየነ የተላለፈ የገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

በሰማይና በምድር ለሚገኙ ነገዶች የእልልታና የምስጋና ምንጭ የሆነው ነቢያት የተመኙት መላእክት ያወደሱት እረኞች ያወሩለት ሰብዓሰገል የሰገዱለት ኃጢያተኞች የዳኑበት ግዞተኞች የተፈተኑበት ለሰዎችና ለመላእክት ታላቅ ደስታ የሆነው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!

ገና የሰው ልጆች ከገቡበት የጥፋት መንገድ ሊያወጣቸው መዳን ሊሆኒልን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማሪያም የተወለደበትን ዕለት የምንዘክርበት በዓል ነው። የሰው ልጆች ከነበሩበት ዝቅታ የመውጣታቸው ተስፋ የተበሰረበት ከጨለማ ወደ ብርሃን የመምጣታቸው ምዕራፍ የተጀመረበት ታላቅ በዓል ነው - የገና በዓል።

የክርስቶስን መወለድ ሲጠብቁ የኖሩት የተወለደውን ሕፃን በማየታቸው የተገባላቸው ቃል ፍፃሜ አግኝቷል። በክርስቶስ መወለድ የሰው ልጆች ለዘመናት አብሯቸው የዘለቀው የውድቀት ጉዞ ተገትቶ አዲስ የከፍታ ጉዞ ብስራትም ታውጇል። በመወለድ፣ መውደቅ በመነሳት፥ ዝቅታም በከፍታ እንዲተካ የግድ ሆኗል።

በዓሉን ስናከብር አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከርና በማጎልበት ሊሆን ይገባል። የጀመርነው ጎልቶ የመውጣት ጉዞ ይበልጥ እንዲሰምር ኅብረታችንን አጠናክረን አንድ መሆንም ይኖርብናል።

በፈተናዎቻችን ትምህርት፣ በችግሮቻችን ጥንካሬ፣ በእንቅፋቶቻችን ብርታት እያገኘን፣ ከእያንዳንዱ ጨለማ ወዲያ ንጋት መኖሩን እያመንን፣ ዐይናችንን ወደ ወጋጋኑ አቅንተን በተራመድን ቁጥር ችግሮቻችን ወደኋላ ይሸሻሉ፤ እኛ ይበልጥ በበረታን ቁጥር የሚንመኘውን ብልጽግናን እናረጋግጣለን፡፡

ብርሃን ጨለማን፤ ሰላም ጦርነትን፣ ፍቅር ጥላቻን፣ አንድነት መለያየትን፣ ብልጽግና ድህነትን ማሸነፋቸው እንዳማይቀር ሁላችንም በቁጭት ከሰራን እና አንድነታችንን ካጠናከርን ሩቅ የመሰለን ህልም በእጃችን መዳፍ ስር እንደሚሆን መጠራጠር የለብንም፡፡

የዞናችን የለውጥ ጉዞ ፍጥነቱ ከምንም በላይ የሚወሰነው መላው የዞናችን ሕዝብ ጥንካሬና አንድነት በመላበስ ሁላችንም በተሰማረነው ስራ መስክ መረባረብ እንደሚያስፈልግም ላሳስባችሁ እወዳለሁ።

በዚህ ወሳኝ ወቅት ሁላችንም ዐቅማችን የፈቀደውን መሥራት ከቻልን፣ ያለ ጥርጥር ነገ ብሩህ ይሆናል፤ የመከራ ዘመንም እስከ ወዲያኛው ይሸኛል። ኢትዮጵያም የማትደፈር፣ የምትታፈር ሀገር ሆና በዐለት ላይ ትቆማለች።

ውድ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች በየጊዜው ለውጡን ለሚፈልገው ማህበረሰብ ጠንክሬን በመሰራት ብልጽግናን ማማ ላይ ለማስቀመጥ ኃላፊነታችንን በአግባቡ መወጣት ይኖርብናል፡፡

ለሁሉም ነገር መሠረት የሆነውን ሠላማችንን እንደዓይን ብሌናችን መጠበቅ ከሁሉም ህብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅ ስለሆን ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን አከባቢያችን መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡

ጥር 29 የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ፍጹም ሠላማዊና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅም የበኩላችሁን ድርሻ እንዲትወጡ እያሳሰብኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምርጫ ምልክት የሆነችውን ነጭ ርግብ እንዲትመረጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡

በዓሉን ስናከብር አቅመ ደካሞችን፣ ረዳት የሌላቸውን አረጋዊያን፣ አዛውንቶችንና እንዲሁም ወላጅ አጥ የሆኑ ሕፃናትን እንድንደግፍ እና ካለን እንድናካፍል ቤተሰባዊ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ ለወላይታ ዞን ሕዝቦች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) በሰላም አደረሳችሁ በማለት በራሴና በፓርቲው ስም መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!!

መልካም የገና በዓል!!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ታኅሣሥ 28 ቀን 2015 ዓ.ም

23/09/2022

ዮ ዮ ጊፋታ!
የ2015 የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል አስመልክቶ የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ዮሐንስ በየነ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መልዕክት፡፡

የተወደዳችሁ መላው የወላይታ ህዝቦች! እንኳን ለ2015 የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

ጊፋታ በዓሉ የአዲስ ዓመት ብርሃን ማብሰሪያ፣ በተለያየ ምክንያት ከአካባቢው ርቀው የሚኖሩ ወገኖች ከወላጆቻቸው ጋር የሚገናኙበት፣ የተጣላ የሚታረቅበት ታላቅ ክብረ በዓል ነው።

ጊፋታ የወላይታ ብሔር ከጥንት ጀምሮ ሲያከብሩ የነበረ የአሮጌው ዓመት ማብቂያና የአድሱ ዓመት መጀመሪያ የዘመን መለወጫ በዓል ነው፡፡

በወላይታ ህዝብ ዘንድ ጊፋታ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ አእዋፋትና የቤት እንስሳትም ጭምር በጋራ የሚያከብሩት በዓል እነደሆነ በዚሁ አጋጣሚ ልገልጽላችሁ እፈልጋለሁ፡፡

የጊፋታ በዓል በውስጡ ማህበራዊ፣ ባህልዊ፣ ፖለቲካዊና ስነልቦናዊ ፋይዳዎችን የያዘ ሲሆን በህዝቦች መካከል ያለው የአብሮነት፣ የአንድነትና የመቻቻል እሴቶች በውስጡ የሚገለጹበት ነው፡፡

በዞናችን ውስጥ ባለፉት ዓመታት ውስጥ የተከናውኑ የልማት፣የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን በማጠናከር በቀጣይም ከህዝባችን ጋር በመሆን ለመሥራት ያቀድናቸውን ተግባራት ከህዝባችን ጋር በመወያየት ጠንካራ የለዉጥ እንቅስቃሴ የምንመራበት ወቅት ሊሆን ይገባል፡፡

ጊፋታ የተጣሉ የሚታረቁበት የእርቅና የሠላም በዓል ነው፡፡ በወላይታ ብሔር ማንም የተጣላ ሰው ሳይታረቅ አዲሱን ዓመት መሻገር ነውር ነው፡፡

መላዉ የወላይታ ህዝብ ይሄ ብርቅዬ ባህል ሳይበረዝና ሳይከለስ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንዲተላለፍና ከነሙሉ ክብሩ ተጠብቆ እንድቆይ የሁል ጊዜ ትጋታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እጠይቃለሁ፡፡

የወላይታ ህዝብ ሀብትና ንብረት የሆነውን የጊፋታን በዓል በቀጣይ የኢትየጵያ ህዝብ በዓል በማድረግ በዓለም ከሚገኙ ከማይዳሰሱ የሰው ልጆች ወካይ እንድታበርክቱ ቅርሶች አንድ አድርገን ለማስመዝገብ ለምናደርገው ጥረት ሁላችሁም የበኩላችሁን አስተዋፆኦ እንድበረከቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

ተፈጥሮ ህጓን ጠብቃ፤ ክረምት በጋውን ስታፈራርቅ፣ መሄር በልጉን ስታመጣ፣ ፀሃይ ብርሃኗን፣ ስማይ ዝናቡን፣ መሬት ቡቃያዋን እንዳትከለክል ፈጣሪያችን እንዲረዳን ምኞተም ጸሎቴም ነው፡፡

ሠላም የሁሉም መሠረት ነው። ሠላም ማለት ሰው፣ ሀገር፣ ይቅርታ፣ ፍቅርና አንድነት ነው። ሠላም ካለ ሁሉም አለ። የሀገራችንን ሠላም በጋራ እንጠብቅ። ጥላቻን አርቀን በፍቅር እንኑር።

የኢትዮጵያዊነት የመጨረሻው መዳረሻው ሠላም፣ ፍቅርና አንድነት ነው። እያንዳንዳችን ለሀገራችን ሠላም የየድርሻችንን እንወጣ።

መረዳዳትና መደጋገፍ የብልፅግና አንኳር እሴት ነው!! ስለዚህ በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ በመተሳሰብ፣ በይቅር-ባይነት፣ በመግባባት፣ በወንድማማችነትና በአብሮነት መንፈስ ልናከብር ይገባናል፡፡

በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የአንድነትና የብልጽግና እንዲሆን በራሴና በዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ስም በድጋሚ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

ዮ ዮ ጊፋታ!
ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን እግዚአብሔር ይባርክ!

የደቡብ ክልል መቀመጫው አርባምንጭ ሄዷል ተብሎ እየተሰራጨ ያለ መረጃ ከእውነት የራቀ ነው_______________________ሰሞኑ ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩ ጥቅት አክቲቪስት ባዮች እድሜ ልካቸው...
04/07/2022

የደቡብ ክልል መቀመጫው አርባምንጭ ሄዷል ተብሎ እየተሰራጨ ያለ መረጃ ከእውነት የራቀ ነው
_______________________
ሰሞኑ ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩ ጥቅት አክቲቪስት ባዮች እድሜ ልካቸውን ከውሸት ዜና ያልተቆጠቡ ዛሬም ቀጥለዋል።

ከዚህ በፊት የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ የወላይታ ህዝብን ዘርፎ በኬንያ አድርጉ አሜርካ ኮብልሏ ብለው ሀሰት መረጃ ስያሰራጩ የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ላይ ደግሞ የደቡብ ክልል መቀመጫ አርባምንጭ ሄዷል ብለው የበሬ ወለደ መረጃዎችን እያሰራጩ ይገኛሉ።

እነዚህ ግለሰቦች ለግል ጥቅማቸው ብለው ከዚህ በፊት ሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨታቸው ምክንያት በወላይታና አከባቢው ሰላም በማሳጣትና በማወክ የህዝቡን ንብረት ዘርፈዋሉ፣ ንጹሃን ዜጎች እንዲሞቱ አድርገዋል።

አሁንም እንዲህ አይነት ግርግር ለማውጣትና ለመዝረፍ ቀንና ሌሊት እየሰሩ መሆናቸውን ከደህንነት አካላት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መንግስት የህዝቡን ጥያቄን ተቀብሎ ህዝቡን በሚጠቅም መልኩ ለመመለስ ቁርጠኛ ነው ከዚህ ውጪ የሚሰራጩ መረጃዎችን ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

ያልተረጋገጥና ምንጩ ያልታወቀ የውሽት መረጃ እያሰራጩ የሚገኙ ግለሰቦች አደብ ልተገዙ ይገባል። አለበለዚያ ዋጋ ሊያስከፍላችሁ ይችላል።

መታሰርን እንደጀግና ሰው አድርጉ የሚያስቡ ሰዎች የአሁን መጨረሻ ሊሆን ይችላል።

ከመታሰርን በኃላ ከመጮህ ይልቅ ጥንቃቄ እናድርግ። የክልል ጥያቄን ተገን በማድረግ የህዝቡን ሰላም ለማወክ በሚደረጉ አካላት ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ ለመወሰድ አይታገስም።

ሠላም ለወላይታ!
ሠላም ለሀገራችን!

Address

Wolaita
Dabat

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Otona Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share