05/06/2023
በኮረኔል ፈንታው ሙሃባና ኮረኔል ሞገስ ዘገየ ከሚመሩት ጫካ ከሚገኘው ፋኖ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ::
መንግሥት የእምነት ተቋማትን ለማውደም ንፁሃንን በግልፅ ለመጨፍጨፍ እንዲመቸው ህግ ማስከበር በሚል ተልካሻ ልብ ወለድ በመድረስ ሆን ብሎ በህዝባችንና በእምነት ተቋሞቻችን ላይ ግልፅ የሆነ ጦርነት በመክፈት ከፍተኛ ውድሙት በአማኞችና በእምነት ተቋሞች ላይ እያደረሰ ይገኛል::
በመሆኑም መንግሥት የራሱን ፍላጎት ፍፁም ጥላቻና እብሪት በህግ ማስከበር ሰበብ እየተወጣና ህዝባችን ላይ ባለው ወደር የሌለው ጥላቻ በግልፅ እየገደለንና ጥላቻውንም ፊት ለፊት እያሳየን ይገኛል:: ህገ ወጡና ሽብርተኛው የአብይ አህመድ መንግሥት የዘር ጨፍጫፊነቱን ህጋዊ ለማድረግ የሄደበት ርቀት ህዝብን እያታለለ የሚኖርበት ያደገበት ቀጣፊ ባህሪው እንደሆነ እኛም እንገነዘባለን ህዝባችንም ጠንቅቆ ያውቃል::
በመሆኑም አንባገነኑ የአብይ አህመድ መንግሥትና ሰራዊቱ በንፁሃን ህዝባችን ላይ እየደረሰ ባለው ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ በእጅጉ ያዘንንና ልባችን የደማ እንደሆነ ለመግለፅ እየወደድን ጉዳትና ሞት ለደረሰባቸው ንፁሃን ጠበልተኞች የገዳም አባቶች እና በመስጊድ ውስጥ ጉዳትና ሞት እንዲሁም በንፁሃን ህዝባችን ላይ የተፈፀመባችሁን ድርጊት እያወገዝን ለቁስላችሁ ምህረትን ለሞታችሁ እረፍትን ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ከልብ መፅናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን::
እንደሚታወቀው መንግሥት እንደ ህዝብ አማራን! እንደ እምነት ተቋም የኢትዮጵያን ህዝብ ነባር እምነት የሆኑትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስና እስልምንና ጠል መሆኑና እነርሱን ለማጥፋትም 7/24 ያለ እረፍት የሚሰራ ነውረኛ ኢትዮጵያ ጠል መንግሥታዊ ስርዓት መሆኑ ይታወቃል::
ይህ የከረፋ መንግሥታዊ ስርዓት የጀመረውን ከስር የዘረዘርናቸውን አፀያፊ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ስንል በጥብቅ እናሳስባለን ::
1ኛ...በታላቁ እስክንድር ነጋና በሚመራው የአማራ ህዝባዊ ግንባር /APF ላይ የሚደረግን ስም ማጥፋትና የማሳደድ ተግባር እንዲሁም በግንባሩ መሪ እስክንድር ነጋ ላይ የታወጀውን የግድያ ትእዛዝ የማንቀበለውና እስከ መጨረሻውም ከፅኑ ታጋያችን ጎን እንደምንቆም እየገለፅን ከግንባሩ የሚወርዱ ማናቸውንም ትእዛዝና ግዳጅ ለመፈፀም ሙሉ ፍቃደኞችና ዝግጁዎችም ጭምር መሆናችንን ከወዲሁ እንገልፃለን::
2ኛ...በመዲናችን አዲስ አበባ በሙስሊሙ እምነት ተከታዮች የሚደረግን ጭፍጨፋና አዲስ ከተማ ለማዋለድ በሚል ፌዝ ወይም ህዝባዊ ንቀት የመስጂድ/የእምነት ተቋማት ውድመትና ማንነት ተኮር መፈናቀሎችን የምናወግዝና ከእንግዲህ የማንታገስ እንደሆነ ለማሳወቅና የትግል ቀይ መስመራችንም እንደሆነ በማወቅ ከልጅ እስከ አዋቂ ከጎናችን እንድትቆሙ ህዝባዊ የትግል ጥሪያችንን አቅርበናል::
3ኛ...በምስ/ጎጃም ደብር ኤሊያስ ገዳም ላይ የደረሰውን አስነዋሪ መንግሥታዊ ሽብር እያወገዝን ህዝባችን ራሱን ለማይቀርለት የሞት ሽረት ትግል ራሱን ከወዲሁ እንዲያዘጋጅና የተጀመረውን ህዝባዊ ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥልና እንዲሁም ያልተቀላቀለ ለቅድስናው ትግል ራሱን እንዲያዘጋጅና በየደረጃው ለሚደረጉ ጥሪዎች ነቅቶና ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ እናሳስባለን::
4ኛ...የሃገር መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይሎች መንግሥት እያደረገ ባለው አፀያፊ ተግባር ባለመሳተፍ ህዝባዊነቱችሁን ከህዝብ ጎን በመቆም እንድታሳዩ ጥሪ እያቀረብን ይህን ማድረግ ያልቻለ ሰራዊት ከህዝብ የተነጠለ የፓርቲ ዘበኛ እንደሆነ አውቆ ከቻለ ከመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም ከማናቸውም የመንግሥት ፀጥታ ተቋማት ራሱን እንዲያገልና ከህዝብ ጎን እንዲሰለፍ በህዝብ ስም ጥሪ