
17/06/2025
►የየም ሣሜ -ኤታ እግርኳስ ክለብ ቅጣት ተጣለበት።
👉የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ እጅግ የተጠና እና በማስረጃ የተደገፈ ውሳኔ በዛሬው እለት አሰተላለፈ።
👉በቀን 08/10/2017 ዓ/ም ወራቤ ከተማ ከየም ሣሜ -ኤታ እግርኳስ ክለብ መካከል ከቀኑ በ9:00 ጀምሮ በአቢዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም ባደረጉት የእግር ኳስ ውድድር የየም ሣሜ -ኤታ እግርኳስ ክለብ የውድድር ደንብ አንቀፅ 6 ተራ ቁጥር 6.7 እና 6.9 ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ በመጣሱ እንዲሁም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አንቀጽ 67 ድንጋጌ በመተላለፍ ምክንያት የሀሰት ማስረጃዎችን /ቲሴራ / በማዘጋጀት ስለማጭበርበሩ እና የተጨዋቾችን ስም በመቀየር ያስመዘገበና ያጫወተ መሆኑ፤ ከኦሮሚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተላከልን የተጫዋች ቲሴራ ላይ የውድድር አመ/ስ/ኮሚቴ የቀረበውን ቅሬታ በማጣራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል ።
►የቅጣት ውሳኔ
👉1ኛ. የየም ሳሚ-ኤታ የእግር ኳስ ክለብ ፌዴሬሽኑ ከውድድሩ በፊት በተላከለት የውድድር ደንብ መሰረት የተጫዋች ተገቢነት ችግር እንዳይፈጠርበት ተዘጋጅቶ ለውድድር መምጣት ሲገባው አይታወቅብኝም በማለት በኦሮሚያ ክልል መጀመሪያ ሊግ ላይ በ2017 ዓ.ም እየተጫወቱ ያሉ ተጫዋቾችን ስማቸውን በመቀየር ያስመዘገበና ያጫወተ በመሆኑ ተጫዋቾቹ ተሰልፈው በተጫወቱባቸው ጫወታዎች በሙሉ በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆን የውድድርና አመራር ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ፡፡
👉2ኛ, ይህንን ተግባር የፈጸሙ የቡድን መሪ እና አሰልጣኝ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አንቀጽ 67 ተራ ቁጥር 1 በፊደል ሀ መሰረት ለአንድ አመት ከየትኛውም ውድድር እንቅስቃሴ እንዳይመሩም ሆነ እንዳይሳተፉ ታግደዋል ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እግር ኳስ ፌደሬሽን የውድድርና አመራር ስነስርዓት ኮሚቴ።
►በተስፋሁን ሽጉጤ