Ghion Multimedia & Promotion - ግዮን መልቲሚዲያና ማስታወቂያ

  • Home
  • Ghion Multimedia & Promotion - ግዮን መልቲሚዲያና ማስታወቂያ

Ghion Multimedia & Promotion - ግዮን መልቲሚዲያና ማስታወቂያ Let's promote our culture, service and product!.

ከሶስቱ የማርቆስ ልጆች በሙያዉ ደብረ ማርቆስን በሚገባ ያስተዋወቀዉ ማን ነዉ?
27/09/2022

ከሶስቱ የማርቆስ ልጆች በሙያዉ ደብረ ማርቆስን በሚገባ ያስተዋወቀዉ ማን ነዉ?

 # የእርዳታ_ጥሪ_ለአሰልጣኝ_ሚልዮን_ማትዮስየእግር ኳስ ደጋፊ እና ባለቤት የሆንከው ያገር ሰው አሰልጣኝ ሚሊዮን ታዬእገዛችን የሚፈልግበት ጊዜ ላይ ነንአሰልጣኝ ሚሊዮን ባህርዳር ተወልዶ ያደ...
03/06/2022

# የእርዳታ_ጥሪ_ለአሰልጣኝ_ሚልዮን_ማትዮስ

የእግር ኳስ ደጋፊ እና ባለቤት የሆንከው ያገር ሰው አሰልጣኝ ሚሊዮን ታዬ
እገዛችን የሚፈልግበት ጊዜ ላይ ነን
አሰልጣኝ ሚሊዮን ባህርዳር ተወልዶ ያደገና ለበርካታ አመታት ባህርዳር
ጨርቃጨርቅ * ባህርዳር ከነማ*አዲሰ አበባ ፓሊስ *ድሬዳዋ ባቡር ተጫውቶ
ያለፈ በአሰልጣኝነት ደግሞ ባህርዳር ከነማ* ወልዲያ ከነማ* አዲግራት እና
ጎጃም ደብረ ማርቆስን ለ3 አመታት ያሰለጠነ ብርቱ አሰልጣኝ ሲሆን በተለይ
ለ3አመት በቆየበት በጎጃም ደብረ ማርቆስ ሁለት ጊዜ ቡድኑን ለቶርናመንት
ያሳለፈ አንዱንም አመት በኮቪድ እስኪቋረጥ ቡድኑን ከመሪዎች ውሰጥ
እንዲገኝ ያስቻለ ብርቱ አሰልጣኝ ነው ዛሬ ግን ከሚወደው ያሰልጣኝነት ሙያው
በልብ ቧንቧ ትቦ መጥበብ ምክንያት አልጋ ላይ ከዋለ አንድ አመት በላይ
ሆኖታል በዚህም አንድ አመት በቀን ከ 10,000 እስከ 18,000 ሺህ ብር
እየከፈለ ሲታከም ቢቆይም በአሁኑ ሰዓት ከአገር ውጪ ታይላንድ ወይም ህንድ
አገር ሄዶ እንዲታከም ስለተወሰነ የማርቆስ ባለውለታችንን ከጎኑ መሆናችንን
ለማሳወቅ ከፈጣሪ በታች የተቻለንን ለማገዝ # የማርቆስ ምርጥ ከ # ባህርዳር
ምርጥ የእግር ኳስ ጨዋታ እሁድ በ 28 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ደብረ ማርቆስ
እስታዲየም እንገናኝና አለንልህ እንበለው
የመግቢያ ዋጋ ክቡር ትሪቡን 25
ቀሪ ቦታዎች 10 ብር
ትኬቱን ከነገ ማለትም ከአርብ 26 ጀምሮ ትኬት ከሚያዞሩ ልጆት ያገኛሉ ።
*ሚሊዮኖች ከሚሊዮን ጋር*
በግል በአካውንት ለመርዳት የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተቀመጠው ሂሳብ
ቁጥር ገቢ ያድርጉ ።

1000472949733 ኢ/ያ ንግድ ባንክ
ጌጡ ፣ አራዶም እና እንዳለው ጥላሁን

ባህርዳርን ከዘንባባዋ ቀጥሎ ዉበት ከሰጧትና ተወዳጅ ከተማ ካደረጓት ዛፎቿ መካከል ይህ የጃካራንዳ ዛፍ አንዱ ነዉ።በቀበሌ 13 ሆስፒታል መስመርና ቤዛዊት በስፋት የሚገኝ ሲሆን የባህርዳር ወጣ...
16/05/2022

ባህርዳርን ከዘንባባዋ ቀጥሎ ዉበት ከሰጧትና ተወዳጅ ከተማ ካደረጓት ዛፎቿ መካከል ይህ የጃካራንዳ ዛፍ አንዱ ነዉ።

በቀበሌ 13 ሆስፒታል መስመርና ቤዛዊት በስፋት የሚገኝ ሲሆን የባህርዳር ወጣቶችና ባለሀብቶች በራሳቸዉ ተነሳሽነት በየአመቱ ጃካራንዳ የመትከል ዘመቻ ያካሂዳሉ። ይህ ተግባር ባህርዳርን ከጥቂት አመት በኋላ ወደር የሌላት ዉብ ከተማ ያደርጋታል።

የደብረ ማርቆስ ወጣቶችና ባለሀብቶች ከዚህ ትምህርት ወስደዉ በመጪዉ ክረምት ይህን ጃካራንዳ ችግኝ የመትከል ዘመቻ ቢካሄድ በተለይም ከተማችን ካላት ተስማሚ የአየር ንብረትና ምቹ አቀማመጥ አንፃር ዉብ ማራኪና ተመራጭ ከተማ ማድረግ ይቻላል!

ከወዲሁ ይታሰብበት!
! !

ሶስቱ የደብረ ማርቆስ አንጋፋ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች❤️❤️❤️1, ድብዛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት2, አብማ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት3, ንጉስ ተክለ ሀይማኖት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤ...
14/05/2022

ሶስቱ የደብረ ማርቆስ አንጋፋ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች❤️❤️❤️

1, ድብዛ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
2, አብማ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
3, ንጉስ ተክለ ሀይማኖት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

የእርስዎ ትዝታ የቱ ነዉ?

ስለ ከተሞች  # ደብረ ማርቆስማርቆስ ወደ ሪጅኦፖሊታን ማደጓ ጥሩ ነው። ጥሩ ተስፋዎችን ይዞ ይመጣል።እንደነ ደብረ ብርሃን ያለ ደረጃ ላይ ተቀምጣ ግን እንደ በዛብህ እና ሰብለወንጌል ታሪክ ...
13/05/2022

ስለ ከተሞች # ደብረ ማርቆስ
ማርቆስ ወደ ሪጅኦፖሊታን ማደጓ ጥሩ ነው። ጥሩ ተስፋዎችን ይዞ ይመጣል።
እንደነ ደብረ ብርሃን ያለ ደረጃ ላይ ተቀምጣ ግን እንደ በዛብህ እና ሰብለ
ወንጌል ታሪክ መነሻ "ማንኩሳ" አዝጋሚ የእድገት ደረጃ ያለች ከተማ ናት።
ከተማዋ የመልማት ከፍተኛ ፀጋ አላት። በክፍለ ከተማም መከፋፈሏ ጥሩ ነገር
ነው። ማርቆስ ከልብ መለወጥ ካስፈለገ የሚከተሉት ተግባራት በፍጥነት
መተግበር አለበት።
1. ለህዝብ መዝናኛ መሆን የሚችል "የራባ ጫካ" ደኑ ውስጥ ለውስጥ የሽርሽር
መንገድ በመስራት የህዝብ ፓርክ ማድረግ። ዙሪያውን ውብና ማራኪ በሆነ
መንገድ ማጠር። ፓርኩ ውስጥ public private partnership በመፍጠር
እንዲሁም ወጣቶችን በማደራጀት የገቢ ምንጭ ማድረግ ይቻላል። የራባ ጫካን
ደኑን መቁጥና ማመናመን በፍፁም የማይታሰብ ተግባር ነው። ህወሓት በነበረች
ግዜ በደን ኢንተርፕራይዙ ስም ቀጥታ ወደ አዲግራት Pulp እና ችፑድ ፋብሪካ
ይጫን እንደነበር መረጃዎች አሉ። በቅርቡም የክልሉ ደን ኢንተርፕራይዝ ለደብረ
ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የራባ ደንን ለምን ጥቅም ላይ ማዋል እንዲቻል ጥናት
እንዲደረግለት ጥያቄ ጠይቆ እንደነበርም መረጃዎች አሉ። በቃ በቀላል አገላለፅ
ደኑ ወደ ፓርክ ተቀይሮ ማርቆስን ሳቢና ማራኪ ገፅታ ማድረግ ይቻላል። ከፓርኩ
ከፍ ብሎ ሀይቅ እንደፈለቀም መረጃ አለ። ይህ ሀይቅ ቻይና በድማሚት ድንጋይ
ስታፈነዳ የተፈጠረ እንደሆነም መረጃው አለ። ስለዚህ አካባቢውን የቱሪስት
መስህብ ማድረግ ይቻላል። ከከተማው እምብር ላይ ከሚገነባው የአማራ ባህል
ጎጃም ማዕከል ጋር ሳቢና ማራኪ የመናፈሻና መዝናኛ ከተማ ማድረግ ይቻላል።
የአየር መንገዱ ስራም እየተጀመረ በመሆኑ ጥሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ሆና
በፍጥነት ማደግ የምትችል ከተማ ናት።
2. ማርቆስን ዙሪያዋን ማካለል የሚችል የቀለበት መንገድ መገንባት። ባዕታ
ሰፈርን ከቦሌ፣ ከባለ እግዛብሔር፣ ቦሌን አዲሱን የመቃ ካምፓስን ዙሮ በኮሌጅ
ሚካኤል ታች፣ ማረሚያ ቤት ኢንዱስትሪ ፓርኩን ዞሮ ፣ አባ አስራት ገዳምን
አልፎ የጁቤ መገንጠያ በኩል አዲሱ የግብርና ምርምርና አዱስ የደ/ማ/ዩ
የግብርና ኮሌጅን ካምፓስን ቀለበት ሰርቶ መጋቢ መንገዶችንም በማስተሳሰር
ማርቆስን ውብ ከተማ ማድረግ ይቻላል።
3. ሌላው ለከተማው ምንም የማይፈይድና የሌሎችን ከተሞች እድገት መረዳት
የማይችልና ከወረዳና ከቀለበሌ ወደ ደ/ማ የተሰገሰገ ሹመኛና ጥቅመኛ
ስብስብ ማስወገድ። Merit based የስራ ድርሻ እንዲወስዱ ማድረግ። ጊዜውን
ወቅቱን መጠን የሚችልና የወደፊት እድገቷን መረዳት የሚችል አመራር
ማዋቀር።
4. የመብራትና የውሃ ችግር በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀስ እንደ ማርቆስ ያለ ከተማ
የለም። የከተማዋ የውሃና የመብራት ስራ አስኪያጆች የቅንነት፣ የአቅም ውስነት
ችግር እንዳለ አንድ ሺ አንድ ማስረጃዎች አሉ።
5. ስግብግብ ነጋዴዎችና መሬት ቸብቻቢ ባለ ስልጣናትም እንደ አሸን እንደፈሉ
መረጃዎች አሉ።
6. አዳዲስ ምሬት ቦታዎች ላይ መንገድ የማስከፈት፣ ኮቦል የመስራት፣ ፕላሉን
ጠብቆ ለኗሪዎቿ ምቹ ከተማ የማድረግ የአመራሩ ከፍተኛ ድክመት እንዳለና
የቀበሌ አመራሮችም በከፍተኛ ሙስናና ጥቅም እንደተሳሰሩ ብዛት ያላቸው
መጃዎች አሉ። አስፈላጊ ከሆነ የቀበሌ አስተዳደሮች፣ ሀላፊዎች ስም ዝርዝር
አለ።
7. የከተማዋ መንገዶች ጥበት ወደፊት ማርቆስን ሱሪ ባንገት ከሚያደርጉ
ከፍተኛ ችግር ውስጥ ቀዳሚው ነው። በአለም ባንክ ብዙ የኮብል መንገዶች
ለመሰራት ተሞክረዋል፣ ጥሩ ጅምር ነው። ከፍተኛ የውስንነትና የአመራር
ድክመት ግን ጎልቶ ይታያል።
Miky Amhara

መልካም ጨዋታ!❤️‍🩹⚪️💙ዉጤቱን ይገምቱ!
13/05/2022

መልካም ጨዋታ!❤️‍🩹⚪️💙
ዉጤቱን ይገምቱ!

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ghion Multimedia & Promotion - ግዮን መልቲሚዲያና ማስታወቂያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ghion Multimedia & Promotion - ግዮን መልቲሚዲያና ማስታወቂያ:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share