Yitbarek Gebrie Misew

Yitbarek Gebrie Misew Worry changes nothing, but trust in God can change everything.

Most Ethiopian's real life❗
17/06/2025

Most Ethiopian's real life❗

 #ሰበር‼️ ‼️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትየሕግ አገልግሎት መምሪያው ከሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ጋር በመሆን አቶ ትዝታው ሳ...
17/06/2025

#ሰበር‼️
‼️

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት
የሕግ አገልግሎት መምሪያው ከሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ
ኮሚቴ ጋር በመሆን አቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ መሰረተ።

የቤተክርስቲያናችን ሕግ አገልግሎት መምሪያ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ክስ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ የምርመራ መዝገቡ መብቱ ለሚፈቅድለት የዐ/ሕግ ዘርፍ እንዲተላለፍለፍ ጠይቋል።

በወንጀል ተጠርጣሪ /ተከሳሽ - አቶ ትዝታው ሳሙኤል
ተጠርጣሪ /ተከሳሹ ነዋሪነቱን በውጪ ሃገር በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካልን ለማዋረድ፣
ለመስደብ እና የምዕመኑን ስሜት ለመንካት ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማሰብ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እና ከ5000 በላይ ተከታዮች ባሉት የራሱ የዪቲዩብ ቻናል በመጠቀም ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

በማያያዝም ግለሰቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶችን፣ በየገዳማቱ ውስጥ የሚገኙ ገዳማውያን መነኮሳትና አገልጋዮችን በማለት፣እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በማለት፣ሲቀሰቅስ የቆየ መሆኑን የገለጸው መምሪያው ግለሰቡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትገለገልባቸውን ሃይማኖታዊ የፀሎት፣የታሪክ ፣የገድላትና ድርሳናት መጻሕፍትን ማለቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቅድስናየምታ
ከብራቸውንና የምትዘክራቸውን ቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን > ናቸው በማለት ግለሰቡ የፈጸመውን የወንጀል አድራጎት በመጥቀስም ክስ መስርቶበታል።

17/06/2025

ፍርድ ቤት ማንኛውም በፍርድ ሊወሰን የሚችል ጉዳይ ሲቀርብለት ሕግንና ማስረጃን ብቻ መሰረት በማድረግ በገለልተኝነት አከራክሮ ለመወሰን የተቋቋመ ሦስተኛ የመንግስት አካል ነው። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግሥት አንቀፅ 79 (1) በግልጽ እንደሚያስቀምጠው በፌዴራልም ሆነ በክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤት ብቻ ነው።

ሕግን በገለልተኝነት ለመተርጎም የተቋቋመው ይህ አካል ከማንኛውም የመንግስት አካል፣ ባለሥልጣን ወይም ከማንኛውም ሌላ ተጽዕኖ ነፃ ሆኖ ስራውን ሊሰራ ይገባል። ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነፃነት ያከናውናሉ፥ ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም። (የሕገመንግስቱ አንቀፅ 79 (2) እና (3) ይመለከተዋል)

ፍርድ ቤቶች ጉዳዮቹን የሚዳኙት በሕግ እና በቀረቡት ማስረጃዎች ብቻ ላይ ተመስርተው ነው። የተከራካሪዎች ማህበራዊ አቋም፣ ሀብት፣ ጾታ፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ብሔር፣ ቀለም፣ የፖለቲካ አቋም ወይም አመለካከት ወዘተ ከግምት ሳይገባ ሰዎች ያለ ልዩነት በሕግ ፊት በእኩል ይዳኛሉ። (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግስት አንቀፅ 25 ይመለከተዋል)

ይህ ሲሆን ነው የሕግ የበላይነት ሊረጋገጥ የሚችለው። መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በተጨባጭ እውን ይሆኑ ዘንድ ነፃ እና ገለልተኛ ፍርድ ቤት ሊኖር ግድ ይላል። ሠላምና ዘለቄታ ያለው ልማት ያለ ነፃና ገለልተኛ ፍ/ቤት ሊረጋገጥ አይችልም።

ለዚህም ነው የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 52 (1) የፍርድ ቤት ወይም የዳኞችን በነፃነት መስራት የሚጋፋ ወይም በዳኞች ላይ ተጽዕኖ የሚያደርግ ወይም ለማድረግ የሞከረ ማንኛውም ሰው በሌላ ሕግ ከፍ ያለ ቅጣት ከሌለ በቀር ከ3 ወር እስራት ባላነሳ ከ2 ዓመት ባልበለጠ ጽኑ እስራት እንደሚያሰቀጣ የሚደነግገው።

ነፃና ገለልተኛ ፍርድ ቤት ስንል ውሳኔያዊ ነፃነትን ከማረጋገጥ ጀምሮ ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸውን ውሳኔዎች፣ ብይኖች ወይም ትዕዛዛት ማክበርን ያጠቃልላል። የዳኝነት ነፃነት ዳኞች በሕግ እና በማስረጃ ላይ ተመስርተው ከውጫዊ ጫና ወይም ተጽዕኖ ነፃ ሆነው እልባት መስጠት ከመቻል ባለፈ የሚሰጡትን ውሳኔዎች ወይም ትዕዛዞችን ማክበር እና ማስከበርን ያካትታል።

ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ፣ ብይን፣ ትዕዛዝ ወይም የፍርድ ሂደቱ ላይ ቅሬታ ወይም ስህተት ካለ በይግባኝ እና ሰበር እስከ ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አለፍ ሲልም እስከ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሄዶ ማሳረምና ማስተካከል ከሚቻል በቀር የፀና ሆኖ ተፈፃሚ ይሆናል።

የትኛውም የመንግስት አካል፣ ተቋም ወይም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም ማንኛውም ሰው ውሳኔዎቹን ወይም ትዕዛዞቹን የመፈጸም እና የማስፈፀም ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህን ግዴታ ያልተወጣ አካል በሕግ ተጠያቂ ይሆናል። (የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ አንቀፅ 52 ይመለከተዋል)

ከዚህ ውጭ ያለ አካሄድ የፍትህ ሥርዓቱን የሚያዳክምና የሕግ የበላይነት የሚሸረሽር ከመሆኑም በላይ ኢ-ፍትሃዊ የሆኑ ውጤቶችን ያስከትላል። የፍትህ ሥርዓቱ ላይ ጣልቃ ገብነትን መጋበዝ ብሎም ለሕግ ውሳኔ ተገዢ አለመሆን እንደ ሀገር ሁላችንንም የሚጎዳ ከመሆኑም በላይ ተጠያቂነትም ያስከትላል።

መልካም ቀን!

16/06/2025

#ዜናመሠረት ከሀምሌ 1 ጀምሮ ከ20 አመት በላይ ያገለገሉ የመንግስት ሰራተኞች ጨምሮ የአስር ሺዎች እጣ ፈንታ ታውቋል

(ይህ ከትናንት በስቲያ በመሠረት ሚድያ የቀረበ መረጃ በብዙ አንባቢዎች ጥያቄ መሰረት ለሁሉም አንባቢዎች ክፍት ተደርጎ በድጋሜ ቀርቧል)

(መሠረት ሚድያ)- ከጥቂት ወራት በፊት የፀደቀው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ "ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲፈፅሙ የሚያስችል ነው" ቢባልም ከአዋጁ ጋር ተያይዞ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ከስራ ሊቀነሱ እንደሚችሉ መሠረት ሚድያ ከወራት በፊት መዘገቡ ይታወሳል።

አሁን የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው ደግሞ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች ከሀምሌ 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ ከስራ ሊቀነሱ እንደሆነ ታውቋል።

በዚህም ሁሉም የመንግስት ተቋማት 'ሪፎርም' በሚል አሰራር ከ20 አመት በላይ ያገለገሉ ሰራተኞችን ጨምሮ ከሀምሌ 1 ጀምሮ ውላቸው እንዲቋረጥ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን መሠረት ሚድያ ከመንግስት ምንጮች አረጋግጧል።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ከፓርላማ ፅህፈት ቤት እስከ ዩኒቨርስቲዎች፣ ከክፍለ ከተማዎች እስከ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ወዘተ ይተገብሩታል በተባለው በዚህ የሰራተኛ ቅነሳ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ከስራቸው ይሰናበታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በአዋጁ አላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ከወራት በፊት ማብራሪያ ሰጥተው በነበሩበት ወቅት በቀጥታ ስለ ሰራተኛ ቅነሳው ያነሱት ነገር ባይኖርም በመንግስት አቅጣጫ ከተያዘባቸው ጉዳዮች አንዱ "ከሚያስፈልገው በላይ የመንግስት ሰራተኛ አለ" የሚለው ዋናው መሆኑን ጠቅሰው ነበር።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌም ሂደቱ የግለሰቦችን መብት ያለአግባብ እንዳይጎዳ ሚዛኑን አስጠብቆ በመሄድ ረገድ ተገቢው ጥንቃቄ ይደረጋል ቢሉም በርካቶች ከስራቸው መቀነሳቸው እንደማይቀር ታውቋል።

የረቂቅ አዋጁን ይዘት በአግባቡ ባለመረዳት በአንዳንድ የሚዲያ ተቋማት የተዛቡ መረጃዎች እየተላለፉ እንደሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ነገሪ በበኩላቸው ግልፀኝነት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ በመወያየት ረቂቅ አዋጁን የበለጠ ለማዳበር እና ህዝቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ለማድረግ ይደረጋል ብለዋል።

አዋጁ እንደ ፍርድ ቤት፣ አቃቤ ህግ፣ ፖሊስ፣ መከላከያ፣ እና ደህንነትን የመሳሰሉ ተቋማት ውስጥ የብሄር ስብጥር ለማድረግም ያለመ መሆኑን የጠቁሙት ምንጮቻችን አዋጁ "የብሔር ብሔረሰቦች ብዙሃነት እና አካታችነት ስርዓትን ይገነባል" በሚል በመንግስት እንደታሰበ አስረድተዋል።

የዚህን የመንግስት ሰራተኞች ቅነሳ የሚጠቁም ነገር ግን ብዙ ሰው ልብ ያላለው አንድ መረጃ በአንድ የመንግስት ሚድያም ተለቆ ነበር።

"ሲቪል ሰርቪሱ ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ መሆኑ ተጠቆመ" የሚል መረጃ በቅርቡ በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ተሰራጭቶ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ያለው የሲቪል ሰርቪሱ ቁጥር ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ መሆኑን ዶ/ር ነገሪ መናገራቸውን ዘግቦ ነበር።

ዶ/ር ነገሪ በዚህ ንግግራቸው እንደጠቀሱት "በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ያለው የሠራተኛ ቁጥር በጣም በርካታ ነው። ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ ነው። ከአደረጃጀት አንጻር ሲታይም በአንድ መሥሪያ ቤት ውስጥ መዋቅሩ የሚሸከመው ብዙ የሰው ኃይልን ነው፤ በተሸከመ ቁጥር ደግሞ የሚያገኘው ጥቅም አናሳ ነው" ብለው ነበር።

ሀላፊው አክለውም "የመንግሥት ሠራተኞች የብዛታቸውን ያህል የሚሠሩት አገልግሎት የሚያረካ አይደለም፣ የተወሰኑ ይሠራሉ፤ ሌሎቹ ግን የተወሰኑ ሠራተኞች በሠሩት ትከሻ ላይ ተንጠላጥለው ይኖራሉ" በማለት የሰራተኛ ቅነሳ መኖሩን በተዘዋዋሪ መንገድ ጠቁመዋል።

ይሁንና ይህ መረጃ መሠረት ሚድያ ላይ ከወጣ በኋላ ለመንግስት ሚድያዎች በሰጡት ሌላ ማብራርያ “አዋጁ በብቃትና በውድድር ላይ የተመሠረተ ነጻና ገለልተኛ ሲቪል ሰርቪስ ይፈጥራል” በማለት አዋጁ የሠራተኛውንም ጥቅማጥቅም ያካተተ እንደሆነም ተናግረዋል።

ሀላፊው አክለውም አዋጁ የመንግሥት ሠራተኛው በብቃትና ውድድር ላይ ተመስርቶ ተገቢ የሆነ ጥቅም እንዲያገኝ የወጣ እንጂ መንግሥት ሠራተኛውን ለመቀነስ ያለመ እንዳልሆነ እና መረጃን በማጣመም ሕዝብን ለማደናገር የሚደረገው ጥረትም መሠረተ ቢስ ነው በማለት ተናግረዋል።

ዶ/ር ነገሪ ይህን ማስተባበያ ቢያቀርቡም መሠረት ሚድያ አሁንም የሠራተኛ ቅነሳውን በተመለከተ የሰራው ዘገባ ትክክለኛ እንደሆነ እንደሚያምን ለተከታታዮቹ ለመግለፅ ይወዳል።

በአሁን ሰአት በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በየማስታወቂያ ቦርዶቻቸው የስራ ድልድል እየለጠፉ መሆኑን እና ከስራቸው የተቀነሱ ሰዎች ከወዲሁ እጣ ፈንታቸውን እያወቁ መሆኑን ያሰባሰብናቸው መረጃዎች ያሳያሉ።

መረጃን ከመሠረት!

16/06/2025

በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 234(1)(ረ) የሚቀርብ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ተከሳሽ የሆነ ወገን ከሳሽ ላይ የሚጠይቀውን ማንኛውንም ነገር እንዲወሰን የሚያቀርበውን ክስ የሚመለከት ሲሆን ክሱ ተገቢው ዳኝነት ተከፍሎበት ፣ ከሳሽ የሆነው ወገን መልስ ሰጥቶበት እንደመደበኛው ክስ ክርክርና ማስረጃ ተሰምቶ ውሳኔ ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡የማቻቻል ጥያቄ ከተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የተለየ እና በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 236 እና 237 አግባብ የመከላከያ መልስ አካል ሆኖ የሚቀርብ ነው፡፡ የማቻቻል ክርክር ተከሳሽ የሆነ ወገን ለቀረበበት ክስ ከሳሽ ከሆነው ወገን የሚፈለግ ክፍያ መኖሩንና ለክሱ ማቻቻያ ሆኖ እንዲያዝ የሚቀርብ ነው፡፡ ክርክሩ የመከላከያ መልስ አካል በመሆኑ እንደተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ዳኝነት ተከፍሎበት የሚቀርብ አይደለም፡፡ ሰበር ሰሚ ችልቱ በመዝገብ ቁጥር 177402 ላይ የማቻቻል ጥያቄ የመከላከያ መልስ አካል ሆኖ ቀርቦ ጉዳዩን መርምሮ መወሰኑን ማየት ይቻላል፡፡
የሰ/መ/ቁ 253530 ጥር 27 ቀን 2017 ዓ/ም

12/06/2025

#ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) እና የአክሲዮን ማህበር ተመሳሳይነትና ልዩነት

በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC ) እና የአክሲዮን ማህበር ይገኙበታል ።

ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።

#ተመሳሳይነታቸዉ

• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑን (የንግድ ህግ 256 እና 501 )
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣

#ልዩነታቸዉ

አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ አንቀጽ 495(4) ላይ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን ( share company ) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ አንቀጽ 248(3) ላይ ይገኛል።

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም (የንግድ ህግ ቁጥር (496)

• አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም (የንግድ ህግ ቁጥር 247)

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል (የንግድ ህግ ቁጥር (495(1)

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም አንቀጽ 495(2) ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ (የንግድ ህግ ቁጥር248)

• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።

• አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( plc) ዉስጥ ቦርድ የለም።

ምንጭ:- የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ

12/06/2025
ከሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ የከተማችን ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታ በማስመልከት ከሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት መግለጫ  ሰጥቷልከነሃሴ 16 ጀምሮ ...
01/08/2023

ከሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የከተማችን ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታ በማስመልከት ከሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት መግለጫ ሰጥቷል

ከነሃሴ 16 ጀምሮ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሚከበረው ተወዳጁና ተናፋቂ የሻደይ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር የዋግ ህዝብም ሆነ ከዋግ ውጭ የሚኖሩ ህዝቦች ፍላጎት ነው።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ቀናት ወዲህ አካባቢያችን ላይ የጸጥታ ችግር ያለ በማስመሰል የማንነታችን መገለጫ የሆነውን የሻደይ በዓል በድምቀት እንዳናከብር ከህዝባችን ታሪክ፣ ማንነት እና ባህል በተቃርኖ ህዝባችን የማይመጥን አጀንዳ በማሰራጨት ሳንካ ለመፍጠር እሚውተረተሩ ጥቂት የማይባሉ አካላት በማህበራዊ ሚድያ ዘመቻ ጀምረዋል ።

መንግስት በሆደ ሰፊነት እስከ ዛሬ ድረስ እራሳቸውን እንዲያስተካክሉ ጊዜ ሰጥቷቸው ቆይቷል። ነገር ግን እራሳቸው አስተካክለው ስለከተማችን የጋራ ልማት ከመጠየቅ ይልቅ በተለያየ ጎራ ተከፋፍሎ ህብረተሰቡን ወደተለያየ ውዥንብር ውስጥ እየፈጠሩበት ይገኛል ።

ይህ አካሄድ ደግሞ ህብረተሰባችን የማይጠቅም አካሄድ በመሆኑ አሁን ካሉበት የተሳሳተ አካሄድ በመመለስ ስለከተማችን ልማት እና ተጠቃሚነት በጋራ ተመካክሮ መስራት ጠቃሚ በመሆኑ ለጋራ ልማት እና ተጠቃሚነት ልንሰራ ይገባል ።

በመሆኑ ይህ የሻደይ በዓል በድምቀት እንዲከበር የሚከተሉትን ገደቦች አስቀምጧል።

1.ስምሪት ከተሰጣቸው የጸጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በሗላ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። ሲንቀሳቀስ የተገኘ የጸጥታ አካሉ አስፈላጊውን እርምት ይወስዳል ።

2.ሰምሪት ከተሰጣቸው ተሽከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። ሲንቀሳቀስ የተገኘ የጸጥታ አካሉ አስፈላጊውን እርምት ይወስዳል ።

3.ስምሪት ከተሰጣቸው የጸጥታ መዋቅር ውጭ ማንኛውም አካል የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

4.ማንኛውም የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚ በድብቅ የሚጽፍም ሆነ በግልጽ የሚጽፍ በማህበረሰቡ ላይ ውዥንብር የሚፈጥር፣ብሔር እና ሃይማኖትን በሚፃረር መልኩ የሚጽፍ የተከለከለ ነው። ሲጽፍ የተገኘ አስፈላጊውን የህግ አግባብ መሰረት በማድረግ የሚጠየቅ መሆኑ ።

5.የከተማችን ነዎሪ አገው አማራ ትግሬ ሳይባባል ለረጅም ጊዜ ተከባብሮ የኖር ህዝብ ነው ይህንን ህዝብ ለማለያየት እና ለማቃቀር የሚደረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በጥብቅ የሚወገዝ ተግባር በመሆኑ ከዚህ አይነት ተግባር እና መሰል ድርጊቶችን ከመፃፍ እና ከማጸባረቅ መቆጠብ ይገባል ።

ሃምሌ 24/2015 ዓ/ም
የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ጽጥታ ምክርቤት
ሰቆጣ

"እንደ ሕዝብ ለመጽናት እንደሀገር  ለመኖር የዉስጥ ሰላም የወል ሀሳባችን እና የጋራ መግባቢያችን ሊሆን ይገባል" የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮሀገር ማለት የሰዉ ልጆች ማኀበራዊ ስ...
30/07/2023

"እንደ ሕዝብ ለመጽናት እንደሀገር ለመኖር የዉስጥ ሰላም የወል ሀሳባችን እና የጋራ መግባቢያችን ሊሆን ይገባል" የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ

ሀገር ማለት የሰዉ ልጆች ማኀበራዊ ስሪት ነዉ። ይህ ማኀበራዊ መስተጋብር በዜጎች መካከል በሚፈጠር ተፈጥሯዊም ሆነ ሰዉ ሠራሽ ልዩነት ዉስጥ በሚፈጠር የተቃርኖ ስንጥቅ የሚሰፋዉ እና የሚደፈርሰዉ በሰላም እጦት ነዉ። ይህ ሁኔታ ሰላም የሰዉ ልጆች የእለት ከእለት ኑሮ ዉስጥ በአጽንዖት ከሚፈልጉት አንኳር ጉዳይ አንደኛዉና ብቸኛዉ መፍትሔ መሆኑን ያስረዳናል።

በዘልማድ ሰላም ከዉስጥ የሚመነጭ መሆኑን ባለመረዳት አንዳንዶቻችን አንጋጠን ሰላምን ከኛ ዉጭ እንናፍቃለን። አለፍ ሲልም ሀሳብን ወደ ጠረጴዛ ከማምጣት ይልቅ ወደ አክሳሪ እና ከፋፋይ ግጭት እንወስደዋለን። ያኔ የሰላም አየር ከባለቤቱ ይርቃል፤ አብሮነት ይናጋል፤ አንድነት ይኮሰምናል።

ሰላም በናፍቆት ወይም በመሻት አይመጣም ይልቅ ከራስ የሚጀምር አልፎም ለሌሎች የሚተርፍ ሰዋዊ እሳቤ ነዉ። በግርግር ወይም በብጥብጥ ዉስጥ ሰላምን መፈለግ ደመናን እንደመጨለፍ ይቆጠራል። በልዩነት እና በግጭት የሚገኝ ሰላም፣ የሚጸና አንድነት እና የሚቆም ሀገር የለም። የሚመለስ የክልሉ ሕዝብ ፍላጎትና ጥያቄም አይኖርም። ፍላጎቶቻችንና ጥያቄዎቻችን ሁሉ የሚመለሱት በሰላማዊ ትግልና በሰላም ብቻ ነው።

እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ የከረሩ ልዩነቶችን ምክንያት አድርጎ እየጎላ የመጣዉ መጠራጠር እና አለመተማመን ሰላምን የሩቅ ሀገር አድርጎብናል። የዚህ ፈተና እያደገ መምጣት ደግሞ ሰላምን ከራስ የሚመነጭ ሳይሆን ከሌሎች የሚቸረን አድርገን በማሰባችን ነዉ።

እንደ ሕዝብ አንድ ሆኖ ሰላም፣ ዴሞክራሲ እና ልማት ለማምጣት ከዉስጥ የጀመረ ሰላም ብቸኛዉ ጋሻ ነዉ። ሰላም ሲኖር አንድነት፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ እድገትና ልማት ተከታትለዉ ይመጣሉ።

የተለያዬ አሰላለፍ ውስጥ የገባ ማኅበረሰብ ወይም ሕዝብ የተሰናኘ የሕዝብ አቅም ኑሮት ችግሮችን በአሸናፊነት መሻገር እንደማይችል የምንረዳበት ጊዜዉ አሁን ነዉ።

ስለሆነም እንደ ሕዝብ ለመጽናት እንደሀገር ለመኖር ሰላም የወል ሀሳባችን እና የጋራ ቋንቋችን ሊሆን እንደሚገባ በመገንዘብ ለሰላም እና ለዉይይት በራችን ክፍት አድርገን ለጋራ ሰላማችን ዘብ በመሆን እንድ ሆነን በአንድ በመቆም በጋራ መሥራት ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑን ልንረዳ ይገባል።

(አሚኮ)

 #𝑉𝐼𝑆𝐼𝑇-𝑊𝐴𝐺-𝐻𝐼𝑀𝑅𝐴  #𝑉𝑖𝑠𝑖𝑡𝑠𝑒𝑞𝑜𝑡𝑎𝑆𝑒𝑞𝑜𝑡𝑎𝑣𝑖𝑙𝑙𝑎𝑔𝑒𝑜𝑓𝑔𝑒𝑛𝑒𝑟𝑎𝑙𝑙𝑠  #𝑉𝑖𝑠𝑖𝑡 𝐸𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 𝑙𝑎𝑛𝑑 𝑜𝑓 𝑑𝑖𝑓𝑓𝑒𝑟𝑒𝑛𝑡 𝑏𝑒𝑎𝑢𝑡𝑢𝑓𝑢𝑙𝑙 𝑐𝑢𝑙𝑡𝑢𝑟𝑒𝑠. #𝐴𝑠ℎ𝑒𝑛𝑑𝑦...
30/07/2023

#𝑉𝐼𝑆𝐼𝑇-𝑊𝐴𝐺-𝐻𝐼𝑀𝑅𝐴
#𝑉𝑖𝑠𝑖𝑡𝑠𝑒𝑞𝑜𝑡𝑎𝑆𝑒𝑞𝑜𝑡𝑎𝑣𝑖𝑙𝑙𝑎𝑔𝑒𝑜𝑓𝑔𝑒𝑛𝑒𝑟𝑎𝑙𝑙𝑠
#𝑉𝑖𝑠𝑖𝑡 𝐸𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 𝑙𝑎𝑛𝑑 𝑜𝑓 𝑑𝑖𝑓𝑓𝑒𝑟𝑒𝑛𝑡 𝑏𝑒𝑎𝑢𝑡𝑢𝑓𝑢𝑙𝑙 𝑐𝑢𝑙𝑡𝑢𝑟𝑒𝑠.
#𝐴𝑠ℎ𝑒𝑛𝑑𝑦𝑒 #𝑆ℎ𝑎𝑑𝑒𝑦

በሃገሩ ቡርኪናፋሶ  ሁለተኛው ቶማስ ሳንካራ ይሉታል። በጉርምስናው ጊዜ የነገሰ በእድሜ ቲኒሹ ፕረዚዳንት ነው። ገና 34 አመቱ ነው። ካፕቴይን ኢብራሂም ሳቦሬ ይባላል።  ጀግናው ወጣቱ አፍሪካ...
29/07/2023

በሃገሩ ቡርኪናፋሶ ሁለተኛው ቶማስ ሳንካራ ይሉታል። በጉርምስናው ጊዜ የነገሰ በእድሜ ቲኒሹ ፕረዚዳንት ነው። ገና 34 አመቱ ነው። ካፕቴይን ኢብራሂም ሳቦሬ ይባላል። ጀግናው ወጣቱ አፍሪካዊው መሪ ከጀግናው ፕረዚዳንት ፑቲን ጋር ተገናኝቷል። ለበርካታ መሪዎችም ምርጥ ንግግር እየተናገረ አስደምሟል!!

ዳግማዊ ቶማስ ሳንካራ ኢብራሂም ላወሬ!!

ሻደይ  ባህል ብቻ ሳይሆን ማንነታችን፣ ታሪካችን፣ ቅርሳችንና ጥበባችን በመሆኑ ባህሉ ሳይበረዝና ሳይከለስልናከብረው ይገባ /አቶ አደራጀው ቀለመወርቅ/ ሰቆጣ፣ሃምሌ 21/2015 ዓ/ም (ሰቆጣ ...
29/07/2023

ሻደይ ባህል ብቻ ሳይሆን ማንነታችን፣ ታሪካችን፣ ቅርሳችንና ጥበባችን በመሆኑ ባህሉ ሳይበረዝና ሳይከለስ
ልናከብረው ይገባ /አቶ አደራጀው ቀለመወርቅ/

ሰቆጣ፣ሃምሌ 21/2015 ዓ/ም (ሰቆጣ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን) በየአመቱ በወርሃ ነሃሴ አጋማሽ የሚከበረውን እንቁና ተወዳጅ የሆነው የሻደይ በዓል ስናከብር ባህሉን፣ ትውፊቱንና እሴቱን በጠበቀ መልኩ ማክበር ይገባል ሲሉ የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ሻደይ ለበርካታ አመታት ከተጫወቱ እናቶች መካከል ወ/ሮ ገነት አንዳርጌ ሻደይ ስንጫወት ቀሚስና መቀነት ለብሰን፣ ድሪና መስቀል ከአንገታችን አድርገን፣ እግራችን በአልቮና ባህላዊ ጫማ አድርገን፣ ተፈጥሮ በሰጠችን ጸጉር ተውበን እንጫወት ነበር፡፡

አሁን ላይ ከባህሉ በማፈንገጥ ሰው ሰራሽ ጸጉር በመሰራትና ባህሉን የማይወክሉ አልባሳት በመልበስ በዓሉን ለማክበር የሚሞክሩ አንዳንድ ወጣት ሴቶች እያስተዋልን ነው፡፡

በመሆኑም ከእናት አያቶቻችን በትውልድ ቅብብሎሽ የወረስነው ቱባ ባህላችን ትውፊቱንና እሴቱን በጠበቀ መልኩ ማክበር ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉ ወ/ሮ ገነት ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ግርማ ጽጌ ይባላሉ ለበርካታ አመታት በባህላዊ የልብስ ስፌት ሞያ ያሳለፉ አንጋፍ ባለሞያ ናቸው፡፡ እሳቸው እንዳሉትም ከ2000 ዓ.ም እና ከዚያ በፊት የሻደይ ባህላዊ አልባሳት በማሰፋትና በዓሉን በማስተዋወቅ በኩሉ በተለይም ሴት ልጃገረዶች የተሻለ እንቅስቃሴ ነበራቸው ፡፡

አሁን ላይ ግን ባህላዊ አልባሳትን በማሰፋት በኩል ወንዶች የተሻለ ሆነው ተገኝተዋል፤ ሴቶች እህቶቻችና ልጆቻችን ግን ከባህላችን ያፈነገጠ አለባበስ እየተለመደ በመምጣቱ ባህላዊ አልባሳትን በማሰፋት ረገድ እየተቀዛቀዘ መጥቷል ብለዋል፡፡

እናም ቱባ ባህላችን ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውልድ ለማስተላለፍ ማህበረሰቡ፣ ወላጆች፣ ባህልና ቱሪዘም ጽ/ቤት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የበኩላችን ድርሻ መወጣት ይኖርብናል ሲሉ አቶ ግርማ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

ሌላው ሃሳብ የሰጡት የባህል ልብስ ሰፌ የሆኑት አቶ አለማየሁ ማሞ ቀደም ሲል ሴቶች በብዛት ባህላዊ አልባሳትን፣ ወጣት ወንዶች ኮርቶና ቁምጣ፣ ትላልቅ አባቶች ደግሞ ሳሪያን ኮት፣ ተፈሪ ቅድ የሚባል ሱሪና ሌሎች መሰል የባህል አልባሳት በማሰፋት የሻደይ በዓል በድምቀት ይከበር ነበር፡፡

በአሁኑ ሰዓት ግን በዓሉ እየደበዘዘና የአለባበስ ባህሉም እየተቀየረ መጥቷል፤ ይህም በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በመረባረብ ባህሎቻችንና እሴቶቻችን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር መደረግ አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የሻደይ በዓል አስመልክተው አስተያየት ከሰጡት ልጃገረዶች መካከል ወጣት ኪዳን ጣምተው ከእናቶቻችን የወረስነውን የሻደይ የሴቶች የነፃነት በዓል ሳይከለስና ሳይበረዝ ባህሉን፣ ወጉንና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በማክበር ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍ ተገቢ ቅድመ ዝግጅት እያደረግ ነው በማለት ተናግራለች ፡፡

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፈ አቶ አደራጃው ቀለመወርቅ በበኩላቸው ቱባ ባህላችን የሆነውን ተወዳጅና ተናፋቂው የሻደይ በዓል በደመቀና ባማረ መልኩ ለማክበር ህፃናት፣ ወጣቶችና እናቶች በእድሜ ክልላቸው ተለይተው ትውፊቱንና ስርዓቱን ጠብቀው እንዲጫወቱና ህዝባዊ በዓል እንዲሆን ሰፊ ቅድመ ዝግጅት እያደረግን ነው፡፡

በዜማ፣ በአለባበስ፣ በውዝዋዜ የሚስተዋሉ ችግሮች እንዲቀረፉና ቱባ ባህላችን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር በዘርፉ በቂ እውቀት ባለቸው ባለሞያዎች የታገዘ ስልጠና በመስጠት ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሻደይ ለእኛ ለአገዎች ባህል ብቻ ሳይሆን ማንነታችን፣ ታሪካችን፣ ቅርሳችንና ጥበባችን በመሆኑ ባህሉ ሳይበረዝና ሳይከለስ በዩኒስኮ ተመዝግቦ አለም አቀፍ ተንቀሳቃሽ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን በምናደርገው ጥረት የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፣ በሃገር ውስጥ ሆነ በውጭ ሃገር የሚኖሩ የዋግ ተወላጆችና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በጌትነት አጉማስ

Address

Debra Markos

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yitbarek Gebrie Misew posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share