የዐማራ አንድነት ማኅበር በሸዋ

የዐማራ አንድነት ማኅበር በሸዋ ፩ ዐማራ

17/06/2025

ዓማራ ጦርነት አያስፈልፈውም

ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት አንድነት ሀይል ነው።ኢትዮጵያ ሀገራችንን ለመገንባት ሁሉም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ያሉ ዜጎች በአንድነት በመሆን ሀገር መገንባት ያስፈልጋልበአንድነት ...
20/05/2025

ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት አንድነት ሀይል ነው።

ኢትዮጵያ ሀገራችንን ለመገንባት ሁሉም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ያሉ ዜጎች በአንድነት በመሆን ሀገር መገንባት ያስፈልጋል

በአንድነት የተገነባ ሀገር ማንም ቢሆን አያፈርሰውም አብረህ ከቆምክ የውጪ ባንዳም አርፎ ይቀመጣል #ዛፍን እንደ ምሳሌ ማየት እንችላለን ሁሉም ስሮቹ ጊዜያቸውን የሚያሳልፋት ለዛፉ እድገት ነው ውሀ በማጠጣትና ዛፉን በየቦታው ተሰራጭተው ከመሬት ላይ ቆንጥጦ በመያዝ ድንገት ባጋጣሚ አንዱ ቢቆረጥ ሌሎቹ ተረባርበው እድገቱን ያስቀጥላሉ እኛም ለሀገራችን እድገት ተግዳሮቶችን በጋራ በመመከት በመከላከል ሀገራችንን ወደ እድገት ጎዳና በአብሮነት ከፍ ማድረግ አለብን

ሁሉም ዜጋ በአንድነት ከቆመ ሀገር ይከበራል የውስጥ ለውስጥ ሽኩቻው ይቆምና በአንድነት ድህነት ላይ ርብርብ ይደረጋል

ጦርነት ለቀስቃሹም፣ ለተኳሹም ሆነ ለገለልተኛው ማሕበረሰብ አይበጅም። ሚሻለው ሰላም ነው! የቁረጠው ፍለጠው የውር ድንብር ጉዞ የኋላኋላ ጸጸት ነው ትርፉ። ሰላም
20/05/2025

ጦርነት ለቀስቃሹም፣ ለተኳሹም ሆነ ለገለልተኛው ማሕበረሰብ አይበጅም።

ሚሻለው ሰላም ነው!
የቁረጠው ፍለጠው የውር ድንብር ጉዞ የኋላኋላ ጸጸት ነው ትርፉ።

ሰላም

14/10/2021

"ኢትዮጵያ ከዘላቂ ጥቅሟ አንጻር የራሷን አማራጭ በመጠቀም የተከፈተባትን ዘመቻ በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ይጠበቅባታል" በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር

ጎንደር፡ ጥቅምት 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብን ሰላም እና የሀገሪቱን ቀጣይነት እስካረጋገጠ ድረስ ለውጪ ጫና ሸብረክ ሳይባል በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ተጠያቂነት የሰፈነበት ማንኛውም አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ ርምጃ መወሰድ እንዳለበት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ወርቁ ካሰው ተናግረዋል።

ሉዓላዊ ግዛት፣ መንግሥት እና ሕዝብ ያላቸው ሀገራት በመርህ ደረጃ ለሰው ልጆች ምቹ እና የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ለመፍጠር በሚል በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የጋራ አደረጃጀት ፈጥረዋል።

ይሁን እንጂ በኢኮኖሚ የፈረጠሙ ሀገራት ለመልካም ዓላማ የተፈጠረውን አደረጃጀት እንደ ሽፋን በመጠቀም ከተቋቋሙበት ቻርተር፣ ሕግ እና ዓላማ ባፈነገጠ መልኩ ድብቅ አጀንዳቸውን ሲያስፈጽሙ ተስተውሏል። በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተረጋገጡ ሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱ፣ በሰላም የመንቀሳቀስ፣ ሠርቶ የመብላት፣ በሕይወት የመኖር፣ ከስጋት ነጻ በሆነ መንገድ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የመፈጸም መብቶች ሲገደቡ ቤንዚን ከመጨመር የዘለለ ሚና እንዳልነበራቸው ከፈረሱ ሀገራት ታሪክ መረዳት ይቻላል ባይ ናቸው አቶ ወርቁ ።

እነዚህ ሀገራት ዝቅተኛ ምጣኔ ሀብት ባላቸው ሀገራት ላይ ተጽዕኖ መፍጠር የሚያስችላቸውን መረጃ በመሰነድ በፈለጉት አቅጣጫ በማይመሩት ላይ ማዕቀብ መጣል፣ በባለስልጣናት ላይ የጉዞ እገዳ ማድረግ እና የምንዛሬ ክልከላን ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን እስከማሳለፍ ይደርሳሉ። እርዳታ ለመስጠት ወይንም ብድር ለማቅረብም ጥቅማቸውን የሚያስከብር ቅድመ ሁኔታ ያመቻቻሉ።

ይህ አካሄድ ኢትዮጵያ በገጠማት ፈተናም ተስተውሏል። ሕዝቡ በሕይወት የመኖር፣ እንደ ሕዝብ አብሮ የመቆየትና ሀገርን የማስቀጠል ትግል ላይ እንደሆነ ይታወቃል። አሸባሪው የትህነግ ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት እንደ ሀገር በግለሰብ ደረጃ የመኖር ሕልውና አደጋ ላይ ወድቋል። ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ ያላደገ፣ በልቶ ማደር ያልቻለ ሕዝብ የበዛባት፣ የኑሮ ውድነት ጣሪያ የደረሰባት፣ የሰላም እጦቱም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ፣ በየመንደሩ ሕገወጥ አደረጃጀት እየተፈጠረ ፈተናዋ የበዛባት ሀገር ሆናለች።

ሰው ከመኖሪያ ቤቱ እየተፈናቀለ ሠርቶ መብላትም ሆነ ሀብት አፍርቶ ቤተሰቡን መምራት አልቻለም። ለረጅም ጊዜ ያፈራውን ሀብቱን በአሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ተዘርፏል፣ ወድሟልም። በረጅም ጊዜ የተገነቡ እንደ ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ፣ ክሊኒኮች እና ሆስፒታሎች የመሳሰሉ መሠረታዊ የሕዝብ መገልገያ ተቋማት ስልታዊ በሆነ መንገድ እየወደሙ ነው። በዚህም የዜጎች የመማር፣ የጤና አገልግሎት የማግኘት እና በሕይወት የመኖር መብት ተጥሷል።

ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ሕዝብ፣ ባህል እና ሀገር እንዳይቀጥል ስውር አጀንዳ ያላቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ተራድኦ ድርጅቶች እና ሀገራት ኢትዮጵያ ለገጠማት ፈተና መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ጥቅማቸውን በሚያስከብር መልኩ ተጽዕኖ ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

ለዚህም አንድን ክልል ብቻ እንደተበደለ አስመስለው የፌዴራል መንግሥትን በተደጋጋሚ ሲተቹ ይስተዋላል። ትግራይ ክልል ተከሰተ ከሚባከው ችግር በበለጠ አማራ፣ አፋር እና ቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን ጨንሮ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተስተዋለ ነው። እነዚህን ችግሮች ዓለም አቀፍ ተቋማትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በዝምታ ማለፋቸው ተግባራቸው የሕዝብን ጥቅም ያላማከለ የመሆኑ ማሳያ ነው።

የሕግ መምህሩ እንዳሉት ጩኸት የበረታው የትግራይ ሕዝብ ጉዳይ አሳስቧቸው ሳይሆን አሸባሪው ትህነግ የአጀንዳቸው ማስፈጸሚያ ስለሆነ ብቻ ነው።

አቶ ወርቁ የኀያላኑን ማስፈራሪያ የተቀበሉ ሀገራት መጨረሻቸው መፍረስ እንደሆነ አንስተዋል፤ አልቀበልም ብለው በአቋማቸው የጸኑ ደግሞ ክብራቸውን አስጠብቀው ከኀያላን ተርታ እስከመሰለፍ ደርሰዋል ነው ያሉት።

በመሆኑም ኢትዮጵያ ከዘላቂ ጥቅሟ አንጻር የራሷን አማራጭ በመጠቀም የተከፈተባትን ዘመቻ በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ይጠበቅባታል። ለዚህም በግዛቷ የተፈጠረውን ችግር በሚገባ የተገነዘበና ነገን ታሳቢ ያደረገ የሥራ መሪ እንዲሁም ለችግሩ ተራማጅ መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል። መንግሥት የሕዝቡን በሰላም ወጥቶ የመግባት፣ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እሴቶችን የማስቀጠል፣ በሰላም ተኝቶ የመነሳት፣ ሠርቶ የመለወጥ ሁኔታን የማመቻቸት የቤት ሥራ ይጠብቃል።

አቶ ወርቁ እንደነገሩን መንግሥት ሕልውናውን አስጠብቆ ራሱ ባወጣቸው ሕጎች እና ባደራጃቸው ተቋማት የሕዝቡን ሰላም እና ደኅንነት የማረጋገጥ ግዴታውን በአግባቡ መወጣት አለበት።

የሕዝቡን ሠርቶ የመብላት እና የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ቀድሞ የሕልውና ዘመቻውን ማጠናቀቅ ይገባል። ለዚህም አሸባሪውን ቡድን ከነአስተሳሰቡ ለመጨረሻ ጊዜ ማጥፋት ይገባል። ዘመቻው ተጠናቀቀ የሚባለው ግን ጠላትን በውጊያ በማሸነፍ ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ ምክንያት የደረሰውን ማኅበራዊ ችግር ማስተካከል እና የውጪ ግንኙነቱን መስመር ማስያዝ ሲቻል ብቻ ነው። ለዚህም የሀገሪቱን ህልውና እና የሕዝቧን ዘላቂ ጥቅም እስካረጋገጠ ድረስ በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ ተጠያቂነት የሰፈነበት ማንኛውም አስተዳደራዊና ሕጋዊ ርምጃ መወሰድ አለበት።

ማኅበረሰቡን በተገቢ እና በተደራጀ አግባብ ማስተባበር፣ ሀገር በቀል ሀብት እና እውቀትን በአግባቡ ተጠቅሞ መልማት አንዱ አማራጭ መሆኑን ነው ያነሱት።

ለፐብሊክ ዲፕሎማሲው ልዩ ትኩረት በመስጠት በመረጃ ስህተት የሚፈጠር ክፍተት ካለ የማጥራት፣ ሆን ተብሎ ተጽዕኖ ለማድረስ የሚሠሩትን ደግሞ ቁርጥ ባለ አቋም ማስረዳት እንደሚገባ ነው የገለጹት።
ፈታኙን ወቅት ለማለፍ ሕዝቡ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ መደራጀት እና መተባበር እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።

የብዙኃን መገናኛ ድርጅቶች ከስሜት ነጻ ሆነው በተናበበ መልኩ የሀገርን ጥቅም እና የሕዝብን ዘላቂ ሰላም ታሳቢ ያደረገ ሥራ ማከናወን አለባቸው ብለዋል።

የሕልውና ዘመቻው ሲጠናቀቅ ፖለቲካው ይስተካከላል፤ የውስጥ አጀንዳዎች መስመር ይይዛሉ፤ በየአካባቢው እያቆጠቆጡ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍም እድል ይሰጣል። ሕዝቡን አደራጅቶ በልማት ለማስተሳሰርም በር እንደሚከፍት አስረድተዋል ።

ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ-ከጎንደር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

18/08/2021

አማራ !

17/08/2021

የሠራዊት ማዕበል
🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹

እንርዳቸው !ኢትዮጵያውያኑ ከአጣዬ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለገቡ 12 ተማሪዎች ሙሉ ዓመታዊ ወጪን ለመሸፈን ቃል ገቡ፡፡ ሌሎች 85 ተማሪዎች ግን አሁንም ድጋፍ ይሻሉ ተብሏል፡፡ https://www...
03/07/2021

እንርዳቸው !

ኢትዮጵያውያኑ ከአጣዬ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለገቡ 12 ተማሪዎች ሙሉ ዓመታዊ ወጪን ለመሸፈን ቃል ገቡ፡፡

ሌሎች 85 ተማሪዎች ግን አሁንም ድጋፍ ይሻሉ ተብሏል፡፡

https://www.facebook.com/AmharaMediaCorporation/posts/1577861319055523?__cft__[0]=AZVjOJVSM7ZqchOUbHvkUxT5LflgSRx1v0ldU2bRDu_lmnTwx8eYtuItsEp6JB02c0cl2lQgHnIzIQVH7rpATyVU2ETFr-ogfYsWH9Nf-AY9oLp8ztzLdyAhyMiMD51DonzeFoFX8hNgCSyycnjzX2Yh&__tn__=%2CO%2CP-R

ከቢጤያችን ጋር እየታገልን እንዳይሆን እንጠርጥር ! ሐሳበ-ግትር ምን? ለምን? እንዴት? ሐሳበ-ግትር ሰዎች ከሚታይባቸው ዋና ዋና ባህሪዎች መካከል፣ የሌላውን ሰው ሃሳብ መቃወም፣ በማያገባቸው...
31/05/2021

ከቢጤያችን ጋር እየታገልን እንዳይሆን እንጠርጥር !

ሐሳበ-ግትር ምን? ለምን? እንዴት?

ሐሳበ-ግትር ሰዎች ከሚታይባቸው ዋና ዋና ባህሪዎች መካከል፣ የሌላውን ሰው ሃሳብ መቃወም፣ በማያገባቸው ነገር ላይ ጥልቅ በማለት አፍራሽ ሃሳብን መሰንዘር፣ ተቃዋሚነት፣ አሳማኝ ነገሮች ቢገኙ እንኳን ሃሳብን አለመለወጥ፣ ክርክርን መውደድና ክርክርን በሃሳብ የበላይነት ማሸነፍ ሲያቅታቸው ሰዎችን በቃላትና ስም በማጥፋት ማጥቃትና የመሳሰሉት ድርጊቶች ይገኙበታል፡፡

ሰዎች በተለያየ ምክንያት ሃሳበ-ግትር ይሆናሉ፡፡

1. አንዳንድ ሐሳበ-ግትሮች ማግኘት የሚፈልጉትን ውጤት የሚያገኙት ግትር በመሆንና ድርቅ በማለት እንደሆነ ስለሚያምኑ ሐሳበ-ግትር ይሆናሉ፡፡

2. አንዳንድ ሐሳበ-ግትሮች ሃሳባቸውን የማይቀበል ሰው ሁሉ እነሱን ራሳቸውን እንዳልተቀበለ የማሰብ የዝቅተኝነት ዝንባሌ ስላላቸው ከዚያ የመጠቃት ስሜት ለማምለጥ ሐሳበ-ግትር ይሆናሉ፡፡

3. አንዳንድ ሐሳበ-ግትሮች የቆየና የተጠራቀመ የስሜት ቁስል ስላለባቸው ያንን አምቀው የኖሩትን ቁስላቸውን በሰዎች ላይ በማውጣት የመበቀል ስሜት ስለሚነዳቸው በሆነ ባልሆነ ተቃዋሚ በመሆን ሐሳበ-ግትር ይሆናሉ፡፡

ሐሳበ-ግትር የሆነን ሰው በሚገባ ለመያዝ ካስፈለገ መጀመሪያ ራሳችንን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ አለ፡፡ “ዓላማዬ ይህንን ሰው ከዚህ ባህሪው እንዲላቀቅ የማድረግ ነው ወይስ ራሴን ከዚህ ሰው ግትርነት የመጠበቅ ነው?”፡፡
ዓላማችን ራሳችንን ከእንደዚህ አይነት ሰው የመጠበቅ ከሆነ፣ ቀላሉ መንገድ ለግትር ሃሳባቸውና ተግባራቸው ምንም ምላሽ ሳይሰጡና ከእነሱ ዘወር በማለት የግል አላማ ላይ ማተኮር ነው፡፡ ሆኖም፣ አንዳንድ ጊዜ ሐሳበ-ግትሩ ሰው የትዳር አጋር፣ የቤተሰብ አባል፣ የቅርብ ጓደኛና የመሳሰሉት ሲሆን ትቶ ከመሄድ ይልቅ የማገዝ ፍላጎት ሊያድርብን ወይም የግድ ሊሆን ይችላል፡፡

ሐሳበ-ግትር የሆነን ሰው ለማገዝ መሞከር እጅግ አድካሚ ጉዞ እንደሆነ በማወቅ መነሳት አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ሐሳበ-ግትሮች አእምሯቸው ከሰው ለሚመጣ ሃሳብ ዝግ ስለሆነ ያንን ሰብሮ መግባት ስለሚያስቸግር ነው፡፡ ይህንን አውቀን ዝግጁ ከሆንን ግን ከላይ ከጠቀስናቸው ሶስት ምንጮች መካከል የሰዎቹ ችግር የትኛው እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡

1. የሚፈልጉትን ውጤት የሚያገኙት ግትር በመሆን እንደሆነ የሚያስቡትን ግትሮች ቀላሉ መንገድ ግትር በመሆን ለማግኘት የሚሞክሩትን ነገር መከልከልና ግትርነታቸው የሚፈልጉትን ውጤት እንደማይሰጣቸው ማሳየት ነው፡፡

2. ሃሳባቸውን የማይቀበል ሰው ሁሉ እነሱን ራሳቸውን እንዳልተቀበለ የማሰብ ዝንባሌ ያላቸውን ግትሮች ለእነሱ ያለንን ቅን ሃሳብ፣ እንደምንቀበላቸውና በሃሳብና በአቋም ተለያይተን፣ እርስ በርስ ግን ተቀባብለን መኖር እንደምንችል በቃልና በሁኔታ ለማሳየት መሞከር ጠቃሚ ነው፡፡

3. የቆየና የተጠራቀመ የስሜት ቁስል ላለባቸው ግትሮች በተቻለ መጠን ካለፈው ቁስል የሚድኑበትን ድጋፍ መለገስና አስፈላጊ ከሆነ ባለሞያ እንዲያማክሩ ማድረግ ተመራጭ ነው፡፡
በነገራችን ላይ፣ ሌሎችን ሐሳበ-ግትሮችን ለመደገፍ ከመሞከራችን በፊት እኛው ራሳችን ሳናውቀው ሐሳበ-ግትርነት ይኖረን እንደሆነ ወደ ውስጣችን እንመለክት! አንዱ ምልክት፣ ሐሳበ-ግትሮችን ልክ ካላስገባንና ካላንበረከክን እረፍት የማይሰማን ከሆነ ምናልባት ከቢጤያችን ጋር እየታገልን እንዳይሆን እንጠርጥር!

via doctor

ለአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት 42 ሺህ 200 ካሬ ሜትር ቦታ ሰጥቷል፡፡  ለማእከሉ ግንባታ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል  ሕዝባ...
23/05/2021

ለአማራ ባሕል ማእከል ግንባታ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት 42 ሺህ 200 ካሬ ሜትር ቦታ ሰጥቷል፡፡
ለማእከሉ ግንባታ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል
ሕዝባዊ መሠረትን ለማስፋት ከ 92 ሺህ በላይ ሁለገብ በጎ ፈቃደኞች እና ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ አባላትን በማፍራት ባለቤትነታቸውን እንዲያረጋግጡ ተደርጓል፡፡

ከ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

የሚወክለኝ አርማዬ ነው። "ይህ ሰንደቅ ልሙጥ አይደለም፤ ባለሦስት ቀለማት ህብረብሔራዊ እና ኢትዮጵያዊ ዘመናትን የተሻገረ... እነ ባልቻ ሳፎ፣ አቡነ ጴጥሮስ፣ በላይ ዘለቀ፣ አብዲሳ አጋ፣ ሸ...
23/05/2021

የሚወክለኝ አርማዬ ነው።

"ይህ ሰንደቅ ልሙጥ አይደለም፤ ባለሦስት ቀለማት ህብረብሔራዊ እና ኢትዮጵያዊ ዘመናትን የተሻገረ... እነ ባልቻ ሳፎ፣ አቡነ ጴጥሮስ፣ በላይ ዘለቀ፣ አብዲሳ አጋ፣ ሸዋረገድ ገድሌ፣ ጃገማ ኬሎ... ሚሊየኖች አርበኞች የተዋደቁለት፤ በዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ፍፃሜዎች የደመቀ... ከውስጥ በመነጨ ስሜት የሚወክለኝ አርማዬ ነው።"

ታየ ቦጋለ አረጋ (ኢልመ ደሱ ኦዳ)

ለሕዝብ ጥያቄ የዘገየው ምላሽ ነገር ግን ተስፋ ያለው👉 የግልበሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ሕዝብ በተለያዩ መንገዶች የጠየቀው ቀደም ብሎ ነበር። ያም ሆነ ይህ “የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕ...
01/05/2021

ለሕዝብ ጥያቄ የዘገየው ምላሽ ነገር ግን ተስፋ ያለው
👉 የግል

በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ሕዝብ በተለያዩ መንገዶች የጠየቀው ቀደም ብሎ ነበር።
ያም ሆነ ይህ “የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል።

የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 23 መሠረት በተመሳሳይተግባር በተሰማሩ እና በዚህ ውሳኔ ሐሳብ መሠረት ከተሰየሙት የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ትብብር፤ ትሥሥር ወይም የሐሳብ እና የተግባር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም ውሳኔ ሐሳቡ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።

በተደራጁ ሽብርተኞች እኩይ ተግባር ሀገራት ነበሩ እስኪባሉ ድረስ ፈርሰዋልና እነዚህን ከዳተኛ በሽብርተኝነት መፈረጅ ውጤቱ ለኢትዮጵያ የትንሳዔ መሠረት እንደሚሆን እገምታለሁ።

Address

Bahir Dar

Telephone

+251929525963

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የዐማራ አንድነት ማኅበር በሸዋ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የዐማራ አንድነት ማኅበር በሸዋ:

Share