
24/02/2025
ግልፅ ለማድረግ...
ስለ አዲሱ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ማወቅ ያለብን ፦
የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ትላንት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም አዲስ ፓስፖርቶችን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የበርካቶች ጥያቄ የሆነው “የቀደሞ ፓስፖርታችንን በአዲሱ መቀየር አለብን ወይ?” የሚለው ነው፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ነባሩ ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው እስኪያበቃ ጥቅም ላይ መዋሉን የሚቀጥል ሲሆን የዕድሳት ጊዜው ሲደርስ በአዲሱ ኢ-ፓስፖርት እንደሚተካ አሳውቋል፡፡
ማንኛውም ግለሰብ የአገልግሎት ዘመኑ ያላለፈበት ፓስፖርት ካለው መለወጥ ሳይጠበቅበት መጠቀም ይችላል፡፡
ይህ ማለት ግዜው ያላለፈ የቀድሞው ፓስፖርትና አዲሱ መሳ ለመሳ አገልግሎት እየሰጡ በመቆየት የቀድሞው የአገልግሎት ግዜው ሲጠናቀቅና ግለሰቡ እድሳት ሲያደርግ አዲሱን ኢ ፓስፖርት ማግኘት ይችላል ማለት ነው፡፡
አዲሱን ኢ-ፓስፖርት የሚጠይቅ ግለሰብ በሁለት ወር ከ10 ቀን ማግኘት የሚችል ሲሆን የአገልግሎት ዘመኑም ወደ 10 ዓመት ከፍ ተደርጓል፡፡
>> አጫጭር መረጃዎች...
• አዲሱን ኢ-ፓስፖርት በሁለት ወር ከ10 ቀን ማግኘት ይቻላል፣
• 14 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት አገልግሎቱን ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል፣
• ከአንድ ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ኢ-ፓስፖርት ታትሞ ተዘጋጅቷል፣
• ከፓስፖርት በተጨማሪ ከ10 በላይ የጉዞ ሰነዶችን ማዘመን ተችሏል፣
• አዲሱ ኢ-ፓስፖርት በነበረው ዋጋ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ይሆናል፤
• ለፓስፖርት ህትመት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት የሚኖረው ፋይዳ ጉልህ ነው፣
• ከዚህ በፊት አገልግሎት እየተሰጠ የቆየው 20 ዓመት ባለፈው ቴክኖሎጂ ነው፣
• ይህንን ቴክኖሎጂ በሀገር ውስጥ መገንባት መቻሉ ትልቅ ድል ነው፣
• አዲሱ ቴክኖሎጂ ደንበኞች ባሉበት ፓስፖርታቸውን በፍጥነት ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋል፣
• ከዚህ በፊት የሚያጋጥሙ የደህንነት ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ይቀርፋል፤
• ነባሩ ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው እስኪያበቃ ጥቅም ላይ መዋሉን ይቀጥላል፤
• የዕድሳት ጊዜው ሲደርስ በኢ-ፓስፖርት ይተካል፤
ምንጭ፦ Sheger Times Media