
24/07/2023
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በይፋ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ፡፡
ዛሬ በተደረገው ይፋዊ የፊርማ ስነ-ስርአት ላይ አሰልጣኝ ውበቱ ፋሲል ከነማን ለ3 አመታት ለማሰልጠን ተስማምቷል፡፡
አሰልጣኙ ከዚህ በፊትም ክለቡን ያሰለጠነ ሲሆን በ2011 ዓ.ም ለፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ ጫፍ ላይ አድርሰውት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
አሰልጣኙ በ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ የማንሳት ግዴታ እንዳለባቸው በኮንትራታቸው ተጠቅሷል፡፡