
28/06/2025
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለቋሚ የሥራ ቅጥር መደቦች የቀን ሠራተኞችን በመቅጠር ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ከሕግ ውጪ ክፍያ መፈጸማቸው ተገለጸ
:
የመንግሥት ተቋማት ያልተጠቀሙበት ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተመላሽ ሆኗል
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለቋሚ የሥራ ቅጥር መደቦች የቀን ሠራተኞችን በመቅጠር ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ መፈጸማቸው ተገለጸ፡፡ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የመንግሥት ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የበጀት ኦዲት አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ ነው የተገለጸው፡፡
ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በሪፖርቱ እንደጠቀሰው 12 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሳይፈቀድላቸው ለቋሚ የሥራ መደቦች ላይ የቀን ሠራተኞችን ቀጥረው ተገኝተዋል ብሏል፡፡
ተቋማቱ በጠቅላላው 61,882,081 ብር ለቀን ሠራተኞች ክፍያ እንደፈጸሙ የገለጸው የፌዴራል ዋና ኦዲተር ጅማ ዩኒቨርሲቲ 25,310,211 ብር፣ አምቦ ዩኒቨርሲቲ 10,938,834 ብር፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 7,888,374 ብር፣ ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ 5,170,600 ብርና ዲላ ዩኒቨርሲቲ 4,414,974 ብር በመክፈል ዋነ...