
16/07/2025
"ኒኮላ ቴስላ/Nikola Tesla"
የቴስላ ህልም ቢሳካ ኖሮ ዓለም የመብራት ኃይልን በነፃ ነበር የሚጠቀመው።
ቴስላ በምርምር እንዳረጋገጠው በከርሰ ምድር ውስጥ ዓለማችንን ለማብራት የሚያስችል የኤሌክትሪክ ኃይል አለ።እሱ እንዳለውም "ከሰው ልጅ የሚጠበቀው ይሄንን ኃይል አውጥቶ በነፃ መጠቀም ነው"።
ሊቁ ቴስላ ይሄንን ግኝት ለዓለም ሲያስተዋውቅ የኤሌክትሪክ ነጋዴ ከሆነው ከቶማስ ኤዲሰን ጋር ግጭት ውስጥ ገባ።
ቴስላ ይናገራል "የቤታችን አምፖል ለመብራት ገመድ አያስፈልገውም በየመንገዱ የምንመለከታቸው የተጠላለፉ የመብራት ገመዶች ጥቅም አልባ ናቸው።"
የስልክና የተለያዩ የመገልገያ መሳሪያዎችን ባትሪ ለመሙላት/ቻርጅ ለማድረግ የገመድ ቻርጀር አያስፈልግም።
በቴስላ አለም ባትሪ አይዘጋም።መብራት የለምም አይባልም።የሰው ልጅ ባለበት ሁሉ መብራት አለ።ያውም በነፃ።
ፕሮጀክቱን ለመተግበር ገንዘብ ያስፈልገው ነበር።ቴስላ ምሁር እንጂ ሃብታም አልነበረም።በገንዘብም እንዲደግፉት ባለሃብቶችንም አናገረ ማንም አብሮት ሊሰራ አልፈቀደም።
እንዲያውም እንደ ጠላት አዩት ምክንያቱም የሃብታቸው ምንጭ የሆነውን የኤሌክትሪክ ኃይል በነፃ ሊያከፋፍልባለው ሆነ።
ቴስላ ቤቱን አሲዞ ከ(JP morgan bank)ገንዘብ ተበደረ።ኤሌክትሪክ ከመሬት የሚያወጣውን ማማ ሰራ።ሆኖም ግን ገንዘቡ ትልቁን ፕሮጀክት ለማሳካት በቂ አልነበረም።እናም በገንዘብ እጥረት ምክንያት አለምን በነፃ የማብራት ህልሙ ሳይሳካ ቀረ።
የክሮሺያ ተወላጅ የሆነው ኒኮላ ቴስላ ወደ አሜሪካ ተጉዞ በቶማስ ኤዲሰን ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ ነበር።አምፖልን የፈጠረው ቶማስ ኤዲሰን ይሁን እንጂ ዛሬ የምንጠቀመው ግን የቴስላን አምፖሎች ነው።
የኤዲሰን አምፖሎች በጣም ብዙ ሃይል ተጠቅመው ትንሽ ብርሃን ብቻ ነበር የሚሰጡት።በትንሽ ኃይል አስደናቂ ብርሃን የሚሰጡ አምፖሎች ባለቤት ግን ኒኮላ ቴስላ ነበር።
👉"ሙከራህን እስከምታቆም ድረስ በህይወት አትሸነፍም"